Get Mystery Box with random crypto!

#ምንሽ_ነኝ . . በአይኔ አይቼሽ በፍቅርሽ ተመትቼ ፣ ስከተልሽ ኖሬ ወሎሽን አጥንቼ ፤ . ቀርቤ | Metsihaf media መጽሐፍ ሚዲያ ®

#ምንሽ_ነኝ
.
.
በአይኔ አይቼሽ በፍቅርሽ ተመትቼ ፣
ስከተልሽ ኖሬ ወሎሽን አጥንቼ ፤
.
ቀርቤ ሳልነግርሽ ፥ ፍቅርሽ በልቤ ቀርቶ ፣
ሀሳቤ ታውኮ ቀልቤ ላንቺ ዛዝቶ ፤
.
አቋሜን ሳልነግርሽ አቋምሽን ሳላውቀው ፣
ያሰብኩልሽን ኪዳን ሳልቋጥር ሳልፈታው ፤
.
እንዲህ ባክኖ ቀርቶ ፥
ህሊና ሀሳቤ በአንቺ ተከፍቶ ፤
.
ላላገኝሽ ተርቤ በናፍቆትሽ ስዋኝ ፣
ተሰቅቄ ኖሬ እኔ አሁን ምንሽ ነኝ ።


:ALEX at°°... 2014 E.C


@metsihafmedia
@metsihafmedia