Get Mystery Box with random crypto!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @wuludeyared
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.38K
የሰርጥ መግለጫ

“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ
ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡
መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት
⬇️⬇️

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 13:13:32

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ቀን የከበረ አባ ሞይስስና እኅቱ ሣራ በሰማዕትነት አረፉ።



የእሊህም ቅዱሳን ወላጆቻቸው ደጎች እጅግም ባለጸጎች ናቸው። የከበረ ሞይስስ ነሓሲ ወላጆቹ ከአረፉ በኋላ እኅቱ ሣራን ሊያጋባትና ወላጆቹ የተዉትን ገንዘብም ሊሰጣት እርሱም ወደ ግዳም ሒዶ ሊመነኩስ አሰበ። ይህን አሳቡንም በነገራት ጊዜ እንዲህ ብላ መለሰችለት እኔን ልታጋባኝ ከወደድክ አስቀድሞ አንተ አግባ እርሱም እንዲህ አላት እኔ ብዙ ኃጢአት ሠርቻለሁ ስለዚህ ኃጢአቴን ለመደምሰስ እመነኵስ ዘንድ እሻለሁ ማግባት አይቻለኝም የነፍሴን መዳኛ አስባለሁ እንጂ። ሁለተኛም እንዲህ ብላ መለሰችለት አንተ ነፍስህን ስታድን እኔን በዓለም ወጥመድ ውስጥ እንዴት ትጥለኛለህ። እርሱም እንዲህ አላት ምንኵስና ከፈለግሽ ስለ ራስሽ የምታውቂ አንቺ ነሽ እኔም የወደድሽውን አደርግልሻለሁ። እንዲህም አለችው ለነፍስህ የምታደርገውን ለኔም እንዲሁ አድርግ እኛ ሁለችን ከአንድ ባሕርይ፣ ከአንድ አባት ከአንዲት እናት የተገኘን ነንና፤ የልቧንም ቆራጥነት አይቶ ወዲያውኑ ከእርሷ ጋራ ተነሣ ገንዘባቸውንም ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተኑ። ከዚህም በኋላ እኅቱ ሣራን ወሰዳት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ወዳለ የደናግል ገዳም ውስጥ አስገባት እርሱም ከወንዶች ገዳም ገብቶ በዚያ ተጋድሎን ተጋደለ። እንዲሁ እኅቱም ጽኑዕ በሆነ ገድል ተጠምዳ እየተጋደለች ሁለቱም ሳይገናኙ ዐሥር ዓመት ኖሩ። በሊቀ ጳጳሳት አባ ድሜጥሮስ የሹመት ዘመን ሳዊርያኖስ የሚባል ከሀዲ ተነሥቶ የክርስቲያንን ወገኖች ማሠቃየት ጀመረ። ከመነኰሳት ገዳማውያም ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። አባ ሞይስስም ተነሣ ሊሰናበታትም ወደ እኅቱ ሣራ ላከ በሰማዕትነት መሞት እንደሚሻም ነገራት። እኅቱም በሰማች ጊዜ ወዲያውኑ ተነሣች፣ ሄዳ፣ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ እንድታሰናብታት እመ ምኔቷን ለመነቻት እመምኔቷም ጸለየችላት ሰላምታም ሰጥታ አሰናበተቻት እርሷም ደናግሉን ሁሉ ተሰናበተቻቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ወንድሟ ሄደች በጐዳናም አገኘችውና እርስ በርሳቸው ሰላም ተባባሉ ወደ እስክንድርያ ከተማም ገብተው በመኰንኑ ፊት ቁመው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ከዚህም በኋላ ራሳቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።



በዚህችም ቀን የከበሩ መነኰሳት አጋቦስና ቴክላ በሰማዕትነት አረፉ።



እሊህም ቅዱሳን በከሀዲው ዮልያኖስ ዘመን መከራ በመቀበል ተጋደሉ። ከመኳንቶቹም አንዱ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው። ሥቃያቸውም ባሰለቸው ጊዜ ለአንበሶች ጣላቸውና ገድላቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።



በዚችም ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች ሣራ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶች አዘዙ።



ይህቺንም ክብርተ ማሕፀን የሆነች ጡቶቿም የተባረኩ ክብርት ሣራን የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ባል እንዳላት ሳያውቅ በወሰዳት ጊዜ እንዳይቀርባት እግ ዚአብሔር ገሠጸው በደዌም ቀሠፈው ባሏ አብርሃምም በጸለየለት ጊዜ ከደዌው ተፈወሰ ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘብ ጋራ ወደ ባሏ መለሳት። ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ተገልጦ ወደ ቤቱ እንግድነት በመጣ ጊዜ ለአብርሃምም የይስሐቅን መወለድ በነገረው ጊዜ ሣራም በድንኳኑ ውስጥ ሳቀች እንዲህ ስትል እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው ሣራን ለብቻዋ ምን አሳቃት እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል እኔም አሁን አርጅቻለሁ ብላ በውኑ ለእግ ዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን ከዚህም በኋላ ፀንሳ እግዚአብሔር ባለው ወራት በርጅናዋ ለአብርሃም ወንድ ልጅን ወለደች። ይስሐቅም በአደገ ጊዜ ልጅዋ ይስሐቅን ከእስማኤል ጋራ ሲጫወት አየችው። አብርሃምንም ሣራ እንዲህ አለችው ያቺን ባሪያ ከነልጅዋ አባራት የባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋራ አይወርስምና። ይህም ነገር ለአብርሃም ስለ ልጁ እስማኤል፣እጅግ ጭንቅ ሆነበት። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው የዚህ ልጅ የዚችም ባሪያ ነገር በፊትህ ጭንቅ አይሁንብህ የምትልህን ሁሉ ሣራን ስማት ከይስሐቅ ዘር ይተካልሃልና። ይህም ነገር ታላቅ ምሥጢር አለው የተመሰገነ ጳውሎስ ቅድስት ሣራን የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጓታልና። ከዚህም በኋላ በበጎ እርጅና በአረፈች ጊዜ ከኬጢያዊ ኤሞር ልጆች በገዛው ቦታ ቀበራት።

ለእግዚአብሔርም ፤ ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረች እናታችን ሣራ በጸሎቷ ይማረን ፣ በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

335 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:40:13
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
383 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:43:02
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
406 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:07:35
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
566 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, edited  11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:48:22 † ምን ብዬ ልጥራችሁ? †
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

… ከሌሎች ከማያምኑት ብልጫ ኖሯችሁ እንዳየው በምፈልገው ሕይወት፥ በኹሉም ረገድ ተቃራኒ ኾናችሁ አያችኋለሁ፡፡

ለምሳሌ

ከቦታ አንጻር፥ ቀኑን ኹሉ የፈረስ እሽቅድምድምንና ተውኔትን፣ ነውርን የተሞሉ ትርኢቶችንና የክፉዎችን ማኅበር፣ ርኵሰትንም የተሞሉ ሰዎችን ስትመለከቱ እንደምትውሉ አያችኋለሁ፡፡

ከፊታችሁ አንጻር፥ ዘወትር ያለ ልክና እንደ አመንዝራ ሴት ስትስቁ እመለከታችኋለሁ፡፡

ከአለባበሳችሁ አንጻር፥ ከተዋንያንና ጠቢባን ነን ከሚሉ ሰዎች ምንም እንደማትለዩ አስተውላችኋለሁ፡፡

ከሚከተሏችሁ ሰዎች አንጻር፥ ብዙ ውዳሴ ከንቱን እንደምትሹ አያችኋለሁ፡፡

ከንግግራችሁ አንጻር፥ ምንም ደኅና ነገር፣ በቁዔት ያለው ቃል፣ ለሕይወታችን የሚረባ ንግግር እንደሌለባችሁ እገነዘባለሁ፡፡

ከማዕዳችሁ አንጻርም ከዚያ ጽኑዕ የኾነ ወቀሳ የሚያመጣባችሁ እንደ ኾነ አያለሁ፡፡

ታዲያ እስኪ ንገሩኝ! ክርስቲያንን ክርስቲያን ከሚያስብሉት ነገሮች እጅግ የራቃችሁ ኾናችሁ እያለ፥ ክርስቲያኖች መኾናችሁን መለየት የምችለው በምንድን ነው? ክርስቲያኖች መባላችሁስ ይቅርና፥ ሰዎች ብዬ ልጠራችሁ የምችለው እንዴት ነው?

ምክንያቱም እንደ አህያ ትራገጣላችሁ፡፡
እንደ ኮርማ ትሴስናላችሁ፡፡
እንደ ፈረስ ከሴቶች ኋላ ኾናችሁ ታሽካካላችሁ፡፡
እንደ ድብ ሆዳሞች ናችሁ፡፡
ሥጋችሁን እንደ በቅሎ ሥጋ ትሰገስጋላችሁ፡፡
እንደ ግመልም ቂም ትይዛላችሁ፡፡
እንደ ተኵላ ትነጥቃላችሁ፡፡
እንደ እባብ ትቈጣላችሁ፡፡
እንደ ጊንጥ ትናደፋላችሁ፡፡
እንደ ቀበሮ ተንኰለኞች ናችሁ፡፡
እንደ እባብ ወይም እንደ እፉኝት በጕረሮአችሁ መርዝ አለ፡፡
እንደ ክፉ ጋኔን ከወንድማችሁ ጋር ትጣላላችሁ፡፡



ታዲያ ክርስቲያኖች የሚለውስ ይቅርና፥ በምናችሁ ሰዎች ብዬ ልጥራችሁ?

ሰው የሚያስብል ምልክት ሳይኖራችሁ እንዴት ብዬ ከሰው ዘንድ ልቊጠራችሁ?

የንዑሰ ክርስቲያኖችና የክርስቲያኖች ልዩነት ባሰብኩ ጊዜ ልዩነቱ የሰውና የበረኻ አውሬ ያህል ይኾንብኛል፡፡

ታዲያ ምን ብዬ ልጥራችሁ? የበረኻ አውሬ ብዬ ልጥራችሁን? እንዲህስ አልላችሁም፤ የበረኻ አውሬዎች እንደዚያ የኾኑት ከተፈጥሮአቸው የተነሣ እንጂ እንደ እናንተ ወደውና ፈቅደው አይደለምና፡፡

ታዲያ ምን ብዬ ልጥራችሁ? አጋንንት ልበላችሁን? እንዲህስ አልላችሁም፤ አጋንንት የሆድ ባሪያዎች አይደሉምና፤ ፍቅረ ንዋይም የለባቸውምና፡፡

ታዲያ ከበረኻ አውሬዎችም ከአጋንንትም የሚብስ ክፉ ግብር ከያዛችሁ፥ ንገሩኝ - ሰዎች ብዬ እጠራችሁ ዘንድ ይገባኛልን?

ሰዎች ለመባል እንኳን የሚበቃ ምግባር ከሌላችሁስ፥ ክርስቲያኖች ብዬ ልጠራችሁ የምችለው እንዴት ነው?

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እኛን ልጆችህን ሰዎች ታደርገን ዘንድ እንማጸንሃለን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

531 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:41:06
468 viewsተስፋ ማርያም, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:41:00


የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የህፃናት ክፍል አባላት
እጅግ በጣም የሚወዱዋትን የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን የንግሥ በዓል በማክበር ላይ

አገልግሎታችሁን ይቀበልላችሁ በቤቱ በሞገስ ያሳድጋችሁ! ፍቅሯን ያብዛላችሁ!



የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእናታችን ቅድስት ክርስቶስሠምራ የቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
በረከት ረድኤት በሁላችን ላይ ይደርብን

483 viewsተስፋ ማርያም, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 05:55:10

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ቅዱስ እንድርያኖስ በሰማዕትነት አረፈ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሃያ አራቱ ባልንጀሮቹ በሰማዕትነት አረፉ።



ይህም እንድርያኖስ ከመክስምያኖስ መኳንንቶች አንዱ ነበረ፤ እርሱም የጐልማሶች አለቃ ነበረ። ለጣዖት መስገድን እምቢ ስለአሉ ንጉሡ ምእምናንን ሲያሠቃያቸው ቅዱስ እንድርያኖስ የሰማዕታትን የልባቸውን ቆራጥነትና በመከራቸው ላይ መታገሣቸውን ተመልክቶ አደነቀ።

እንዲህም አላቸው ይህን ያህል ስትታገሡ ምን ታገኛላችሁ ቅዱሳን ሰማዕታትም የሚጠብቀንን ተስፋ ለመናገር አንደበታችን አይችልም አሉት ስለ ዓለም ድኅነትም ክርስቶስ መከራ እንደተቀበለ ከብሉይና ከሐዲስ መጽሐፍ ነገሩት።

እንድርያኖስም በሰማ ጊዜ ጽሕፈትን ወደ ሚያውቁ ብልሆች ሰዎች ሔደና እኔ ከዛሬ ጀምሮ ክርስቲያን ነኝ ስሜን ከገድለኞቹ ጋራ ጻፉ አላቸው። ለንጉሥ መክስምያኖስም እንዲህ እንዳለ በነገሩት ጊዜ ጠርቶ እንድርያኖስ ሆይ አበድክን አለው እንድርያኖስም ከቀድሞው እብደቴ ተመለስኩ እንጂ እኔ አላበድኩም ብሎ መለሰለት። ንጉሡም ሰምቶ ወደ ወህኒ ቤት ከንጹሐን ሰማዕታት ጋራ እንዲጨምሩት አዘዘ። ከአገልጋዮቹም አንዱ ሄዶ ለሚስቱ እንጣልያ ነገራት በሰማችም ጊዜ ደስ እያላት ወደ ወህኒ ቤት ሄደች ሃያ አራቱ ቀዱሳን ሰማዕታት የባሏን ልብ ያጽናኑ ዘንድ ለመነቻቸው።

እርሱንም እንዲህ አለችው እንግዲህ ላህይህ ደምግባትህም ርስትህም ጥሪትህም አያስትህ ሁሉም ከንቱ ነውና ነገር ግን በእርሱ ዘንድ የማያልፍ መንግሥትን ትወርስ ዘንድ የክብር ንጉሥ ክርስቶስን ተከተለው ይህንንም ብላ ወደቤቷ ገባች።

ከዚህም በኋላ እንድርያኖስን ለፍርድ እንደሚያቀርቡት በአወቀ ጊዜ ሊሰናበታት ወደ ሚስቱ ሔጅሄደ መምጣቱንም ሰምታ የሸሸ መሰላት ደጇንም ዘግታ በውስጥ ሁና እንዲህ እያለች ዘለፈችው ትላንት ትላንትና ሰማዕት ተብለህ ዛሬ ክርስቶስን ካድከውን እንድርያኖስም ሰምቶ የሃይማኖቷን ጽናት አደነቀ እንዲህም አላት እኅቴ ሆይ እንድስናበትሽ ክፈችልኝ አላት። በሰማችም ጊዜ ከፈተችለት ከዚህም በኋላ ሁሉን እያነጋገራት እስከ እሥር ቤት ወሰዳት እንጣልያም ከዚያ በደረሰች ጊዜ የታሠሩትን ቅዱሳን ተሳለመቻቸው ሰማዕታት የታሠሩበትን ማሠሪያቸውንም ሳመች ቍስላቸውንም አጠበች።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ቅዱሳኑን ከእሥር ቤት እንዲያመጧቸው አዘዘ በመጡም ጊዜ ከሥቃይ ብዛት የተነሣ እንደደከሙ አያቸው። እንድርያኖስንም በፊቱ አቁሞ ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱሱም እርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ ንጉሡም የሆድ ዕቃው እስኪፈስስ ሆዱን እንዲደበድቡት አዘዘ በዚያን ጊዜም የእንድርያኖስ ዕድሜው ሃያ ስምንት ዓመት ነበር። ከዚህም በኋላ እንድርያኖስን ከባልንጀሮቹ ሰማዕታት ጋራ ወደ እሥር ቤት መለሱት እንጣልያም መጥታ የቅዱሳንን ደማቸውን ጠራረገችላቸው። እሊህ ቅዱሳንም እንድርያኖስን እንዲህ ብለው ተሳለሙት እንድርያኖስ ሆይ ስምህ በሰማያት በሕይወት መጽሐፍ ተጽፏልና ደስ ይበልህ።

ንጉሡም መስፍ አምጥተው የቅዱሳኑን ሁሉ ጭናቸውን በድጅኖ ይሰብሩ ዘንድ አዘዘ እንጣልያም የእንድርያኖስን እጆቹንና እግሮቹን በመስፍ ላይ ለማኖር ቀደመች ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሰጠ ድረስ የእንድርያኖስን ዐጥንቶቹን ወታደሮች ቀጠቀጡ የቅዱሳኑንም ሁሉ ጭናቸውን ሰብረው ወደ እሳት ወረወሯቸው እሳቱ ግን ከቶ አልነካቸውም። ምእመናንም መጥተው በጨለማ ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱአቸው የመከራውም ወራት እስቲያልፍ ሠወሩአቸው እንጣልያም የእንድርያኖስን የእጁን ቁራጭ ወስዳ በትራሷ ውስጥ አኖረችው ከዚህም በኋላ የሀገሩ ገዥ እንጣልያን ሊያገባት ወደደ በአወቀችም ጊዜ የባሏን የእጅ ቁራጭ ይዛ በመርከብ ሸሸች የቅዱሳኑ ሥጋ ወዳለበትም ደርሳ ወደ እነርሱ ይቀበሏት ዘንድ ለመነች ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ አሳረፋት ከእነ ርሱም ጋራ ተቀበረች።

ለእግዚብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።



በዚህችም ቀን ቅዱሱ አባት አባ ቢጻርዮን አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ነበሩ። ባደገም ጊዜ የምንኵስና ልብስን ለብሶ እግዚአብሔርን ሊያገለግል ወደደ ዓለምንም ንቆ ወደ አባ እንጦንስ ሄደ ለእርሱም ደቀ መዝሙር ሁኖ ብዙ ዘመናት አገለገለው። ከዚህም በኋላ ወደ አባ መቃርስ ሄዶ፣ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትንም አገለገላቸው። በአስቄጥስም ገዳም ይዘዋወር ነበር በቤት ውስጥም አያድርም ነበር። ምንጣፍና ልብስ እስኪያጣ ድረስ ምንም ምን ጥሪት አልነበረውም መነኰሳቱም የማቅ ጨርቅ ይሰጡት ነበር። ወገቡንም ታጥቆ በመነኰሳቱ መንደር ይዞር ነበር በቤቶቻቸውም ደጃፍ እያለቀሰ ይቀመጥ ነበር። የማያውቀውም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ አባቴ ሆይ ምን ያስለቅስሃል ይለው ነበር። እርሱም ንብረቴን ስለዘረፉኝ እንዳልሞት ሸሸሁ ከወገኔም ክብር ተለይቼ በጕስቍልና ወደቅሁ ይለው ነበር። የቃሉንም ምልክት የማያውቅ የጠፋውን ገንዘብህን እግዚአብሔር ይመልስልህ ብሎ ካለው ይሰጠው ነበር። እርሱም ተቀብሎ ይሄድና ለሌለው ይሰጥ ነበር። የቃሉን ምልክት የሚያውቅ ግን በፈቃደ ነፍስ የሚሠሩ ትሩፋትን ሰይጣን ከሰዎች የማረካቸው መሆኑን ልብ ብሎ ያስተውል ነበር። አባቶችም ጭንቅ የነበረ ተጋድሎውን ስለርሱ ይናገሩ ነበር። እርሱ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ከቶ ሳይተኛ ቁሞ ኖሯልና። በምንኵስናውም ወራት ብዙ ጊዜ በየአርባ ቀን ጾመ እነሆ እንዲህ እየተጋደለ ድንቆችንም እያደረገ ኀምሳ ሰባት ዓመታት ኖረ። ቅዱሳን አባ ዱላስና አባ ዮሐንስም ከተአምራቱ ተናገሩ እነርሱ ከርሱ ጋር ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሄዱ እጅግም በተጠሙ ጊዜ እንደተጠሙ አውቆ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መራራውንም ውኃ ጣፋጭ አድርጎላቸው ጠጥተዋል።

በሁለተኛም ጊዜ ወደ ፈሳሽ ውኃ ደርሶ መሸጋገሪያ አጣ ወደ ጌታችንም ጸለየ ያን ጊዜም እንደ የብስ በባሕሩ ላይ ሄደ። በአንዲት ቀንም የከበሩ አባቶች በጸሎታቸው ያድኑት ዘንድ ጋኔን ያደረበትን ሰው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሰዎች አመጡ አባቶችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ስለሚሸሽ ብንነግረው ይህን ጋኔን የያዘውን አያድነውም። ከዚህም በኋላ ምክንያት አድርገው አባ ቢጻርዮን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለጸሎት ወደሚቆምበት ቦታ ያንን ጋኔን ያደረበትን ሰው አስተኙት። አባ ቢጻርዮንም በገባ ጊዜ ያን ጋኔን ያደረበትን ሰው ተኝቶ አገኘውና ቀሰቀሰው እጁንም ይዞ ተነሥ አለው ያን ጊዜም ድኖ ተነሣ አእምሮውም ተመለሰ። ያዩትም እጅግ አደነቁ ለሚፈሩት ስለሚሰጠው ጸጋውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት። የዚህም ቅዱስ ተአምራቶቹ ከነገርናችሁ የበዙ ናቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ያማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።



ዳግመኛም በዚህች ቀን የሰማዕት ኤልያኖስና የእኅቱ አውዶክስያ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

523 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 03:28:52
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
9 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 00:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:18:39
"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"

ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ዓ.ም. ጋብቻሽን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸምሽው - እናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ውሉደ ያሬድን ለበርካታ ዓመታት በልማትና ተራድዖ ክፍል ስታገለግዪ የቆየሽው እህታችን- ዓለም ደርብ እና ወንድማችን በድሉ ደጀኔ

የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ

ስታገለግሉት የኖራችኹት ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!

የዘገየነው መልእክቱ እና ፎቶግራፉ ዘግይቶ የደረሰን በመሆኑ ነው።
275 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ