2022-07-15 20:16:16
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የኦሮሚያ ክልል ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል አሉ
ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለአገራዊ ምክክሩ መሳካት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አረጋገጡ፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አባላት ጋር ዛሬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ብትፈተንም ችግሮቹን ወደ ዕድል እየለወጠች እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡
በቀጣይም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በሕዝቦቿ አንድነት እና ትብብር በመቅረፍ አመርቂ ውጤት እንደምታስመዘግብም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አገራዊ ምክክሩ በግልጽነት እና በፍትሃዊነት ያለምንም የፖለቲካ ጫና ሕዝቦችን በማሳተፍ መካሄድ እንዳለበትም ነው የጠቆሙት፡፡
የኦሮሞ ሕዝብ ሰላም እና ልማት ወዳድ እንደመሆኑ መጠን ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት ከኮሚሽኑ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል፡፡
አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በበኩላቸው አገራዊ ምክክሩ በአገራዊ ጉዳዮች የሕዝቦችን አስተያየት መሰረት በማድረግ ነፃ፣ አካታች እና ታአማኒ በሆነ መልኩ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
በአፋን ኦሮሞ የተተረጎመውን የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አዋጅም ለርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ማስረከባቸውን የክልሉን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.3K views17:16