Get Mystery Box with random crypto!

በሀዘን ላይ ሌላ ሀዘን . . . በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የቅርብ ዘመድ ሲሞት የሟች አ | TIKVAH-MAGAZINE

በሀዘን ላይ ሌላ ሀዘን . . .

በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የቅርብ ዘመድ ሲሞት የሟች አስክሬን ግብአተ መሬት ሲፈፀም እንደ ሀዘን መግለጫ ጥይት የመተኮስ ባህልና ልማድ የሆነባቸዉ አካባቢዎች አሉ።

በደቡብ ኦሞ ዞን ባኮ ዳውላ ወረዳ አሊ ቀበሌ ታህሳስ 23/ቀን 2015 ዓ.ም በቤተ ዘመድ ለቅሶ ላይ የተገኘ ግለሰብ ለሟች ያለዉ ፍቅርና የተሰማዉ የሀዘን ስሜት ለመግለፅ የተኮሰዉ ጥይት አቅጣጫ ስቶ ከለቀስተኞች መሀከል ሶስት ሴቶች በጥይት መመታታቸዉ ተነግሯል።

በጥይት ጉዳት ከደረሰባቸዉ ሶስቱ ሰዎች የአንዷ ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በሁለት ሴቶች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱና የተጎጂዎች ህይወት ለማትረፍ ወደ ሆስፒታል ተልከዉ በህክምና እየተረዱ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ከደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine