Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 148

2023-01-03 13:45:50
ድምጻዊት አስቴር አወቀ "ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም ለአድማጮች ልታደርስ ነው።

የድምጻዊት አስቴር አወቀ የጥምቀት ዋዜማ ላይ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች እንደምታደርስ ተገልጿል። በዛሬው ዕለትም ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አከናውናለች።

ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት 24 የሚደርሱ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው ተብሏል፡፡

መረጃው የሰዋሰው መልቲ ሚድያ ነው።

@tikvahethmagazine
25.2K viewsedited  10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 13:02:03
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክርቤት ተመሠረተ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ13 ነባር ብሔረሰቦች የተወከሉ 70  አባላት ያሉት የብሔረሰቦች ምክርቤት ተመስርቷል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የብሔረሰቦች ምክርቤት መመስረት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች የሚያጎለብቱበት ሁኔታን ይፈጥራል ሲሉ በምስረታው ወቅት ገልጸዋል።

ከ13 ነባር ብሔረሰቦች 5 ተወካዮች እና ከ1 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለበት ተጨማሪ 5 ተወካዮችን በማከል ምክርቤቱ 70 አባላት እንደሚኖረው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

ምክርቤቱ በዛሬው ዉሎው አቶ መቱ አኩን በዋና አፈ ጉባኤና አቶ መሠለ ከበደን በምክትል አፈ ጉባኤ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር መስራች ጉባኤው አጠናቋል።

መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
24.9K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 12:52:55
በሀዘን ላይ ሌላ ሀዘን . . .

በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የቅርብ ዘመድ ሲሞት የሟች አስክሬን ግብአተ መሬት ሲፈፀም እንደ ሀዘን መግለጫ ጥይት የመተኮስ ባህልና ልማድ የሆነባቸዉ አካባቢዎች አሉ።

በደቡብ ኦሞ ዞን ባኮ ዳውላ ወረዳ አሊ ቀበሌ ታህሳስ 23/ቀን 2015 ዓ.ም በቤተ ዘመድ ለቅሶ ላይ የተገኘ ግለሰብ ለሟች ያለዉ ፍቅርና የተሰማዉ የሀዘን ስሜት ለመግለፅ የተኮሰዉ ጥይት አቅጣጫ ስቶ ከለቀስተኞች መሀከል ሶስት ሴቶች በጥይት መመታታቸዉ ተነግሯል።

በጥይት ጉዳት ከደረሰባቸዉ ሶስቱ ሰዎች የአንዷ ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በሁለት ሴቶች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱና የተጎጂዎች ህይወት ለማትረፍ ወደ ሆስፒታል ተልከዉ በህክምና እየተረዱ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ከደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine
22.7K viewsedited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 12:52:48
ለወዳጅ ዘመድ የሚሆን አስገራሚ የገና ስጦታ እንጨት ላይ

ለ4 ቀን ብቻ ይሚቆይ የ5 % የበዓል ቅናሽ
Quality Matters @hanosengraving

Paw Shape
Price 900 ብር
Free delivery in Addis Ababa

Contact: 0956447743 or @hanos_order

For more:- Join our telegram channel https://t.me/hanosengraving
18.7K views09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 12:33:54
የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በቀጣይ ዓመት ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ።

ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ሥልጠና ወስደውበታል በሚባለው ቦታ ላይ እየተሰራ ያለው የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም የላንድስኬፕና የዲዛይን ሥራው በዚህ ወር ተጠናቅቆ ርክክብ እንደሚደረግና የእድሳት ሥራዎቹም በተያዘው ዓመት ተጠናቅቆ በሚቀጥለው ዓመት ለጉብኝት ክፍት ይሆናል ተብሏል።

ይህ ታሪካዊ ቦታ የሚገኘው በኮልፌ 18 የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ሲሆን የሙዚየም ግንባታው በአዲስ መልክ የሚገነባ ሳይሆን የነበረውን ቅርስነቱን አስጠብቆ በውስጡ ያለውን ታሪካዊ የሆነ ኪነ ህንጻ እድሳት በማድረግ ታሪኩን የማስቀጠል ሥራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል።

አክለውም፣ ሙዚየሙ የማንዴላን ታሪክ ከመዘከርና ይፋ ከማውጣት አኳያ ጅማሬው ጥሩ ነው፤ ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ባለሀብቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቦታውን ጎብኝተዋል። ከጎበኚዎቹ ጋርም በተደረገው ውይይት ሥራውን ለመደገፍም ፍቃደኝነታቸውን ገልጸዋል ሲሉ አንስተዋል።

አፍሪካውያንም ሆነ የዓለም ጎብኚዎች ወደ ከተማዋ ሲመጡ ከአፍሪካ ሕብረት በተጨማሪ በተጨባጭ ኢትዮጵያ ተከናውነው ያለፉ ክስተቶች ለማሳየት ሙዚየሙ ትልቅ ሚና እንዳለውም ኃላፊዋ አመልክተዋል።(EPA)

@tikvahethmagazine
19.6K viewsedited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 12:12:45
ጾታዊ ግንኙነት ከልክላኛለች በሚል ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ . . .

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ገመቺስ አራዳ ግርያ ጎርባ ቀበሌ ባል ባለቤቱን ለጾታዊ ግንኙነት ሲጠይቃት አሞኛል አልችልም ትላለች።

በዚህ ጊዜ "ሌላ ሰው ወደሽ ነው" በሚል ቂም በመያዝ የሶት ልጆች እናት የሆነች ባለቤቱን ስትተኛ ጠብቆ በስለት ህይወቷ እንዲየልፍ አድርጓል።

ልጆቻቸውም የወላጅ እናታቸውን ሁኔታ ለጎረቤት ያስረዳሉ፤ የጎረቤት ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ ተከሳሽን ቁጥጥር ስር ያውላል።

ተከሳሽም ድርጊቱን መፈጸሙን ያምናል፤ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተነግሯል።

Credit፦ Bisrat FM 101.1

@tikvahethmagazine
20.5K viewsedited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 10:59:21
በመዲናዋ ጎዳና ላይ ውሎ አዳራቸውን ያደረጉ ታዳጊዎች ጉዳይ . . . የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) መረጃ ድንበር አቋርጠው፤ ተሰደው ከሚሰደዱት ኢትዮጵያዊያን ባልተናነሰ ከክልል ክልል የሚደረጉ ፍልሰቶች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩን ያመለክታል። አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ በየጎዳናው ዳቦ ግዙልኝ፣ ማስቲካ፣ ሶፍት ግዙኝ የሚሉ እንዲሁም ት/ቤት በመዋያ እድሜያቸው የታክሲ ረዳትነት፣ጫማ ማስዋብ፣…
21.3K viewsedited  07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 10:56:30
ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ላይ የሚሰራው ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለጸ።

ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ላይ የሚሰራው ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

በ2014 በጀት ዓመት በነበረው ግምገማ ከተያዘው 300 በላይ የሀሰተኛ ሰነድ ማስረጃ 82.5 በመቶ የሚሆነዉ ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ አሁንም በዚህ ላይ የሚታየው የሀሰተኛ ሰነድ ዝግጅት እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

ከወረዳ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በትክክል መታወቂያ የተሰጣቸው ግለሰቦች ወደ ተቋሙ መጥተው የያዙትን ሰነድ ለማጣራት ሲሞከር ጥለው እንደሚሄዱ እና ይህም ከወረዳ ጀምሮ ችግር መኖሩንና ለአገልግሎቱም አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ተብራርቷል።

ተቋሙ ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃን ለመከላከል አጠራጣሪ ነገሮች በሚያጋጥሙት ወቅት ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ተቋማት እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጥብቅ የመረጃ መለዋወጫ ስርዓት እንደዘረጋ ተነግሯል።

አገልግሎቱ በውስጡ ባለው አሰራር ከተቋሙ የሚወጡ ሰነዶች ሃሰተኛ እንዳይሆኑ ለማድረግ የውክልና ማስረጃ ሰነድ አሰጣጥ ላይ የሲኣር ኮድ ስርዓት እና ሌሎች አሰራሮችን እንደሚጠቀምም ተገልጿል፡፡ (EBC)

@tikvahethmagazine
19.4K viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 10:56:09
በኢትዮጵያ #ሪል_ስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደሙ እና የዘርፈ ብዙ ድርጅቶች ባለቤት የሆነው አያት አክስዮን ማህበር በከተማችን እምብርት ካሳንችስ እና በግዙፋ ሲ ኤም ሲ ሳይታችን በሽያጭ ላይ ከሚገኙት ዘመናዊ አፓርትመንቶች በተጨማሪ የኩባንያውን አክሲዮኖች ለሽያጭ አቅርቧል።

➛ቀጣይነት ያለው ገቢ እንዲኖርዎትና እስከ 44% የሚደርስ የትርፍ ክፍፍል (ዲቪደንድ) ተካፋይ ለመሆን የዚህ ግዙፍና ትርፋማ ድርጅት ባለቤት ለመሆን አሁኑኑ ይወስኑ።
➛ በካሳንችስ ሳይታችን ከ90% በላይ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ውስን ቤቶች ለሽያጭ የቀረቡ ስለሆነ ለመግዛት ይፍጠኑ።
አያትን የሰማ ትርፋማ!
#ለበለጠ_መረጃ:
0930653333 ላይ ይደውሉ
17.6K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 10:56:01
ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለገና በዓል ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ

ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!

ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764

#Adresss  Addis Ababa, 22, tigat bldg  next to axum hotel

ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ BLUEBELL FLOWER & GIFTS

t.me/bluebellgiftstore 
22.3K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ