Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ጎጆ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_gojo — የፍቅር ጎጆ
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_gojo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 479
የሰርጥ መግለጫ

Call us if you want to promote your product and service !!
FOR ANY PROMOTION
CONTACT ☎️ 251923715770 📩 @AbenaG

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 85

2022-08-31 13:13:28
የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ
በኮፍያህ ይተምኑልሃል፤ ጫማ ከሌለህ እግርህ አይታይም፤ መከራ ተሸክሞ
ሲኖር ያላዩትን ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ...
ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማል።
***

እያዩ ፈንገስ


#መልካም ጊዜ !!


ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@abenag አድርሱን

┄┉┉✽‌
»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉
2.1K viewsBiruk, edited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:55:52
ወንድሜ እኮ ነው! አ ይ ከ ብ ደ ኝ ም ::

ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ታሪክ በጃፖን አገር የሆነ እውነተኛ ክስተት ነው :: ልጁ በጃፓን በጦርነቱ ወቅት : የሞተውን ወንድሙን በጀርባው አዝሎ አብሮት ካለው ወታደር ጋር ረዥም የእግር ጉዞ ያደርግ ነበር::

ወታደሩ ክስተቱን አስተውሎ ልጁን በጉዞው እንዳይዝልበት በማሰብ በቃ "ወንድምህ ሞቷል : ቅብረውና ጉዟችንን እንቀጥል" ብሎ ይጠይቀዋል :: ልጁም መልሶ ወንድሜ እኮ ነው! ለእኔ አይከብደኝም ሲል መለሰለት:: ወታደሩም ልጁ ለወንድሙ ያለውን እውነተኛ ፍቅር ተመልክቶ እንባውን አፈሰሰ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምስል በጃፓን አገር የአንድነት ምልክት ሆኖ ይኖራል::

ምንም እንኳን ታሪኩ በጃፓን አገር የሆነ ቢሆንም :የዚህ ፎቶ እውነተኛ ታሪክ ለእኛም የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እውነተኛ ፍቅር ምልክት ነው!

"ወንድምህ ለአንተ አይከብድህም ምክንያቱም ወንድምህ ነውና... እህትህም ለአንተ አትከብድህም እህትህ ናትና:: ከዚህ እውነት ውጭ ተፈጥሮአዊ አይደለም ስለዚህ:-

ቢወድቅ አንሳው::
ቢደክም ደግፈው::
ቢቸግረው እርዳው::
ፍትህ ቢነፈግ ስለፍትህ ድምጽ ሁንለት::
እርሱን በመሸከም ድከም::
እርሱን ለመደገፍ ጥረት አድርግ::
ስህተት ቢያደርግ ይቅር በለው::
ቢስት መልሰው !
ሰዎች ጀርባቸውን ቢያዞሩበት አንተ ግን በጅርባህ ተሸከመው ::
ለአንተ አይከብድህም :ወንድምህ ነውና ::
ካነበብኩት ያጋራዋቹሁ
@Yefiker_Gojo
2.7K viewsAbela ŵiž ~V~, edited  05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:01:09 አልማዝ የሚሆነው የድንጋይ ከሰል ነው !
አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው
HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High
Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት
ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።
አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ።
ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ
መቀመጥ።
ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት።
አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት !
እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር
ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ
ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ
ብትተዉት ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።
አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ
አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል።
በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree centigrade ቃጠሎ ውስጥ
አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ
"ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣
ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....
"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው?" ስትሉ ....
አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣
ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣
የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣
እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !
አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት:-
አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ
ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት
ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል።
አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።
ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው።
refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ
አለው። ያንጸባርቃል።
ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ
ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።
አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ
የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።
አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ
ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል
አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው
እናገኘዋለን።
የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ
ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም።
አይበላሽም።
የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ
ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል።
በጣም ውድ ነው።
ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ
ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ
አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ።
ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው።
... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ
ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ
ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።


..ዶ|ር ወዳጄነህ...

ቸር ጊዜ!

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@abenag አድርሱን

┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉
561 viewsBiruk, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:00:27 ወሎ

የወሎ ሰው ጨዋታ አዋቂና ወግ አሳማሪ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡
ለምስክር እንዲሆን ከሱፊስቶች ጋር የሚመሳሰል ጨዋታቸውን ከብዙ በጥቂቱ
እነሆ፡፡ [በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጨዋታ የነገሩኝ ወዳጆቼን አመሰግናለሁ]
የቡና ቁርስ
ወሎ ውስጥ ነን፡፡ አንድ እንግዳ ቡና እንዲጠጣ ከጎረቤቶቹ ጥሪ ይደርሰዋል፡፡
ቤታቸው ሄዶ ቁጭ እንዳለ ቡና ከመቅረቡ በፊት ምግብ እንዲቀምስ የእጅ ውኃ
አመጡለት፡፡ እንግዳው በቅርብ ስለበላ ቡና ብቻ መጠጣት እንደሚፈልግ
ይነግራቸዋል፡፡ ሰዎቹም ፤ እንግዳው ሊያፍር ይችላል በሚል እጁን እንዲታጠብ
ገፋፉት፡፡ በቀላሉ እንደማይለቁት ሲያውቅ መብላቱን በመሀላ አስረግጦ ተናገረ፡፡
ይሄን ጊዜ ሴትዮዋ ሳቅ አሉና፤
"ተው?! ወጡን ቀምሶ ነበር ወላሂ ማለት" አሉ፡፡ እነሆ ጨዋታ . . .
[አቦል]
ደሴ ውስጥ የነበረ ምግብ ቤት አሉ፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በጋራ
ይጠቀሙበታል፡፡ ከፈለጋችሁ ስሙን "ቄስ መሐመድ" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡
የክርስቲያን እና የእስላም ምግቤት ይላል፡፡ አንድ ከመሀል አገር የሄደ ሰው
በከተማው ሲዘዋወር ምግቤቱን ያየዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ ስለ ወሎ ሙስሊምና
ክርስቲያን ተስማምቶ መኖር ይሰማ ነበር፡፡ እንዴት እንደሚኖሩ ለማየት ፍላጎት
ስላደረበት ጎራ አለ፡፡
ፈራ ተባ እያለ ወደ ምግብ ቤቱ ገቤቶ የቤቱን አንድ ምግብ እንድያመጡለት አዞ
ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ሳይቆይ የታዘዘው ምግብ ቀረበ፡፡ ማዕዱን ሲያይ ከመደነቁ
የተነሳ ከጉርሻው በፊት ሳቁ ቀደመ፡፡ የቀረበለት ሽሮ ነበር! የምግብ ቤቱ ስም
ኀብረታቸውን ለማጠናከር ያደረጉት መላ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ገባው፡፡
[ቶና]
አንድ በመንደሩ የታወቀ ጀግና አንድ ቀን ምንሽሩን ታጥቆ ከቤት ወጣ፡፡ ሰው ሁሉ
አገር አማን ብሎ በተቀመጠበት ወደ ሰማይ ካልተኮስኩ ብሎ ይገላገል ጀመር፡፡
አንድ ወዳጁ ደርሶ ምን ለማድረግ እንዳሰበ ይጠይቀዋል፡፡
"አላህን ልገለው ነው!" አለ ፈርጠም ብሎ፡፡ ሰውዬውም ቀበል አድርጎ፤
"ካገኘኸው ገላገልከን፡፡ ከሳትከው ግን አስጨረስከን" አለው፡፡
[በረካ]
ይህቺ ደግሞ ባቲ ውስጥ ያለች አነስተኛ ምግብ ቤት ነች፡፡ [ አሉ ናት ] የምግብ
ዝርዝር መጻፊያ "ሜኑ" የላትም፡፡ በቤቱ የሚዘጋጀው ሁለት ዓይነት ምግብ ብቻ
ስለሆነ የምግቡ ዓይነት እና ዋጋ ግድግዳው ላይ ነው የተጻፈው፡፡
1. ቀይ ወጥ
2 .ስፔሻል ቀይ ወጥ
አንድ እንግዳ ወደ ምግብ ቤቷ ገብቶ አስተናጋጁን ጠራና ምሣ ምን እንደደረሰ
ይጠይቀዋል፡፡ አስተናጋጁም ወደ ግድግዳው እየጠቆመ፡፡ "ቀይ ወጥ፣ ስፔሻል
ቀይ ወጥ" ይለዋል፡፡ እንግዳው ትንሽ ካሰላሰለ በኋላ ስፔሻሉ ቀርቶ ቀይ ወጥ
ብቻ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡
ምግቡ ቀርቦ መብላት ሲጀምር በቤት ውስጥ ያሉ ድመቶች፤ ሠላሳ ይሆናሉ፡፡
በሙሉ ወደ እሱ መጡ፡፡ አንዳንዶቹ የሚበላውን ለከፉበት፡፡ ከቁጥጥሩ ውጭ
ሲሆን የሚበላውን ትቶ በዛውም ስፔሻል ቀይ ወጡን ለማየት ሌላ ምግብ አዘዘ፡፡
ትንሽ ቆይቶ አስተናጋጁ ያንኑ ቀይ ወጥ ከዱላ ጋር ይዞለት መጣ፡፡
[ምርቃት]
አንድ ደረሳ [ዲያቆን እንደማለት ነው] ብዙ ዓመት አብራው የኖረች ሚስቱ
ትሞትበታለች፡፡ ጓደኞቹ የሐዘኑን ክብደት አይተው ሌላ እንዲያገባ አግባቡት፡፡
እርሱ ግን እንደ ሚስቴ የሚሆን አላገኝም በሚል እምቢ አለ፡፡
ከሁለት ዓመት ውትወታ በኋላ አንድ ጓደኛው አንዲት ልጅ ፈልጎ ይድረዋል፡፡
ዐዲስ ሕይወትም ይጀምራል፡፡ ለሱ ሁሉም ነገር እንግዳ ስለሆነበት በጣም
ተገረመ፡፡ በተለይ አልጋ ላይ ያለው ቆይታ ከጠበቀው በላይ አስደሳች ሆኖ
አገኘው፡፡
አንድ ቀን ይሄ ወዳጁ ትዳር እንዴት ነው ለማለት እሱ ዘንድ ይሄድና፤
"እህ ልጅት እንዴት ናት አንተው?" ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
"አጃኢብ ነው ወላሂ፡፡ መቼም አላህ አያልቅበትም፤ ምነው ይቺንም በገደላት"

ቸር ጊዜ!

#መልካም ምሽት !!


ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@AbenaG አድርሱን

┄┉┉✽‌»‌ ••✿•• »‌✽‌┉┉
2.8K viewsBiruk, edited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:21:19 ከአንቺ ሲያገናኘኝ
ሰአትን ደቂቃን አርዝሞ የፈጠረው
ከአንቺ ሲያገናኘኝ ለምን አሳጠረው
ይሄን ምጠይቀው አንዱን ፈጣሪን ነው
አንቺን ያገናኘኝ ምክኒያት ቢኖረው ነው
ከዛስ አትይኝም...
ልክ አንቺን ሳገኝሽ ሰአቱ ይሮጣል
ዝምተኛውን ልጅ ወሬኛ አርገሽኛል
ብዬ አልዋሽሽም...
ግን...በፊት ከነበርኩት አሁን ብሶብኛል
ከዛስ አትይኝም?...
እድለኛ እኮ ነኝ እያልኩ አወራለው
ለምን ይሆን እንዲ የምታስብልኝ እያልኩ አስባለው
ከዛስ አትይኝም?...
ወደ ላይ አግጥጬ ፈጣሪን አያለው
የውስጧን ባላውቅም ከልቧ ከሆነ የምታስብልኝ
መቼም አትቀይራት እንዳንሰለቻች አንተ ጠብቅልኝ እያልኩኝ ፀለይኩኝ
ከዛስ አትይኝም....
ብቶጅኝ ባትወጅኝ እኔ እወድሻለው
አንቺን ስለሰጠኝ አመሰግናለው።


ከወደዱት አጋሩ

#Share

  ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                   •═••• •••═•
  
     @Yefiker_Gojo    ,,,,,, @AbenaG
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
3.3K viewsReal waver , 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:23:39 የኔ ውድ አንድ ልዪ ቃል ህይወቴን
ሊያስደስተዉ እንደሚችል ታዉቂያለሽ? ይሄንን ቃል
በጆሮዎቼ ለመስማት ማንኛውንም
መስዋት እከፍላለው ....ልብን በሚያስደነግጠው ድምፅሽ እወድሃለው በይኝ

Join
@yfiker_gojo @abeloo_neww
3.4K viewsAbela ŵiž ~V~, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:55:21 የውይይት ጥያቄ

ለእናንተ ውበት ምንድነው?
4.9K viewsBiruk, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:28:01 ​​. ​           ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

   ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_53


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ(የሸዋ ልጅ)



... ሄዋን ጋደም ካለችበት ተነስታ ቦስን
የሚለበስ ነገር አለበሰችው።
ከዛ ሄዋን አዳምን "ወደ በረንዳው እንሂድና እዛ እናውራ" ብላው
እሱም እሺ ብሉዋት ወጡ። ከዛ በረንዳው ላይ ቁጭ ብለው ሄዋን
"ስለ ጀመርክልኝ ታሪክ ንገረኝ" አለችውና መናገር ጀመረ። "ዛሬ
የምነግርሽ ልጁ ለልጅቷ ቀለበት ያስረላትን ጊዜ ነው"።አላት ሄዋን
"እሺ ደስ ይለኛል ከእዛ በፊት ግን አንድ ጥያቄ አለኝ ቆይ
ለምንድነው ሁሌ እጀ እና አንገተ ሙሉ ልብስ የምትለብሰው
በሙቀት ስአትም በብርድ ስአትም ልክ እንደ ቦስ ለምንድነው
ቲሽርት ቦዲ ምናምን የማታረገው" አለችው። አዳም ደንገጥ አለና
ፈገግ ብሎ "አይ የአየር አላርጂክ ስላለብኝ ነው"። አላት። "እና
መድሀኒት የለክም" አለችው። "አይ መዳኒትማ አለው እስቲ ቦስ
በቀጣይ ወር በረራ ስላለው ያመጣልኛል" አላት። "እንዴ የምን
በረራ አልገባኝም" ስትለው "ከዲና ጋር ለመሄድ አስቧል" አላት።
"ወዴት" አለችው "እሱን አላውቅም" አላት። አዳም ይህን ምክንያት
እንዴት እንደፈጠርው ገረመው። በእርግጥ "አንገተ ሙሉ እና እጀ
ሙሉ ልብስ የምለብስው አንቺ አንገቴ እና እጄ ላይ ያለውን
ንቅሳት እንዳታይብኝ ነው" ብሎ ቢነግራት ደስ ይለው ነበር። ግን
አይሆንም በጭራሽ የዶክተር ድምፅ ያቃጭልበታል "ስለ ወደፊት ህይወቷ አሁን ላይ ብታውቅ ምን አልባት በትንሹ ልታስታውስ
ትችል ይሆናል። ግን በድጋሜ ትረሳለች በድጋሜ ከረሳች ደሞ
መቼም አታስታውስም" የሚለው ንግግር አዳም በሀሳብዋ ተዋጠ።
አዳም አለችው ሄዋን። ደንገጥ ብሎ "ወዬ" አላት። "ምን ሆነካል
ችግር አለ?" አለችው። "አይ አይ አታስቢ ምንም ችግር የለም"
አላት።
፨ ሄዋን "እንዲ ስትሆን አልወድም ካንተ በበለጠ እኔ
እጨነቃለው" አለችው። አዳም ይህንን ከሄዋን ስለስማ በጣም
ተደስተ። "እሺ አልጨነቅም በቃ ታሪኩን ልንገርሽ?" አላት። "እሺ
ደስ ይለኛል ቀጥል" አለችው።
፨አዳም ያኔ ወዳሳለፉት ጊዜ በሀሳብ ተጓዘ። ያንን ጊዜ እያሳለፈው
መስለው።ሄዋንም ፈገግታው ተጋብቶባት ፈገግ አለች።የእዛን ጊዜ
ፈገግታ በታከለበት መልኩ አንድ በአንድ ነገራት። ሄዋን በጣም
ተገርመች።
፨ አዳም ዲና ትዝ ብላው "እስቲ ልደውልላት" አለና ደወለላት
ስልኳ አይነሳም ዲና የስልኳን ድምፅ አጥፍታ ከዶክተር ጋር
እያወሩ ነው። በጣም ወደራቀና ስው ወደማያቸው ቦታ ሄደው።
ዲና የተፈጠርውን ለዶክተር ስትነግራቸው ዶክተር በጣም አዘኑ
ተበሳጩም። "አዳምን እንዴት ከእዚህ ጉድ እናውጣው?" ብለው
ተማከሩ ምንም አይነት ሀሳብ ሊመጣላቸው አልቻለም። ግን
ይህንን ነገር ለማንም ላለ መናገር እና በእየ ግላቸው አስበውበት
በቀጣይ ቀን ለመገናኘት ወስነው። በዲና መኪና ገብተው ወደ
መጡበት ጉዞ ጀመሩ።
፨የዶክተርን መኪና እዛው ከተገናኑበት ቦታ አቅራቢያ ባለው
የመኪና ማቆያ አስገብተዋታል። ዲና መኪናዋን ከማስነሳቷ በፊት
ስልኳን ድምፅ ላይ ለማድርግ ከለበሰችው ሊዘር ጃኬት
አወጣችው። አዳም ደጋግሞ ደውሎላት ነበር። አዳም ጋር
ደወለች። አዳም ቦስ ከእንቅልፋ ተነስቶ ስለነበር ከእሱና ከ ሄዋን
ጋር ያቆርጡትን ውድድር እያዩ ነው። ፈጠን ብሎ ስልኩን አነሳው።
ዲና "ሄሎ አዳምዬ" አለችው።አዳም ፈጠን ብሎ "ሄሎ እንዴት ነሽ"
አላት። ሄዋን ስልኩን ከአዳም መንጭቃ "እህቴ ኧር ናፈቅሽኝ"
አለቻት። ዲና "እየመጣው ነው" አለች። የማታውቀው ቁጥር
ዊቲንግ ሲገባ አየችው። "በቃ እየመጣው ነው ባሌን
ተንከባከቡት" ብላ ስልኩን ዘጋችው። ወዲያው ያንን የማይታውቅ
ስልክ አነሳችው "ሄሎ" አለች አይስማም ዘጋችው።ከዛ መኪናውን
ማሽከርከር ጀመርች በድጋሜ ጠራ ዶክተር አንሱት እና ላውድ
አርጉት አለች።ፈርታለች። ጋቢና የተቀመጡትን ዶክተር አነሱት።
ሄሎ አለ ጌዲዮን ነበር። "አሁን ከፊት ለፊትሽ የምልክልሽን በፀጋ
ተቀበይ ሞትሽ ቀርቧል" አላት። ዲና ቀና ስትል ግዙፍ መኪና ከፊቷ
እየከነፈ ሲመጣ ታያት ከጉኑ ሁለት መኪኖች በተመሳሳይ ፍጥነት
እየመጡ ነው። ዶክተር ደርቀው ቀሩ።ዲና መኪናዋን አቁማ ልክ
እንደ ዶክተር ደርቃ ቀርች...

                    ይቀጥላል...


.............. ••● ●•..............        

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን
                    
           https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን
                     
            https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                      
            https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን
                       
            https://bit.ly/3mDyzfx

                 ◎◦#ሼር◦◎
                 ◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo   ||       @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
5.1K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, edited  16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:26:28
#አሜን_LUXURY ለአዲስ አመት የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ብራንድ ሽቶዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዞላቹ መቷል።


CONTACT US   +251964593642
                             +251906495051
                             +251907495051


➵ ENLIGHTED LUXURY

➵ AMAZING FRAGRANCE

➵ PACKED

➵ FROM PARIS

➵ WITH FAIR PRICE

➵ FREE DELIVERY


CONTACT US ON TELEGRAM
                                   t.me/AM_CS
                                        t.me/AM_CS1
                                        t.me/AM_CS2
4.0K views♕𝙰𝙱𝙴𝙽𝙸 𝙹𝙲❥̟, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:32:16 አንቺን ለመሳም የመጨረሻው
እስከሆንኩ ድረስ መጀመሪያ ማንም
ቢስምሽ ግድ የለኝም።

ከልባቸው ሚያፈቅሩ ቶሎ አያረጁም።

ምን አልባት አንድ ቀን ምን ያክል
አፈቅርሽ እንደነበር ትረጅ ይሆናል
ታዲያ አንቺም ተፀፅተሽ ልታፈቅሪኝ
ትሞክሪ ይሆናል ያኔ ግን አንቺን
እየጠበኩ ላይሆን ይችላል

ከልብሽ የሚወድሽ ሰው
አይጎዳሽም።ም/ክ ከጎዳሽ ጉዳትሽ
አይኖችሽ ውስጥ ይመለከታልና።ይህ
ደሞ እሱንም ይጎዳዋል።

ላንቺ ሁሉንም ነገርሽ ለሆነ ለሱ ግን
ምንም እንዳልሆንሽ ከተረዳሽው ጎን
መቀመጥ በእርግጥ ያማል

ያገኘሀትን ሴት በቀላሉ እንዳገኘሀት
ከማሰብ ይልቅ በፍቅር ልትይዛት
ይገባል ም/ክ ድንጋይ ስትሰበስብ
እንቁህን ልታጣ ትችላለህና።

#ሼር

#Share

  ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                   •═••• •••═•
  
     @Yefiker_Gojo    ,,,,,, @AbenaG
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━
     
4.2K viewsReal waver , 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ