2022-09-04 16:52:34
የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው
ነሐሴ 29/2014 (ዋልታ) 10ኛው የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
ለመጨረሻ የዳኞች ውሳኔ 27 እጩዎች 1 ልዩ ተሸላሚ መለየታቸው የሚታወቅ ሲሆን ተሸላሚዎችን በእውቀታቸው እና በሞያቸው መሰረት የረዥም ጊዜ ልምድ ባላቸው ዳኞች ይመረጣሉ ተብሏል።
ኪነ-ጥበብ፣ መምህርነት፣ መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነት፣ ሚዲያ፣ ንግድና ሥራ ፈጠራ፣ በጎ አድራጎት፣ ዲያስፖራ፣ ቅርስና ባህል እንዲሁም ሳይንስ በሽልማት መርኃ ግብሩ የተካተቱ ዘርፎች ናቸው።
የበጎ ሰው ሽልማት ቦርድ አባል ነፃነት ተስፋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ባለፉት 9 ዓመታት መርኃ ግብሮች 187 ሰዎችና ድርጅቶች እውቅና ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
አክለውም የዘንድሮው መርኃ ግብር ቁጥሩን ወደ 225 ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።
በመርኃ ግብሩ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ፣ አርቲስቶች፣ አትሌቶች እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።
በትዕግስት ዘላለም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!
602 views13:52