2022-09-21 18:44:57
. ◉●◦
አለሜ ነሽ ◦◉
ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ▣
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ ▣
#ክፍል_59
ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ(የሸዋ ልጅ)
... ዲናና ባለ ታክሲው ጊዲዮንን ማብሸቁን
ተያይዘውታል።
ሄዋን ዛሬ የምርቃት ቀኖ እንደመሆኑ አዳም በትዛዝ ባሰፋላት
ቀሚስ አሽብርቃለች ዲናም እንደዛው ቦስና አዳምም ሙሽራ
መስለዋል። ኬብሮን የሜካፕ ስራዋን ለሁሉም ተጠባባቸዋች።
የሚያውቋቸው ስዎች በሙሉ ተገኝተዋል የምርቃት ስነስርዓቱ
አዳራሽ በአስመራቂ ቤተስቦች በአስመራቂ እና በተመራቂ ባለ
ስልጣናት መምህራን ተሞልቷል።
፨ሁሉም ደስተኞች ናቸው። በጣም ደስተኞች። ቦስ ዲና በስልክ
ከባለ ላዳው ጋረ ስታወራ ቅናቱን ተያይዞታል። ሁሌም "ማነው?"
ይላል "መቼም ሴት አትሆንምም። ይላል ግን ዛሬ የቃል ኪዳን
ቀበት ሊያረግላት ወስኖ ቀለበት ይዟል።ቦስ አዳምን "አብረን ለሁለቱም እንሰረላቸው" ብሎ ጠይቆት ነበረ። አዳም ግን አይሆንም
ለፍቅረኛሞች ቀን ነው የማስርላት ብሎ ግግም አለ። ቦስ
ሊጫነው አልፍለገም እና ተወው። ሄዋን ከተመራቂ ተማሪዎች
አንደኛ ጎበዝ እና ቆንጆ ነበረች። ሳቂታ ተጫዋች ፍንድቅድቅም
ጭምር እና ደሞ ተሸላሚ ነበረች።
፨ሁሉም በድሬደዋ ከተማ ላይ ፏ እያሉ ነው። አዳም ፣ዲና፣
ዶክተር፣ ዶክተርሉሊት ፣ቦስ ፣ ሄዋን፣ የዲና ጓደኞች እና
ሰራተኞቹ። ምርጡን ሆቴል አዘግተው ግማሽ ለሊቱን ሲጨፍሩ
አመሹ። የሆነ ሰአት ላይ ቦስ ማይኩን ይዞ መድረክ ላይ ወጣ።
ቦስ "አንዴ አንዴ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ" አለ። ሁሉም ምን ሊናገር ነው
ብሎ በጉጉት መጠባበቅ ጀመሩ። ወደ ዲና እያየ "ነይ ወደዚህ"
አለ ፈገግ ብሎ።ዲና በግራ መጋባት ወደ እሱ ቀረበች።
፨ ቦስ ተንበረከከ ዲና አሁንም ግራ እንደገባት ነው።ቦስ እንዲ
አለ። "ዲናዬ አንቺ ማለት ለእኔ በህይወቴ ትልቅ ዋጋ ካላቸው
ስዎች በላይ ቦታ ያለሽ ነሽ። እናማ ባለፈው ህይወታችን ፍቅረኛዬ
ሁኒ ብዬ ጠይቄሽ ጥያቄዬን እንደተቀበልሽኝ አሁን ደማ ሚስቴ
ባለቤቴ ሁኒ ስልሽ ምን እንደምትይኝ ለመስማት ጓግቻለሁ ዲናዬ
ታገቢኛለሽ" አላት ውድ የአልማዝ ቀበት ከፊቷ አቀርበላት። ዲና
እንደፈዘዘች ቀረች። አለቀሰች በጣምምም የደስታ እንባ ከዛ እጆን
ዘረጋችለት ቦስ በቀስታ የቃል ኪዳን ቀለበቱን እጇ ላይ ስካላት።
፨ ሁሉም አጨበጨቡ ሄዋን ሮጣ ሄዳ አቀፈችው እቅፍ ፤ጭምቅ፤
አረገቻት "እንኳን ደስ አለሽ እህቴ ላንቺ በጣም ደስ
ብሎኛል" አለቻት። አዳምም ወደ ዲና መጣና አቅፎ "እንኳን ደስ
አለሽ ዲናዬ እህቴ" አላት። ዲና አዳም እና ሄዋንን እንዲሁም ቦስን
ሁሉንም በጋራ አቅፋ አመሰግናለው አለቻቸው። ከዛ ፕሮግራሙን
ካቆመበት ቀጠሉ።
፨ ሁሉም ዲናን እንኳን ደስ አለሽ እያሉ ሳሟት። የደስታ ምሽት
አሳለፉ ከዛም በተያዘላቸው ክፍል ገብተው ሁሉም ተኙ የደስታ
እንቅልፍ ፤የፌሽታ እንቅልፍ፤ ሁሉም ጭንቀቱን ማራገፍ ባይችል
እንኳን የተወበት ነበር። ምሽቱ በእንቅልፍ አለፈ። ልክ ከንጋቱ
2:30 ሲሆን ሁሉም ሆቴሉ በእስፔሻል ባዘጋጀላቸው ቁርስ ላይ
ታደሙ።
፨ከሰአት በእየግል መኪናቸው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። የሄዋን
የምርቃት ዝግጅት እና የዲና ያልታሰበ የቃልኪዳን ቀበት ስነስርአት
በእዚህ መልኩ አበቃ።
ይህ ቀን መቼም ላይረሳ ሁሉም ጭንቅላት ላይ ተፃፈ።
፨ይህ ከሆነ በሳምንቱ። ለሊት 12:35 ላይ የዲና ስልክ ጠራ።
የማታውቀውን ስልክ ቁጥር መገመት ለእሷ ቀላል ነው። ያው
ጌዲዮን ነው አነሳችው ። "ትሰሚኛለሽ እንደምትፏክሪው
የማትፈሪኝ ከሆነ ከ30 ደቂቃ በኋላ ነይ በርሽ ላይ መኪና
እልክልሻለው" አላት። ዲና ብትፍራም "እሺ ጥሩ እመጣለው
ጠብቀኝ" ብላ ስልኩን ዘጋችው። ዲና በጣም ፈራች ስልኳን
እንደያዘች የስልክ ቁጥረ ማውጫው ላይ የባለ ላዳውን ቁጥረ
አውጥታ ደወለች።ብዙ ሳይጠራ አነሳውና እንቅልፍ ባከረደደው
ድምፅ አቤት አላት። ዲና እየተርበተበተች "ስስስስማማ ጌዲዮን
ከ 30 ደቂቃ በኋላ ላግኝሽ አለኝ እኮ" አለችው። "ኣ አምላኬ ምን
ይሳንካል በጣም ደስ ይላል ሰጠብቀው የነበረው ነገር ደረስ።
በጣም አሪፍ እየውልሽ አሁን ምንም መፍራት አይጠበቅብሽም
ለቤተሰቦችሽ ቤተ ክረስቲያን አልያም ደሞ ጓደኛዬ ታማ ብለሽ
ውጪ እና አግኝው" አላት። ባለ ላዳው። ዲና "ፈጣሪዬ ይረዳኝ እሺ
በቃ" አለች። ባለ ላዳውም "አይዞሽ በቃ አሁን ስልኩን ዝጊው
ሁሌም ከጎንሽ እንደሆንኩኝ አስቢ ደሞ የምትወጃቸውን ሰዎች
ከሰቀቀን ለማዳን እንዲሁም አስቢ" አላት። ዲና "እሺ በቃ ልክ
ነክ" አለችና ስልኩን ዘጋችው።
፨ዲና መዘጋጀት ጀመረች። ጊዲዮን ብዙ ጊዜ ሊገላት እንደዛተባት
ስለነገራት ግን ደሞ ዲና "የእኔ ሞት የምወዳቸውን ከአዳነ 99
ጊዜ እሞታለው" ብላ እራሷን አሳምናለች። ዲና ወዲያው ሉክ እና
እስኪብረቶ አውጥታ መፃፍ ጀመረች። ለአዳም ፣ለሄዋን ፣ለቦስ እና
ለሰራተኞቹ። ጌዲዮን ጋረ ሄዳ የምትተርፍ አልመስላትም በህይወት
መጥታ እነሱን የምታገኛቸው አልመስላትም ባወጣችው ሉክ ሙሉ
ፆፈችላቸው። ስትጨርስ ከቤቱ በር ልትወጣ ስትል ዘበኛው
ከክፍሉ ወጥቶ "ምነው በእዚህ ሰአት ዲና በሰላም ነው የት
ልትሄጂ ነው" አላት። ዲና "ጓደኛዬ ችግር ገጥሞት ነው ቤተ
ክርስቲያን ላገኛት ልሄድ ነው" ብላ ወጣችና የውጩን በር
ዘጋችው። ፊቷ ልክ ባይሆግም ዘበኛው ግን በነገረችው ምክንያት
እንዲ የሆነች ነው የመሰለው። ዝም ብሎ ፊቱን ለመታጠብ ሄደ።
ዲና ከበር እንደወጣች ባገኘችው የጊዲዮን መኪና ገባች። ነጠላ
ለብሳ በነጠላዋ ተሸፋፍና ነበር።
፨ከመኪናው ኋላ ገባች ሹፌሩ ያለ ማቋረጥ እየነዳ እያከነፈ
ወሰዳት ዲና በጣም ፈራች። ቀስ ብላ ስልኳን አብረታ የመልክት
መፃፊያ ላይ የአዳምን፣ለቦስ እና የሄዋንን ስልክ አወጣችው
በአንዴ ለሳስቱም እንዲ ብላ መልክት ላከችላቸው። "ይህንን
መልክት ስታዩ በጭራሽ እንዳትደነግጡ እስከ ማታ ካልመጣው
እና ካልደወልኩኝ መኝታ ቤቴ ጠረጴዛ መሳቢያ ውስጥ
ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አለ አንብቡት እወዳችዋለው። ይህንን
መልክት እንዳያችሁት በጭራሽ መኝታ ቤቴ እንዳትገቡ ምክንያቱም
ካያችውት ሞቴን እንዳፋጠናችሁት ቁጠሩት እወዳችዋለው" የሚል
መልክት ላከች። ሹፌሩ እየነዳ ስለነበረ አላያትም። ሄዋን
፣አዳምእና ቦስም ተኝተው መልክቱን አላዩትም። ዲና በጠዋት
ውሀ እረጭታ ስታስነሳቸው እንጂ አስደንጋጭ መልክት
በስልካቸው ስትልክ አይተው አያቁም...
ይቀጥላል...
........... ••● ..........
☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን
https://bit.ly/2XS2ecv
☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን
https://bit.ly/3ja9o3O
☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
https://bit.ly/3rM2yop
☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
https://bit.ly/3mDyzfx
◎◦#ሼር◦◎
◎◦#ሼር◦◎
@Yefiker_Gojo || @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
5.4K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, edited 15:44