Get Mystery Box with random crypto!

#ይታየኛል : : ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ ምትደውለው ማና | የፍቅር ጎጆ

#ይታየኛል
:
:
ሴት ከሆን ማናግር ስልክ ተደውሎ
አናትሽ ላይ ወቶ የሆነ ዛር ዘሎ
ምትደውለው ማናት?
የት ነውስ ምታውቃት?
ደርሶ ቁጥርክን ለምንስ ሰጠሀት?
አምጣው ስልኩን በቃ!! እንደውም ላዋራት!!
ሁሌ ባልሺኝ ቁጥር አላማርርሽም
አሁንስ ሰለቸሺኝ መቼም አልልሽም።
:
:
ሁለታችን ሆነን ስናቀና መንገድ
በፊት ከማታውቂያት ወይ ወዳጅ ወይ ዘመድ
ድንገት ስንገናኝ ከሁሉ አስቀድመሽ
እኔ ባለቤቱ አንቺ ግን ምኑ ነሽ?
ባልሺም ጊዜ ከቶ አልነደድኩብሽም
ለሰው ይምሰል እንጂ ለኔ ግን በፍፁም ጨቅጫቃ አይደለሽም።
:
:
ስልኬን ስትነካኪ ካየሽ የሴት ፎቶ
ቁጣሽ ግሎ ንሮ ወዲያው ደምሽ ፈልቶ
ባይንሽ ቂጥ እያየሽ የጥያቄ ውርጅብኝ
ገና አንዱን ሳልመልስ ስላዘነብሺብኝ
ጭራሽ አይከፋኝም
አዎንታዊነቱ እኔን አይጠፋኝም።
:
:
እቤታችን ሆነን ተቃቅፈን በደስታ
እየተሳሳቅን ፊልም ያየንም ለታ
አንዲቷን ተዋናይት እንደው ሳላስበው
ያልኩሽ እንደሆነ በጣም ነው ምታምረው
ከባጡም ከቆጡም ሰበቦች ደርድረሽ
እየገላመጥሺኝ ቻናሉን ቀይረሽ
ሌላ ሌላ ነገር ስትከፍቺብኝም
ጨቅጫቃነት መስሎ እኔን አይሰማኝም።
:
:
አንዳች ጉዳይ ገጥሞኝ
ከደጅ ውዬ ማታ እቤቴ ስመጣ
እየቀየጥሺብኝ ሰላምታና ቁጣ
ከማን ጋር የት ገብተክ ከማን ጋር የት ወጣ
ከማን ጋራ ምን በልተ ምንስ ደግሞ ጠጣ
ብለሺኛል ብዬ አልበሳጭ እኔ
የልብሽ ነው እንጂ የአፍሽ ለምኔ።
:
:
የሚገርመው ነገር ...
ዘንድሮ ሰው ሁሉ የት ገባ የት ወጣ ጭቅጭቅ መስሎታል
"ቅናት" ካሉት ቅኔ ሰሙን ብቻ አንግቦ ወርቁን ዘንግቶታል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ ...
ገብቶኛል ድብቁ
ጌጥ ሆኖኛል ወርቁ።
:
:
እንዲ አረግሺኝ ብዬ እንዲያም አልሺኝ ብዬ
አላፈገፍግም ፍቅራችንን ጥዬ።
:
:
እንደውም የኔ ውድ
በየቀኑ ቅኚ በየቀኑ በዪኝ እጅግ ደስ ይለኛል
ከቅናትሽ ጀርባ ፍቅርሽ ይታየኛል
"ቅናት" ሚሉት ቅኔ ወርቁ በርቶልኛል።

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢