Get Mystery Box with random crypto!

በልብሽ አስበሽ የኔን ልብ ለመስበር እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ ላለ | የፍቅር ጎጆ

በልብሽ አስበሽ የኔን ልብ ለመስበር
እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር
እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ
ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር

ሚል ግጥም ሰጥቼሽ ከቤቴ እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አንገቴን ቀብሬ
ቁጭ ብዬ አነባው

አየሽ! መለየትሽ ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው
ምን ላርግ ወንድ ልጅ ነኝና
ባደባባይ ስቄ ቤቴ ነው የማለቅሰው

Join & Share

@Yefiker_Gojo
@Yefiker_Gojo