Get Mystery Box with random crypto!

'ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ!' እመጓ በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ሀይማኖት እንጅ እምነት የላች | Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

"ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ!"

እመጓ

በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ


ሀይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም ..በድን አስከሬናችሁን ልካችሁ የወገን ልብ ትሰብራላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣ባፍ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፣ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፣ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፣ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፣ የረገጣችሁን ትይዛላችሁ፣ ምኞታችሁ ልክ የለውም፣አምሮታችሁ ብዙ ነው፣ ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ ባንዱ ግን አትጠቀሙበትም፣ ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ፣ ሃይማኖት እንጂ ዕምነት የላችሁም፣ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትፀፀታላችሁ፣ ታማችኋል፣ ከታሪክ ፍቅርና ልማትን ሳይሆን ጥላቻና ልማትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፣ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣ ደረታችሁን ነፍታችሁ፣ሳትመርጡ ሁሉና ባደባባይ ትዘሩታላችሁ" ስል ግል ኑሮዓችን የምንኳትን ምስኪኖች ነን፤ አንተ ደግሞ ፍለጋው የማያልቀው የዚህ ትውልድ ናሙና ነህና አምነህ ሂድ ብልህ አትቀበለኝም እንደ ቶማስ በእጅህ ዳሰህ ካላየህ አትረካም፣ የትውልዱ ሕመምም ይህ ነው፣አንተም የዚህ ትውልድ ተጠቂ ምሳሌ ነህና….አንተን ሊያቆምህ የሚችለው የመንገዱ ማለቅ ብቻ ነው፤ ሩቅ መንገደኛ የሚያቆመው አንድም መንገዱ ሲያልቅ አለዚያም መንገደኛው እራሱ ሲያልቅ ነውና፡፡

@metsihafmedia
@metsihafmedia