Get Mystery Box with random crypto!

የጠፋው ሬሳ ╚═══❖• •❖═══╝ ክፍል አራት ፡ ...የእጅ ባትሪ እያበራ ወደኛ የሚመጣ ሰው ተ | የፍቅር ጎጆ

የጠፋው ሬሳ
╚═══❖• •❖═══╝
ክፍል አራት


...የእጅ ባትሪ እያበራ ወደኛ የሚመጣ ሰው ተመለከትኩ ከዛም ወደ ድንኳኔ መግባቴን ትቼ ዘፈኑን
አጠፋሁትና ወደኛ አቅጣጫ ሰው እየመጣ መሆኑን ነገርኳቸው "ምን አባቱ ነው ሚመጣው" አለ ባባ "ዝም
በል ቅድምም ያንን መኪና ተናግራችሁት ነው የሚከታተለን አሁን ደግሞ ድጋሜ ትናገራላችሁ" ብዬ
በተናደደ ስሜት ውስጥ ሆኜ ተቆጣሁ "ለማንኛውም መሳሪያዪን ልያዝ" ብሎ ባባ ወደ ድንኳኑ ገባ እነ
ቅድስቴ በጣም ደንግጠዋል ፍራቻቸው ከፊታቸው ላይ ይነበባል መብራቱ እየቀረበን መጣ ለመሞቅ ብለን
ያነደድነው እሳት አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ ተረዳሁ ከዛም በውሃ አጠፋሁት ሁላችንም አንድ ቦታ ላይ
ቆመን ጫካው ፀጥ አለ አንዳች ድምፅ አይሰማማም ጭንቅ ውስጥ ሆነናል በድንገት ወደኛ ይመጣ የነበረው
መብራት ደብዛው ጠፋ ምንም የተዋጠልኝ ነገር የለም ባለንበት እንድንቀመጥ ነገርኳቸው አሁን ከምሽቱ
ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው ከትንፋሻችን ውጪ የማንም ድምፅ አይሰማም ፀጥ እንዳልን ረዘም ያለ ደቂቃ
ተቆጠረ ከግራ ከቀኝ እያማተርን..."ባክሽ ምንም የለም እኛ ብቻ ነን" ከማለቱ የቅድስት ጓደኛ የእጅ ባትሪው
ወደኛ አቅጣጫ በረጅም ተለቀቀ አሁን የባሰ ጭንቅ ውስጥ ገባን ትንሽ ተረጋግተን ነበር...ምን ያህል
እንደጠላሁት ከበፊትም ቀልቤ አይወደውም "የሚነገርህን ብትሰማ ትሞታለህ" አልኩት "ይቅርታ
ሜርሲዬ..."ብሎ ወሬውን ሊቀጥል ሲል "በቃ" ብዬ አቋረጥኩት...ባትሪው ድንኳኖቻችን ላይ እየበራ ነው
ሰውዬውም እየተጠጋን ነው...ግን ድንኳኖቹ ጥቁርና የማያንፀባርቁ መሆናቸው ድንኳን አያስመስላቸውም
ድንጋይ እንጂ ለዛም ይመስለኛል ባለ ባትሪው ሰው ትኩረት አልሰጣቸውም...ባትሪው አሁንም በድጋሜ
ጠፋ ብቻ የሆነ ሰው በዙሪያችን እየተፈታተነን እንደሆነ ይሰማኛል...ያ ባለመኪና ሳስታወሰው ይከነክነኛል
ከሱ ውጪ ማንም አይሆንም እዚ ቦታ ላይ ከሱ ውጪ ያየን የለም እኛም ከሱ ውጪ የተናገርነው የለም በገዛ
አንደበታችን ራሳችን ላይ ገዳይ ገዛን..."ነግቶ የማለዳዋን የፀሀይ ወገግታ፣የማይሰለቸውን የአዕዋፍ ዝማሬ፣
የጠዋቱ የአየር ቅዝቃዜ ደግሜ ስለማላያቸው ናፈቁኝ የኔ ጊዜ የዛሬዋ ምሽት ነችነገ የኔ አይደለም"...እያልኩ
ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ "ሜርሲዬ ካሁን በሗላ የሚመጣ አይመስለኝም ሄዷል" አለች ባርሰናይት ዝግ
ባለ ሹኩሽኩታ "ሰውዬው ሊሄድ ይችላል ግን ምሽቱን እንደዚ እየተጠባበቅን ማሳለፍ አለብን" አልኩኝ
ለሁላችንም ደህንነት አስቤ..."ግን ማን ሊሆን ይችላል" ብላ ጠየቀችኝ ቅድስቴ "ቀን ላይ የወደቀ መኪና
የሚያነሳውን ሹፌር ተናግረነው ነበር ከሱ ውጪ ማንም አይሆንም" ብዬ መልኩላት "ሜርሲ ያን ያህል እኮ
የሚያስከፋ ንግግር እኮ አይደለም ከተማ ውስጥ ከዚ የባሰ እላፊ እንነጋገራለን እኮ" አለ ባባ በተጨነቀ እና
ራሱን በወቀሳ ስሜት ውስጥ አስገብቶ..."ይሄ ሰውዬ ንግግርን እንዴት እንደሚረዳ ባላውቅም በትንሽ ነገር
የሚቆጣ አይነት ሰው ይመስለኛል" አለች የኔ ውድ ጓደኛ ባርሰናይት "ልክ ነሽ ባርሳ እኔም እንደዛ ነው
ማስበው" ብዬ ሀሳቧን ደገፍኩላት...አንድ ነገር ገርሞኛል ያ ሰውዬ መጥፎና ገዳይ መሆኑን ጓደኞቼ
ማመናቸው...አይ የጭንቅ ጊዜ...ምነው በሰላሙ ሰዓት ያልኳቸውን ሰምተው ከዚ ቦታ በሄድን ነበር አሁን
ከረፈደ በሗላ ቢያውቁት ቢያውቁት ምን ጥቅም ይኖረዋል..."ጅብ ከሄደ ውሻ" አልኩኝ በሆዴ...እዛው
እንደተቀመጥን ደቂቃዎች ሰዓትን ወለዱ የጫካው ቅዝቃዜ እጅግ እየጨመረ መጣ ጣቶቼ እስከማይታዘዙ
ድረስ በብርድ ቆረፈዱ..."አረ ይበርዳል ወደ ውስጥ እንግባ" አለች ባርሰናይት "አይሆንም ከተነጣጠልን
ለጥቃት እንመቻለን አብረን ብንሆን ለኛ መልካም ነው" ብዬ በሀሳቧ አለመስማማቴን ገልፅኩላት "በርዶኝ
እኮ ነው ሜርሲዬ ግን እሺ በቃ እዚው እንሁን" አለች ባርሳ "እሽሽሽ ዝም በሉ ቆይ" አልኳቸው ረጋ ብሎ
በቀስታ የሚራመድ የእግር ኮቴ ይሰማኛል ባባ ሽጉጡን አቀባበለ ይመስለኛል ሰውዬው ከድንኳናችን ጀርባ
ነው...ነፍሴ ተጨነቀች ልቤ አካሌን ቀዶ እስኪወጣ መምታት ጀመረ ላቤ ልብሴን እስኪያረጥበው እንደ ጉድ
ይወርዳል እጅና እግሬ አቅም አጥተው ይብረከረካሉ ብቻ መላ ሰውነቴ ተዳክሟል...የማን ስልክ እንደሆነ
እኔንጃ ከተቀመጥበት ቦታ ጮኸ
እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን
ይቀጥላል.
በእናንተው ተደጋጋሚ ጥያቄ ከ 200 like በፊት
ከ 200 like ብሆላ ክፍል 6 ይቀጥላል