2022-09-11 18:10:54
አንዳንድ ቀን.
ዘሬ ያለወትሮዬ አርፍጄ ነበር ከእንቅልፌ የነቃሁት። የማታ ስካሬን ማስታወስ አልፈልግም እረ እንደውም ከዛች ገንዘብ ወዳጅ ብርቄ ጋር ሁለተኛ ድርሽ አልልም ብዬ ለራሴ ቃል ገብቻለሁ። ድሮውንም የሷን ማድያት የወረረውን ፊቷን እና ጨጓራ የሚንጠውን አረቄዋን ላንቃርርላት ?
፣አድሮ ሲውል ደግሞ ጢንቢራ የሚያዞር ፣እራስ ምታት የሚለቀ አያስቆም ፣ አያስወራ መርዝ ነው ወይስ ''ቢራ''?
ፈጠን ብዬ ከብርድ ልብሱ ወጣሁና የራሴን ጭንቅላት ልክ እንደ ትርፍ እቃ ተሸክሜ መስታወት ፊት ቆምኩኝ።
ፊቴን ሳየው የተቀቀለ ጉበት መስሏል ፤ አይኔ መደፍረሱ ሳይበቃው የቀዘነ ባትሪ መስሏል፣ በዛ ላይ ከአይኔ ዳር ዳር ቢጫ ክብ ሰርተው ( አይንአር ) ሳያቸው የእውነት አፈርኩ አንዲያው ሳላካብድ ቀለል አድርጌ ብገልፀው ''የአንድ መለስተኛ ህፃን አይነምድር ያክላል ፈግግ አልኩ ለራሴ ፤ከጆሮዬ ተነስቶ ሙሉ ጉንጬን አልብስ እስከ አገጬ መጨረሻ ድረስ ሰንበር በሰንበር ሁኗል የፊቴን ውበት ቢያደበዝዘውም አልከፋኝም። እንደውም ጣናን የወረረው እንቦጭ አረም እና የኮንሶን እርከን አስታውሶኛል።
እንደነገሩ ፊቴን በውሀ አስነክቼ ከቤት ወጣሁ ግራ ቀኝ ሳላማትር አውራ መንገዱን ተያያዝኩት ዝናቡ ላመሉ ጠብ ጠብ ይላል ውርጩ ለጉድ ነው የዝናብን ማካፋት አስመልክተው ወደፊት የተኙት ዐጉሮቼ ላይ የጃኬቴን ኮፍያ ጣል አድርጌ መንገዱን መዝገም ቀጠልኩኝ።
ከብርቄ መጠጥ ቤት ስደርስ ውስጥ ለመግባት አቃታኝ እንደምንም ችዬው ላልፍ ፈለኩ ገና ከመጠጥ ቤቱ አንድ እርምጃ ሳልራመድ ለዝብ ያለ ሰካራም በድሉ በድሉ አለኝ ዞር ስል መላኩ ነው።
መላኩ የመጠጥ ቤቱ አድማቂ ነው ሰፈር ውስጥ ማያቀው ሰው የለም አብዛኛው ሰው ግን መላኩ ስሙ እንደሆነ አያቁም ጮሌው እያሉ ነው ሚጠሩት እኔም ላናደው ስፈልግ
ስምህን እኳ ስለማያምኑበት ነው በትክክለኛ መጠሪያ የማይጠሩህ እለዋለሁ።
ወዬ ጮሌ አልኩት
በመጠጥ ፣ በሲጋራ በጫት ለዘብ ያሉትን ጥርሶቹን ብልጭ አደረጋቸውና አውቆ ነገር ሲፈልግ ስሜን አቆላመጠው በ* አለኝ ሳቅ እያለ።
ስልክ ይፈልግሀል አለኝ
ወደ ጥሪ ማዕከሉ ለመቅረቡ ወደ ግሮሰሪው ዘለኩ።ቤቱ ደምቋል አረቄ፣ቢራ፣ጠጅ ፣ጠላ ሁሉ በየአይነቱ ቀርቧል ህዝብ አዳም ሰካራም በጥዋቱ ይጋታል ፣ አንዱ በስካር ያለቅሳል ፣ ሌላው ይጨፍራል ፣ ሁሉም በራሱ አለም ላይ ነው ።እንደ ገባው ጋሽ ሀይሉን ነበር ያየዋቸው በጥዋቱ ይሄን ቢራ ተያይዘውታል። የእውነት አዘንኩላቸው ይሄ ምናምንቴ አልኩ ነገሩን አጣርቼ እስክደርስበት ። ሁሉንም mark አድርጌ አንድ ላይ ሰላም አልኳቸው አፀፌታውን መለሱ ጋሽ ሀይሉ ግን ኖር ብለው ከጠቀመጡበት ብድግ እንዳሉ ከመቅስፈት በቅንድባቸው ቆሙ። ወደ ቤታቸው ደጋግፈው ወሰዷቸው እኔም ወደ ተነሳው ስልክ አቀናሁ የቤት ስልኩን እጀታ ወደ ጆሮዬ ደቀንኩ እና ሄሎ አልኩ
<ሄለው"በዴ" ነክ አይደል አለችኝ >
ቁልምጫው ደስ አላለኝም <ሆሆ አልኩ ዱቄት ልል ነበር አምልጦኝ >
<አው ነኝ ማን ልበል
<አልማዝ ነኝ በጥዋቱ ከፍቼ ነው ምደውልልህ >
<በጥዋት ከፍቼ ገርሞኝ ውስጤን ደስ እያለው መቀባጠሬን ጀመርኩ >
<እኔኳ ምንድነው እንደዚት ፊቴን በብርሀን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው
ምንድነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም
በጥዋት ሚፈልቀው እያልኩ አስባለው>
<ለካ አንቺ ከፍተሽ ነው አልኩ ሳቅ ሳቅ እያልኩ ለመሆኑ የት ነሽ የት ልምጣ አልኩ የሸሚዜን ቁልፍ በአንድ እጄ እየቆለፍኩ>
<ግራ እየገባት እንዴ ምን ሁነሀል በዴ የቃል ግድፈት አለ መሰለኝ>
#ከፊቼ_ነው ምደውልልህ አልማዝ እኮ ነኝ አላወከኝምም
መልካም አዲስ አመት
እንኳን አደረሳቹ
,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@Yefiker_Gojo ,,,,,, @Yonishabby
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
121 viewsŶòňĩ, 15:10