Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሓትን የመከፋፈል ሴራ ለማክሸፍ እንደሚሰሩ የዞን አመራሮች ገለጹ ነሐሴ 29/2014 (ዋልታ) | Walta

የሕወሓትን የመከፋፈል ሴራ ለማክሸፍ እንደሚሰሩ የዞን አመራሮች ገለጹ

ነሐሴ 29/2014 (ዋልታ) የአሸባሪውን ሕወሓት የመከፋፈል ድብቅ ሴራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅበር ለሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ የምዕራብ ጉጂ ዞን እና የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ፡፡

የጉጂ እና የጌዴኦን የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥርን ለማጎልበት በማሰብ በምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ከአባላቱ በሰበሰበው ገንዘብ በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ አንጨቢ ቀበሌ በድንበር ተሻጋሪ የበጎ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስና መስራት ጅምሯል፡፡

መርኃ ግብሩ በኦሮሞ ጉጂ እና በጌዴኦ ሕዝቦች መካከል እውነተኛ ሠላም እንዲፈጠርና የቀደመው ቁርሾ በሁለቱም ወገኖች እንዲረሳ የተዘጋጀ መሆኑን ከገላና ወረዳ ኮሙዩኒኬሸን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTA_TV_Eth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!