Get Mystery Box with random crypto!

Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafmedia — Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ® M
የቴሌግራም ቻናል አርማ metsihafmedia — Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®
የሰርጥ አድራሻ: @metsihafmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 235
የሰርጥ መግለጫ

#ሰላም የምንወዳችሁ ይሄ ''Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ® ቻናል ነው ''
ሀሳብ፣ አስተያት እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ
👇
@metsihafmediabot
#ሀሳባችሁን_ለማንሸራሸር👇
@metsihafmediagroup
#You_tube 👇
https://www.youtube.com/channel/UCMUDsPTgSmhO0g-kXG7OQjw
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
👆👆👆

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-30 17:57:44 Watch "ጣፍጭ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ታሪክ /The history of etege taytu btul /Tafach yeetege taytu btul." on YouTube


149 views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 09:45:35
ሰላም ውድ የደብረ ብርሃን ከተማ የጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ አርብ 19 / 9 / 2014 ዓ.ም በከተማችን ልናቀርበው የነበረው #ፍቅርዬ የተሰኘው ፊልም በአንዳንድ ጉዳዮች ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እየገለፅን ወደፊት የምናቀርብበትን ጊዜ የምንገልፅ መሆኑን እንገልፃለን።
#እናመሰግናለን


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
165 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 18:56:07 #ምንሽ_ነኝ
.
.
በአይኔ አይቼሽ በፍቅርሽ ተመትቼ ፣
ስከተልሽ ኖሬ ወሎሽን አጥንቼ ፤
.
ቀርቤ ሳልነግርሽ ፥ ፍቅርሽ በልቤ ቀርቶ ፣
ሀሳቤ ታውኮ ቀልቤ ላንቺ ዛዝቶ ፤
.
አቋሜን ሳልነግርሽ አቋምሽን ሳላውቀው ፣
ያሰብኩልሽን ኪዳን ሳልቋጥር ሳልፈታው ፤
.
እንዲህ ባክኖ ቀርቶ ፥
ህሊና ሀሳቤ በአንቺ ተከፍቶ ፤
.
ላላገኝሽ ተርቤ በናፍቆትሽ ስዋኝ ፣
ተሰቅቄ ኖሬ እኔ አሁን ምንሽ ነኝ ።


:ALEX at°°... 2014 E.C


@metsihafmedia
@metsihafmedia
137 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:07:00
ፍቅርዬ .......... ወዬ ወዬ
.
የኔ አለም .......... ወዬ ወዬ
.
እኔ ናፍቄሀለሁ አንገናኝም ወይ ፣
.
.
ኸረ ልቤ ተቸገረ በናፍቆትሽ ታሞ ፣
በምን ላስደስታት ሲል በፍለጋ ደክሞ ።
ምረጭ አንድ ቦታ ፣
እንድንገናኝ ማታ ።
.
እኔ መርጫለሁ የፍቅር ማረፊያ ፣
.
እደብረ-ጥበቦች ጋር ከጥበባቱ መናኸሪያ ።
.
ጎን ለጎን ተቃቅፈን እንድንኮመኩመው ፣
.
ፍቅርዬ በፊልሙ እየጠበቀን ነው ።


አዎ ለፍቅርዎ ማረፊያ ደግሞም እንዲህ ፍቅር በሸሸበት ፣ ፍቅርዬን ነው እንጂ ማየት ሆኖ በአንድነት ።
የሁል ጊዜም አገልጋያችሁ የሆነው #ደብረ_ጥበብ የቲያትር እና የስነ-ፅሁፍ ቡድን ጊዜዎን እንዲያሳምሩበት ይህን ምርጥ ፊልም እነሆ ብሎታል ።

መቼነው ? .... ፦ እስካሁን አልሰማችሁም ምን እያላችሁኝ ነው አርብ 19 / 09 / 2014 ዓ.ም ነዋ ።

ቦታው ፦ በዘራያእቆብ ከተማ አደባባዩ ላይ በደብረብርሃን ሲኒማ አዳራሽ ።

ሰአቱ ደግሞ ፦ ልክ ከድካምዎ ሲያርፉ ከስራ ሰአት በኋላ ማታ 11 : 30

መግቢያ ፦ እንደው ዝም ነው እኛ ኑሮ ቢወደድም አናስወድድም ኪስዎን እማይጎዳ 40 ብር ብቻ ።



#በደብረ_ጥበብ_ቲያትርና_ስነፅሁፍ_ቡድን_የተዘጋጀ


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
149 views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 08:43:42 ድምፅህን አጥፍተህ ተለወጥ!

የራስህን ዋጋ ስታውቀው ዋጋቸውን ያልተረዱ ሰዎች ያሳዝኑሀል፤ አንተ ከልብህ መለወጥ ስትጀምር ሌሎች እንደፈዘዙ ታያለህ፤ መሮጥ ስትጀምር ብዙዎች ቆመው እንደቀሩ ትታዘባለህ። ብትነግራቸው ግን አይሰሙህም፤ ሰዎች ብዙ ርቀት ላልተጓዘ ጆሮ አይሰጡም፤ ለዛ ነው ድምፅህን አጥፈተህ እስከጥግ መለወጥ ያለብህ።

መጀመሪያ አንተ ሳትቀየር ሌሎች እንዲቀየሩ አጠብቅ! ለምትወዳቸው የምትደርሰው አንተ ቆራጥ ሆነህ ያመንክበትን ስታሳካ ነው፤ ያኔ ስኬትህ ጮክ ብሎ ይናገራል!


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
141 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 10:47:56 ሳትናገር ያደምጡሀል!

ራስህን ለማስረዳት ብዙም አትድከም፤ ሰዎች ከንግግርህ በላይ ተግባርህ ነው የሚያሳምናቸው። ምን እንደምታስብ ለሁሉም ሰው አትናገር፤ ከጎጆ ቤት ያልዘለለ ህልም ላላቸው ስለ ፎቅ ቤት ብታወራ ምቀኛ ነው የምታተርፈው። ወዳጄ ፀጥ ብለህ አድርገህ አሳያቸው፤ ሳትናገር ያደምጡሀል!

@metsihafmedia
@metsihafmedia
160 views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 13:46:48 ጊዜው መሄዱ አይቀርም!

በዚህ አለም ትልቁ ሽልማት ይሄ ቅፅበት ነው፤ ይቺ ቅፅበት ካለፈች አለፈች ነው፤ ማንም አይመልሳትም። የማይጠቅምህን ወሬ ስትሰማ ወይ ተራ ቪዲዮ ስታይ ከእድሜህ ላይ 10 ደቂቃም ቢሆን ቀንሰህ እየሰጠሀቸው መሆኑን አስታውስ።

እድሜህን እንዴት በነፃ ትሰጣለህ?! የምናደንቃቸው ታላላቅ ሰዎች ከፍታው ላይ የወጡት ዕድሜያቸውን ለሚጠቅማቸው ነገር ሰጥተው ነው። አንተ ብታነብ ባታነብ ጊዜው መሄዱ አይቀር፤ ብትሰራ ስራ ብትፈታ አመቱ ማለፉ አይቀር፤ ብትማር ባትማር ደቂቃው መክነፉ አይቀር፤ ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ! ነገ የተሻለ ቦታ ለሚያደርስህ ነገር ቅድሚያ ስጥ!


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
174 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 07:53:40 ነግሬሽ ነበረ

ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።

ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።

ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia
192 views04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 09:37:41 ውሀ እራሱ አጋር አለው

እኔ ግን እስካሁን single ነኝ

159 views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ