Get Mystery Box with random crypto!

#ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ? ( ኤልያስ ሽታኹን ) ~ ~ ~ ~ ~ ቅድ | Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

#ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ?
( ኤልያስ ሽታኹን )
~ ~ ~ ~ ~

ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ
ራስ ዳሽን እየገፋሁ
ወይስ
እየሰራሁ የኖኅ መርከብ
ሳፈላልግ የሰው ኮከብ..
ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

እየዘመርኩ?
እየዘፈንኩ?
እያረመምኩ?
ግራ ገባኝ እኮ
ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ።

ምን ስሆን ልጠብቅሽ?
አባይን ስጠልቀው
ኤርታሌን ስሞቀው
ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው
ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው።

ማን ጋር ልጠብቅሽ?
ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ
በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ።
ካብርሃም ቤት አጋር
ወይስ
ባቢሎን ግንብ ጋር።

የት ጋር ትመጫለሽ?

በዘመን የት ዘመን?
በቦታ የት ቦታ?

ከንጉሥ የት ንጉሥ?
ከባህር ምን ባህር?

ከጫካ የት ጫካ?
ከደብር የት ደብር?
:
ከሶላት ምን ሰዓት?

ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ?
ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ
የዛፍ ቆዳ ስልጥ...

ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ
ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ....

ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ
ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ...

ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ
ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ...

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

#join & #share

@metsihafmedia
@metsihafmedia

#For_comment

@metsihafmediabot
@metsihafmediabot

#YouTube

https://www.youtube.com/channel/UCMUDsPTgSmhO0g-kXG7OQjw