Get Mystery Box with random crypto!

'ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክር | ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"

ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

ነሐሴ ፳፪ ፳፻፲፬ዓ.ም. ጋብቻሽን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸምሽው - እናት ሰንበት ትምህርት ቤታችን ውሉደ ያሬድን ለበርካታ ዓመታት በልማትና ተራድዖ ክፍል ስታገለግዪ የቆየሽው እህታችን- ዓለም ደርብ እና ወንድማችን በድሉ ደጀኔ

የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ

ስታገለግሉት የኖራችኹት ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!

የዘገየነው መልእክቱ እና ፎቶግራፉ ዘግይቶ የደረሰን በመሆኑ ነው።