2022-09-03 15:10:23
ለውጭ ተላላኪ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አሳልፈን አንሰጥም - የዳማ ወረዳ ነዋሪዎች
ነሐሴ 28/2014 (ዋልታ) ለውጭ ተላላኪ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አሳልፈን አንሰጥም ሲሉ በጉጂ ዞን የዳማ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።
በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች አሸባሪዎቹን የትሕነግና ሸኔ ቡድኖች የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፉ እየተካሄደባቸው ከሚገኝባቸው ወረዳዎች አንዷ ዳማ ስትሆን ሀገራችን ኢትዮጵያን ለውጭ ተላላኪ ቡድኖች አሳልፈን አንሰጥም ሲሉ በሰልፉ የተሳተፉ የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
አሸባሪ ቡድኖቹ ትሕነግና ሸኔ ሰዋዊ መንፈስ የሌላቸውና ለጥፋት ብቻ የተፈጠሩ መሆናቸውን የሚያነሱት የወረዳ አስተዳዳሪ ታሪካየው ተስፋዬ እነዚህን ቡድኖች ከስር በመንቀል ማጥፋት እንደሚገባ ገልጸዋል።
አሸባሪዎችን ድል አድርጎ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ህይወቱን እስከ መስጠት እየተዋጋ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊታችንን መደገፍና ማበረታታት ያስፈልጋልም ብለዋል።
እንደ ዳማ ወረዳም በአንድ ቀን ብቻ የምግብ እህልን ጨምሮ 43 በሬዎችንና ከ63 በላይ በጎችን ለመከላከያ ሰራዊት ከማህበረሰቡ መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።
ድጋፉ በዚህ አያበቃም የሚሉት አስተዳዳሪው ደም መስጠትን ጨምሮ ለመከላከያ ሰራዊታችን አስፈላጊ የሆኑ ቁሶችን በሙሉ እንደሚያደርጉም ለዋልታ ቴሌቪዥን ገልፀዋል።
እኛ በሰላም እንድንኖርና እንድንቀሳቀስ መከላከያ ሰራዊታችን በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ነው የሚሉት የዳማ ወረዳ ነዋሪዎች ሁሌም ከሰራዊታችን ጎን ነን ብለዋል።
ታምራት ደለሊ (ከጉጂ ዞን ዳማ ወረዳ)
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
3.3K views12:10