Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርዬ .......... ወዬ ወዬ . የኔ አለም .......... ወዬ ወዬ . | Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

ፍቅርዬ .......... ወዬ ወዬ
.
የኔ አለም .......... ወዬ ወዬ
.
እኔ ናፍቄሀለሁ አንገናኝም ወይ ፣
.
.
ኸረ ልቤ ተቸገረ በናፍቆትሽ ታሞ ፣
በምን ላስደስታት ሲል በፍለጋ ደክሞ ።
ምረጭ አንድ ቦታ ፣
እንድንገናኝ ማታ ።
.
እኔ መርጫለሁ የፍቅር ማረፊያ ፣
.
እደብረ-ጥበቦች ጋር ከጥበባቱ መናኸሪያ ።
.
ጎን ለጎን ተቃቅፈን እንድንኮመኩመው ፣
.
ፍቅርዬ በፊልሙ እየጠበቀን ነው ።


አዎ ለፍቅርዎ ማረፊያ ደግሞም እንዲህ ፍቅር በሸሸበት ፣ ፍቅርዬን ነው እንጂ ማየት ሆኖ በአንድነት ።
የሁል ጊዜም አገልጋያችሁ የሆነው #ደብረ_ጥበብ የቲያትር እና የስነ-ፅሁፍ ቡድን ጊዜዎን እንዲያሳምሩበት ይህን ምርጥ ፊልም እነሆ ብሎታል ።

መቼነው ? .... ፦ እስካሁን አልሰማችሁም ምን እያላችሁኝ ነው አርብ 19 / 09 / 2014 ዓ.ም ነዋ ።

ቦታው ፦ በዘራያእቆብ ከተማ አደባባዩ ላይ በደብረብርሃን ሲኒማ አዳራሽ ።

ሰአቱ ደግሞ ፦ ልክ ከድካምዎ ሲያርፉ ከስራ ሰአት በኋላ ማታ 11 : 30

መግቢያ ፦ እንደው ዝም ነው እኛ ኑሮ ቢወደድም አናስወድድም ኪስዎን እማይጎዳ 40 ብር ብቻ ።



#በደብረ_ጥበብ_ቲያትርና_ስነፅሁፍ_ቡድን_የተዘጋጀ


@metsihafmedia
@metsihafmedia
@metsihafmedia