Get Mystery Box with random crypto!

Wõrld is fúll œf lâgñiäppë✌️

የቴሌግራም ቻናል አርማ halaandniha — Wõrld is fúll œf lâgñiäppë✌️ W
የቴሌግራም ቻናል አርማ halaandniha — Wõrld is fúll œf lâgñiäppë✌️
የሰርጥ አድራሻ: @halaandniha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 104
የሰርጥ መግለጫ

As long as u have Allah there is no reason to loss hope, to give up ለዚህም ነው ሁሌም አለማችን full of lâgñiäppë ማለትም ህይወት በስጦታ የተሞላች ናት ... So don't ever be pessimistic rather than be optimistic.
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት @Nihuhoney_bot and @Halanihu_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-18 11:02:51 የራሳችሁን ጽሑፍ ማረም አትችሉም!

ብዙ ጊዜ ሞክሬ ያቃተኝ ነገር ልንገራችሁ፡፡ ጽሑፍ ስጽፍ የምሰራቸውን የፊደልም ሆነ የአገላለጽ ስህተቶች እኔው ራሴው ለማረም በማደርገው ደጋግሞ የማንበብና ጽሑፌን የመከለስ ሙከራ አንድም ቀን ተሳክቶልኝ አያውቀም፡፡

ያንን ካደረኩኝና “አሁን ጽሑፌን ጸዳ አድርጌዋለሁ” ብዬ ከደመደምኩኝ በኋላ ባለቤቴ ያንን ተቀብላ በማንበብ ቁጥር ስፍር የሌለው ስህተት በቀይ ቀለማት አቅልማ ትመልስልኛለች፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያ ሰው ራሱ የሰራውን ስህተት ራሱ የማየትና የማረም እድሉ እጅግ ጠባብ በመሆኑ ነው፡፡ ስህተቱን የሰራው አስተሳሰብና ምልከታ እርማቱን ለማድረግ ያለው አቅም አናሳ ነውና!

ራሳችንን ለማረምና ለማሻሻል ከፈለግን አጠገባችን ያሉ ሰዎች የሚነግሩንን እርማት እንስማ! አለቀ!

አዋቂ ናችሁ ማለት፣ አለቃ ናችሁ ማለት፣ ጎበዝ ናችሁ ማለት፣ ባለጠጋ ናችሁ ማለት፣ ስልጣን አላችሁ ማለት . . . አትሳሳቱም ማለት አይደለም፡፡ ለእርማት ልቦናችሁን ብትከፍቱ ሕይወት እጅግ ቀላል ትሆንላችኋለች፡፡

ግትር አትሁኑ! እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ አትበሉ!
70 viewsMame eta , 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 06:43:01
የነገው ጉጉት!

አንድ ሰው እንደዚህ አለ፣ “የእኔ ጉጉት በወደፊቱ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የቀረውን ዘመኔን የማሳልፈው አዚያ ስለሆነ”፡፡
በትናንትናው ሕይወት ከመኖር ይልቅ ካሳለፍነው ነገር ተምሮ ማለፍ የተሻለ ነው፡፡ ከትናንቱ ከመማር ይልቅ በዚያ ላይ መኖር ኋላ ቀር ያደርጋል፡፡

በዛሬው ሕይወት ከመማረር ይልቅ በደስተኛነት መኖር የተመረጠ ነው፡፡ በዛሬ ሕይወት ደስተኛ ከመሆን ይልቅ ማማረር ተስፋ ቢስ ያደርጋል፡፡

በነገው ላይ መጓጓት ማለት ራእይንና ሕልምን መለየት፣ ወደዚያ የሚወስደንን እቅድ ማውጣት፣ ሁሉንም ነገር ከዓላማ አንጻር በመቃኘት መኖርና በየቀኑ ወደዚያ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ማለት ማለት፡፡

ከትናንት ተማሩና እደጉ!!! ዛሬን በመኖር ተደሰቱ! በእቅድና በታላቅ ጉጉት ደግሞ ወደ ነገው ተንቀሳቀሱ!
78 viewsMame eta , 03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 12:43:09 እውነተኞች እንሁን!

የአንድን ሰው እውነተኛ ማንነት ለማወቅ ከፈለክ እኩዮቹንና የበላዮቹን ሳይሆን የበታቾቹን በእንዴት አይነት ሁኔታ እንደሚያስተናግድ ተመልከተው፡፡ ከሰዎች ጋር ያለውን አቀራረብም ሆነ ለሰዎች የሚያሳየውን ሁኔታ በወቅቱ ከሚያገኘው ጥቅም አንጻር ሳይሆን በእውነትም ካለው ትክክለኛ አመለካከት በመነሳት የሚያደርግ እውነተኛ ሰው የሚታወቀው በዚህና በዚህ ብቻ ነው፡፡

እውነተኞች እንሁን! ትክክለኞች እንሁን! ጨዋነት ይገኝብን!
70 viewsMame eta , 09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 12:28:56 የዓላማና የተስፋ ግንኙነት

በአንድ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታራሚዎች በቂ የሆነና የተሟላ የምግብ አቅርቦት ነበራቸው፡፡ ከተወሰነ የማረሚያ ቤት ቆይታቸው በኋላ እርስ በርሳቸው ስለተላመዱ በተለያዩ ጨዋታዎች እየተደሰቱና አንዳንድ ሞያ ነክ ነገሮችንም እየሰሩ መረጋጋት ጀምረዋል፡፡

ብዙም ሳይቆዩ ግን ሁሉንም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተጫጫናቸው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተስፈኛ ሆነው የመቆየት አቅማቸውንም አጡ፡፡

የሆነው ነገር ይህ ነው፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሲነሱ በማረሚያ ቤቱ ግቢ አንድ ጥግ ላይ የተከመሩ አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ነበሩና እነዚህን ጆንያዎች ካሉበት በማንሳት ወደሌላው የማረሚያ ቤቱ ግቢ ጥግ እንዲወስዱና እንዲከምሯቸው ተነገራቸው፡፡ ሁሉም ታራሚዎች በመነሳሳት ያንን ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ ከዚያም ወደማምሻው ላይ ጠዋት ወስደው የከመሩትን የጆንያ አሸዋ ክምር ወደ ነበረበት እንዲመልሱ ታዘዙና ይህ ስራ በየቀኑ እንደሚቀጥል ተነገራቸው፡፡

እነዚህ ታራሚች በተወካያቸው በኩል አሸዋ የሞላባቸው ጆንያዎች ወዲያና ወዲህ የሚመላለሱበት ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ምንም ዓላማ የሌለው ተግባር እንደሆነና አርፈው እንዲታዘዙ ተነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ስሜታቸው በጣም የወረደው፡፡

ምንም ዓላማ የሌለውን ተግባር ሲደጋግሙ መኖር ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ምናልባት ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ የሚጫጫነን የመኖራችንን ዓላማና ትርጉም እንዲሁም በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች ለምን እንደምናደርጋቸው ዓላማቸውን በሚገባ ስላላወቅነው ይሆን?
95 viewsMame eta , 09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 06:26:31 “የመገፋት ስስነት”
(“የመገፋት ህመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በስነ-ልቦናው ቋንቋ “የመገፋት ስስነት” (Rejection Sensitivity) የተሰኘው ሃሳብ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ጥቃቅን የሰዎች ሁኔታ ከመገፋትና ከመገለል ጋር የማዛመድ ስስነትንና ዝንባሌን የሚያሳይ ጽንሰ-ሃሳባ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በመገፋት ዙሪያ እጅግ ስስ ከመሆናቸው የተነሳ እንደተገፉ የመሰላቸው ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሲመለከቱ የመደናገጥና የመዋረድ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰዎች ሲያስጠብቋቸው፣ ስልካቸውን ካልመለሱላቸውና እንደዚህ የመሳሰሉ “አናሳ” የሆኑ ክስተቶች የዝቅተኝትን፣ የመናቅንና የመገለልን ስሜት ያመጣባቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ዝንባሌን አስመልክቶ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የዚህ ተጽእኖ ሰለባዎች፣ ሰዎች በፊት ገጽታቸው የሚያሳዩት ሁኔታ እነሱን ያለመቀበልና የመግፋት ምልክት እንዳለው ሲሰማቸው የአንጎል እንቅስቃሴያቸው (Brain Activity) በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም፣ እነሱን የመግፋት ወይም የማግለል ገጽታ ሊኖረው የሚችልን ማንኛንም እንቀስቃሴም ሆነ ንግግር በንቃትና ሁኔታዎችን በማዛመድ የመመልከትና የመጠባበቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡

የዚህ ዝንባሌ አንዱ ጫና፣ አድልዎ-ተኮር ምላሽ (Attention Bias) ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ለአስር ሰዎች የፍቅር ጥያቄ አቅርበው ዘጠኙ ተቀብለዋቸው አንዱ ብቻ ፍላጎት እንደሌለው ቢገልጽላቸው፣ እነሱ የሚያተኩሩትና ስሜታቸውን የሚነካው የዘጠኙ እሺታ ሳይሆን የአንዱ እምቢታ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረትን ከመገፋት አንጻር ብቻ የመቃኘት አድሎአዊ አመለካከት የሚያስከትልባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በማሕበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም (ምንጭ፡- verywellmind.com)፡፡

ሁኔታውን ስንጨምቀው፣ በመገፋት ስቃይ ውስጥ ያለፈ ሰው የሰዎችን፣ በተለይም በእነሱ ሕይወት ስፍራ እንዳላቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እያንዳንዱን ተግባር በመገመት በመላ-ምት የመኖር ዝንባሌ ያጠቃቸዋል፡፡ ይህ አሉታዊ-ገማችነት ገደብ የሌለው ሃሳብ-ወለድ አለም ውስጥ እንዲዋዥቁና የሌለንና ያልተፈጠረን ነገር በውስጣቸው እንዲያሰላስሉ ያደርጋቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች አንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት አለም ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያሰላስሉት ውለው ያደሩት ነገር በእነሱ ውስጥ “የሌለ እውነታ” ሆኖ ይኖራል፡፡ የዚህ ስሜት ውጤት ሰዎች የሚያደርጓቸውንም ሆነ የማያደርጓቸውን ነገሮች እየለቀሙና እየቆጠሩ ካለባቸው “የመገፋት ስስነት” ጋር የማዛመዝ ሁኔታ ነው፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት በእርግጥም ከእውነተኛ የመገፋት ልምምድ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመገፋት ስሜት ስስ እንዲሆኑ ከዳረጋቸው ከእውነታ የራቀ እይታም ሊነሳ ይችላል፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ፣ ሰዎች በዚህ የስሜት ተጽእኖ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላለባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ትክክለኛውን መፍትሄ እንዲፈልጉ ይመከራሉ፡፡

(ከመገፋት ህመም የመላቀቂያውን እውቀት ለማግኘት መጽሐፉ ይነበብ)
l
75 viewsMame eta , 03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 23:00:30
በታላቁ የረመዳን ውድድር ተሳትፈዋል
የ800,000 ብር ዋጋ ያለው ሽልማት
እስከ ረመዳን 30
የውድድር መድረክ አገናኝ (www.tafseerinfo.com )
ለወዳጅ ዘመድዎ ማጋራትዎን አይዘንጉ
60 views 𝓗𝓪𝓵𝓪 𝓑𝓮𝓪𝓾𝓽𝔂, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 08:14:20 ከተሸነፈ ሰው ጋር የመኖር ካባድነት

አብረውን ያሉ ሰዎችን ስሜታቸው ጎድተን፣ ስነ-ልቦናቸው አድቅቀንና አካላዊ የበላይነትን ተቆጣጠርንና ተጭነን ለማሸነፍ መሞከር መዘዙ ረጅም ርቀት ነው የሚሄደው፡፡ አጠገባችን የሚገኙ ሰዎችን በግድ የበላይነትን ስንቆጣጠርባቸውና በጉልበት ስናንበረክካቸው አጠገባችን የቆሰለ፣ ያመረረና ጊዜ ጠብቆ ሊጎዳን የሚችልን ሰው እያከማቸን መሆኑን አንርሳ፡፡

ይህ እውነታ ከትዳር አጋር፣ ከቤተሰብ አባል፣ ከጉርብትና፣ ከሕብረተሰብና ከብሔር-ለብሔር ግንኙነት አንጻር ሲታይ ያለው ተግራዊነት ያው ነው፡፡ በጉልበት፣ አጉል የበላይ ሆነንና ስሜቱን አድቅቀን ካሸነፍነው ሰው ጋር መኖር አደገኛ ነው፡፡ ይንን ባደረግን ቁጥር ነገ ጊዜን ጠብቆ የሚነሳብንን ሰው ጡንቻ እንደማዳበር ይቆጠራል፡፡ የነበረው እንዳልነበረ፣ የበላዩ የበታች፣ አቅም-የለሹ አቅመኛ፣ ያቀረቀረው ቀና የሚልበት ጊዜ ተለውጦ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም፡፡

ሰዎችን እናክብር! ከሰዎች ጋር ተስማምተን እንኑር! አጉል የበላይነትና ያሸናፊነት ስሜት አይደርብን! በኃይለኛነት ስሜት ካቆሰልናቸው ሰዎች ጋር መኖር እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ነፋሱ ለእነሱ የሚነፍስበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርምና!
59 viewsMame eta , 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:21:19 እምቅ ብቃታችንን አፍኖ የያዘው ብቸኛ ነገር!

ማንም ሰው በእኛ ላይ ከሚኖረው አመለካከት በበለጠ ሁኔታ እኛ ራሳችን በራሳችን ላይ ያለን አመለካከት ትልቅ ተጽእኖ አለው፡፡ አንድ ሰው ራሱን ሙሉ ለሙሉ ሲቀበልና ቀና ብሎ መኖር ሲጀምር ሰዎች በእሱ ላይ ያላቸው አመለካከት አቅም እያጣ ይሄዳል፡፡

ራስን አለመቀበል የዘመናችን ችግር ነው፡፡ መቀየር የምንችለውን ለመቀየርና መቀየር የማንችለውን ነገር ተቀብለን ቀና ብለን እንድንኖር እንመከራለን፡፡

#ራሳችሁን ተቀበሉ።
69 viewsMame eta , 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 06:50:06
አልፋችሁ ሂዱ!

ፈጣሪ በዚህች ምድር ላይ እንድትኖሩ የሰጣችሁ ይህ ሕይወት በራሱ፣ ምንም ነገር ሳይጨመርበት እጅግ ውብ ነው፡፡ ይህንን ውብ የሆነ ሕይወት ምንም ነገር እንዲያበላሽባችሁ አትፍቀዱ፡፡

• በአንድ ሰው ተግባር ብቻ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ ወይም ካላደረጉላችሁ ነገር አልፋቸሁ ሂዱ!

• በአንድ ነገር አለመሳከት የተነሳ ውስጣችሁ ወድቆ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ጊዜያዊ ከሆነው የመሳካትና ያለመሳካት ገጠመኝ አልፋችሁ ሂዱ!

• ሰዎች ከሚያደርጉብን፣ ከሚያደርጉልንና ከከለከሉን ነገሮች ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከተሳካውና ካልተሳካው ሁኔታ ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ እጥፍ ይበልጣልና ከሁኔታዎች አልፋችሁ ሂዱ!

በሕይወት መኖር ስለተፈቀደልን ብቻ ፈጣሪን በማመስገን በደስታ ለመኖር በቂ ምክንያት አለን፡፡
72 viewsMame eta , 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 08:52:14 እያንዳንዱን ቀን በድፍረት ኑር
በምትሰራው ስራ ኩራ።
ሁልጊዜ የጀመርከውን ጨርስ።
መሰራት ያለበትን ስራ
ጠንካራ ግን ጨዋ ሁን።
ቃል ከገባህ ቃልህን ጠብቅ።
ቃል በገባኸው ተልዕኮ ላይ ሂድ።
ትንሽ አውራ ብዙ አትናገር።
አንዳንድ ነገሮች የማይሸጡ መሆናቸውን አስታውስ
መስመሩን የት ማሰመር እንዳለብህ እወቅ

የስኬት ቀመር ገፅ 97
64 viewsMame eta , 05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ