Get Mystery Box with random crypto!

Walta

የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta W
የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta
የሰርጥ አድራሻ: @walta_tv_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://www.facebook.com/waltainfo
#ሼር #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-07-15 16:38:52
ህግ ተላልፈው የተገኙ ከ367 ሺሕ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) በ2014 በጀት ዓመት በተደረገ የዋጋ ማረጋጋትና ህገ-ወጥነት ቁጥጥር ህግ ተላልፈው በተገኙ 367 ሺሕ 880 ነጋዴዎችና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ ከፌዴራል አስከ ወረዳ ባለው የሚኒስቴሩ መዋቅር ዋጋ የማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ግብረ ኃይል በተሰሩ ሥራዎች ህግ ተላልፈው በተገኙ 192 ሺሕ 850 ነጋዴዎች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 167 ሺሕ 592 የንግድ ተቋማትን የማሸግ፣ 3 ሺሕ 741 ነጋዴዎችን ከንግድ ሥራ የማገድ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን 1 ሺሕ 723 ነጋዴዎች ደግሞ ክስ ተመስርቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ያለንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ፣ ያለደረሰኝ የተገበያዩ፣ በምርቶች ላይ ባዕድ ነገር ቀላቅለው ለገበያ ያቀረቡ፣ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች ለገበያ ያቀረቡ እንዲሁም ያለአግባብ ዋጋ የጨመሩ መሆናቸው ተገልጿል።

እርምጃው የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ያልለጠፉ እና ምርትን ያለአግባብ በክምችት የያዙ ነጋዴዎችንም እንደሚያካትት የንግድ ሥርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ አማካሪ ግዛው ተክሌ የዘርፉን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ለሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ባቀረቡበት ወቅት አብራርተዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በተቋማቱ የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በአዳማ ከተማ እየተወያዩ እንደሚገኙ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.8K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:38:52
2.0K views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:01:19
2.6K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:01:19
2.4K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:01:18
2.1K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:01:18
ዩኒቨርሲቲው በነገው እለት 1 ሺሕ 167 ተማሪዎችን ያስመርቃል

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በነገው እለት ለ9ኛ ዙር 1 ሺሕ 167 ተማሪዎችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርኃ ግብር ያስመርቃል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔትም በትናንትናው እለት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በ2004 ዓ.ም 623 ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሥራ የጀመረው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት 22 ሺሕ 764 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ማስመረቁ ተመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:01:18
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበትና ከፍተኛ ውጤት እንደሚያመጡ የሚጠበቅበት 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ቀናት ይካሄዳል።

በአሜሪካ ኦሬጌን በሚካሄደው በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 47 አትሌቶችን በተለያዩ ርቀቶች ላይ እንደምታሳትፍ የኢትዮጵያ አቲሌትክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ዛሬ ሐምሌ 08/2014 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:15 የወንዶች 3 ሺሕ ሜትር መሠናክል እና የሴቶች 1 ሺሕ 500 ሜትር ማጣሪያዎች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 10:10 ላይ እንደሚካሄዱ የወጣው መርኃ ግብር አመላክቷል።

ምንጊዜም ኢትዮጵያ የምትደምቅበት ይህ ሻምፒዮና በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በቀጥታ ይተላለፋልም ነው የተባለው።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.0K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ