Get Mystery Box with random crypto!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @wuludeyared
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.38K
የሰርጥ መግለጫ

“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ
ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡
መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት
⬇️⬇️

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 16:34:38
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
473 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, edited  13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:20:27 ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግና ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሰጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቈርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ። አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ጥቂት ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርግና አረፈ።

ደቀመዛሙርቱም በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

እግዚአብሔር አምላክ ከአባታችን ረድኤቱን በረከቱን ይክፈለን።

                 አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
                                         ቅዱስ ያሬድ


495 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:20:27

   ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

አባታችን ተክለ ሃይማኖት የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ። በዚህም ነገር እያለ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስኪገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደም ግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶቹ ያደርጋቸዋል። በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ፣ በባሕሩ ውስጥ ተሸሽገ። ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት በአያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም  እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ። እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረሚ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት ። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ እያት አድንቆ በልቡ ፕ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ። የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዚእ ኀረያ እንደሆነች አገወቃት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱስ ተፀንሶ በታኅሣሥ ወር በሃያ አራት ተወለደ። በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ በቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው። ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመንፈስ ቅዱስ ጸና። ከዚህም በኋላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት። በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደሀገሩ ተመለሰ ጐልማሳም በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሄደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ በሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህስ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን ። እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኅፀን መርጬ አክብሬሃለሁና። እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኵሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ። ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርጕዙን ይዞ በሌሊት ወጣ። ከጳጳስ ዘንድ ሄዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ  ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ በአንድ ቀንም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣዖት የሚሠዉበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከኪሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ። ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሄዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲው ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው። እርሱ ግን በደኅና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችና በመድኃኒታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው። ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት በጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር። ዜናውንም ሰምተው ወደእርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኅነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመንም ያጸናቸዋል።

ከዚህም በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ። በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ። በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር። በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በኋላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሄደ። እርሱም የምንኵስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሄዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሃም በአንድነት ኖሩ። ከዚያም ግራርያ ወደሚባል አገር ሄዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኰሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስ በርሳቸውም አይተዋወቁም። እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ስለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እንደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም። ከዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በኋላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው ከዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስኪሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ፣ ውኃም ሳይጠጣ ቆየ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞም የከበሩ ነቢያትና  ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን  የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆች ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ። በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ   አንተ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። ዳግመኛም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን
450 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 05:45:42

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት በዚህች ቀን የክርስቶስ ምስክሩና ሐዋርያው የሆነ ተጋዳይ ቅዱስ ቶማስ የመርዓስ ኤጲስቆጶስ አረፈ።



የዚህንም አባት ትሩፋቱንና ገድሉን ሰው ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም እርሱ አስቀድሞ በጾም በጸሎት በሰጊድ ቀንና ሌሊትም በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖች በመራራት ተጠምዶ የሚኖር ነው። ከዚህም በኋላ መርዓስ ለሚባል አገር ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መረጠው መንጋውንም እንደ ሐዋርያት ጠበቀ። ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን ያሠቃያቸው ዘንድ ከመኳንንቶቹ አንዱ ወደዚያች አገር ደረሰ እርሱም ቅዱስ ቶማስን ወደ እርሱ ያቀርቡት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ እነርሱም እየደበደቡ በምድር ላይ እየጎተቱ ወሰዱት ደሙም እንደውሃ ፈሰሰ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ቅዱስ ቶማስን ለአማልክት ስገድ አለው ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ከእግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ ጣዖታት አልሰግድም ለረከሱ ጣዖታት የሚሰግድ ሁሉ የተረገመ ነውና" አለው።

መኰንኑም ተቆጥቶ እጅግ የበዛና ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው የነዳጅ ድፍድፍን አፍልተው በላዩ በአፉና በአፍንጫው ውስጥ ጨመሩ እንዲህም እያደረጉበት እስከ ብዙ ዘመናት ኖረ የእሊህ ከሀድያን ልባቸው እንደ ድንጊያ የጸና ስለሆነ ቅዱስ ቶማስ ቶሎ እንዲሞት አልፈለጉም። ሌሎች ብዙዎች ሰዎችን ያሰፈሩአቸው ዘንድ የክብር ባለቤት ክርስቶስንም ይክዱት ዘንድ የሥቃዩን ዘመን አስረዘሙ እንጂ። እርሱ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የጸና ነውና፤ ማሠቃየቱ አድክሟቸው ከሀድያን በተቸነፉ ጊዜ ስለ ስሕተታቸውም ይዘልፋቸው ስለነበር ስለዚህ በጨለማ ቦታ ጣሉት በዚያም ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ። ከሀድያንም በየዓመቱ ወደ እርሱ ገብተው ከሕዋሳቱ አንዱን ይቆርጣሉ። በዚያም ቦታ አፍንጫውን፥ ከንፈሮቹን፥ ጆሮዎቹን፥ እጆቹንና እግሮቹን ቆረጡ መንጋዎቹም ያረፈ መስሏቸው በየዓመቱ መታሰቢያውን ሲያደርጉ ኖሩ። ነገር ግን እንዲት ክርስቲያናዊት ሴት በጣሉት ጊዜ ስለአየችው ቦታውን ታውቅ ነበር እርሷ በሌሊት ወደ እርሱ ተሠውራ በመሔድ ትመግበዋለች። ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከ ነገሠና የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ክብር እስከ ገለጠ ድረስ እንዲህ ሲሠቃይ ኖረ።

ይህም ንጉሥ ክርስቶስን በመታመን የታሠሩ እሥረኞችን ሁሉ በሀገሮች ሁሉ በወህኒ ቤት ያሉትን ይፈቷቸው ዘንድ አዘዘ። ይችም ሴት ሄዳ ስለ ቅዱስ ቶማስ ከእርሱ የሆነውን ሃያ ሁለት ዓመት ተጥሎ እንደኖረ ለካህናቱ ነገረቻቸው በውስጡ ወደሚኖርበትም ቦታ መራቻ ቸው ። እነርሱም አንሥተው ተሸከሙት እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተክርስቲያን አደረሱት በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በወንበሩ ላይ አስቀመጡት ምእመናንም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ ከእርሱ ይባረኩና የተቈረጡ ሕዋሳቱን ይሳለሙ ነበር። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም የከበሩ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳትን የአንድነት ጉባኤን በኒቅያ አገር በሰበሰበ ጊዜ ይህ የከበረ ቶማስ ከእሳቸው አንዱ ነው። ንጉሡም ወደ እነርሱ ገብቶ ሰላምታ ሰጣቸውና ከእርሳቸውም ቡራኬ ተቀበለ። የዚህ የቅዱስ ቶማስን ተጋድሎውን በነገሩት ጊዜ ወደርሱ ቀርቦ ሰገደለት ሕዋሳቱም ከተቈረጡበት ላይ ተሳለመው አዝኖና እጅግም አድንቆ ሕዋሳቱን ዳሠሠው ፊቱንና ዐይኖቹን አሻሸው። ከሀዲ አርዮስንም ተከራክረው ከረቱ በኋላ አውግዘው ለይተው ከወገኖቹ ጋር ከቤተ ክርስቲያን አሳደዱት። ከዚህም በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንደአስተማራቸውና እንደመራቸው የሃይማኖትን ትምህርት በአንደበታቸው ተናገሩ ሕግና ሥርዓትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ፍርድንም ሠሩ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ቶማስ ወደ መንበረ ሢመቱ ሔደ ካህናቱንና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ አነበበላቸው እርሱንም እንዲአስተውሉት እንዲጠብቁትም በመጠበቅም እንዲጸኑ አዘዛቸው። ጥቂት ዘመናትም ከኖረ በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ የሹመቱም ዘመን አርባ ዓመት ነው በዚህም እግዚአብሔርን አገለገለው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛ ንም በዚህ ተጋዳይ አባት ጸሎት ይማ ረን።በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።



ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ዐረፈ።



ዳግመኛም በዚህች ቀን ኢትዮጵያዊት የሆነች ተጋዳይ የከበረች ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው ዳግመኛም የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብም መታሰቢያቸው ነው።

የኒህ ቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

511 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 05:10:07
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
463 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:09:51
እንኳን አደረሰን እንኳን አደረሳችሁ የዓመቱ ፍሬዎቻችንን ልናይ.......
607 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, edited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 05:30:50

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን በእስክንድርያ አገር ከክርስቲያን ወንድሞቻችን ሠላሳ ሺህ ሰዎች በሰማዕትነት ሞቱ።



ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርትያኖስ አባታችን ዲዮስቆሮስን ወደ ደሴተ ጋግራን በአጋዘው ጊዜ ብዙ ዘመናት በእስክንድርያ አገር ሁከትና ብጥብጥ ሆነ። መርትያኖስም በሞተ ጊዜ በእርሱ ፈንታ ልዮን ነገሠ፤ እርሱም አብሩታርዮስ የተባለውን መለካዊ ከሮማውያን ወገን ለእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሾመ፤ ይህም መለካዊ በኬልቄዶን ጉባዔ የሚያምን ነው፤ ስለዚህም ከጥቂት ግብዞች ሰዎች በቀር የእስክንድርያ ሰዎች አልተቀበሉትም። ያልተቀበሉትም ሰዎች አስቀድሞ አባታችን ዲዮስቆሮስ ከሾማቸው ቀሳውስት ሥጋውንና ደሙን የሚቀበሉ ሆኑ። ከዚህም በኋላ በቃሉ ለሚያምኑ ባልንጀሮቹ ጉባኤ አደረገላቸውና የክርስቶስ መለኮቱ ከትስብእቱ ተቀላቀለ የሚል አውጣኪን አወገዘው። አብሩታርዮስም ይህን ማድረጉ የእስክንድርያን ሰዎች ሸንግሎ ወደ ከፋች እምነቱ ሊስባቸው ወዶ ነው እንጂ ስለዚህ ነገር አባ ዲዮስቆሮስ አውጣኪን አስቀድሞ አውግዞታል ። የአባታችን የዲዮስቆሮስ ሃይማኖት እንደ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ እንደ ቅዱስ ቄርሎስ ቃል ከሥጋ ጋር ከተዋሐደ በኋላ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብለው እንደሚያምኑ የሚያምን ነውና። ከጉባኤውም በኋላ የሰበሰባቸው የአብሩታርዮስ ተባባሪዎቹ ወደየቦታቸው ተመለሱ። እርሱም ራሱ አብሩታርዮስ በቤቱ ውስጥ ተገድሎ ተገኘ ለባልንጀሮቹም የአባታችን ዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት ወይም የአውጣኪ ባልንጀሮች ወይም ሌቦች ገንዘቡን ለመውሰድ የገደሉት መሰላቸው ይህም እውነት ይመስላል። የአብሩታዮስም ባልንጀሮች ወደ ንጉሥ እንዲህ ብለው መልእክትን ላኩ እነሆ የዲዮስቆሮስ ወገኖች የንጉሥን ትእዛዝ በማቃለል ደፍረው የሾምከውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት። በዚያንም ጊዜ ወንድሞቻችን የእስክንድርያ ሰዎች በላያቸው ጢሞቴዎስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። እሊህ መናፍቃንም ከዚህ በኋላ ሁለተኛ እንዲህ ብለው ወደ ንጉሥ መልእክትን ላኩ። እነሆ አብሩታዮስን የገደሉት ሰዎች አሁንም ያለ ንጉሥ ፈቃድ ደፍረው ሊቀ ጳጳሳት ሾሙ። መልእክቶቹን ንጉሡ በሰማ ጊዜ ከሁለቱ መልእክቶች የተነሣ እጅግ ተቆጣ። ሰይጣንም በልቡ አድሮ፣ ጭፍሮቹን ልኮ ሃይማኖታቸው ከቀና ወንድሞቻችን ክርስቲያኖች ታላላቆችና ታናናሾች ሠላሳ ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ ጢሞቴዎስንም ወደ ደሴተ ጋግራን አጋው በዚያም ሰባት ዓመት ኖረ። ከአባታችን ዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት አንዱ የገደለውስ ቢሆን ስለ አንድ ሰው ፈንታ ሠላሳ ሺህ ሰው መግደል ይገባልን ስለዚህ ከሰይጣን ሥራ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ከከፋ ዕልቂት በኋላም ወንደሞቻችን የሆኑ የዲዮስቆሮስ ደቀ መዛሙርት አብሩታርዮስን እንዳልገደሉት ንጉሡ ተረዳ እጅግም አዘነ ጢሞቴዎስንም ከተሰደደበት መልሶ በመንበረ ሢመቱ አኖረው ታላቅ ክብርንም አከበረው። መንጋውንም እያበረታ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፤ ለዘላለሙ አሜን።



ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ ድምያኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህንንም ቅዱስ የአንጾኪያ አገር መኰንን ብዙ ወራት አሠቃየው ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

648 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:51:47
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
597 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:40:22

ወዳጄ ሆይ

ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!

እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ ዓይነቱ ሕይወት ያብቃን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
691 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 05:52:58

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ታላቅ ነቢይ የሞራት ልጅ ሚክያስ አረፈ።



ይህም ነቢይ በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት በመናገር አስተማረ። ስለ ጌታችን መውረድም እንዲህ አለ። እነሆ እግዚአብሔር ከልዑል መንበሩ ወደዚህ ዓለም ይወርዳል።

ሁለተኛም ስለ ልደቱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የኤፍራታ ዕጣ የምትሆኚ አንቺም ቤተልሔም የእሥራኤል ነገሥታት ከነገሡባቸው አገሮች አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና። ስለ ምኵራብ መቅረት ስለ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ መታነፅ ትንቢት ተናግሯል። ዳግመኛም ስለ ሕገ ወንጌል መሠራት ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል አለ።

የትንቢቱም ወራት ሲፈጸም ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሄደ። የትንቢቱም ዘመን ከጌታችን መምጣት በፊት በስምንት መቶ ዓመት ነው። ማርታ በምትባልም ቦታ ተቀበረ።



ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን። የነቢየ እግዚአብሔር ሚኪያስ በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘለዓለሙ ትሁን አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

620 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ