2022-09-04 20:46:20
በጎነት ለተወሰነ ሰው፣ ዘር፣ ሃይማኖት የተሰጠ አይደለም- ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ነሐሴ 29/2014 (ዋልታ) በ10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርኃ ግብር ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጎነት ለሆነ አካል ብቻ የተሰጠ ተግባር አይደለም ሲሉ ተናገሩ።
በጎ ሰው የሚሰራውን ስራ በንፁህነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የሚሰራ ማለት ነውም ብለዋል።
የበጎ ሰው ተሸላሚዎች ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው የሚችሉትን ያደረጉና ብዙ የፈፀሙ ናቸውና ይገባቸዋል ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ።
የሚሰሩ ሰዎችን እውቅና የመስጠትና የማመስገን ልምዳችን ዝቅተኛ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ ምስጋና እና እውቅና መስጠትን ሁላችንም ልናደርገው የሚገባ ነው ብለዋል።
መርኃ ግብሩም እውቅና የመስጠትን ልምድ የሚያበረታታ በመሆኑም አዘጋጆቹን አመስግነዋል።
"በጎ ሰዎችን በመሸለምና ዕውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎች እናፍራ" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ተጠናቋል።
በትዕግስት ዘላለም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
3.1K views17:46