Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ጎጆ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_gojo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 479
የሰርጥ መግለጫ

Call us if you want to promote your product and service !!
FOR ANY PROMOTION
CONTACT ☎️ 251923715770 📩 @AbenaG

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-04 22:53:16
ፍቅር እስከ መቃብር

ዴርቶ ጋዳ

ዣንቶዣራ

ዝጎራ አንዲሁም የተለያዩ መጽሐፍትን በpdf ይፈልጋሉ? እንግዲያዉስ የፈለጉትን አማርጠዉ ያንብቡ

https://t.me/+TrYulHfpxS4yY2I0
54 viewspetelare Stay true, 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:48:02 ምኞት ክፋል 52 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . #የመጨረሻ ክፍል . . ድንገት እመካከላቸው ወጣ ገባ ስትል የነበረች አንዲት መኪና አቅጣጫ ቀይራ ከመሀላቸው ስትወጣ ሚኪ ዞሮ መኪናዋን የሚያሽከረክረው መሳይ መሆኑን ሲመለከት በድንጋጤ እየጮኽ ፅናት መንገድ መንገድ ዘግታ እንድታስቆመው አደረገ። መሳይም በሁኔታው እየተደነባበረ ከመኪናው ወርዶ ሮጦ ከመጣው ሚኪ ጋር ተቃቀፈ። ተያይዘው ወደ አንድ ሆቴል…
10.3K viewsflawoless , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:47:30 ምኞት

ክፋል 52

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
#የመጨረሻ ክፍል
.
.
ድንገት እመካከላቸው ወጣ ገባ ስትል የነበረች አንዲት መኪና
አቅጣጫ ቀይራ ከመሀላቸው ስትወጣ ሚኪ ዞሮ መኪናዋን
የሚያሽከረክረው መሳይ መሆኑን ሲመለከት በድንጋጤ እየጮኽ
ፅናት መንገድ መንገድ ዘግታ እንድታስቆመው አደረገ። መሳይም
በሁኔታው እየተደነባበረ ከመኪናው ወርዶ ሮጦ ከመጣው ሚኪ
ጋር ተቃቀፈ። ተያይዘው ወደ አንድ ሆቴል በማምራት እንዴት
ነገሮች ተቀይረው ለዚህ እንደበቃ እየጠየቀው በመሀል የፅናት
ስልክ ጠራ ። ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ተመለከተችው። ፊቷ
ተለዋወጠ።
" እኼ የማያፍር ሰይጣን ደግሞ ስልኬ ይደውላል እንዴ!" ብላ
ስልኩን በመዝጋት በንዴት ስትንጨረጨር ከመሳይ ጋር የጀመረውን
ጫወታ አቋርጦ•••
"ማነው ፅኑዬ?
" ያ ብሩክ ተብየው ነዋ!"
"ተይው አትበሳጪ ስራው ካንቺ በላይ እኔን ማበሳጨት
እንደነበረበት አውቃለሁ። ግን ደነዘዝኩ ባንዱ ጉዳት የተሰበረው
ልብሽ ሳይጠገን በጉዳት ላይ ጉዳት ሲደራረብብሽ የመበሳጨትም
አቅም ያጥርሽና ትደነዝዣለሽ። እንደ ብሩኬ አይነት ሰዎች ብዙ
ናቸው። ሲበዛ እራስ ወዳዴች ከመሆናቸው የተነሳ አንቺ ችግር
ውስጥ ስትገቢ ከዛ ችግር እንድትወጪ ከመርዳት ይልቅ
-በችግርሽ
-በእጦትሽ
-በስጋት እና በፍርሀትሽ
ሁሉ ተጠቅመው አንቺን እንዴት አድርገው ለፍላጎትና ለጥቅማቸው
መሳካት እንደሚጠቀምቡሽ ነው የሚያስቡት።
ብሩኬም እንደዚሁ ነው ያደረገው። በምኞት ላይ በፈፀምኩት
ክህደትና በደል ከባድ ፀፀት ውስጥ መውደቄን በፀፀት ውስጥ
ባገረሸው ፍቅሯ መጎዳቴንና የትም አለች ቢሉኝ እሷን ለማግኘት
የማልወጣው ተራራ የማልፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ሲረዳ
ሰው ቢሆን ኖሮ አጠገቤ ሆኖ ጉዳቴን በተጎዳ። ፍቅሬን ምኛቴን
ፀፀቴን እንዳገኛት ከጎኔ ሆኖ በደከመ። ግን እሱ ሰው ቢሆንም
እንደሰው እየኖረ አልነበረምና የኔን መጥፎ አጋጣሚ እራሱን
ጠቅሞ እኔን ለመጉዳት ተጠቀመበት አንድ ያለችኝ መፅናኛ እህቴን
አንቺን ሊያሳጣኝ ተሯሯጠ። ፈጣሪም ሩጫውን ገታው። ሀሳቡ
ሳይሳካ መንገድ ላይ አስቀረው። የኔ ምኛት ግን ጠፍታ አትቀርም!"
አለና እንባ ያቀረሩ አይኖቹን ጨምቆ አቀረቀረ።
መሳይ ሚኪ ያወራውን ሲሰማ በተቀመጠበት ልቡ መምታት
ያቆመች መሰለው ምድርና ሰማዩ ተገለባበጠበት።
በዛች ቅፅበት ምን እንደሚያወራ ፣ምን እንደሚል፣ ምን ማድረግ
እንዳለበት ማወቅ ተሳነው!።
ምኛት ታየችው የሚያጣት ሚኪ የሚወስድበት መሰለው። ብድግ
ብሎ ወደ ሽንት ቤት ለመኼድ አሰበና ጭንቅላቱ ውስጥ
የተፈጠረው ውጥረት፣ፍጭት እና ጩኸት ገና ከወንበሩ ሲነሳ
አዙሮ የሚደፋው መሰለውና መነሳቱን አልደፈረም።
እዛው በተቀመጠበት በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ እሱም እንደሚኪ
አቀረቀረ።
መሀላቸው ቁጭ ያለችው ፅናት ብሩክ ሲደውል የተንቀለቀለው
ንዴቷ ጠፍቶ በረዶ ሆነች።
የሁለቱንም ስሜት በየተራ እየተመለከተች ነበርና ሚኪ ባውራው
ነገር መሳይ ለእብደት የዳረገውን ያለፈ መጥፎ የፍቅር ሂወቱን
አስቦ የተረበሸ መሰላት ።
"እባክህ ሚኪ እንደዚህ አትሁን እሱንም ረበሽከው እኮ! እባክህ
ተረጋጋ!"
ብላው ደሞ ወደ መሳይ ዞራ "ድንገት አግኝተንህ ማሰብ
የማትፈልገውን መጥፎ ትዝታህን ስለቀሰቀስንብህ ይቅርታ እባክህ
አትረበሽ።
መሳይ ለፅናት መልስም አልሰጣትም። ቀናም አላለም።
ግራ ሲገባት ወደ ሚኪ ተጠግታ ገና ሚኪዬ ብሏ እንደተጣራች
ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ድፍት ያለውን መሳይን
እየተመለከተ•••
"ከሁሉም ነገር በፊት ትልቅ ይቅርታ እጠይቅሀለሁ መሳይ
ወንድሜ! ይቅርታ የምጠይቅህ ግን ዛሬ ስለረበሽኩ ሳይሆን ለቆየ
በደሌ ነው። በደሌ ምን እንደሆነና ለምን ይቅር በለኝ እንዳልኩህ
ኑዛዜየን ስጨርስ ትረዳዋለህ።
"አዋ ዛሬ ትክክለኛው ቀን ነው ከዚህ በፊት ብዙ ግዜ አግኝቼህ
ሊሆን ይችላል። ፍቅርህን ናርዶስን ከማጣትህ በፊትም እሷን
አጥተህ ልክ እኔ ዛሬ ቀን እንደጨለመብኝ በቀን ጨለማ
ተውጠኽም እንዳገኘሁኽ አስታውሳለሁ።
ግን መጎዳትህን አየሁ እንጂ ጉዳትህን አልተጎዳሁትም ነበር።
በፍቅር ህመም ክፉኛ መታመምህን ተመለከትኩ እንጂ ህመምህን
አልታመምኩትም ነበር። ካጠገብህ ዘወር ስል እረሳዋለሁ። ያንተ
እንደዛ መሆን አይገባኝም፣ አያስጨንቀኝም፣ አይቆረቁረኝም።
ዛሬ ግን ሕመምኽን ታምሜዋለሁና ጉዳትህን ተጎድቼዋለሁና ልክ
እንዳየሁኽ ስላንተና ስለናርዶስ የማውቀውን ሚስጥር ሳልነግርህ
ማለፍ አልቻልኩም። አቃተኝ።
ሚኪ ስለፍቅረኛው ናርዶስ እኔ የማላውቀውን ሚስጥር ይነግረኛል
ብሎ አልጠበቀምና ስለምኛት እያሰበ እሱን ከማድመጥ ውጪ
ቀናም አላለም።
"መሳይ ወላጅ አባትህ ጓደኛዬ ነው እሱን ይቅር የማለት እና
ያለማለት ያንተ ፋንታ ነው ለኔ ግን ሁለቱም ጓደኛቼ አንድ አይነት
ሰይጣኖች ናቸው አባትህ እና ብሩኬ!" አለ። እኼን ግዜ እንኳንስ
የመሳይ የፅናት የልብ ትርታ እጥፍ ሆነ ሚኪ ምን ሊያወራ ነው
ብላ ሁሉ ነገሯ ስራ ፈትቶ ሚኪ ላይ ተተከለች።
መሳይ "እኼ ሰው ደሞ ምን ሊያሰማኝ ነው ፈጣሪዬ እባክህ
የምችልበትን አቅም ስጠኝ። አለ አንገቱን እንደደፋ ፍርሀት ከላይ
እስከታች እየናጠው። ሚኪ ቀጠለ•••
" አባትህ ከናርዶስ ጋር የነበረኽን የፍቅር ግኑኝነት በጭራሽ
አይፈልገውም ነበር።
ይኽን አንተም ታውቀዋለኽ። ናርዶስን ያልፈለጋት ያጠፋችው ወይ
ያጎደለችው ነገር ስለነበር አይደለም። ጥፋቷም ጉድለቷም ድኻ
መኾኗ : ከድዃ ቤተሰብ መፈጠሯ ብቻ ነበር።
ባባትህ አይን ይቺ ያንተ ድኻዋ ናርዶስ እሱ ሊድርኽ ለፈለገው
ሰው እንዳይድርኽ መዃል የገባች የፍላጎቱ
መታከሚያ ሆስፒታል ሰው
ለመጠየቅ መጡ። ከሌሎቹ ህሙማን ጋር አልግባባ በማለቱ
ለብቻው ተገሎ በአንድ ሰፊ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ ወደ
ተፈረደበት አንድ የአይምሮ ህመምተኛ ( እብድ ) ክፍል እንደደረሱ
ወደ መስኮት ተጠግተው ወደ ውስጥ ሲመለከቱ•••
ክፍሉ ሰፊና ባዶ ነው። እክፍሉ ግድግዳ ላይ ሁለት ስእሎች አሉ።
አንደኛው ስእል የሴት ሲኾን ሌላኛው ደግሞ የወንድ ስእል ነው።
ከስእሎቹ ፉት ህመምተኛው ቆሟል። የወንዱን ስእል በቡጢና
በቴስታ ይመታል ግንባሩና እጁ ተጋግጧል ። የሴቷን ስእል
እየደጋገመ በፍቅር ይስማል። ወንዱን ሚኪ ሴቷን ፅናቴ እያለ
ይጠራ ነበር ። ያ ሰው ብሩክ ነው።
                  .
                  .
                  .

**ተፈፀመ**"


#ታሪኩ ይሄን ይመስላል...በትእግስት ስለተከታተላችሁን ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው.....ምን ያህሎቻችሁ ወዳችሁታል...? እስኪ በLike አሳዩኝ

ሀሳብ አ ስተያየት

አድርሱን!! እናመሰግናለን።።

መልካም -ምሽት

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
9.6K viewsflawoless , 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:47:30 የፒያሳዋ ወፍ #ክፍል አንድ እነሆ ተጀመረ ደራሲ ፦ ዘሪሁን ገመቹ ዋቅቶላ እባላለው፡፡ከክልል ለስራ ነው የመጣውት ፡፡እርግጥ አዲስ አበባ ስመጣ የመጀመሪያ ቀኔ አይደለም፡፡በተለያ አጋጣሚዎች በአመት አንዴም ሁለቴም ለቀናቶች ቆይታ እመጣለው፡፡አዲስ አበባ ለስራ ስመጣ ደስተኛ ሆኜ አይደለም የምመጣው፡፡አብዛኞቹ ነገሮቾ አይመቹኝም፡፡ልክ ከሆነ ሰርጐ ገብ ጠላት ጋር ለመፋለም ወደ በረሀ የተላኩ አይነት…
7.3K viewsflawoless , 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:47:30 የፒያሳዋ ወፍ
#ክፍል አንድ እነሆ ተጀመረ

ደራሲ ፦ ዘሪሁን ገመቹ


ዋቅቶላ እባላለው፡፡ከክልል ለስራ ነው የመጣውት ፡፡እርግጥ አዲስ አበባ ስመጣ
የመጀመሪያ ቀኔ አይደለም፡፡በተለያ አጋጣሚዎች በአመት አንዴም ሁለቴም ለቀናቶች ቆይታ
እመጣለው፡፡አዲስ አበባ ለስራ ስመጣ ደስተኛ ሆኜ አይደለም የምመጣው፡፡አብዛኞቹ
ነገሮቾ አይመቹኝም፡፡ልክ ከሆነ ሰርጐ ገብ ጠላት ጋር ለመፋለም ወደ በረሀ የተላኩ አይነት
ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ወደ ጦርነት እንደምሄድ አይነት፡፡
ሁለ ነገሯ የተጨናነቀ ነው፡፡ወከባ እና ኳኳታ የሚመረትባት የትርምስ ፋብሪካ
ትመስለኛለች፡፡የሰው ልጅ ከሰባአዊነት ዝቅ ብሎ በየጥጋ ጥጉ የተወሻሸቀባት ..እናት
ልጆቾን ለመለመኛነት የምትገለገልበት….ጎልማሳው ለማኝ የሰውን ልብ ለማራራት ሰውነቱን
የሚያቆሳስልባትና የሚቆራርጥባት መኖር የየእለት ፈተና የሆነባት….ሰው ለሆዱ ብቻ
ሲባትት የሚውልባት …ለአብዛኛው የወር የቤት ኪራዩን ከወር ደሞዙ እኩል የሆነባት….
የብዙ ምንድባኖች ማጠራቀሚያ መጋዘን ትመስለኛለች፡፡
ይሄን ስል በተቃራኒው በድሎት የሚቃትቱ ቱጃሮችን በውስጧ ሳላይ ቀርቼ አይደለም፡፡
በከተማዋ ዳርቻዎች እየታነፁት ህንፃዎች ከተማዋን የሲወዘርላድን ከተማ ነች እንዴ …?
ብለን እንድንገረም የሚያደርጉትን አፍን የሚያሲዙ ድንቅ መንደሮችም ታዝቤያለው.. ግን
ፖሊስ ስለሆንኩ መሰለኝ ዓይኖቼ ወደ ተገፉት ያደላሉ…ትኩረቴ ጓስቆሎች መንደር መክርም
ይወዳል፡፡
ላዳር የመረጥኩት ፒያሳን ነው፡፡ለምን ብትሉኝ ምክንያጽ የለኝም፡፡ግን አላውቅም
ጨለምለም ሲል እግሬ ወደእዛ መራኝ ፡፡የለበስኩት የሲብል ልብስ ነው፡፡በእጄም ምንም
አይነት ሻንጣ ወይም ሌላ ዕቃ አልያዝኩም፡፡ምክንያቱም ዕቃዎቼ ጠቅላላ ይዘናት የመጣነው
መኪና ውስጥ ነው ያስቀመጥኩት፡፡
ትንሽ ዞር ዞር ካልኩ ቡኃላ ከጣይቱ ሆቴል ቀጥለው ካሉ ሆቴሎች መካከል ወደ አንድ ጐራ
ብዬ ማደሪያዬን 150 ብር ተከራየው፡፡ቤርጐዋ መፈናፈኛ የሌላት በጣም ጠባብ ብትሆንም
ብዙም ግድ አልሰጠኝም፡፡‹‹ደግሞ ለአንድ ቀን…›› አዳር ብዬ እራሴን አጽናንቼዋለው፡፡
ቤርጐ ከያዝኩበት ክፍል ወጣውና በእግሮቼ መንቀሳቀስ ቀጠልኩ፡፡እራቴን እንዳልበላው
ያወቅኩት በመንገዴ ላይ የይሆሚያ ክትፎ ቤትን ሳይ ነው፡፡አንጀቴ በምግብ አምሮት
ግልብጥብጥ ስላለብኝ አላወላወልም ገባው፡፡
በጥንድም በብድንም የሆኑ ተመጋቢዎች በብዛት ይታያሉ …እኔም እጄን ታጥቤ መቀመጫ
ያዝኩ፡፡የቤቱ አብዛኛውን ነገሮች ባህላዊ እንዲመስሉ ለማድረግ ተሞክሮል …ያዘዝኩትም
ክትፎ ሲቀርብልኝ የበላውት በጣም ጣፍጦኝ ነው፡፡ቢሉ እጄ ላይ ሲደርስ ግን በተቃራኒው
እንዴት እንደጐመዘዘኝ አትጠይቁኝ፡፡አይ አዲስ አበባ …አንድም ለዚህ ነው የምታስጠለኝ..፡፡
እንድከፍል የተጠየኩት ብር እኮ በሀገሬ አንድ ደህና ጠቦት ይገዛል፡፡
ለማንኛውም ከፈልኩና ስወጣ ሰዓቱም ገፋ ብሎ ነበር ፡፡ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ›…በዚህ
ሳዓት ወደ መኝታዬ መመለስ አልፈለግም..በዚህ ሰዓት ገብቼ ልተኛም ብል እንቅልፍ እሺ
አይለኝም.. ..የአስፓልቱን ጥግ ይዤ በቀጥታ መንገዴን ቀጠልኩ…ግራና ቀኝ ያሉ አጥሮች
ሁሉ በቆነጃጅት ተሞልተዋል….በ14 ዓመት እና በ40 ዓመት መካከል ያሉ ሴቶች
እራሳቸውን ለገበያ አቅርበዋል፡፡ብቲክስ ውስጥ ለሽያጭ እንደተሰቀሉ የልብስ ሞዴሎች
ይመስላሉ ፡፡ልክ ሸማቹ መጥቶ በዓይኖቹ መርምሮ በእጆቹ ደባብሶ ይሆነኛል አይሆነኝም
ብሎ አመዛዝኖ ሂሳብ ተደራድሮ ቀንሱ አልቀንስም ተባብሎ ቀልቡ ከወደደለት ከፍሎ
አስጠቅልሎ ይዞቸው እንደሚሄድ ከልሆነው ደግሞ እዛው እነበሩበት ማንጠልጠያ ላይ
ሰትሮቸው ጉዞውን እንደሚቀጥል አይነት ነው፡፡
እኔም ልክ እንደሸማች እያንዳንዷን በአይኔ እየመረመርኩ፤ እየተደነቅኩ እና እየተገረምኩ
ጉዞዬን ቀጠልኩ …ያ ብቻ አይደልም የሚያስደንቀው እነዛው ቆነጃጅት የቆሙበት አጥር
ወይንም ግንብ ወይንም ቤት ግድግዳ ስር ማዳበሪያ ውስጥ ገብተው የተኙ፡በላስቲክ
ተጠቅልለው የተጋደሙ ፤በለበሱት ልብስ ተኮራምተው በተቀመጡበት ድፍት ያሉ የጓዳና
ልጆች ይታያሉ…የሚበላ ዕንቁላል ቅቅል የሚያዞሩ ጨቅላ ወጣቶች..ጥግ ይዘው ሲጋራና
መስቲካ የሚቸረችሩ..ኮንደምና ብሱክት በካርቶን ዳርድረው ሚሸጡ… ብዙ ብዙ ትዕይንት
ይታያል፡፡ነፍሱ አንድ ብር ስጠኝ…ቆንጆ አትለፈኝ…..ልጅ አዝለው በስራቸው ወደላይ እና
ወደታች ሚመላለሰውን ሰው የሚማፀኑ…….
ወታደሮችም መሳሪያቸውን ደቅነው በቡድን አምስትና ስድስት በመሆን በየሁለት መቶ ሜትር
ርቀት ልዩነት ይንጎራደዳሉ…አንዳንዴም መንገዱ ላይ የተኮለኮሉትን የምሽት ንግስቶችን
ከአንዱ የመንገዱ ጠርዝ ወደ ሌላው ያባርራሉ….ይመቶቸዋል መሰለኝ ሲመጡባቸው ግር
ብለው ይሸሾቸዋል፡፡
ብቻ ለእኔ ለገጠሬው ከማሰብ አቅሜ በላይ የሆኑ ብዙ የሚገርሙና ናላ የሚያዞሩ
ትዕይንቶችን ፒያሳን በመሽለኩለክ ስታዘብ ከቆየው ቡኃላ ደከመኝና ወደ አንዱ ሆቴል ጎራ
ብዬ ..አንድ ሁለት ማለት ጀመርኩ…ሆቴል ውስጥም ከጠጪዎች ቁጥር በላይ ቁጥር
ያላቸው ሴቶች ይርመሰመሳሉ‹‹አሁን እኚ ሁሉ እናትና አባት አላቸው አይደል…?እሺ እናት
አባት አይኑራቸው ወንድም እና እህት ያጣሉ..?እሺ እሱስ ይቅር አጎትና አክስት…?እኔ እንጃ
እኔ የገባኝ ብዙ ቤተሰቦች እዚህም እዛም እየፈረሱ እንደሆነ ነው…ምክንቱም እነዚህ ከፈረሰ
ቤተሰብ …ባይፈርስ እንኳን ተሸንቁሮ ማፍሰስ ከጀመረ ቤተሰብ ሾልከውና ተመዘው የመጡ
ብኩኖች ናቸው…ብዙ ቤተሰብ እዚህም እዛም መፍረስ ሲጀምር ደግሞ አገርም እየተናደች
መሆኑ ማሳያ ነው…እንደዛ ነው የተሰማኝ..፡፡ይንን እያሰላሰልኩ መጠጤን ከቢራ ወደ አልኮል
አዘዋውሬ ስጋት ..እናም ደግሞ በተከፈተው ሙዚቃ ስደንስ ..ከማላቃቸው መስል ጠቺዎች
እየተጋፋውን እየተሻሸው ሀገርኛውንም ፈረንጅኛውንም ሳስነካው ቆየውና ሺደክመኝና
ሽከሬም ጠንከር እያለ ሲመጣ …ምነካህ ዋቅቶላ ?አዲስ አበባ እኮ ነው ያለሀው
ይበቃሀል››አልኩና እራሴን በመምከር ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሂሳቤን ከፍዬ እራሴን
ላለመንገዳገድ እየጠራኩ የነበርኩበትን ሆቴል ለቅቄ ልወጣ ስል አብሬያቸው ስደንስ
ከቆየዋቸው የስካር ጎደኛቼ አንድ ጎትቶ ወደ ኃላ መለሰኝና አንድ ሙሉ ቢራ በእጄ
እያስጨበጠኝ ‹‹ነፍሱ በጣም ተመችታሀኛል..በዚህች መዚቃ የመጨረሻ ፈታ እንበል እና
ትሄጃለሽ›› አለኝ
ተወዳጅ መሆንን የሚጠላ የለምና ተወዳጅና ተመራጭ በመሆኔ ኩራት በውስጤ እየተሰማኝ
የተጋበዝኩትን ቢራ እየተጎነጨው በተከፈተው ሙዙቃ እስኪያልበኝ መወራጨት ጀመርኩ
አራት ሆነን ሆቴሉን መሀከል ክብ ሰርተን ቀወጥነው..ሙዚቃው እንዳለቀ አመስግኜቸው
ሹልክ ብዬ .ወደ ቤርጎዬ መንገድ ጀመርኩ…. እንሰደተቃረብኩ አንደ ልጅ እግር በብዥታ
ውስጥ ቢሆንም ደማቅ ቀይ መሆኖ የሚያስታውቅ እንስት ሳለስበው እየተጋላመጥኩ
ሳስተውላት ‹‹ሀይ ቆንጆ›› አለችኝ…ውስጤ ያለው የሴት ፍቅር ይሁን የጠጣውት መጠጥ
ፊቴን አዞርኩና ወደእሷ ቀረብኩ ተጠጋዋት..ጮርቃ ወጣት ብትሆንም ታምራለች…ግን
ሁለመናዋ የተንቀዠቀዠ ነው..አይኖቾ ራሳቸው ከወዲህ ወዲያ ይሽከረከራሉ..እጆቾም ከቀኝ
ወደ ግራ ይወናጨፋሉ..ምርቅን ቅን ብላለች መሰልኝ ከንፈሯንም እያኘከች ነው
‹‹እሺ ሰላም ነሽ?››ብዬ እጄን ዘረጋውላት..እንደመጨበጥ በመዳፎ ነካ አድርጋ መልሳ
ግንባሯን በማቀርቀር ፀጉሯን መጠቅለል ጀመረች‹‹..ቆንጆ ነሽ››አልኳት ሌላ ምላት ጠፍቶኝ
‹‹ሾርት ነው አዳር››አለችኝ እኔ ያልኳትን እንዳልሰማ ሆና
የምለው ግራ ገባኝ…የመዳራት ዕቅድ ፈፅሞ
8.0K viewsflawoless , 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 17:16:47 ጅንጀና Style part 1


1.1K views Star Waver , 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:06:30 ስሜን እረስቼ በስምሽ ልጠራ
አራዳው ይቅርብኝ እኔም ልሁን ፋራ
መቼም ያፈቀረ አይሆንም ቀብራራ

ስልጣኔው ይቅር ሱሪ ዝቅ ማድረጌ
መሰራቱን ልተው ፀጉር ማሳደጌ
እከተልሻለሁ በፍቅርሽ ወድቄ
እርሀቡንም ልርሳው ምክርሽ ይሁን ስንቄ


  ,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
         •═••• •••═•
  
    
    @Yefiker_Gojo    ,, @Pop_Muba
  ━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
3.2K views 𝖕𝖔𝖕 𝖒𝖚𝖇𝖆 , edited  09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 12:04:26

                     . . . #እሷ  . . .

      ማግኘትም ማጣትም በኔ አልተጀመረ
         ብዬ እፅናናለው አልሆን ሲለኝ ቀኔ
                 እሷን ያጣው እለት ግን
                  እራሴን አልሆንም እኔ

       ሁሉን ነገሬ ተወስዶ ትቅርልኝ እሷ ብቻ
         የህይወቴ ትርጉም የኑሮ ቅኔ መፍቻ

         በጨለማ ከመኖር ያወጣችኝ ደርሳ
            ለጎደለው ሀብቴ ሰላሜ ናት እሷ

          እሷ ብቻ ትኑርልኝ ትታይ ከፍ ብላ
    ህይወቴ ለርሷ ብቻ ነው አይደለም ለሌላ

         ፍቅር ማለት ያ ነው እንዲ ያለ ስሜት
ልብ እስኪጠፋ መውደድ ነብስን እስከመስጠት


━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
@Yefiker_Gojo    ,, @Pop_Muba
 
3.1K views 𝖕𝖔𝖕 𝖒𝖚𝖇𝖆 , edited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 22:03:11
#ሰይጣን_የማይችላቸው_8ቱ_ትምህርቶች



#አንድ- ደጋግማችሁ  የምታስቧቸው ሀሳቦች አካላዊ ተጓዳኞቻቸውን/አቻዎቻቸውን እንደሚስቡ አስታውሱ። ስለዚህ ስለምታስቡት ሃሳብ ተጠንቀቁ።

#ሁለት- ሁለት አካላት ሰውነታችንን እንደሚቆጣጠሩት ማወቅ አለብን።  ከእነዚህ አካላት አንዱ ለፍርሃት የሚነሳሳና ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን፣ ሌላው ለእምነት የሚነሳሳና ምላሽ የሚሰጥ ነው። 

በእምነት ትመራለህ ወይንስ ፍርሃት እንዲቆጣጠርህ ትፈቅዳለህ?

#ሶስት- ተስፋ ሳይቆርጡ ውድቀትን አልፎ የመሄድ አቅም በየትኛውም የህይወት ጥሪ ውስጥ የላቀ ስኬት ላስመዘገበ ሰው ሁሉ ዋና ሀብት ነው።

#አራት- ውድቀት ሰው ሰራሽ ነው።  ሰው እንደ ቋሚነት እስካልተቀበለው ድረስ ፈጽሞ እውን አይሆንም።

#አምስት- የአንተ ብቸኛ ገደብ በራስህ አእምሮ ውስጥ የፈጠርከው ነው።

#ስድስት- ተፈጥሮ ስራ ፈትነትን ወይም ባዶነትን አይታገስም።  ሁሉም ቦታ በአንድ ነገር የተሞላ መሆን አለበት።  ግለሰቡ አእምሮውን  ለአዎንታዊ እና ለፈጠራ ሀሳቦች መገለጫነት ካልተጠቀመበት ተፈጥሮ አእምሮን በአሉታዊ ሐሳቦች ላይ እንዲሠራ በማስገደድ ክፍተቱን ይሞላል።

#ሰባት- አንድ ሰው እውቀትን እንዲጨምር ወይም ዋናውን የህይወት አላማውን ለማሳካት የሚያስችሉ ልማዶችን እንዲያዳብር ሲያስገድድ ውድቀት ሁሌም በረከት ነው።

#ስምንት እርግጠኛ በሆነ የህይወት አላማ የሚንቀሳቀስ ሰው በጊዜያዊ ሽንፈት እና ውድቀት መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘባል። ዕቅዶቹ ሲከሽፉ ሌሎችን እቅዶች ይተካል እንጂ ዓላማውን አይለውጥም። በፅናት ይቀጥላል!

#የስኬት_ፍልስፍና መጽሐፍ

የናፖሊዮን ሂል መጽሐፍ

የስኬት_ፍልስፍና 10ኛ ዕትም

teklu ጥላሁን
8.7K viewsflawoless , 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:30:18 አይንሽ ሲርበኝ ሳቅሽ ሲጠማኝ
ህመምሽ ህመም ሆኖ ሲሰማኝ
ስሜ ይመስል ስምሽ ሲጠራ
ድንግጥ እርብትብት ስል እያየሽኝ
                  .
                  .
                  .
''ጠላሁሽ ስልሽ ለምን አመንሽኝ''





     ,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
         •═••• •••═•
  
    
    @Yefiker_Gojo    ,, @AbenaG
  ━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
8.6K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ