Get Mystery Box with random crypto!

Walta

የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta W
የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta
የሰርጥ አድራሻ: @walta_tv_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://www.facebook.com/waltainfo
#ሼር #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-09-02 20:18:24
ምክር ቤቱ አሸባሪው ሕወሓት ሀገርን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ወረራ አወገዘ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት አሸባሪው ሕወሓት ሀገርን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ወረራ አውግዟል፡፡

የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔ አሳልፏል።

የደቡብ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው 247ኛ መደበኛ ስብሰባው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል።

በዚህም ምክር ቤቱ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምሥረታ እና ነባሩን ክልል በአዲስ ክልል የማደራጀት ተግባር ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ማቋቋሚያና የአሰራር ሥርዓት መወሰኛ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ መንግስት ለሰላም ያለውን ፅኑ አቋም በተኩስ አቁም ማሳየቱን እና አርሶ አደሩ ከነበረበት የጦርነት ስጋት ወጥቶ ወደ ግብርና ስራው እንዲያተኩር ለማድረግ መንግስት የተኩስ አቁም ማድረጉ በምክር ቤቱ ገልጿል፡፡

ሆኖም ግን አሸባሪው ህወሓት መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት ወደ ጎን በመተው በህዝብ ላይ ግልጽ ወረራ መፈፀሙን ምክር ቤቱ ጠቅሷል።

መንግስት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ብሎም በሀገሪቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ተገዶ የገባበትን ጦርነት መስተዳድር ምክር ቤቱ የሚደግፍ ሲሆን ሂደቱንም በቅርበት እንደሚከታተል አጽንኦት መስጠቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽ ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።


ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
3.3K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:24
በበዓላት ወቅት የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) በበዓላት ወቅት ከሚፈፀም ግብይት ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 396 ባለ200 ሃሰተኛ የብር ኖት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሃሰተኛ ገንዘቡን ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር የዋሉት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ቦታው ኦሮሚያ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቦቹ ባጃጅ ተሳፍረው ለመጓዝ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ኅብረተሰቡ በተመለከተው አጠራጣሪ ጉዳይና ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተደረገ ፍተሻ 396 ሃሰተኛ ባለ200 የብር ኖቶችን ይዘው ተገኝተዋል።  

በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ግብይት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ የብር ኖቶችን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ስለሚያጋጥሙ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥሙት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.8K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:24
ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የዶክተር ቴድሮስን የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ድርጊትን እንዲያስቆም ጠየቀች

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከተቋሙ ሰራተኞች ሥነ ምግባር በተፃረረ መንገድ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሀሰት መረጃ የማሰራጨት ድርጊትን እንዲያስቆም በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያን ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት ጠየቀ።

ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ በፈረንጆቹ ኅዳር 3 ቀን 2020 አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታዉሶ ፤ጥቃቱን ተከትሎ ከሕወሓት አመራሮች አንዱ የሆነዉ ዶክተር ቴድሮስ በሕወሓት የቁጥጥር ሠንሠለት ሥር ሆኖ ትዕዛዝ በመፈፀም የሽብር ቡድኑን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያሠራጭ መቆየቱን አመላክቷል፡፡

ሕወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትን፣ የህዝብ አገልግሎት ተቋማትን እና መሠረተ-ልማቶች ሲያወድም ዶክተር ቴዎድሮስ ሲያወግዝ አለመታየቱን መግለጫዉ ጠቁሟል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ አብዝቶ የሚደግፈው ይህ ቡድን አሁንም በአጎራባች ክልሎች ላይ የፀብ-ጫሪ ተግባሩን መቀጠሉን አመላክቷል፡፡

ባለፈው ወረራ የፈጸማቸውን የህዝብ ተቋማት የማውደም ፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን የመፈጸም እና የመጨፍጨፍ ተግባራት አሁንም በክልሎቹ መቀጠሉንም አውስቷል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት ውስጥ ያለውን ስልጣን የኢትዮጵያን መንግስት ስም ለማጥፋት እየተጠቀመ መሆኑን ያመለከተዉ መግለጫዉ በዚህም ተግባሩ የዓለም ጤና ድርጅት መልካም ስምን፣ ገለልተኝነት እና ተዓማኒነት ክፉኛ መጉዳቱን አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
2.6K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:24
ፌዴሬሽኑ በዘር እና በሃይማኖት ስያሜ የሚጠሩ ክለቦች የስም ማሻሻያ እንዲያደርጉ አሳሰበ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዘር እና በሃይማኖት ስያሜ የሚጠሩ ክለቦች የስም ማሻሻያ እንዲያደርጉ አሳሰበ፡፡

በፌደሬሽን ስር የሚከናወኑ የ2015 የሊግ ውድድሮች የዝውውር ጊዜ የሚከፈትበት ቀን ይፋ ሆኗል፡፡

በዚህም መሰረት የ2015 የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ እንዲሁም ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ዝውውር መፈፀም የሚችሉት ከጳጉሜን 4 እስከ ኅዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ከዘር እና ከሐይማኖት ነፃ የሆነ የክለብ መጠሪያ ስያሜ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው የእግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.4K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:24
ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀረበ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀረበ፡፡

በዚህም ዲያስፖራው ወደ ኢትዮጵያ የሚልከውን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ እንዲልክ እንዲሁም በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለኢትዮጵያ ለሚቆሙ ወገኖች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ማለትም፡-

1000439142832 (ዩሮ)
1000239142786 (ዶላር)
1000443606304 (ፓውንድ)
መደገፍ እንደሚችሉ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.3K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:23
አሸባሪው ህወሓት ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚመጡ ምግቦችን ለእኩይ አላማው እንደሚያውል ዳግም ተጋለጠ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ቡድን በህዝብ ስም ወደ ትግራይ ክልል የሚገባውን ምግብ ከተራበው ህዝብ ቀምቶ ለታጣቂዎቹ ብቻ እንደሚያቀርብ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምሽጉ ተደርምሶ አጭበርባሪነቱ ዳግም ተጋልጧል።

ይህም በምሽጉ ውስጥ የእርዳታ እህልና ሌሎች የምግብ አቅርቦቶችን ከዝኖ ለታጣቂዎቹ እንደሚያቀርብ በተግባር መረጋገጡን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.3K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:18:23
ሕወሓት በወልቃይት ግንባር ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል - ምርኮኞች

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ፡፡

የሽብር ቡድኑ የትግራይ ወጣቶችና ታዳጊዎችን በየግንባሩ ለጦርነት በመማገድ ላይ እንደሚገኝም መግለፃቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

አሸባሪው ሕወሓት ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን ወልቃይትና ራያን አስመልሰን ታላቋ ትግራይን እንመሰርታለን ብሎ ጦርነት ቢያስገባንም ሳናሳካ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነናል ሲሉ ምርኮኞቹ ተናግረዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.6K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:31:49
ኮሚሽኑ ከ472 በላይ ወረዳዎች ላይ የአደጋ ስጋት ልየታ መስራቱን አስታወቀ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) በቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ማደራጀት ስራ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ472 በላይ ወረዳዎች የአደጋ ስጋት ልየታ መሠራቱን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በተያዘው 2015 በጀት ዓመት የፖሊሲ ሪፎርም በማድረግ ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጡን በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት እቅድ ውይይት እንዲሁም የተቋሙን አዳዲስ አመራሮች የማስተዋወቅ መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን ተቋሙ ባለፉት ዓመታት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና አደጋን አስቀድሞ በመለየት የስጋት ቀጣናዎችን ሊደርስ ከሚችለው አደጋ በመከላከል ረገድ አመርቂ ስራ መስራቱን አንስተዋል፡፡

ሆኖም ግን በየጊዜው እየተከሰቱ ካሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ብዛት እንዲሁም ወቅቱ በሚፈልገው ቴክኖሎጂ መታገዝ ባለመቻሉ የሚፈለገው ውጤት መምጣት አለመቻሉን አንስተዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት እንኳ በአገሪቱ ካሉ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ወረዳዎች የ472ቱን የስጋት ልየታ በመስራት የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ማደራጀት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ርምጃ አወሳሰድና የመረጃ ጥራት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ እንዲሁም የፖሊሲ ሪፎርም በማድረግ ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጡን በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየሰተራ እንደሚገኝ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
700 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:31:49
የአሸባሪዎቹን ትህነግና ሸኔን ሴራ እናወግዛለን፤ መከላከያ ሰራዊታችንን እንደግፋለን - የአዶላወዩ ከተማ ነዋሪዎች

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን የተዘረጋለትን የሰላም አማራጭ አሻፈረኝ በማለት ሶስተኛውን ዙር ጦርነት መክፈቱና ሌላኛው የጥፋት አጋሩ የሸኔ ሀይልም እያደረሰ ያለውን ወድመት የሚቃወምና ለሀገር ትልቅ መስዋትነትን እየከፈለ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በጉጂ ዞን አዶላወዩ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተመቻቸ ሂደት ውስጥ አልፋ አይደለም ለዛሬ የበቃችሁ የሚሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ይልቅስ የእናቶቻችን፣ የአባቶቻችንና የቅድመ አያቶቻችን ደምና አጥንት ተከፍሎባት ነውም ብለዋል።

ታድያ እኛም የዛሬ ትውልዶች ምን እንኳ ብዙ ሴራዎችና ጫናዎች ቢኖሩብንም ይህቺን ብዙ ዋጋ ተከፍሎባት ለኛ የበቃችን ሀገር ክብሯን አናስደፍርም በኛ ትውልድ ኢትዮጵያም አትፈርስም ብለዋል።

አሸባሪው የትህነግ ሀይል የተዘረጋለትን የሰላም አማራጭ አሻፈረኝ ማለቱ ቡድኑ ለጥፋትና ለውድመት የተራበ መሆኑን ማሳያ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ቡድኑ ከስር መሰረቱ ተነቅሎ መደምሰስ አለበትም ብለዋል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
600 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:31:48
ሰራዊታችን በሰው ሀይል፤ በአደረጃጀትና በትጥቅ የተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል - የመከላከያ ሚኒስትር አብርሀም በላይ

ነሐሴ 27/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሀም በላይ (ፒኤችዲ) ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ባለፉት አመታት በተቋሙ በተሰሩ የሪፎርም ስራዎች በሁለንተናዊ መልኩ የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

ሰራዊቱ በሰው ሀይል፤ በአደረጃጀትና በትጥቅ የተሟላ ቁመና እንዲይዝ ከመደረጉም በላይ ኢትዮጵያን የሚመስል ሰራዊት መገንባት መቻሉንም ገልፀዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በጠንካራ ዲሲፒሊን አክባሪነቱ፤ ህዝባዊነቱና ጀግንነቱ ዓለም የመሰከረለት ሰራዊት መሆኑን በተግባር የሀገሩን ሉአላዊነትና ክብር በማስጠበቅ ያስመሰከረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በቀጣይም ሠራዊቱ የሚሰጡትን ማንኛውም ግዳጆች በብቃት ለመወጣት በተሟላ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
654 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ