Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ጎጆ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_gojo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 479
የሰርጥ መግለጫ

Call us if you want to promote your product and service !!
FOR ANY PROMOTION
CONTACT ☎️ 251923715770 📩 @AbenaG

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 84

2022-09-03 22:00:01 ​​ብር ያለው ሳይሆን ላንቺ ክብር ያለው አግቢ! ወንድማዊነት ምክሬ ነው

መልካም ምሽት
1.1K viewsBiruk, edited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:35:04 እራስህን ብሎም ህይወትህን ለመቀየር ብዙ አማራጮች አሉህ። አንደኛው አማራጭ O.Q.P (Only Quality People) ይሰኛል። ጥራት ያላቸውን ሰዎች ብቻ ትወዳጃለህ፣ ከህልመኞችና ከባለራዕይዎች ጋር ታብራለህ፣ በአዎንታዊነት ከተሞሉ፣ ከዛሬ ጨለማ በላይ የነገ ተስፋን ከሚመለከቱ፣ በእራሳቸው የሚተማመኑ፣ ፈተናዎቻቸውን በእራሳቸው ለመጋፈጥ የሚጥሩና በፍቅር፣ በሃሴት፣ በደስታ የተሞሉ ጥራት ያላቸውን ሰዎች በቻ ታቀርባለህ፣ ትወዳጀለህ። በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ማንነት በቸልተኝነት አትመልከት፤ የትናንሽ ሃሳቦች ባለቤት ከሆኑ አንተም እንደዛው መሆንህ አይቀርም፤ አጀንዳቸው ሁሉ ጊዜያዊ ጉዳይ ከሆነ አንተም ከዛ ውጪ ልታቀነቅን አትችልም። እራስህን ስትመለከት በህይወትህ ትልቅ ስፍራ የሰጠሃቸውን ሰዎችም መመልከትን እንዳትዘነጋ።

@yefiker_gojo
1.6K viewsAbela ŵiž ~V~, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 20:24:53 አያቴ ከመሞቱ በፊት ያለኝን መቼም አልረሳውም
.
.
"አንተ ደነዝ መንሰላሉን በደንብ ያዝ"
2.3K viewsBiruk, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 22:01:57 #ይታየኛል
:
:
ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ
አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ
ምትደውለው ማናት?
የት ነውስ ምታውቃት?
ደርሶ ቁጥርክን ለምንስ ሰጠሀት?
አምጣው ስልኩን በቃ!! እንደውም ላዋራት!!
ሁሌ ባልሺኝ ቁጥር አላማርርሽም
አሁንስ ሰለቸሺኝ መቼም አልልሽም።
:
:
ሁለታችን ሆነን ስናቀና መንገድ
በፊት ከማታውቂያት ወይ ወዳጅ ወይ ዘመድ
ድንገት ስንገናኝ ከሁሉ አስቀድመሽ
እኔ ባለቤቱ አንቺ ግን ምኑ ነሽ?
ባልሺም ጊዜ ከቶ አልነደድኩብሽም
ለሰው ይምሰል እንጂ ለኔ ግን በፍፁም ጨቅጫቃ አይደለሽም።
:
:
ስልኬን ስትነካኪ ካየሽ የሴት ፎቶ
ቁጣሽ ግሎ ንሮ ወዲያው ደምሽ ፈልቶ
ባይንሽ ቂጥ እያየሽ የጥያቄ ውርጅብኝ
ገና አንዱን ሳልመልስ ስላዘነብሺብኝ
ጭራሽ አይከፋኝም
አዎንታዊነቱ እኔን አይጠፋኝም።
:
:
እቤታችን ሆነን ተቃቅፈን በደስታ
እየተሳሳቅን ፊልም ያየንም ለታ
አንዲቷን ተዋናይት እንደው ሳላስበው
ያልኩሽ እንደሆነ በጣም ነው ምታምረው
ከባጡም ከቆጡም ሰበቦች ደርድረሽ
እየገላመጥሺኝ ቻናሉን ቀይረሽ
ሌላ ሌላ ነገር ስትከፍቺብኝም
ጨቅጫቃነት መስሎ እኔን አይሰማኝም።
:
:
አንዳች ጉዳይ ገጥሞኝ
ከደጅ ውዬ ማታ እቤቴ ስመጣ
እየቀየጥሺብኝ ሰላምታና ቁጣ
ከማን ጋር የት ገብተክ ከማን ጋር የት ወጣ
ከማን ጋራ ምን በልተ ምንስ ደግሞ ጠጣ
ብለሺኛል ብዬ አልበሳጭ እኔ
የልብሽ ነው እንጂ የአፍሽ ለምኔ።
:
:
የሚገርመው ነገር ...
ዘንድሮ ሰው ሁሉ የት ገባ የት ወጣ ጭቅጭቅ መስሎታል
"ቅናት" ካሉት ቅኔ ሰሙን ብቻ አንግቦ ወርቁን ዘንግቶታል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ ...
ገብቶኛል ድብቁ
ጌጥ ሆኖኛል ወርቁ።
:
:
እንዲ አረግሺኝ ብዬ እንዲያም አልሺኝ ብዬ
አላፈገፍግም ፍቅራችንን ጥዬ።
:
:
እንደውም የኔ ውድ
በየቀኑ ቅኚ በየቀኑ በዪኝ እጅግ ደስ ይለኛል
ከቅናትሽ ጀርባ ፍቅርሽ ይታየኛል
"ቅናት" ሚሉት ቅኔ ወርቁ በርቶልኛል።

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
2.7K viewsBiruk, edited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 21:05:08 አንተ አንተ ነህ!
፨፨፨//////፨፨፨
አዎ! አንተ አንተ ነህ ማንም አይደለህም፤ የፈለከውን ለማግኘትም ማንንም መሆን አይጠበቅብህም፤ ያሻህበት ለመድረስም ሙሉ ማንነትህን መቀየር አያስፈልግህም። እራስህን ሆነህ የተመኘሀውን ህይወት መኖር ትችላለህ፤ በእራስህ ማንነት ከፍ ማለት ትችላለህ፤ በእራስህ ገፅ መድመቅ፣ ማጌጥ፣ መዋብ ትችላለህ። ባለማስመሰልህ አንዳች የምታጣው ነገር ያለ እንዳይመስልህ። ሌሎች የሚመኙትን አይነት ጥንካሬና ብርታት ማጎልበት ትችላለህ። ከመመኘት በዘለለ፣ ከመፈለግ በዘለለ ብዙዎች የሚመኙትንና የሚፈልጉትን ህይወት መኖር ትችላለህ።

አዎ! አብረውህ ላሉ ሰዎችም ሁለት ምርጫ ትሰጣቸዋለህ፤ አንድም እውነተኛውን ማንነትህን ተቀብለው፣ ልዩነትህን አክብረው አብረውህ እንዲጓዙ ካልሆነም መንገዱን እንዲለቁልህ። እያንዳንዱ ሰዎችን ለመሳብ፣ ለማሳመን፣ ለመማረክ የምታባክነው ጊዜና ስሜት እጅግ ውድ ነው፤ መልሰህ የምታገኘው አይነት አይደለም። በሌሎች ህይወት ውስጥ ቦታ ለማግኘት የገዛ ብረሃንህን ስታጣ፣ በጨለማ ስትዋጥ፣ ነገሮች ሲደበዝዙብህ ተመልከት። እይታህን ወደራስህ ካላዞርክ የሚያርፍብህ አይን እንደማይ ኖር እወቅ። በየጊዜው ውጪውን እያማተርክ፣ ከሚመጣውና ከሚሄደው ጋር እየተንከራተትክ፣ የእራስ ሰው ፈለጋው አድክሞህ፣ የተወዳጅነት ጡዘቱ ታክቶህ፣ አሳቢና አዛኝ ማሳደዱ ሰልችቶህ የእራስህን ተፈላጊ ማንነት ከመገንባት ይልቅ ፈልገህ የምትሸሸግበትን ሌላ ማረፊያ ማማተርህ ያጠፋሃል እንጂ በፍፁም አጉልቶ ሊያሳይህ አይችልም።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ አንተ ነህ!የሚመወድህ ይወድሃል፤ የሚሸሽህም ይሸሽሃል። በእራስህ ላይ መስራትህ፣ ጠንካራውን አንተ መፍጠርህ ያስከብረሃል፣ ያስወድድሃል። ተፈላጊነትን፣ ተወዳጅነትን ፍለጋ ማስመሰልህና ማሽቃበጥህ ግን ዋጋ ያስከፍልሃል፤ እያሳሳቀ አጉል ቦታ ይጥልሃል። የተገነባ ህንፃ ውስጥ ሄዶ መጠለል ለጊዜው ቀላል ሊሆን ይችላል፤ ህንፃው የፈረሰ እለት ወይም ባለቤቱ ያባረረ እለት ግን ማረፊያም ይጠፋል፣ መጠለያም ይናፍቃል። የሌሎች ህንፃ ማድመቂያ፣ ማሳመሪያ መሆን አይጠቅምህም፤ በጊዜ የእራስህን ህንፃ ገንባ፣ የእራስህን ተወዳጅ ማንነት ፍጠር፣ ተፈላጊ ስብዕናን ገንባ። የእራስህን መታወቂያ አዘጋጅ፤ የእራስህን ድንቅ ማንነት አሳይ፤ ማንንም ሳትጠብቅ በእራስህ ጎልተህ መታየቱን እወቅበት፤ ተፈላጊነትህን ለእራስህም አስመስክር።
Join

@yefiker_gojo
3.1K viewsAbela ŵiž ~V~, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:57:55 ❥...ሴት ልጅ!

ፀጥ ስትል ብዙ ሚሊዮን ሀሳቦችን እያሰበችና
እያብሰለሰለች መሆኑ ይግባህ።!

አፍጣ ስታይህ ለምን እንደዚህ እንደምትወድህ እና
ይህን ሁሉ መሰዋትነት እንደምትከፍልህ እያሰበች ነው።!

አብሬህ እቆማለሁ ስትልህ ማዕበል እንኳ ቢመጣ
አልንቀሳቀስም ማለቷ ነው።

☞አትጉዳት ወይም በተሳሳተ መንገድ አታስባት ......አንተ
ስትራብ ተርባ ፣ ስትቸገር ተቸግራ ፣ ስትራቆት ተራቁታ ፣
ገበናህን ሸፍና የምትኖረው ሚስትህ የልጆችህ እናት
ሚስትህ ናት።

አንተ ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ወንድ ሁን።

@yefiker_gojo
3.1K viewsAbela ŵiž ~V~, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:02:07

ጓደኝነት

ሁለት ተማሪ ጓደኛሞች የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው፡፡ ወደ ትምህርት ቤትም ዘውትር አብረው ነው የሚሄዱት፡፡ አንደኛው ታዲያ የጓደኛውን ቦርሳ ተደብቆ በመፈተሽ ቼኮሌቱን የመስረቅ መጥፎ አመል ነበረበት፡፡

አንድ ቀን በዚህ አመሉ ክፉኛ የጥፋተኛነት ስሜት ተሰማው እና ያደረገውን ሁሉ ለጓደኛው ሊናዘዝ ፈለገ፡፡ ነገር ግን በቀጥታ በጓደኛው ፊት ለመናገር ድፍረት አጣ፡፡ ስለዚህም ደብዳቤ ጻፈለት፡፡

‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ከቦርሳህ ውስጥ ቼኮሌቶቹን ስሰርቅህ የነበርኩት እኔ ነኝ፡፡ ለዚህም በድርጊቴ በጣም ነው የማዝነው፡፡››

ጓደኛውም ደብዳቤውን ሲያነብ ሳቀ፡፡ መልሶ ሌላ ደብዳቤ ላከለት፡፡

‹‹ብዙም አትጨነቅ፡፡ ቼኮሌቶቹን ከቦርሳዬ ውስጥ አንተ እንደምትወስድ አውቅ ነበር፡፡ ለዚያም ነው ቼኮሌቶቹን በተመሳሳይ ስፍራ ሁሌም የማስቀምጣቸው፡፡›› ይላል፡፡
________
ስንቶቻችን እንሆን ጓደኛችን እያስቀየመንም ቢሆን ለጓደኝነት ጥንካሬ ስንል አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን የምናልፈው???
ስንቶቻችንስ ለመጣላት እንሮጥ ይሆን እስኪ እራሳችን እንይበት፡፡
1.5K viewsBiruk, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:11:47 ​​. ​           ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

    ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_54


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ(የሸዋ ልጅ)



... ልበልሽ ?" አላት። ሄዋን ወዲያው "አለሜ" ብላ ቃሉን እርግጥ
አርጋ ደገመችው። ከኮማ የነቃች ስሞን አለሜ ብሎ የጠራትን
አስታወሰች።
፨አዳም ይህንን አላስተዋለም እንጂ ትንፍሽ አይልም ነበር።
ይልቅም በውስጡ ያሰበውን ያንን ሀሳቡን ይነግራት ነበር።ሄዋን
ዝም አለች። አዳምም ዝም ብሎ ወደ ጨዋታው ተቀላቀለ። ቦስ
ዲናን ፈዞ ያያታል እሱም እንደነ አዳም እና ሄዋን ዲናን አቅፎ
እሳት እየሞቀ በጋራ ጋቢ መልበስ ፈለገ።
፨ዲና ቡናውን አፈልታ ጨረስች። ከዛም ልታነሳሳው ስትል
አንደኛዋ ስራተኛ "ተይው እኔ አነሳዋለው" አለቻት።ዲና "እሺ አንቺ
ካነሳሽውማ" ብላ ቦስ ጋር ሄደች። ቦስ ጋቢውን በጋራ እንዲለብሱ
አመቻችቶ ተቀመጡ። ሁሉም በጋራ ማውራትና መሳሳቅ ጀመሩ።
እዚህው ፓርኩ ላይ እንቆይ ብላ ዲና ባመጣችው ሀሳብ
ተስማሙ።
፨ ሌላኛዋ ሰራተኛ ተነስታ ሻይ አፈልታ በኩባያ ፔረሙዝ ሻይ እና
ወተት አመጣችላቸው ሁሉም የመረጠውን ይዞ ጨዋታቸው እስከ
ምሽቱ 6:45 ቆየ። ዲና ድህረ-ገፅ ላይ ስላየቻቸው ቀልዶች
እየነገረቻቸው ስታስቃቸው ቆዩ በተጨማሪም ቦስ ዲናን
በሚቀጥለው አመት ጥር ላይ እንደሚያገባት ተናገሩ አያይዞም
ፍቃድ ጠየቃትና ተስማሙ።
፨ ከእሩቅ አደለም ከቅርብ ላያቸው እንኳንስ በህይወታቸው ከባድ
ነገር እያሳለፉ ያሉ ቀርቶ ለአንድ ቀንም ቢሆን መጥፎ ነገር ያሳለፉ
አይመስሉም ወይም ደሞ ክፉውን አልፈው ደስታን እያጣጣሙም
ይመስላል ። በመጨርሻ ሁሉም ስለደከመው ዘበኛው እሳቱን
አጥፍቶ ሁሉም ወደየ አልጋቸው ሄደው ተኑ።
፨ የጓሮ ቤት ዶሮ 12 ሰአት መሆኑን ለማብስር ፤"እስይ ደስ
ይበላቹ አምላካቹ የዛሬ ሰው እንድትሆኑ ፈቅዶላችዋል ፤ እኔም ልክ
እንደ እናንተ ነግቶልኛል። ምስጋኔዬን በጩከት ገልጫለው
፤እናንተም ተነሰታቹ ፈጣሪን አመስግኑ የሚለውን መልክት
ለማስተላለፍ ጫኸ።
፨ዲና ተነሳች 12 ስአት ከሆነ በኋላ እንቅልፍ ባይኖ አይዞርም ኧር
እንደውም ከዶሮውን ጩከት ቀደማ ነው የተነሳችው። ተነስታ
አንድ ነገር እየፃፈች ነው ይህንን ነገር ማድረግ ከጀመረች 6 ወር
ከ 15 ቀን ሆኖታል። የምትፅፈው ስለ አዳም እና ሄዋን ታሪክ ነው።
አዳም ስለነገሯት ታሪኮች እና እሷ ሳይካትሪስት እንደመሆኗ
የምታስበውን በሌላ መንገድ ደሞ ሳይካትሪስት ባትሆን እና እንደ
ሳይካትሪስት ሳይሆን በሙያው ውስጥ እንደሌለ ሰው ስታስበው
የሚስማትን ስሜት እሷ በመማር ያላመጣችውን የሰውን ፀባይ
ማወቁን ብቻ አዳምን የታዘበችበት እና ያየችበት መንገድን
አስፍራለች።ይህንን መፅሀፍ መምህሬ ብላ ሰይማዋለች።
ግን ይህንን ከእሷ በቀር ማንም አያውቅም የቀን ተቀን ውሏቸውን
በሚገባ እና ሳቢ በሆነ መልኩ አስፍረዋለች። ዲና 1:15 ሲሆን
ሁሉንም ለመቀስቀስ ከመኝታ ቤቷ ወጣች።
፨ከዛም ካሜራዋን እንደተለመደው አመቻችታ ዝግጁ ሆነች። ዛሬ
ዲና ፈርታለች። "ምን አልባት የቀጠረኝ ስውዬ የጌዲዮን ሰው
ቢሆንስ? እና አዳም እንደነገረኝ ጊዲዮን ስው ለመጉዳት ሲያስብ
መጀመሪያ በዙሪያቸው ያሉትን ስዎች እንደሚጎዳ አዳም የነገራት
ትዝ አላት
፨ሮጥ ብላ መኝታ ቤቷ ገብታ ልሙጥ ሉክ አውጥታ ለአዳም
ለሄዋንና ለቦስ የሚሆን ደብዳቤ ለ15 ደቂቃዎች ፃፋ ስትጨርስ
ካሜራዋን አብርታ ሄዋን ጋራ ሄደች።አልተኛችም ሄዋን አሟት ፊቷ
ገርጥቶ ነበር።ሄዋን ትራሷን ተደግፋ ተቀምጣ ነበር። ዲና ስታያት
በጣም ደነገጠች።
፨"እህቴ ምን ሆንሽ?"አለቻት ሄዋን ግን መልስ አልስጠቻትም ዲና
ተነስታ አዳም እና ቦስን በጩከት ጠራቻቸው። ሁለቱም በእሩጫ
መጡ። "ምነው አሉ?" ሄዋን መኝታ ቤት በር ላይ ደርሰው።
ዲና"ሄዋን አሞታል ፊቷ በጣም ያስፈራል"አለች። አዳም ዲናን
ከበሩ ዞር አድረጎት ገባ። ቦስም ተከተለው። ስራተኞቹም በፍጥነት
ሮጠው መጡ።ሄዋን እንድታወራ ብዙ ሞከሩ እሷ ግን ትንፋሽም
አላወጣችም።ዲና ለዶክተር ልደውል አለች። አዳም ግን ወደ
ህክምና ቦታ እንውሰዳት አለ። ቦስ በበኩሉ ትንሽ እንድትረጋጋ ቤት
እርፍት ብታረግ እና ከባሰባት ደሞ ወደ ህክምና እንውሰዳት
"ምኗን አመማት ብለን እንወስዳታለን?"አሉ ዲና በመጨርሻ አንድ
ሀሳብ አመጣች።"ለዶክተር ሉሊት ደውለን እሷ ሳይካትሬስትም
ስለሆነች በቀላሉ ሄዋንን ትረዳታለች"አለች። ሁሉም አዎ ጥሩ
ጥሩ ነው አሉ።ዲና ወዲያው ደወች። ዶክተሬት ወዲያው
አነሳችው። ዲና ስላምታ አስቀድማ የተፈጠረውን ለዶክተር ሉሊት
ነገረቻት። ዶክተር ሉሊት በፍጥነት እንደምትመጣ እርፍት ላይ
ስለሆነች ሙሉውን ጊዜ ከሄዋን ጋራ እንደምታሳልፍ ነገረቻት። ዲና
የዶክተር ሉሊትን እርጋታ ሰምታ ግራ ተጋባች።"እሺ በቃ ነይ
ቶሎ" አለቻት ዶክተሪት "እሺ እንዲህ ያለ ነገር ለእንደ ሄዋን አይነት
ሰዎች ጥሩ ነገር ነው" አለችና ስልኩን ዘጋችው። ዲና አዳምና
ቦስን ወደ በረንዳ ይዛቸው ወጥታ ዶክተሪት ያለችውን ነገርቻቸው።
፨ ከ 1 ስአት በኋላ ዶክተሪት መጣች።ሁሉንም አስወጥታ ሄዋንን
መኝታ ቤቷ አስቀረቻት።ሁሉም ሳሎን መንጎራደድ ጀመሩ።ዶክተሪት
ከቆይታ በኋላ ወደ ሳሎን ዶክተሪት መጣች።ሁሉም ምን ተፈጠረ?
ምን ሆና ነው? አልዋት። ዶክተሪት እንዲረጋጉ እና ለማስታወስ
የሚረዳት የምትውጠው መዳኒት ስላልተስማማት እንደሆነ
በተጨማሪም ደሞ ብዙ ስዎች እንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ያሉትን
ሰዎች በህክምና ስራዋ እንደምታቃቸው ነገረቻቸው።
፨ይህንን እያወሩ ሳለ ከ ሄዋን ክፍል መስታወት ሲሰበር ሰሙ
ሁሉም እሩጠው ሄዱ። እናም ባዩት ነገር ተደናገጡ። አዳም
ሄዋዋዋዋዋንንንንንንን ብሎ ጮከ...

                  ይቀጥላል...


.............. ••● ●•..............        

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን
                    
           https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን
                     
            https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                      
            https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                       
            https://bit.ly/3mDyzfx

                 ◎◦#ሼር◦◎
                 ◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo   ||       @AbenaG
  ━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
3.0K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, edited  16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:43:23 አንቺን ማፍቀር ባለመቻሌ
ልትወቅሽኝ አይገባም

ምክንያቱም ልቤ ውስጥ
ያለውን ቁስል መመልከት ስለማትችይ

@yefiker_gojo
3.9K viewsBiruk, 09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:11:05 #የኔ አዳም

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም
#ወዴት ነህ?


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@yefiker_gojo
@yefiker_gojo
የፍቅር ጎጆ
2.3K viewsBiruk, edited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ