Get Mystery Box with random crypto!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuludeyared — ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @wuludeyared
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.38K
የሰርጥ መግለጫ

“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ
ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡
መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት
⬇️⬇️

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-28 00:51:05
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
573 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 21:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:09:02

የሁለት ካፌዎች ወግ

ባሕርዳር ከተማ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ ገበያው ሲታጠፉ የዱሮው ትራፊክ መብራት ያለበት አካባቢ ሁለት ፊት ለፊት የተፋጠጡ ካፌዎች ይገኛሉ። አንደኛው ኦርቶዶክሳዊው ከራድዮን ነው። ከራድዮን ካፌና ሬስቶራንት ከንጽሕናም፣ ከጥራትም፣ ከብቃትም፣ ከዓላማም አንጻር ምንም የማይወጣለት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ነው። ይሁን እንጂ የራሱ ሰዎች የካዱት፣ ደንበኛ የተጠማ፣ ምናልባትም ከማኅበረ ቅዱሳን ጥቂት አባላት በስተቀር ሌሎች የማይገቡበት ድርጅት ነው። ባሕርዳር ከተማ የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የትየለሌ ቢሆንም፣ ኦርቶዶክሳውያን ግን የተጣለባቸውን አዚም እንጃ ወደ ከራድዮን ካፌና ሬስቶራንት ለመግባት ይቸገራሉ።

በአንጻሩ ከከራድዮን ፊት ለፊት አውርስ የተባለ ፕሮቴስታንታዊ ካፌ አለ። እንደ ከራድዮን ሁሉ ይህንን ካፌ በደንብ አውቀዋለሁ። በጥራትም፣ በብቃትም፣ በደረጃም ፈጽሞ አይገናኝም። ይሁን እንጂ ከዚህ ካፌ ገብቶ ለመጠቀም ወንበር ማግኘት የእድለኝነት ያህል ይቆጠራል። ይህ ማካበድ አይደለም እውነታ ነው። ታዲያ የካፌው ደንበኞች እነማን ናቸው ብንል ከ90% በላይ ኦርቶዶክሳውያን እንደሚሆኑ ጥርጥር የለኝም። ባለማዕተቦቹ የራሳቸውን ቤት አልፈው ወደ ሌላ ቤት የመሄዳቸው ምሥጢር እስካሁን አልተገለጸልኝም።

አውርስ ካፌ ችግሩ ባለቤቱ ፕሮቴስታንት መሆኑ አይደለም፤ አላማው እንጂ። በመስተንግዶነት የሚቀጠሩ ኦርቶዶክሳውያን ፕሮቴስታንት እንዲሆኑ ከፍተኛ ጫና ሲያደርግ እንደቆየ መረጃው አለኝ። በትናንትናው ዕለት ደግሞ ሥዕለ ማርያምንና የጸሎት መጽሐፍን በመቅደድ ፀረ ኦርቶዶክስነቱን አስመሥክሯል። ፍጹም ጥላቻውንና ንቀቱን ኪሳቸውን በሚያልባቸው ኦርቶዶክሳውያን ፊት አሳይቷል።

የብዙ ኦርቶዶክሳውያን ድክመታችን እምነታችን ፌስቡክ ላይ ብቻ መሆኑ ነው። ችግር ሲገጥመን ፌስቡክ ላይ እንደሽሮ እንገነፍላለን። አገንፍለው ሲያወጡን በርደን ለበይዎቻችን የምንመች ሰዎች ነን። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ነጋዴ የመቶ ብር እቃ ብትገዛውና ከመቶ ብሩ እቃ 10 ብር ቢያተርፍ፣ ከትርፉ 10% አሥራቱን ያወጣል። በተቃራኒው ለቤተ ክርስቲያን አሥራት እንዲገባ የድርሻችንን ተወጣን ማለት ነው። ይህ ለብዙዎቻችን ተሰውሮብናል። በተቃራኒው ኦርቶዶክስን ከሚጠሉ፣ ጥፋታችንን ከሚመኙ፣ ተረኝነትና ምቀኝነት ካጠቃቸው አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ስንገዛ ከገዛነው እቃ ትርፍ በፐርሰንት ለገጀራ መግዣ ለፀረ ኦርቶዶክስነት እንቅስቃሴ ይውላል። ታዲያ ገንዘብን ለአሥራት ከማዋልና ለመጥፊያችን ከመስጠት የቱ በለጠብን? አለማወቅ ነውን? ስንፈት ነውን? ግዴለሽነት ነውን? አዚም ነውን?
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ከሙስሊም ወይም ከሌላ ቤተ እምነት ተከታይ እንዳይገዛ የሚል ፍጹም አቋም የለኝም። አብሮ መገበያየቱን፣ አብሮ መብላት መጠጣቱን፣ የጋሪ እሴቱንና ማኅበራዊ ኑሮውን ኖረንበታል፤ እንኖርበታለንም። ነገር ግን ሙስሊምም ይሁን ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክም ይሁን ተሐድሶ፣ ዋቄፈናም ይሁን ጠንቋይ ፀረ ኦርቶዶክስ ከሆነ ከቤቱ ገብቶ መጠቀምም ይሁን ከእርሱ ጋር ግብይት መፈጸም ቤተ ክርስቲያንን መግፋት ነው። እኛነታችንን ከሚያከብሩ የሌላ እምነት ተከታዮች ጋር እንኳን ግብይት ደግሰን እየተጠራራን መኖራችንን እንቀጥል። እኛነታችንን ለሚጠሉና ሃይማኖታችንን ለማጥፋት በዓላማ ከሚንቀሳቀሱት ጋር ግን አንድነት የለንም።

ከ " ታደለ ሲሳይ"

'ስለተቀደደው የጸሎት መጽሐፍ ካፌው (አወርስ ካፌ) "ይፋዊ ይቅርታ የጠየቀ ቢሆንም?" አስተዳደራዊ እርምጃ በግለሰቡ ላይ መውሰዱን ግን አላረጋገጥንም'

?

ሁላችንም በአጓጉል አዋቂነትና በከንቱ አመዛዛኝነት እሳቤ ተጠምደን በአንድም በሌላም የአጥፊዎቻችን ተባባሪ ከመሆን ራሳችንን እናድን።

642 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:12:54

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አንድ በዚህች ቀን አምላክን በሥጋ የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው እርሷ ስለእኛ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሕይወትና የድኅነት ወደብ ትሆነን ዘንድ እርሷን እናቱን ስለሰጠን በረከቷም በሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን።



በዚችም ቀን ቅድስት ኄራኒ የስሟ ትርጓሜ ሰላም ፍቅር የሆነ ለንጉሥ ሉክያኖስ ልጁ ምስክር ሁና ሞተች። እርሱም አባቷ ያማረ አዳርሽ ሠራላት መስኮቶቹንም ስምንት አደረገ ቅጽሩንም በዙሪያው ዐሥራ ሁለት አደረገ ማዕድንም ሠራላት። የወርቅና የብር የሆኑ ሣህኖችና ጽዋዎችንም አዘጋጀላት። የሚያስተምራትም አንድ ሽማግሌ ሰው አደረገላት። ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አኖራት የሚያገለግሏትም ሦስት አገልጋዮችን በእርሷ ዘንድ አድርጎ ደጃፎችን በላይዋ ዘጋ መምህርዋም በውጭ ሁኖ ያስተምራታል። ዕድሜዋም ሰባት ዓመት ሆናትና ያንጊዜ ራእይን አየች በማዕዷ ላይ ርግብ ስትቀመጥ በአፍዋም የወይራ ቅጠል አለ። በማዕዱም ላይ አኖረችው ሁለተኛም ንስር መጣ ከእርሱ ጋር አክሊል አለ በማዕዷ ላይም አኖረው ። ደግሞ ቍራ መጣ ከእርሱ ጋራ ከይሲ አለ በማዕዷ ላይም አኖረው። ደነገጠችም ለመምህሯም ነገረችው እርሱም እንዲህ ብሎ ተረጐመላት ርግብ የሕግ ምልክት ናት የዘይቱም ቅጠል የክርስትና ጥምቀት ናት ንሥርም ድል አድራጊነት ነው አክሊልም ለሰማዕታት የሚሰጥ ክብራቸው ነው። ቍራ የንጉሥ ምሳሌ ነው ከይሲውም መከራ ነው አንቺም የክብር ባለቤት በሆነ ክርስቶስ ስለስሙ ትጋደዪ ዘንድ አለሽ አላት። ከዚህም በኋላ ይጐበኛት ዘንድ አባቷ ወደርሷ መጣና ልጄሆይ ከመንግሥት ታላላቆች ለአንዱ ላጋባሽ እኔ እሻለሁ አላት እርሷ ግን ከልቡናዬ እስከምማክር ሦስት ቀኖችን አባቴ ሆይ ታገሠኝ ብላ መለሰችለት። አባቷም በሔደ ጊዜ በጣዖታቱ መሠዊያ ፊት ተነሥታ ቆመችና ስለጋብቻ የሚሆነውን ይገልጡላት ዘንድ ለመነቻቸው እነርሱም ምንም ምን ከቶ አልመለሱላትም። ከዚህም በኋላ ዐይኖቿን ወደ ሰማይ አቅንታ የክርስቲያን አምላክ ሆይ ወደ ምትፈቅደው ምራኝ ብላ ጸለየች ያንጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንዲህ አላት ። እነሆ ነገ ከጳውሎስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ወደዚች አገር ይመጣል፤ እርሱም የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቅሻል። በማግሥቱም ያ ሐዋርያ መጥቶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃት። በሦስተኛውም ቀን እንደቀጠረቻቸው አባቷና እናቷ መጡ እርሷም እንዲህ አለቻቸው እኔ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ።
አባቷም ሰምቶ በእርሷ ላይ ተቆጣ ወደ ከተማው መካከልም አውጥተው በጐዳና ላይ እንዲጥሏትና በፈረሶች እግር እንዲአስረግጧት አዘዘ። ወታደሮችም ንጉሥ አባቷ እንዳዘዘ አደረጉባት ግን ምንም ምን ክፉ ነገር ከቶ አልደረሰባትም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አባቷና እናቷ በአዩ ጊዜ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።

መንግሥታቸውንም ትተው ለርሷ ወደተ ሠራው አዳራሽ ሔደው በውስጡ ተቀመጡ። በጐረቤታቸው ያለ ንጉሥም ዜናቸውን በሰማጊዜ ወደ ርሳቸው መጥቶ ወደ መንግሥታቸው እንዲመለሱ ተናገራቸው። እነርሱም አልፈለጉም እርሱም መንግሥታቸውን ያዘ ቅድስት ኀራኒንም ይዞ አሠቃያት ከዚያም አንበሶችን እባቦችን በላይዋ ሰደደ ምንም አልቀረቧትም። ሁለተኛም በመጋዝ መገዛት በአንገቷም ውስጥ ታላቅ ደንጊያ አሥሮ ከባሕር ጣላት የክብር ባለቤት ጌታችንም ከዚህ ሁሉ አድኖ ያለጥፋት በጤና አሥነሣት። ከዚህም በኋላ እርሷን ያጠመቀ ሐዋርያን አባቷ ጠርቶ ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ ቍጥራቸውም ሦስት መቶ ሆነ ከዘመዶቹና ከሀገር ሰዎችም ብዙ ዎች ተጠመቁ። ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ኑማርያኖስ የቅድስት ኂራኒን ዜናዋን ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ቀላኒካ ወደሚባል አገር ወሰዳት። በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በበሬ አምሳል በተሠራ የናስ በርሜል ውስጥ ዘጋባት የክብር፤ ባለቤት ጌታችንም ያንን በርሜል ሰብሮ ቅድስት ኄራኒን ያለ ጥፋት በጤና አወጣት። ከዚህም በኋላ ኑማርያኖስ ሙቶ በርሱ ፈንታ ሳፎር ነገሠ እርሱም የቅድስት ኄራኒን ዜና በሰማ ጊዜ ወደ ርሱ አስቀርቦ በእጁ ውስጥ በአለ በታላቅ ጦር ወጋትና ነፍሷን አሳለፈች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሞት አስነሣት። ንጉሥ ሳፎርም በአየ ጊዜ እጅግ አደነቀ ሰገደላትም በጌታችን ኢየሱስም አመነ። ከእርሱም ጋራ ከሀገር ሰዎች ብዙ ወገኖች አመኑ ቍጥራቸውም ሠላሳ አንድ ሺህ ሆነ ከዚህም በኋላ በዚያች አዳራሽ ውስጥ አባቷና እናቷ አረፉ እርሷን ግን አምላካዊት ኃይል ተሽከመቻት ወደ ኤፌሶን አገርም አድርሳት በዚያ ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገች። በፋርስ ነገሥታት በመቄዶንያ በቀላኒካና በቍስጥንጥንያ ነገሥታት ፊት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከመሰከረች በኋላ ወደ ወደደችው ክርስቶስ፤ ሔደች። የድልና የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛ ንም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር። ለዘለዓለሙ አሜን።

አሜን።

602 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:13:07
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
620 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:46:05

የቱ ይሻላል?

የሌሎችን ስህተት መዳኘቱ ቀላል ሲሆን፣ የራሳችንን ድካም ማስተዋሉ ደግሞ ከባድ ነው፡፡

ቀላሉ ሳያገናዝቡ ማውራት ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ምላስን መግታት ነው፡፡

የሚወደንን ሰው መጉዳት ቀላል ሲሆን፣ የሚከብደው ደግሞ ያንን ቁስል ማዳኑ ነው፡፡

ሌሎችን ይቅር ማለት ቀላል ሲሆን፣ ይቅርታን መጠየቅ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

ሕግጋትን ማውጣት ቀላል ሲሆን፣ እነርሱን መከተሉ ደግሞ ከባድ ነገር ነው፡፡

ቀላሉ በእያንዳንዱ ምሽት ማለሙ ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ለስኬታማነቱ መዋጋት ነው፡፡

ሙሉ ጨረቃን ማድነቁ ቀላል ሲሆን፣ ሌላኛውን ጎን ማየቱ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

ቀላል የሆነው ለአንድ ሰው የሆነ ቃል ኪዳን መግባቱ ሲሆን፣ የሚከብደው ደግሞ ያንን ቃል መፈጸሙ ላይ ነው፡፡

"እወዳችኋለሁ" ማለት ቀላል ሲሆን፣ ከባዱ ደግሞ ያንን በሕይወት ማሳየቱ ነው፡፡

ሌሎችን መተቸት ቀላል ሲሆን፣ ራስን ማሻሻል ደግሞ ከባድ ነው፡፡

ስህተት መሥራት ቀላል ሲሆን፣ ከዚያ መማሩ ደግሞ ብርታትን ይጠይቃል፡፡

ስላጣነው ፍቅር ማንባቱ ቀላል ሲሆን፣ ላለማጣት መንከባከቡ ግን ይከብደናል፡፡

መቀበል እጅግ ቀላል ሲሆን፣ መስጠት ደግሞ ልባዊ ርኅራኄን ይጠይቃል፡፡

ስለ መሻሻል ማሰብ ቀላል ሲሆን፣ ከባዱ ግን ወደ ተግባር መቀየሩ ላይ ነው፡፡

ወዳጅነትን በቃላት መጠበቁ ቀላል ሲሆን፣ ትርጉማቸውን መጠበቁ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡

ልጅ እያለን ከሰማናቸው ነገሮች መካከል አንዱ በአካባቢያችን ውሻ ሲያላዝን (የተለየ ድምጽ ሲያሰማ) 'ሰው ሊሞት ነው' የሚለው አባባል ነው፤ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ግን "እኔ ልሞት ነው" የሚል ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፤ በተለይ አልጋ የያዙ ካሉ የሰዉ ሁሉ ትኩረት መጠቋቆሚያ የመኾናቸው ጉዳይ አጠያያቂ አይሆንም፡፡

ግን የቱ ይሻላል?
ሰውን ማስተካከል ወይስ ራስን ማስተካከል፤ እነርሱ ልክ አይደሉም ማለት ወይስ እኔ ልክ አይደለሁም ማለት፤ የሌሎችን ስህተት መዳኘት ወይስ የራስን ድካም መታገል፤ የቱ ይሻላል?

ተወዳጆች ሆይ ለሚከብደውና ለሚበልጠው እንትጋ!

738 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:32:22

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ በዚህች ቀን መጻሕፍትን የተረጐመ አባ ሰላማ አረፈ ። የቅድስት ሄዛዊም የመታሰቢያዋ በዓል ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር። ለዘለዓለሙ አሜን።



በዚህችም ቀን በከሀዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ዘመን የነበሩ ከኤፌሶን ሀገር ሰባቱ ደቂቅ አረፉ። እሊህም ሰባቱ ደቂቅ ከንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ውስጥ በመዛግብቱ ላይ የሾማቸው ነበሩ። አምልኮ ጣዖትን በማምለክ ሥራ አልተሳተፉም እሊህንም ቅዱሳን በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ይዞም አሠራቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ለመሔድ በፈለገ ጊዜ እስከሚመለስ ድረስ ፈትቶ ለቀቃቸው ምናልባት ከምክራቸው ቢመለሱ ብሎ በልቡ አስቦ። ከዚህም በኋላ እሊህ ቅዱሳን ለረከሱ ጣዖታት እንዳይሰግዱ የጭፍራነት ሥራቸውን ትተው በተራራ ውስጥ ወደአለ ዋሻ ሄደው በዚያ ተሠወሩ የዋሻውን አፍ ዘጉ ከእሳቸውም ጋራ በንጉሥ ዳኬዎስ ስም የተቀረጸ ብር ነበር። ከእርሳቸውም አንዱም አንዱ በየተራቸው ወጥቶ ምግባቸውን ገዝቶ ወደእሳቸው ይመለስ ነበር። ዳኬዎስም ከሔደበት እንደተመለሰ በሰሙ ጊዜ የዋሻውን ደጃፍ ዘግተው ተኙ። የእሊህንም ቦታቸውን የሚያውቅ አማኒ የሆነ ከጭፍሮች ውስጥ አንድ ሰው ነበረ ወደ ከተማ ሲወጡ ያገኛቸው ዘንድ ጠበቃቸው ባልመጡምጊዜተነሥቶ ወደ ዋሻቸው ሄደ። ዋሻዋንም ከውስጥ እንደ ዘጓት ሁና እገኛት እርሱም በረሀብ የሞቱ መሰለው ታላቅም የደንጊያ ሠሌዳ አምጥቶ ከእሳቸው የሆነውን ገድላቸውን ጽፎ በቀዳዳ ወደ ዋሻው ውስጥ አስገባው። እሊህም ቅዱሳን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዘመናት አንቀላፉ ዳኬዎስም ሙቶ እስከ ቴዎዶስዮስ ብዙ ነገሥታት ነገሡ። በዚህም ምእመን ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዎች ተነሥተው ብዙዎች ተከተሏቸው። በዚያንምጊዜ እሊህን ቅዱሳን ሰባቱን ደቂቅ እግዚአብሔር አነቃቸው ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ግልጽ ያደርግ ዘንድ። ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው አንዱ ምግባቸውን ሊገዛ የከሀዲ ዳኬዎስንም ወሬ ይሰማ ዘንድ ብር ይዞ ወጣ ወደ ከተማም በገባ ጊዜ የከተማዋ ሁኔታ ተለወጠበት። በከተማውም በር መስቀሎችን አየ በየቅጽሮቿም የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ስሙን ያለ መፍራት ሲጠሩ ሰማ አንዱንም ሰው ይህች አገር ኤፌሶን አይደለችምን ብሎ ጠየቀ እርሱም አዎን ናት አለው። ያንንም ብር አውጥቶ ለባለሱቁ ሰጠው ምግባቸውን ይሸጥለት ዘንድ ባለሱቁም ያን ብር ተመለከተው የንጉሥ ዳኬዎስም ስም ተቀርጾበት አገኘውና ያንን ሰው ይዞ በአንተ ዘንድ የተሸሸገ መዝገብ አለ ይህ ምልክት ከአንተ ተገኝቷልና አለው። እንዲህም ሲጣሉ ወደእርሳቸው ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እንዲህም ብለው ጠየቁት አንተ ከወዴት ነህ ከዚህችአገር ነኝ አላቸው። ማንን ታውቃለህ አሉት እርሱም ዕገሌንና ዕገሌን አላቸው ከዘመን ብዛት የተነሣ የጠራቸውን ሰዎች የሚያውቃቸው የለም። ስለዚህም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ወደ ዳኞችና ወደ ኤጲስቆጶስ አባ ቴዎድሮስ ወደ ንጉሥ ቴዎዶስዮስም አቀረቡት። ንጉሡና ኤጲስቆጶሱም ከአንተ የሆነውን እውነቱን ንገረን ከወዴት አገር ነህ አሉት። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው እኛ ሰባታችን የከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ ጭፍሮች ነን እርሱም ወጥቶ ወደ ሌላ አገር በሄደ ጊዜ ከአንዷ ዋሻ ውስጥ ገብተን የዋሻዋን በር ዘግተን ተኛን። እነሆ ስንነቃ የምንመገበውን ምግብ እገዛ ዘንድ ላኩኝ። ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ በሰሙ ጊዜ ተነሥተው ወደዚያ ዋሻ ከእርሱ ጋራ ሔዱ ከእርሳቸውም ጋራ ብዙ ሕዝቦች አሉ ቅዱሳኑንም ተቀምጠው አገኙአቸው። የዘመኑም ቁጥር በውስጡ የተጻፈበትን በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን የሆነውን ሠሌዳውን ወድቆ አገኙት ዘመኑም ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት እንደሆነ ታወቀ። ንጉሡና ኤጲስቆጶሱ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉትም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው ትንሣኤ ሙታን እንዳለ አመኑ። እሊህ ሰባቱ ደቂቅንም በጠየቋቸው ጊዜ ከእርሳቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩአቸው። ከዚህም በኋላ ተመልሰው ተኙ። ነፍሳቸውንም ከእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ንጉሥም የወርቅ ሣጥን ሠራላቸው በሐር ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው። ከሥጋቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ስማቸውም
መክሲማኖስ፣ ታሙኪሮስ፣ መርዳዲሞስ፣ ዮሐንስ፣ ቈስጠንጢኖስ፣ አዝሚ እና ዲዮናስዮ ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የእሊህም ቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

አሜን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

673 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 05:36:31
"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
634 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 02:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:29:16

ፀሓይን ገዝቶ ያቆመው የአንዲት ሴት ጽኑ እምነት

"የአባታችን የቅዱስ ኤዎስጣቴዎስን መታሰቢያ የምታድርግ አንዲት ሴት ነበረች፡፡ በዐርብ ቀንም ከልጆቿ ጋር ቃርሚያን ትቃርም ዘንድ ወደ እርሻ ተሰማራች፤ እየቃረመችም ዋለች፡፡ ፀሐይም ሊገባ መሽቶ ነበር፡፡ እርሷም ከልጆቿ ጋር የምትሰነብትበት ያበሰለችው እንጀራ እንደሌላት አሰበች፡፡ ለዚያችም ሴትዮ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ልማድ ነበራትና ስለሰንበት ክብር ብላ ከዐርብ ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኞ ቀን ድረስ እንጀራ አትጋግርም፣ ውሃም አትቀዳም ነበር፡፡ አሁንም በዕለት ዐርብ ማምሻ ላይ በእርሻ ቃርሚያ ቦታ ሳለች ፀሐይን ባየች ጊዜ እነሆ ሊገባ አዘቅዝቆ (መሽቶ) ነበር፡፡ እርሷም ‹‹እንጀራዬን እስካበስል ድረስ አንተ ፀሐይ እንዳትገባ ተአምራትን በሚያደርግና ባሕርን በሚከፍል በቅዱስ አባታችን በኤዎስጣቴዎስ ጸሎት አምየሃለሁ›› አለችው፡፡ ፀሐይም ወዲያው ባለበት ቆመ፡፡ ከዚህም በኋላ በላዳን (በቆሮስ) የስንዴ ዱቄት ወስዳ ለወሰችውና ለሁለቱ ሰንበታት የሚሆን ምግብ ዳቦዎችን ጋገረች፡፡

ከጨረሰችም በኋላ ፀሐይን በአባታችን በቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ጸሎት እንዳማለችው በመግቢያው በምዕራብ አንጻር ትይዩ ቆሞ ታየው ነበር፡፡ ያች ሴት ግን አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለእርሷ ስላደረገላት ስለዚህ ድንቅ ተአምር ፈጽማ እያደነቀች በብዙ ትጋት ምግቧንና ፍላጎቷን ታዘጋጅ ነበር፡፡ ይልቁንም የመንፈስ ቅዱስን ደመና የሚጫን የአቡነ ኤዎስጣቴዎስን ስም በመጥራት ከቃሏ ንግግር ስለወጣው መሐላ ፀሐይን ቆሞ ባየችው ጊዜ ፈጽማ ትደሰት ነበር፡፡ ምግቧንም አብስላ ከጨረሰች በኋላ ዳግመኛ ወደውሃ ሔደች፡፡ ቀድታም ወደ ቤቷ አስገባች፡፡ ከልቧም እግዚአብሔርን እያመሰገነችና አባታችንን ገባሬ መንክራት አቡነ ኤዎስጣቴዎስን እያደነቀች ትዘምር ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ያች ሴት በፍጥነት ያይደለ በእርጋታ የፈለገችውን ሥራ ሁሉ በጨረሰች ጊዜ ፀሐይን ‹‹በቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ አፍ የተፈታህ ሁን›› አለችው፡፡ ያንጊዜም ፀሐይ ወዲያው ገባ፡፡"

አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ከደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር የተሻገሩት የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

ከገድለ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የተወሰደ

የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ልደታቸው ታኅሣሥ 15 ዕረፍታቸው መስከረም 18 ነው በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።

አሜን።

740 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:57:51
656 viewsውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት, 10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:17:44
ወርኃዊ የዝክረ ቅዱስ ያሬድ ጉባኤ

የተወደዳችኹ!

የፊታችን እሑድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ወርኃዊው የዝክረ ቅዱስ ያሬድ መርሐ ግብራችን እንደአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ በሰንበት ትምህርት ቤታችን አዳራሽ ይካኼዳል።

በጉባኤው ቅዱስ ያሬድን የሚዘክሩ መሰናዶዎች ተዘጋጅተው ይጠብቁናል። በቅዱስ ያሬድ ቃል ኪዳን ለመሳተፍ ኹላችንም በወር አንድ ጊዜ በሕብረት የምንገኝበት ነው።

ከእርሶ የሚጠበቀው ሌሎች ወንድም እና እህቶችን በመጋበዝ ከጠዋቱ ፫:፴ ጀምሮ መገኘት ነው።

በረከት የሚያተርፉበት ጉባኤ ነውና እንዳትቀሩ ይኹን!

473 viewsተስፋ ማርያም, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ