Get Mystery Box with random crypto!

Walta

የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta W
የቴሌግራም ቻናል አርማ walta_tv_eth — Walta
የሰርጥ አድራሻ: @walta_tv_eth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8
የሰርጥ መግለጫ

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.
For more updates please visit https://www.facebook.com/waltainfo
#ሼር #በማድረግ_አጋርነታችሁን_አሳዩን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-09-01 21:01:22
“ኢትዮጵያ የወታደሮች ላብ፣ ደም እና አጥንት ያፀናት ታላቅ ሀገር ናት!” - የገንዘብ ሚኒስቴር

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የወታደሮች ላብ፣ ደም እና አጥንት ያፀናት ታላቅ ሀገር ናት ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

“ኢትዮጵያ የወታደሮች ላብ፣ ደም እና አጥንት ያፀናት ታላቅ ሀገር ናት!”

አፈር ገፍተው፣ አረም ጎልጉለው የሚያበሏት ባለ እርፍ ወታደሮች ሀገር ናት።

መንገዷን በእውቀት ብርሃን የሚተልሙላት የባለአዕምሮ ወታደሮችም ሀገር ናት ሃብት የሚያፈሩላት፣ የሚመጥኑላት፣ የሚያከፋፍሉላት ባለ ላብ ወታደሮች ሀገር ናት። ሁላችንም የኢትዮጵያ ወታደሮች ነን፤ ሁላችሁም የኢትዮጵያ ወታደሮች ናችሁ። ጥቃት የማንሸከም፣ ዳሯ መሃሏ በክብር እና በሰላም እንዲያድር የምንዋደቅ ወታደሮቿ ስጋችን ፈርሶ፣ ደማችን ፈሶ፣ አጥንታችን ተከስክሶ በታላቅ ሀገርነት ኢትዮጵያን እናፀናታለን።

የኢትዮጵያ በመሆናችን ሁሌ እንኮራለን። በደስታ እና በክብር እንጠብቃታለን። በደስታ እና በክብር እንሰዋላታለን ዛሬ ኢትዮጵያ ተበታትና፣ ተዳክማ፣ እንድትወድቅ እና እንድትፈርስ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቿ ከውስጥ አሸባሪ ቡድኖች ጋር በመተባበር ጥቃት ከፍተውባት በጽኑ መከላከል ላይ ትገኛለች።

በተለያየ ዙር ጠላቶቿ ልጆቿን ደፍረው-አጎሳቁለው-ገድለው፣ ንብረታቸውን አጥፍተው፣ መማሪያ-መታከሚያ-መኖሪያ-ማደሪያ-ማምለኪያ-ፈጣሪን መለማመኛቸውን አውድመው ማጥቃታቸው መራር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.1K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:01:22
ጉባኤው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ በመግለጫው የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁንም የሰላም ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና የሰላም ጥረቱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሁሉ ሌሎችም ወገኖች ለዚሁ መልካም ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አሳስበዋል።

ለወታደራዊ ዘመቻ ህፃናትን ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል ያለው ኢዜአ ነው።

በአገራዊ ጉዳይ በተለይ ወጣቶች ሁኔታውን በጥልቀት በማጤን ከስሜት በወጣ፣ ነፃና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ እንዲመረምሩ ጠይቀዋል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
1.9K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:29:07
የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ማንኛውንም ህጋዊ እርምጃ እንደግፋለን - የሰሜን አሜሪካ የሲቪክ ማኅበራት ኅብረት ጥምረት

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መንግስት የተከፈተበትን ጦርነት ለመከላከል የሚያደርገውን ማንኛውንም ህጋዊ እርምጃ እንደሚደግፍ የሰሜን አሜሪካ የሲቪክ ማኅበራት ኅብረት ጥምረት አስታወቀ፡፡

ኅብረቱ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ አሸባሪው ሕወሓት ፖለቲካዊ ለውጦችን ባለመቀበል በመተው በኅብረ ብሄራዊ አንድነት እሳቤ የመጣውን ለውጥ ባለመቀበል የለውጥ ጎዳናዎችን ሲያደናቅፍ መቆየቱን አንስቷል፡፡

ከለውጥ አደናቃፊነት ባለፈም ያጣውን የጭቆና አገዛዝ እንና የፖለቲካ የበላይነት እመልሳለሁ በሚል ከንቱ ምኞት ተነሳስቶ ብቸኛ የሀገር እና የሕዝብ ጠባቂ የሆነውን የሰሜን ዕዝ በማጥቃት ሀገሪቱን ለውጭ እና ለውስጥ አደጋ ማጋለጡን አብራርቷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ከሰሜን አሜሪካ የሲቪክ ማህበራት ህብረት ጥምረት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

የህዋሃት መራሹ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለ27 ዓመታት የጫነው ኢፍትሃዊነት፤ ኢዴሞክራሲያዊነት፤ የከፋፍለህ ግዛና ወደር የለሽ ዘረፋ ያንግፈግፍው የኢትዮጵያ ሀዝብ ይህን ከህግ በላይ መኖርን ድርጅታዊ ባህሉ ያደረገውን የፖለቲካ ቡድን ወደ ማይሸከመው ምእራፍ በመድረሱ አሽቀንጥሮ መጣሉ ይታወቃል።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
3.7K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:29:07
በመዲናዋ 17 ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ በተያዘው በጀት ዓመት ሰርቶ ለማጠናቀቅ የተያዙ 17 የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

ፕሮጀክቶቹንየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቆንጂት ደበላ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ነው የተመረቁት።

የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ፣ የወረዳ አስተዳደር ህንፃ ማስፋፊያ፣ የዳቦ መጋገሪያና ሌሎችም ፕሮጀክቶች ለምረቃ ከበቁት መካከል ይገኙበታል።

ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ 171 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉም ተነግሯል።

ማህበሩን በማሳተፍ ደግሞ ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ 108 ፕሮጀክቶችን ደግሞ ከህብረተሰቡ እና ከአጋር አካላት በተገኘ 85 ሚሊየን ብር መገንባት መቻሉ ተገልጿል።

የኮሚኒቲ ሴንተር ግንባታ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ድልድይ እና 104 የአቅም ደካማ ቤቶች እድሳት ያካተተ ሲሆን ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውም ተነግሯል።

በተጨማሪም የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ግንባታን ለማከናወን የሚያስችል ቦታ ርክክብም ግንባታውን ስፖንሰር ላደረገው ኬዌይ ካምፓኒ ለቤተ-እስራኤል ብሪቶለም ተደርጓል።

ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ሁሌም ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
3.1K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:29:07
ጄኖሳይድ የሚለው ተረት በሕወሓት ተደርሶ በሕወሓት ዳይሬክት ተደርጎ ለዓለም የቀረበ ምርጥ የሕወሓት ፊልም ነው።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.7K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:29:07
ም/ጠ/ሚ ደመቀ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ አደረጉ

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮችና የሚሲዮን መሪዎች ገለጻ አደረጉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ለሰላም ቢሰራም ህወሀት ግን ራሱን ለዳግም ጦርነት በማዘጋጀት በአፋርና በአማራ ክልል ወረራ በመፈጸም ጥቃት እያደረሰ ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ መንግስት በህወሀት የሚሰነዘረውን ጥቃት እየመከተ ለሰላም እጁን አላጠፈም ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ጥቂት ሀገራትና ግለሰቦች የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በሚጻረን መልኩ ለህወሃት ብዙ እርቀት ሄደው ድጋፍ እያደረጉ እንዳሉ ጠቁመው ለአብነት ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳርያ ሊያቀብል የነበረ አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር ሀይል መመታቱን ገልጸዋል፡፡

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ  እና ሚዛናዊ በመሆን  ከእውነታው ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሸባሪው ህወሀት በዜጐች ላይ ዳገም ጥቃት እያደረሰ መሆኑንም በመግለጽ መንግስት የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ይገደዳል ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.6K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:29:07
“ሕወሓት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል”- የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም:-

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሓት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው ርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት ርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሓት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሓት የሽብር ቡድን እየደረሰሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሓት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።
ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.8K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:23:32
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ አዲስ አገልግሎት ይፋ አደረገ

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ክፍያን በቴሌ ብር መፈፀም የሚያስችል አዲስ አሰራር ይፋ አደረገ።

የዲጂታል ኢትዮጵያን ሀሳብ እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም በጥሬ ብር ይደረግ የነበረውን እንቅስቃሴ በቴሌብር ማድረጉ ጊዜና ወጪን ከመቆጠቡ ባሻገር ለተቋማት ጥቅሙ የጎላ እንደሆነ አስታውቋል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት እስካሁን ይሰጥ የነበረውን የጥሬ ገንዘብ አገልግሎት በቴሌ ብር አማካኝነት በማድረግ ደንበኛው ሰነዶችን በድረገፅ በመሙላት አገልግሎቱን የሚያቃልል አዲስ አገልግሎት ነው ይፋ የሆነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገልፀው ጊዜ ከመቆጠብ ባለፈ ያለንን ውስን ሀብት ተጠቅመን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንድናገኝ ያስችለናል ብለዋል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን በቀን ከ7ሺሕ 300 በላይ ደንበኛ እንደሚያስተናግዱ ገልፀው አሁን ላይ በኢትዮ ቴሌኮም ይፋ የተደረገው አዲስ አገልግሎት ለደንበኛው ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት አድርገዋል::

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
2.0K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:23:32
የትምህርት ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል የትምህርት ዝግጅት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዝግጅት ሥራዎችን እየጎበኙ ይገኛል።

ሚኒስትሩ በሐረር ከተማ በሚገኘው መንፈሳዊ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ከመማር ማስተማሩ አቅጣጫ ጋር በተያያዘ የመማርያ ክፍል ዝግጅቶችን ተመልክተዋል።

እንዲሁም በሐረር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎችን ለማብቃት እየተሰጠ የሚገኘውን የማጠናከርያ ትምህርት ሥራ ገብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በምልከታቸው በሐረር ከተማ የሚገኘውን የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅን እና የህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ቲቺንግ ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴ ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ በመገኘት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር እንደሚወያዩ የኢዜአ ዘገባ አመልክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.6K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:23:32
አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው

ነሐሴ 26/2014 (ዋልታ)አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

“በአገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ ማክሰኞ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ሰልፉ እንደሚካሄድ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ ለአገር መከላለከያ ሰራዊት ፣ለጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለውም የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለፈጣን መረጃዎች:-
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!
1.7K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ