Get Mystery Box with random crypto!

Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafmedia — Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafmedia — Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®
የሰርጥ አድራሻ: @metsihafmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 235
የሰርጥ መግለጫ

#ሰላም የምንወዳችሁ ይሄ ''Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ® ቻናል ነው ''
ሀሳብ፣ አስተያት እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ
👇
@metsihafmediabot
#ሀሳባችሁን_ለማንሸራሸር👇
@metsihafmediagroup
#You_tube 👇
https://www.youtube.com/channel/UCMUDsPTgSmhO0g-kXG7OQjw
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
👆👆👆

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 14:22:10
ተወዳጁ የእረኛዬ ድራማ ሐምሌ 18 ይጀምራል ተባለ

@metsihafmedia
@metsihafmedia
42 views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 14:29:27
እህህህ ....

ሌሎች ስራዎችን ለማግኘት

join

ይቀላቀሉ
79 views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 14:17:08 #ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ?
( ኤልያስ ሽታኹን )
~ ~ ~ ~ ~

ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ
ራስ ዳሽን እየገፋሁ
ወይስ
እየሰራሁ የኖኅ መርከብ
ሳፈላልግ የሰው ኮከብ..
ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

እየዘመርኩ?
እየዘፈንኩ?
እያረመምኩ?
ግራ ገባኝ እኮ
ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ።

ምን ስሆን ልጠብቅሽ?
አባይን ስጠልቀው
ኤርታሌን ስሞቀው
ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው
ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው።

ማን ጋር ልጠብቅሽ?
ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ
በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ።
ካብርሃም ቤት አጋር
ወይስ
ባቢሎን ግንብ ጋር።

የት ጋር ትመጫለሽ?

በዘመን የት ዘመን?
በቦታ የት ቦታ?

ከንጉሥ የት ንጉሥ?
ከባህር ምን ባህር?

ከጫካ የት ጫካ?
ከደብር የት ደብር?
:
ከሶላት ምን ሰዓት?

ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ?
ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ
የዛፍ ቆዳ ስልጥ...

ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ
ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ....

ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ
ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ...

ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ
ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ...

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

#join & #share

@metsihafmedia
@metsihafmedia

#For_comment

@metsihafmediabot
@metsihafmediabot

#YouTube

https://www.youtube.com/channel/UCMUDsPTgSmhO0g-kXG7OQjw
86 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 11:11:46
ለስነ_ፅሁፍ

@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
129 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 17:52:29 Watch "መታየት ያለበት ድንቅ ቲያትር ለጥበብ አፍቃሪያን" on YouTube


110 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 19:40:11 "ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ!"

እመጓ

በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ


ሀይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም ..በድን አስከሬናችሁን ልካችሁ የወገን ልብ ትሰብራላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ባፍ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፣ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁን ትይዛላችሁ፣ ምኞታችሁ ልክ የለውም፣አምሮታችሁ ብዙ ነው፣ ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ ባንዱ ግን አትጠቀሙበትም፣ ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ፣ ሃይማኖት እንጂ ዕምነት የላችሁም፣ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትፀፀታላችሁ፣ ታማችኋል፣ ከታሪክ ፍቅርና ልማትን ሳይሆን ጥላቻና ልማትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፣ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣ ደረታችሁን ነፍታችሁ፣ሳትመርጡ ሁሉና ባደባባይ ትዘሩታላችሁ" ስል ግል ኑሮዓችን የምንኳትን ምስኪኖች ነን፤ አንተ ደግሞ ፍለጋው የማያልቀው የዚህ ትውልድ ናሙና ነህና አምነህ ሂድ ብልህ አትቀበለኝም እንደ ቶማስ በእጅህ ዳሰህ ካላየህ አትረካም፣ የትውልዱ ሕመምም ይህ ነው፣አንተም የዚህ ትውልድ ተጠቂ ምሳሌ ነህና….አንተን ሊያቆምህ የሚችለው የመንገዱ ማለቅ ብቻ ነው፤ ሩቅ መንገደኛ የሚያቆመው አንድም መንገዱ ሲያልቅ አለዚያም መንገደኛው እራሱ ሲያልቅ ነውና፡፡

@metsihafmedia
@metsihafmedia
107 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 19:52:14 አሸንፈሀል እኮ!

በሚገርም ሁኔታ እኮ በጣም ብዙ በገንዘብ የማይተመኑ ድሎችን አስመዝግበሀል! ጀግና ነህ ከዚህ ቀደም በጣም ከባድ የሚባሉ ፈተናዎችን በድል አልፈሀል ፣ ይቻላል ብለህ የማታስበው የነበረውን ሁሉ ችለህ አሸነፈሀል ፣ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ጎበዝ ያለህ ሰው የለም ፣ ስታሸንፍ አልተጨበጨበልህም ማንም ድል ማድረግህን አልሰማም ምክንያቱም ስትቸገር አላገዙህም እርዳታ አልጠየቅህም ፣ ስለዚህ ጉብዝናህን ሌሎች አያውቁትም ለዛ እኮ ነው የማያደንቁህ አቅም እንደሌለው እንደ የሰነፍ የሚያዩህ፤ ስለዚህ አይግረምህ አንተን ካንተ በላይ ማንም አያውቅህምና ሰዎች ዝቅ አድርገው ስለተመለከቱህ ብቻ ከፍ ያልህ መሆንህን አትዘንጋ ፈጣሪ የሰጠህን አቅም በዐግባቡ ስለመጠቀምህ ብቻ እርግጠኛ ሁን! ድልህን በሌሎች ሰዋች መስፈርት አትለካ ምን ያህል ዋጋ እንዳገኘህበት እኮ የምታውቀው አንተ ነህ!

@metsihafmedia

@metsihafmedia

@metsihafmedia
146 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 16:00:51

124 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 19:36:46 #እመጓ........

"በአፍላ ትጀምሩታላችሁ በወረት ትተውታላችሁ። ያወቃችሁትን ትረሱታላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ። ምኞታችሁ ልክ የለውም፣ አእምሮአችሁ ብዙ ነው። ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል። ተው የተባላችሁትን ትሰራላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ። ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተ መቅደሱን በመስታወት ሠርታችሁ መቅደስ ባትገቡም እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ።

ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም፤ ሁሉ አላችሁ ፣ ግን ባዷችሁን ናችሁ። ሃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም!" ቀጠሉ አባ። ሰውነታቸው እንደ ቅኔ ዘራፊ ይናጣል።

"መድኃኒት ነው ያልከው? መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ብቻ ትሄዳለህ። ጥበብን "ሀ ግእዝ" ብዬ ላስተምርህ ብሞክር መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት "ሆ ሳብዕ" ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ። የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተለከፈከፈ የተማሪ ኩፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል። ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ። ትቀጥላላችሁ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ። ትቸኩላላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ። በጽኑ ታማችኋል!"

ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ። ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፣ እናም ወደ ኋላ ስለ ታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል። ስለሆነን ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትና የተሸናፊነት ትርጉም የያዙ ሃውልቶች በአንድ ላይ ታቆማላችሁ። ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ።

ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ። በዚህ አለም ጥድፊያ ታማችኋል። ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፣ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፣ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ። በቁማችሁ የናቃችሁትን የሃገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ። ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ። ግብዝነታችሁ መጠን የለውም። ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፣ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ። ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም። ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል። ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም።

በዚህም የተነሳ ሚስጥር ለመካፈል ቅርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብዕና አልገነባችሁም። እኛ የመገናኛውን ድልድይ ስላልሰራንና ከእናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት ወይም ማየት ስለማትፈልጉት አለበለዚያ እንደ ልብወለድ ገፀ ባህርይ የራሳችሁን ያሸበረቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈልጋችሁ ስለምታጡት ነው። እኛ ደግሞ እናንተ ታዩት ዘንድ አላሸበረቅንም፣ ማሸብረቅም አንፈልግም። በዚህ ምክንያት ለእናንተ ምስጥር ለመንገር ቅርስ ለማውረስ ከባድ ሆኗል። እኛ አባቶቻችንን እናምናለን። በእነርሱም ደስ ይለናል። የነገሩንን ተቀብለን ቃልኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን።

"ፅላተ ሙሴ አክሱም ፂዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አላልንም"

"ጌታ የተሰቀለበት ግማደ መስቀሉ ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም"

"ቅዱሱ ፅዋ መንዝ ውስጥ አለ ሲሉንም ዋሻ እናስስ አላልንም"

አባቶቻችንን አምነን ሀገራችን የበረከት ምድር መሆኗን ተረድተን የጌታችንን የጸጋ ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራለን። ምንም የለንም ሁሉ ግን የእኛ ነው። ድሆች ብንባልም ባለጸጎችም ነን። የተራቆትን ብንመስልም የጸጋ ልብስ አለን። ሐዘንተኞች። ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሀገራችን መባረክ ፣ ቅድስት ሀገር መሆን፣ ቅዱስ ቅርስ በእጃችን እንዳለ አለም እንዲያረጋግጥልን አንፈልግም። የሌለንን አለን፣ ያልተሰጠንን ተቀበልን ብለን የምንኮፈስ ግብዞችም አይደለንምና። የሌለን ነገር ለመጠበቅና ለመታመን ስንል ሥጋችንን እየጎሰምን በገዳም ለመኖር የምንወስን ጅሎችም አይደለንምና"።

Credit :- "እመጓ" በዓለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር) ገጽ 162 - 164


@metsihafmedia
@metsihafmedia
155 views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 19:12:18

132 views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ