Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ጎጆ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_gojo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 479
የሰርጥ መግለጫ

Call us if you want to promote your product and service !!
FOR ANY PROMOTION
CONTACT ☎️ 251923715770 📩 @AbenaG

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 86

2022-08-29 15:31:48 #እንዳልፈቀር

እኔስ ልውደድ ላፍቅር
ልቤም ይሰባበር
ይሁን አይጎዳኝም
እራሴው ልቸገር
ግን አምላክ አደራ
አትስጠኝ አፍቃሪ
ልቤ ማፍቀር ሳያውቅ
አልሁን ተፈቃሪ

#Share

  ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                   •═••• •••═•
  
     @Yefiker_Gojo    ,,,,,, @AbenaG
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
4.5K viewsReal waver , 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:26:35 አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ
━━━━━━━━━━━━━━

አ =አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈ =ፈልጌው አደለም አላበዛም ሰበብ
ቅ =ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ር =ርሀብን ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻ =ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለ =ለማንም አልፈቅድም እንዲለዩሽ ከ#እኔ
ሁ =ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እስከማይሽ በአይኔ

#Share

  ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                   •═••• •••═•
  
     @Yefiker_Gojo    ,,,,,, @AbenaG
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
4.5K viewsReal waver , edited  12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:51:37 #የኔ አዳም

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም
#ወዴት ነህ?


⓯ Join
@yefiker_gojo @abelo_neww
5.2K viewsAbela ŵiž ~V~, edited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 22:05:51 የፍቅር ግጥም:
የኔ ውድ
         አንተ ማለት ለኔ
   በአይኔ ተለኩሰህ
   በልቤ የበራህ
   መቼም የማትጠፋ
   የልቤ ሻማ ነህ
      የኔ ፍቅር
                          አንተ ማለት ለኔ
                      ከማለዳው ፀሀይ
                      ብርሀን ፍንጣቂው
                       ከውቧ ጨረቃ
                       ምሽቱን አድማቂ
                       ከሚያምሩት ኮከቦች
                       ነህ የምትልቅ
                     የኔ ህይወት
            አንተ ማለት ለኔ
          ከልቤ ላይ ውለህ
         በልቤ የምታድር
    የውስጤ ንጉስ ነህ
       ሁሌም የምትኖር
Join and share....

@Yefiker_Gojo
1.1K viewsReal waver , 19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:12:46 ​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_37


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ



... እኔ ማን ነኝ?" ሁለቱም የሚሉት ጠፈባቸው ጓደኛው ስለ እነሱ ፍቅር ያለውን
እውነት ቢነግራት ደስ ባለው ግን አዳም ስለ ዶክተሩ
ማስጠንቀቂያ እና ህመሟ ስለ ነገርው እንዴት ብሎ ይንገራት ?
ቦስ የማያውቀው ስለ አደጋው ምክንያት እና ስለ ጊዲዮን
ነው።አዳምም እኔ ማለት ፍቅርኛሽ ነኝ የመኪና አደጋ ደርሶብሽ
ነው።የመርሳት ችግር የገጠመሽ አደጋውን ያደረስብሽ ደሞ የእኔ
ሁነኛ ጠላት ነው። ላንቺ ያለኝን ፍቅር ስለሚያውቅ ነው። ዲናም
በተራዋ እኔ ማለት ብላ ማንነቷን መዘርዘር ቢፈልጉም ግን
አይችሉም ምክንያቱም ዶክተሩ በእዚህ ጉዳይ እንዳይሳሳቱ ስለነገራቸው ነው።ሁሉም በጭንቀት ተውጠው ቤቱ በዝምታ ነገሰ።ሄዋን ሁሉንም
በአትኩሮት ምላሽ የሚፈልጉ ዓይኖቿ ማየት ቀጥላለች። ከረጅም
ዝምታ በኋላ ዲና "እህቴ ሄዊዬ እኛ እኮ ሁሉንም ነገር ማወቅ
እስካለብሽ ድረስ ነግረንሻል"። አለቻት ሄዋን ንዴት እና ጩከት
በተቀላቀለበት ድምፅ። በቃቹ በቃ አሁንስ በጣም አበዛችውት ቆይ
ልታሳብዱኝ እየሞከራቹ ነው እንዴ?። ምንድነው ችግራችሁ እ
ሲላቹ ጆሮ ለጆሮ ትንሾካሾካላቹ ፤ ሲያሰናቹ የምትጠይቃችውን
ጥያቄ አዛብታቹ ትነግሩኛላቹ ፤ እና ደሞ ስላለፈ ማንነቴ ስጠይቃቹ
ለምንድን ነው ለመመለስ ግራ የሚገባቹ፤ ያለፈ ህይወቴ የሚነገር
አደለም?፤አሳፋሪ ነው?" ስትል።አዳም ጮክ ባለ ድምፅ "በጭራሽ
አንቺ ማለት በጣም ጥሩ እና ማንም ለመሆን የሚመኘው አይነት
ሰው ነሽ፤ አንቺ ማለት የፍቅር ምሳሌ ነሽ፤ አንቺ ማለት ሄዋን
ለሰዎች አስፈላጊ ከሆኑት ስዎች መካከል ነሽ፤ በተለይ ለእኔ አዎ
አንቺ ማለት የኔ" ሲል ዲና አዳም ዝም በል ብላ ጮከች።
ሄዋን "እ ጨርሰዋ ቆይ ለምንድን ነው ያስቆምሽው? ለምን
አለች" እና ሄዋን እንባ ያርገዙ ዓይኖቿ ፊቷን አጠቡት። ተንስቅስቃ
አለቀስች አዳም አደንዝዞ ቀረ። ቦስ ሄዋንን ሄዶ አቅፎ አስገብቷ
ደርቱ ላይ ልጥፍ አርጋት። አዳም ከፍዘቱ ሲነቃ በሩጫ ወደ ውጭ
ወጣ። ዲና ልትከተለው ፈለገች ግን ብትከተለው ሄዋንን ይበልጥ
ማናደድ ይሆናል ብላ ራሷን ገታ አረገች።
ሄዋን በቦስ እቅፍ ውስጥ ሆና ለብዙ ደቂቃዎች ካለቀሰች
በኋላ ቀና አለችና።"አንተስ ስለ እኔ አታውቅም? ወይስ እንደ እነሱ
ልትነግረኝ አትፈልግም እባክህ ልለምንክ ስለ እኔ የምታውቀውን
ንገረኝ"። አለችው። ቦስ አለቀሰ። ሄዋንን
በሁለት መዳቹፎ ጉንጮቿን ያዛቸው። የቦስ አይኖች ከሄዋን
አይኖች ጋር ተገጣጠሙ።
ሄዋን የቦስን አይኖች እየተቁለጨለጨች በደፈረሱ ዓይኖቿ
እያየችው። አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አለችው እንደ በረዶ
በቀዘቀዘ ድምፅ። ቦስም በዓይኖቹ እንድትቀጥል ምልክት ሰጣት።
የሄዋን እንባዎች በቦስ የእጅ መዳፎች እና በሄዋን ጉንጮች
መሀል ፈሰሱ። ሄዋን በአሳዛኝ ድምፅ። ለምድነው አዳምን ሳየው
ደስ የሚለኝ ፤ማለቴ ሁላቸውንም ሳያቹ ደስ ይለኛል ግን ደሞ
እሱን ሳየው አለችና ጉንጮቿ ላይ ያሳርፈውን የቀኝ እጁን አንስታ
ልቧ ላይ አድርጋው እሱን ሳየው እዚህ ጋር ነው ደስታዬ፤ ለምንስ
ነው አንተ ስታቅፈኝ ያልተሰማኝ የደስታ ስሜት እሱ ባለፈው
ሲያቅፈኝ የተስማኝ አንተ ስታቅፈኝ ደስ ብሎኛል።ግን ልቤ
አልመታም። እባክህ ንገረኝ እባክህ ባለፈው ህይወቴ ይህ ሰው
ምን አይነት ቦታ ነው ያለው?
በሚነግርኝ የፍቅር ታሪክ ውስጥ እኔና እሱን ሁሌም ተክቼ
እንደሳልኩኝ ነው። ንገርኝ ልለምንክ ብላ ሁለቱን እጆቹን ጥብቅ
አድርጋ ይዛቸው ተንበረከከች። የቦስ እና የዲና ዐይኖች በእንባ
ታጠበቡ እና የሄዋን ዐይኖችም በእንባ ታጥበዋል።
ቦስ ከሄዋን ጋር አብሮ ተንበረከከና "አታልቅሽ አታልቅሽ ሄዋን
እባክሽ ልለምንሽ። ለጊዜው ልነግርሽ እና ላስርዳሽ የምፈልገው
ጥሩ ሰው እንደሆንሽ በተጨማሪም እኔ ድጋሜ ብፈጠር እንኳን
እንዳንቺ ጥሩ ልሆን እንደማልችል ብቻ ነው"። አላት።
ዲና ወደ ሄዋን ተጠግታ ሄዋንን ጥምጥም አድርጋ አቀፈቻት ።
ሄዋንም ዲናን የበለጠ ጭምቅ አድርጋ አቀፈቻት። "እኔም እኔም"
አለች ዲና ። ደጋግሜ ብፈጠርም አንቺን መሆን አልችልም ጥሩ
ሰው ነሽ። እባክሽ አታልቅሺ ለቅሶ አደለም መከፋት አይገባሽም"።
አለቻት። ሄዋንም በደከመ ድምፅ "ታዲያ ጥያቄዬን መልሱልኛ"
አለች። ዲና "እሺ እህቴ አሁን እርፍት አድርጊ "አለች እና
እንድትነሳ እረድታት ወደ መኝታ ቤቷ እየወሰደቻት ሳለ ሄዋን ዲናን
"እህቴ" አለቻት። ዲና "ወዬ"
ስትላት። "አንቺ ባታስቆሚው ኖሮ እኮ እሱ ለእኔ ምኑ እንደሆንኩኝ
ሊነግርኝ ነበር ግን ለምን አስቆምሽው ለምን"አለቻት።ዲና የሄዋንን
ጥያቄ ምን ብላ እንደምትመልስ ጨነቃት። ከዛም ነይ እህቴ
እረፍት አርጊ ብላ ወደ መኝታ ቤት ወስዳት አልጋዋ ላይ
አስተኛቻት። ሄዋን አልጋዋ ላይ ሆና ማልቀሷን አላቆመችም።
ዲና የሄዋንን ፀጉር እያሻሸች ልክ እንደ እናት አባብላ አስተኝታት
ወጣች። ወደ ሳሎን ስትመለስ ቦስ የለም። ከሳሎን ወጥታ
ግቢው ውስጥ አየችው የለም ግራ ገባት "ወዴት ሄዶ ይሆን?"
አለች ለእርሷ ዘበኛውን በጩከት ጠርታው እየከነፈ መጣ
"አቤት" አላት። ዲና "እእእእ ቦስን አይተከዋል" አለችው። ዘበኛው
"አዎ አይቼዋለው
ከአዳም ጋር ነው የሄዱት አዳም መናፈሻው ጋር ቁጭ ብሎ
እያለቀሰ ነበር...

ይቀጥላል...


.............. ••● ●•..............

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን

https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን

https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3mDyzfx

◎◦#ሼር◦◎
◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo || @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
2.6K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, edited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 16:23:49
መልካም ልደት በፍቅር ጎጆ ስም


@yfiker_gojo
3.5K viewsAbela ŵiž ~V~, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:54:16 ቤተሰብ ለእናንተ ምንድን ነዉ?.የምታመሰግኑት ካለ አድርሱን?
3.5K viewsAbela ŵiž ~V~, 12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:43:54 ወደ LIVE ገባ ገባ በሉ
3.5K viewsAbela ŵiž ~V~, 12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:29:34 የማልቀይረው የማለውጠው ላንተ ያለኝ እኔ ፍቅር
ቃላት የለኝም ግን አብሮኝ ይኖራል ያንተ ውለታ እስከ መቃብር
muba

@Yefiker_Gojo JOIN US
3.8K viewsReal waver , edited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:19:02 በልብሽ አስበሽ የኔን ልብ ለመስበር
እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር
እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ
ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር

ሚል ግጥም ሰጥቼሽ ከቤቴ እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አንገቴን ቀብሬ
ቁጭ ብዬ አነባው

አየሽ! መለየትሽ ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው
ምን ላርግ ወንድ ልጅ ነኝና
ባደባባይ ስቄ ቤቴ ነው የማለቅሰው

Join & Share

@Yefiker_Gojo
@Yefiker_Gojo
5.2K viewsReal waver , 04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ