Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 149

2023-01-05 23:05:40
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ 355 ሺህ 86 ኩንታል ማዳበሪያ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከሞሮኮው ኦሲፒ ኩባንያ 7 ሚሊዮን 875 ሺህ 520 ኩንታል ማዳበሪያ (2 ሚሊዮን 188 ሺህ 940 ኩንታል NPS እና 5 ሚሊዮን 686 ሺህ 580 ኩንታል NPSB) ገዝቷል።

ከዚህም ውስጥ፦

* ከታህሳስ 19-27/2015 ዓ.ም. ድረስ 355 ሺህ 86 ኩንታል ማዳበሪያ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል።

- ባለፈው ሳምንት 572 ሺህ 950 ኩንታል NPS የአፈር ማዳበሪያ የጫነች #የመጀመሪያዋ መርከብ ወደብ ደርሳለች።

- ትላንት ታህሳስ 26/2015 ዓ.ም. MV SEA RIDER የተባለች #ሁለተኛዋ መርከብ 600 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ (NPSB) ጭና ጅቡቲ ወደብ መድረሷ ታውቋል።

- ከጥር 2-10/2015 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ #ተጨማሪ 1 ሚሊዮን 800 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ሦስት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) የግብርና ሚኒስቴር በየአመቱ አጥንቶ በሚያቀርበው ሀገራዊ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሰረት ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ማዳበሪያ ከውጭ እየገዛ የሚያቀርብ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ነው።

@tikvahethmagazine
8.3K viewsedited  20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 18:22:09
ጥቆማ!

የፊንጢጣ አካባቢ ፊስቱላ በክሮንስ ምክንያት ህክምና የሚያስፈልገው ሰው ታውቃላችሁ?

እንዲሁም ሰገራ/ፈስ መቆጣጠር አለመቻል ህመም በቀዶ ጥገና እንዲታከሙ የታዘዘሎት ከሆነ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ!

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከኖርዌይ ሀገር ከሚመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በሚቀጥለው ሳምንት ህክምና ይሰጣል።

ከሰኞ እስከ ሀሙስ ብቻ የሚቆየው ይህ የህክምና ፕሮግራም በሆስፒታሉ በመቅረብ መገልገል ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ ዶ/ር ቢንያም ዮሀንስ @Binyjohny2 በቴሌግራም ያዋዩ!

@tikvahethmagazine
8.0K viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 18:20:45
የኢትዮጵያ ቡናን በኤሌክትሮኒክ ንግድ ለዓለም ገበያ ማቅረብ የሚያስችል ፕላትፎርም ወደ ስራ መግባቱ ተገለጸ።

"ክሮፕ ኮኔክስ" የተሰኘው የአሜሪካ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስርዓት አንቀሳቃሽ ኩባንያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢ-ኮሜርስ ንግድ መደብ ፍቃድ ያገኘ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።

ሥርዓቱ የቡና አምራች እና ላኪዎችን ቀጥታ ከተጠቃሚው ጋር በማገናኘት ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ እንደሚረዳ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

የክሮፕ ኮኔክስ ባለቤት ብሪያና ዲኬይ በበኩላቸው በንግድ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ እና የእሴት ሰንሰለት በማበጀት የንግድ እድሎችን መፍጠር ዋናኛ ዓላማችን ነው ብለዋል።

ስርዓቱ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ፣ ቡናን ለማስተዋወቅ፣ የቡና ግብዩቱን ከመነሻው እስከ መዳረሻው ለማስተዳደር ያስችላል ተብሏል። (MinT)

@tikvahethmagazine
7.5K viewsedited  15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 18:20:31
የመጀመሪያ መኪናችሁን ይሁን አስረኛ መኪናችሁንም ቢሆን ለመግዛት ያሰቡት፤ ያገለገሉ መኪና መሸጫ ቻናሎች የመኪና ዋጋ ማጣራት እና መግዛት ሂደቱን ያቀለዋል። ነገር ግን የመኪና መሸጫ ቻናሎች መኪና መግዛት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመው ለመኪና ባለቤቶችም መኪናቸውን ለመሸጥ ሲያስቡ ገዢ እንዲያገኙ ይጠቅማል።

ለገዢዎች የሚፈልጉትን መኪና በማቅረብ ለሻጭ ደግሞ ገዢ(ብዙ ጊዜ በዛ ያሉ ገዢዎችን) በማምጣት ደግሞ @ethiocar2 በ online ገቢያው ላይ ጥሩ ስም አለው።

ከታች ያለውን Link በመንካት ለራስዎ ያረጋግጡ።

Telegram: https://t.me/+_x7unWpf80thMGU0

www.ethiocarbroker.com

በምርጫዎ ይደሰታሉ።
6.2K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 18:20:22
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me
0909255008
0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ ቤተሰብ ይውኑ
https://t.me/used_phone_ethiopia
2.1K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 17:39:42
በ2022 የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ለ328 የልብ ሕሙማን ነጻ ህክምና ማድረጉን ገለጸ።

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ባሳለፍነው የ2022 የሥራ ዘመን በልብ ማዕከል ውስጥ ለ8,674 ሕሙማን የልብ ሕክምና ክትትል እንዲሁም ለ328 ሕሙማን የልብ ቀዶ ሕክምና እና በደም ስር በኩል የሚከናወን የልብ ሕክምና አገልግሎት በነፃ ለመስጠት መቻሉን ገልጿል።

ይህ ቁጥር ከማዕከሉ የመስራት አቅም እና ወረፋ ከሚጠብቁ ሕሙማን ቁጥር አንፃር እጅግ አነስተኛ አገልግሎት ቢሆንም ከሕብረተሰቡ እና ከተለያዩ ተቋማት በተገኘው ድጋፍ አገልግሎቱን ማስቀጠል መቻሉን የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚክሎል መንግስቱ አንስተዋል።

በልብ ማዕከል ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ከ7,400 በላይ ሕሙማን ወረፋ በመጠበቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን የአገልግሎቱን ቁጥር ለመጨመር ማዕከሉን በ6710 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ላይ “OK” ብሎ በመላክ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@tikvahethmagazine
8.8K viewsedited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:43:58
የ18 ዓመት ልጃገረድ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በአራዳ ቀበሌ መንደር ሃያ ነዋሪ የሆነው ወጣት እሸቱ ባለቸው በመስከረም 15/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ላይ ተበዳይ የሆነችውን የ18 ዓመት ልጃገረድ አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል።

ተበዳይ ከቤት ወደ ጽዳት ሥራ እየሄደች ባለችበት በዕለቱ ዶፍ ዝናብ ሲዛንብ ስለነበር ለመጠለል በገባችበት ቤት ተከታትሎ በመግባት በእጁ በያዘው ሰንሰለት አስሮ አስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን አቃቤ ህግ ባቀረባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል።

በዚህም 8/04/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሹ ወጣት እሸቱ ባለቸው ላይ የአምስት ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት መወሰኑን የሆሳዕና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ደኛ ሙልጌታ ከበደ ገልጸዋል።

የከተማው አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰ እንዳሉት በሴቶች እና ህፃናት ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ከሚያስከትለው ጉዳት አንፃር የተሰጠው ውሳኔ ተመጣጠኝ አለመሆኑን ጠቁመዋል።

መረጃው የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
19.7K viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:43:29
በቀን ከ288 ሺህ በላይ እንጀራ ለሚያመርት የእንጀራ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በአዲስ አበባ ከተማ 1000 ሺህ የእንጀራ ምጣድ የሚኖረውና በቀን ከ288 ሺህ በላይ  እንጀራ የሚያመርት የእንጀራ ፋብሪካ ለመገንባት በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ፕሮጀክቱ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገነባ ሲሆን ሺህ ለሚደርሱ እናቶችና ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር እና በ3 ወር ውስጥ ተገንብቶ ወደ ስራ እንደሚገባ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ፋብሪካው በአካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች የጤፍ ምርት በመግዛት የሚጠቀም ሲሆን የእንጀራ ምርትን ለዓለም አቀፍ ገበያም ኤክስፖርት ለማድረግም በእቅድ መያዙ ነው የተገለጸው።

@tikvahethmagazine
17.9K viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:43:08
ልዩ ቅናሽ ከአያት ሪል ስቴት
እንዳያመልጥዎ


በሲ ኤም ሲ ሚኬኤል ግዙፋ የአያት መኖሪያ መንደር ከልዩ የ 5% የበዓል ቅናሽ ጋር እየጠበቅንዎት ነው! ዞሮ መግቢያ ቤትዎትን በ15% ቅድመ ክፍያ ይግዙ!

የአያት አክስዮኖችን በመግዛት ዛሬውኑ የስመ-ጥሩ ድርጅት ባለቤት በመሆን እስከ 44% የሚደርስ ትርፍዎን ይካፈሉ!

አያትን የሰማ ትርፋማ

ለተጨማሪ መረጃ
                       0930653333
16.7K views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 12:42:46
https://t.me/Mikimobiles

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ
       MIKI_MOBILE_AND_LAPTOP

በአልን ምክንያት በማድረግ ስልኮት ላይ መጠነኛ ብር በመጨመር በተሻለ ዋጋ የተመረጡ ስልኮችን ይውሰዱ::
ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም
ቻናል በመቀላቀል ORIGINAL ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ::

https://t.me/Mikimobiles
16.4K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ