Get Mystery Box with random crypto!

ቃልህ እውነት ነው ዘኦርቶዶክስ /Your word is Truth Zorthodox/

የቴሌግራም ቻናል አርማ zorthdox — ቃልህ እውነት ነው ዘኦርቶዶክስ /Your word is Truth Zorthodox/
የቴሌግራም ቻናል አርማ zorthdox — ቃልህ እውነት ነው ዘኦርቶዶክስ /Your word is Truth Zorthodox/
የሰርጥ አድራሻ: @zorthdox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 609
የሰርጥ መግለጫ

🔶 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድሁም አጫጭር ትንታኔዋችና ዳሰሳ

🔵 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶች #ከሽልማት ጋር

🔷 የጥያቄዎቻችሁ መልስ

🔶 መጽሐፍ ቅዱሳዊ የቁጥር ዳሰሳዎችና ሌሎችም... #ቤተሰብ ይሁኑ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-28 08:40:13 በቅርቡ የመጽሐፍ ቅዱስ የቁጥሮች ዳሰሳ እንጀምራለን።
ለጥያቄና ለአስተያየት @Apophatism
145 viewsAbeni, edited  05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 15:32:18 ‍ ይህ የምትመለከቱት መጽሐፍ የእኔ የአይዋሽም መስቀሉ ሊታተም ያለ መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ማተሚያ ዋጋ 123500 አንድ መቶ ሃያ ሦስት ሺ አምስት መቶ ብር ሆነ። ከዚህ ውስጥ 50.000 ብር አረብ አገር በሚኖሩ አምስት እህቶቼ የተሸፈነ ነው። የጎደለኝን ማሳተሚያ ዋጋ ለመሙላት ግን ሁለት አመት የታገስኩ ቢሆንም በጦርነትና በኮረናም ምክንያት ሥራ ባለመኖሩ አልተሳካልኝም። አሁን ይህንን መጽሐፍ የማሳተሚያ ወጭ ለመሸፈን የሚጎድለኝ 50.000 ብር ነው። መለመን ከባድ ቢሆንም "ሕመሙን ያልተናገረ መድኃኒቱ አይገኝለትም" እንዲሉ ሕመሜን በመረዳት የተዋሕዶ ልጆች ሁላችሁ "አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለአምሳ ሰው ግን ጌጥ ነው" እንዲሉ አበው ። የምትችሉትን ታግዙኝ ዘንድ በእመቤቴ ስም እጠይቃለሁ።

የባንክ አካውንት ቁጥር
ንግድ ባንክ 1000 195 834 699
አቢስንያ ባንክ 91 97 12 16
ስልክ፦ 09 14 46 33 34
736 viewsAbeni, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 20:02:16 #አድስ_ስጦታ_በአድስ_ዓላማ

አድስ አመት አድስ ስጦታ ነው። ስጦነቱ ለግልም ለቤተሰብም ለሀገርም ጭምር ነው። በአድሱ አመት ምን ያህል እንደምንመላለስ ባናውቅም ብንጨርሰውም ባንጨርሰውም ከላይ የተሰጠ አድስ ስጦታ ነው። " በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው" ያዕ 1:17 እንዲል የሕይወት መጽሐፍ። በአድሱ ስጦታ በአድስ አላማ መማለስ ደግሞ የተሰጭው ግደታ ነው። " በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።" (የማቴዎስ ወንጌል 9:17)

አድስ ስጦታን (አድስ አመት) ተቀብለን ስናከብር መልካምና የሚያሳድግ አልፎም የሚለውጥ አድስ አላማና ግብ ሊኖረን ይገባል። አሮጌውን እርሾ ትተን በአድስ መነሳሳትና በአድስ መለወጥ መቀበል አስፈላጊ ነው።

አሮጌ እርሾ ለማንም አስፈላጊ አይደለም። "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።" ማቴ 16:6 እንዲል ከትክክለኛው ማንነትና ሕይወትም አውጭ ነው። ቃሉ እንዳለ የእርሾው መነሻ አዎቂ አስተማሪዎች የእምነት መሪዎች ነን ከሚሉት ከፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን (በአንጻሩ በወንበሩ ከተቀመጡት መሪዎች) እንደሆነ ይነግረናል። ለራሳቸው ዳቦቸውን በአሮጌ እርሾ እያቦኩ የሰውንም አብረው የማያውቁት ከማያቦኩ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው።

ትናንት አለፈ ዛሬ አድስ ነው። ትናንት በወሰነው ዛሬን ብንኖርም ነገን ግን የተሻለ ነው። ነገን የተሻ ለማድረግ ዛሬ መወሰን ዛሬ የማያሰፈልገንን ነገር ሁሉ ማስወገድ ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው። ከአላማም ከሰውም ከእርሾም ጠቃሚን አላማጣት የማይጠቅመንን መተው ለአድሱ የነገ ሕይወታችን አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው።

ሁሉም የተሰጠውን ስጦታ በመልካምም ይሁን በመጥፎው የተሰጠውን ስጦታ ይመላለሳል። ነገር ግን በዚያ በሎጥ ዘመን በሰአቱ የኃጢአትን ክብደት በሚነግረን ነገር ግን በከፈው (አሁን ደግሞ ያን የሚያስረሳ በሚፈጽመት ዘመን ሆነን) " ራስህን አድን፤ ወደ ኃላ አትይ" (ዘፍ 19:17) ላይ ሆነን ስጦታ ስንቀበል እንደ ሎጥ #ራስን_ማዳን ላይ ማተኮር አለብን። እኛ ስንኖር ነው አላማችን የሚሳካው። እኛ ስንኖር ነው አድስ ስጦታ የሚሰጠን።

በአሮጌው አመት ብዙ ነገሮች ተፈራርቀው ይሆናል። የእኛ የምንለውን አተን ፣ የአመነውና የምንወደው ከድቶንና ዋሽቶን ፣ ወንድም የምንለው ክብራችንን ዝቅ አድርጎን ፣ ለእሱ የምናስብለት ለእኛ ጉድጓድ ቆፍሮብን ወዘተ ይሆናል። በመልካሙም ጥሩ አጋጣሚዎች ተፈጥረውልን ፣ ሕይወትን የሚያጣፍጡ ወንድሞች የሕይወት አጋር ፍቅረኛ ተሰጥቶን ፣ አላማችንና ግባችንን ከአቀድነው በላይ አሳክተን ይሆናል። እነዚህ ሁሉ አለፈ በምንለው አመት ውስጥ የነበሩና ያለፍ ናቸው። ገምግመን በአድሱ ስጦታው ውስጥ ማለፍ ያለባቸው አልፈው መተው ያለባቸው ተትተው አድሱን ስጦታ መቀበል አለብን።

በሕይወት መስመር ሕይወትን የሚያበላሹ እሾኆች እንዳሉ ሁሉ ሕይወትን የሚያጣፍጡ መልካም ዘሮች መኖሩ ሕይወትን በአንጻራዊ ሚዛናዊ ያደርጋታል።

በአሮጌው አመት መልካም እርሾ ለሆናችሁኝ ሁሉ ክብር ይስጥልኝ። በአድሱም ስጦታ መልካምነታችሁ እንደማገኛው ተስፍ አለኝ። ነገር ግን የፈርሳውያንና የሰዱቃውያን እርሾ #ለሆናችሁብኝ_ለሆንኩባችሁ #በይቅርታ አሮጌውን እንዝጋው። በአድሱ ስጦታ ይህ እንደማይቀጥል ተስፍ አለኝ።

በስጦታየ ውስጥ ስጦታ ለሆናችሁ ሁሉ ለእናንተ ፤ አድሱ ስጦታችሁን በመልካም በደስታና በሀሴት ያኑርልኝ።

አድሱ ስጦታ #ለሁላችንም አላማችንን የምናሳካበት ፣ ተያይዘን የምንለወጥበት ፣ መልካምነት የሚነግስበትና አመቱ የምንጨርስበትና አድስ ስጦታ በመልካም የምንቀበልበት ያድርግልን።
1.5K viewsAbeni, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-23 11:51:08 ምክረ አበው

እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል፡፡ እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል፡፡ ጊዜ በማንኛውም ሰዓት ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ

ምን አልባት አንተ ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ጊዜ ግን ካንተ የበለጠ ጉልበተኛ ነው አስብ አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡

አንድ መጥፎ ስራም ብዙ መልካምነገሮችን ታጠፋለች፡፡ ዋናው ነገር በአስተሳሰብ መልካም ሁን ረጋ ብለህ አስብ ለሁሉም ጊዜ አለው አትጨነቅ !
መልካም/// አዳር
1.4K viewsAbeni, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-19 11:48:11 የመጽሐፍ ቅዱስ አስገራሚ እውነታዎችና ታሪኮች/Amazing Bible Facts/

ነብዩ አሞጽ ላም ጠባቂ እና ዋርካ ለቃሚ ሰው ነበር።" [አሞጽ 7:14]

ብቸኛ ነብይት ሚስት የነበረችው ነብይ ነብዩ ኢሳይያስ ነው። [ትንቢተ ኢሳይያስ 8:3

በመጽሐፍ ቅዱስ በረዝመት ከሚጠቀሱት ስሞች ቀዳሚው #ምርኮ_ፈጠነ_ብዝበዛ_ቸኰለ ይባላል። (ትንቢተ ኢሳይያስ 8:4)

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 136 ላይ ብቻ "ምህረቱ ለዘላለም ነውና" የሚለው 26 ጊዜ ተጠቅሷል።

መጽሐፈ መክብብ ውስጥ 24 ጊዜ "ከፀሐይ በታች" የሚለው ቃል ተጽፏል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ረጅም ስም ያለው ንጉስ "ቴልጌልቴልፌልሶር" ይባላል። [2ኛ ነገ 16፥10]

@zorthdox
1.6K viewsAbeni, 08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-13 20:57:52 _ የሕይወትትምህርት _
አራት ልጆች የነበሩት አንድ ሰው ነበር፡፡ እናም ልጆቹ በነገሮች ችኩል እንዳይሆኑና ቀድመው ማደማደምን (#quick judgment) እንዳይለምዱ የሕይወት ትምህርት ያስተምራቸው ዘንድ ወደደ፡፡

ስለሆነም ከአካባቢያቸው በብዙ ርቀት የሚገኝ ዛፍን አይተው ያዩትን ነገር ይዘው እንዲመጡ ተልዕኮ ሰጥቶ አሰማራቸው፡፡

የመጀመሪው ልጅ፡ በበጋ ሁለተኛው በበልግ ሦስተኛው በክረምት አራተኛውና የመጨሻውን በመከር ደርሰው ያዩትን ይዘው እንዲመለሱ አደረገ፡፡

የመጀመሪያው ያየውን ሲያቀርብ…ዛፉ በጣም አስጠሊታ ነው፡፡ ተጣጥፏል፣ ተሰባብሯልም አለ፡፡

ሁለተኛው ቀጠለ በአረንጓዴ ልምላሜ የተሞላ ቅርንጫፍ አውጥቷል ለወደፊትም የማፍራት ተስፍ ይታይበታል ሲል ያየውን አብራራ፡፡

ሦስተኛው በዚህ አባባል አልተስማማም እሱ ያየውን ለአባቱ ሲያቀርብም ዛፉ በአበባ ተጨናንቋል ያበቦቹ መዓዛም እጅግ ያውዳል እናም በጣም ቆንጆ ነው፡፡ እንደዛ አስደሳች ነገር ከዚህ በፊት በሕይዎቴ አላየሁም ሲል ባግራሞት ተናገረ፡፡

የመጨረሻው ልጅ ቀዳሚዎቹ ሦስቱ ወንድሞቹ ባቀረቡት አልተስማማም፡፡ እናም እንዲህ አለ ዛፉ በበሰሉና እጅግ ባማሩ ፍሬዎች ተጨናንቋል ሕይወትንም በደስታ ይሞላል፡፡ አለ።

አባት የሁሉንም እይታ ካዳመጠ በኋላ ሀላችሁም ትክክል ናችሁ ምክንያቱም ያያችሁት አንድ ዛፍ ቢሆንም ያያችሁበት ወቅት ግን ለዛፉ ሕይዎት የተለያየ ትርጉም ባላበት ወቅት ነው፡፡

አስከትሎም እንዲህ አላቸው ሰውንም ሆነ ዛፍን በአንድ ወቅት ገጽታ ብቻ እንዲህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም፡፡#ሕይዎትን በችግራችን ወቀት ብቻ ከተረጎምናት፤ በበጋው ዛፉ ደርቆ እንደታየው ካየናት እንጠላታልን የበልጉን ተስፋና የክረምቱን ውበትም አናየውም፡፡ የሕይዎት ጥፍጥና የሚመዘነው በሁሉም ወቅቶች ድምር እንጅ አንደኛው ወቅት በፈጠረው ገጽታ ብቻ አይደለም ፡፡

#የሕይወት ትምህርት፡
ያንድ ወቅት ችግር የቀሪ ሕይወትህን ደስታ እንዲያበላሸው አትፍቀድለት፤ሕይዎትንም ባስቸጋሪው ወቅት በነበረህ መነጸር አትያት፣ ሕይወትን በአንድ ክፉ አጋጣሚ ወክለን አንያት፣ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ነገም ሌላ ቀን ነው ብለህ ጽና እናም የተሻለው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሁን።

https://t.me/Hesychasm
https://t.me/Hesychasm

አስተያየት ከአላችሁ
https://t.me/aywashimmeskelu
1.4K viewsAbeni, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-13 20:57:52 https://t.me/Aywashimmeskelu/276
975 viewsAbeni, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 17:06:08 #የነገሮች_ክብደት_የሚለኩት_በባለቤቱ_ነው


ኤርያል ካስትሮ ከአስር ዓመት በፊት ሶስት አሜሪካውያን ወጣት ሴቶችን አፍኖ ቤቱ አስቀመጠ። ለ 10 ዓመት ያህልም የፈለገውን እያደረገ ሲያሰቃያቸው ኖረ። ዋጋ የማይተመንለትን ወጣትነታቸውን
ወሰደባቸው (ሰረቃቸው)፣ በዚያ ጨለማ በምድር ቤቱ ውስጥ አስቀምጧቸው አስር ዓመት ያህል ሲቆዩ እንወጣለን ብሎ ማሰብ ረስተው ነበር።

ቦ ጊዜ ለኩሉ (ለሁሉም ጊዜ አለውና) አንድ የተመረጠች ቀን ምክንያት ተፈጥሮ ነጻ ወጡ። ከዚያ ኤርያል ካስትሮ ተያዘ አሜሪካም የቀረውም ዓለም ጉድ
አለ !

ጨካኙ ካስትሮ ፍርድ ቤት ቀረበውሳኔ ተሰጠው ፣ የፍርድ ቤቱም ውሳኔ - ሞትን አስቀረና ዕድሜ ይፍታህ ፈረደበት። እዚያም ሞትን አመለጠ። ከዚያ እስር ቤት ገባና የ እስር ኑሮውን ሀ ብሎ ጀመረ። ለካ ከዚህ ሁሉ ከውጭ ሊመጣ ይችል ከነበረው የሞት ፍርድ ያምልጥ እንጂ፣ ህሊናው ፈርዶበት ነበር። ከሁሉም የህሊናው ፍርድ ፣ ጸጸቱ ፣ የጥፋተኝነት ስሜቱ ፣ የበደለኝነት ግለቱ አላስቀምጥ ቢለው ራሱን አንቆ የራሱን ህይወት አጠፋ ተባለ።

በምንሰራው ግፍና በደል ከሌላው ዓለም ፍርድ እናመልጥ ይሆናል። ከራስ ህሊና ግን የት እናመልጣለን? ሰዎች ላይ ግፍና
በደል ሰርተን ፣ አገር በመቀየር ፣ በገንዘብ ፍርድ በመግዛት፣ ስማችንን በመቀየር፣ በትልቅ ግንብ በመከለል የምናመልጥ
ይመስለን ይሆናል ፤ ትልቁ ፈራጅ ህሊናችንን ግን የትም አናመልጠውም።


የቦታና የጊዜ እንድሁም የተዘራበትና የሚታጨድቀት ሁኔታ ቢለያይም ሆነ ቢራራቅም #እውነታው ግን በምድርም ይሁን በሰማይ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል።
1.1K viewsAbeni, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-01 13:36:54 አንተ ካልወሰንክ ሌላ ሰው ይወስንልሃል!

/

የአሜሪካ 40ኛው ፕሬዘዳንት ሆኖ ያገለገለው ሮናለድ ሬገን (Ronald Reagan) ውሳኔ የማስተላለፍን አስፈላጊነት ገና በልጅነቱ እንደተማረ ይናገራል ፡፡

ገና በልጅነቱ አንድ ጊዜ አክስቱ አዲስ ጫማ ልታሰራለት ወደ ጫማ ሰሪ ቤት ወሰደችው ፡፡ ጫማ ሰሪው እግሩን ከለካው በኋላ ...

“ እንዲሰራልህ የምትፈልገው ጫማ ቅርጹ ከእግር ጣቶች ጋር ክብ እንዲሆን ነው ወይስ አራት ማዕዘን እንዲሆን ነው የምትወደው?” ብሎ ጠየቀው፡፡

ሮናልድ ሬገን መወሰን አቅቶት ሲወላውል ጫማ ሰሪው “ ችግር የለውም ትንሽ ቀናት አስብበትና ትነግረኛለህ” አለው፡፡

ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጫማ ሰሪው ሬገንን መንገድ ላይ አገኘውና፣ “የጫማውን ቅርጽ ጉዳይ ወሰንክ?” ብሎ ጠየቀው፡፡

ሬገንን፣ “ገና አልወሰንኩም” ብሎ መለሰለት፡፡

ጫማ ሰሪው “እሺ” ብሎ መንገዱን ከቀጠለ በኋላ በሚቀጥለው ቀን ጫማውን ሰርቶ እቤቱ ድረስ ላከለት፡፡ ሬገን ጫማውን ሲያየው የቀኝ እግር ጫማው ቅርጽ ክብ የግራ እግር ጫማው ቅርጽ ደግሞ አራት ማዕዘን መሆኑን ሲመለከት በጣም ደነገጠ፡፡

“ከዚያን ጊዜ ጀምሮ” ይላል ሬገን፣ “እነዚያን የግራና የቀኝ እግር ጫማዎች ባየኋቸው ቁጥር ስለ ውሳኔ ትልቅ ትምህርትን ያስታውሱኝ ነበር::

“አንተ የራስህን ውሳኔ ካልወሰንክ፣ ሌላ ሰው ለአንተ ይወስንልሃል፡፡ የውሳኔውን ውጤት የምትኖረው ግን አንተው ነህ :: "

በሕይወትህ በፍጹም ለሰው የማትተዋቸው “ወሳኝ ውሳኔዎች” እንዳሉ ታውቃለህ?!

በተለይም የሕይወትህን አቅጣጫ እስከወዲያኛው በሚያስቀይሩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔህን ችላ ባልከውና ሰው እንደፈለገ እንዲያደርገው በፈቀድክ ቁጥር ሌላ ሰው ይወስንልሃል፡፡

በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ሌላ ሰው የወሰነልህን ውሳኔ መራራ ፍሬ እየበሉ እንደመኖር አስቀያሚ ነገር የለም፡፡

በሕይወታችን “ሁለት አይነት ጫማ አድርገን” ወዲህና ወዲያ የምንንገላታው የምንፈልገውን ነገር ቁርጥ አድርገን አውቀን ውሳኔያችንን እኛው ስላልወሰንን ነው፡፡

በጥንቃቄ፣ በጥበብና በሚዛናዊነት ከሰው ምክርንና ጥበብን ለመቀበል ክፍት የመሆንህን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ . . .

// //

• የሕይወትህን ዓላማ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡

• የቀረውን ሕይወትህን ከማን ጋር በፍቅር እንደምትኖር ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡

• የምትማረውን የትምህርት ዘርፍ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡

• ከፈጣሪ የተቀበልከውን ማንነትህን የመኖርና ራስህን የመሆንህን ጉዳይ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡

ሰዎች በአንተ ውስጥ ሆነው የመኖራቸውና የመወሰናቸው ዘመን ያብቃ!

ከbookforall ገጽ የተወሰደ
1.1K viewsAbeni, 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-19 12:16:54 አልመህ ተኩስ

አንድ ንጉስ ከአጃቢዎቹ ጋር በአንድ ጫካ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ዛፍ ላይ ያየው ነገር ትኩረቱን ሳበው፡፡ በዚህ ትልቅ ዛፍ ላይ የተለያዩ ክብ ቅርጽ ያላቸው ኢላማዎች ተስለዋል፡፡ የገረመው ነገር፣ እያንዳንዳቸው ኢላማዎች መካከል ምንም ሳይስቱ ኢላማቸውን በትክክል የመቱ ቀስቶች ተሰክተው ይገኛሉ፡፡ ንጉሱ በጣም ተገረመና፣ “እነዚህን ኢላማዎች ሁሉ በትክክል አነጣጥሮ የመታውን ሰው ለሰራዊቴ አለቃነት እፈልገዋለሁና ፈልጋችሁ አግኙልኝ” አለ፡፡

ልክ ይህንን ተናግሮ እንደጨረሰ አንድ ወጣት ልጅ ብዙ ቀስቶችን ተሸክሞ እየገሰገሰ ንጉሱ ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሱ፣ እነዚህን ሁሉ ኢላማዎች በትክክል የመታው ሰው እሱ መሆኑን ጠይቆ የአዎንታ መልስ ካገኘ በኋላ እንዴት እንደዚህ አነጣጣሪ ሊሆን እንደቻለ ጠየቀው፡፡ የልጁ መልስ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “በመጀመሪያ ቀስቴን ወጥሬ በዛፉ ላይ እሰካዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ዛፉ በመሄድ በተሰካው ቀስት ዙሪያ የክብ ምልክትን አስቀምጥበታለሁ” በማለት እንደዚያ አነጣጣሪ ያስመሰለውን እውነት ፍርጥ አደረገና ነገረው፡፡

ይህ መሰረታዊና ቀላል አፈ-ታሪክ የብዙ ሰዎችን የሕይወት ዘይቤ ያንጸባርቃል፡፡ ይህ ወጣት በመጀመሪያ ዓላማን አድርጎ አልነበረም ያንን ዓላማ ለመምታት ጥረት ያደረገው፡፡ በቅድሚያ ወዳሻው ቀስቱን ከለጠጠና ከሰነዘረ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ስፍራ ነው እንደዓላማ በመቁጠርና ልክ ዓላማውን እንደመታ ለማስመሰል በዙሪያው ክብን ያበጀለት፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ዒላማንና ግብን አቅደው በዚያ ባቀዱት መሰረት ሊተኩሲ ሲገባቸው ከተኩሱ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ነው እንደግብ የሚቆጥሩት፡፡ በሌላ አባባል፣ ያገኘነውን፣ የመሰለንንና የቀለለንን ነገር ካደረግን በኋላ በዚያ ባደረግነው ተግባር ዙሪያ ዓላማን ለመፍጠር መሞከር የሞኝነት ሁሉ ሞኝነት ነው፡፡ ዓላማ ከሌለን የምንሄድበትን አናውቅም፡፡ ግብም ከሌለን ተኩሰን የመታነው ነገር ሁሉ እንደ ግብ ስለሚቆጠር ይህንና ያንን ስናደርግ ጊዜያችን ይባክናል፡፡ ለዚህ ነው በዓላማና በግብ የምንመራ ሰዎች መሆን ያለብን፡፡

አንድ በር ተከፍቶ ስላገኘህ ብቻ ከገባህ በኋላ የገባህበትን ዓላማ ለማግኘት አትሯሯጥ፤ በመጀመሪያ በዚያ በር የመግባትህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማ ጋር መስማማቱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሃገር የመሄድ እድል ስለተገኘ ብቻ ከሄድክ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትሂድ፤ በመጀመሪያ ወደዚያ ሃገር የመሄድህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማህ ጋር አለመጣረሱን አረጋግጥ፡፡

አንድ ሰው ትኩረትና የመፈቀር ስሜት ስለሰጠህ ብቻ ሁለንታንህ በመስጠት ግንኙነት ውስጥ ከገባህ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትታገል፤ ጓደኛንም ሆነ ፍቅረኛን ከዓላማህ አንጻር ምረጥ፡፡

ስራህንም እንደዚያው! ትምህርትህንም እንዲዚያው! የሕይወትህን ዋና ዋና ክፍሎችም እንደዚያ!

ከዓላማ ተነሳ እንጂ ተነስተህ ከተጓስክ በኋላ ዓላማህን ለማግኘት አትባክን፡፡ ዓልመህ ተኩስ እንጂ የተኮስከው ነገር የመታውን ነገር ሁሉ ዓላማህ እንደሆነ በማሰብ ራስህን በማታለል ዘመንህን አታባክን

ዶ/ር ኢዮብ
1.2K viewsAbeni, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ