2022-08-31 12:47:09
አሻባሪው ህወሓት የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን - የሀረሪ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
ነሐሴ 25/2014 (ዋልታ) አሻባሪው ህወሓት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያ እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ሲሉ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ ተናገሩ፡፡
የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ እንዳሉት አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ለሦስተኛ ጊዜ በሀገራችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።
መንግሥት የሠላም አማራጭ የተከተለው የትግራይን ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም በማሰብ እንደሆነ ጠቁመው፣ ቡድኑ ግን ለሶስተኛ ጊዜ ወረራ መፈጸሙን ተናግረዋል።
አሻባሪው ህወሃት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያ እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መላው የክልሉ ሕዝብ ባለፋት ጊዜያት በአገር ህልውና ላይ ከውስጥና ከውጭ የተቃጣብንን አደጋ ለመመልከት በተደረገው ጥረት ምልአተ ህዝቡን በማነቃነቅ ግንባር ቀደም የድጋፍ ተሳትፊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደተቻለም ገልጸዋል።
ሰርተን መለወጥ የምንችለው ሀገር ሰላም ስትሆን መሆኑን የገለጹት ኃላፊው አሸባሪው ህወሓት የሀገርን አንድነት ለመናድ የሚያደርገውን ሙከራ ለመመከት የክልሉ መንግሥትና ሕዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
3.2K views09:47