2023-01-04 10:23:40
በ5 ወራቱ በወባ በሽታ መያዛቸው ለተረጋገጠ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በላይ የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል።
በሀገራችን የወባ በሽታ የሚከሰተው በአብዛኛው ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ድረስ ዋናውን የክረምት ዝናብ ተከትሎ ነው። ከባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ስርጭት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተገልጿል።
የወባ ማጥፋት ፕሮግራም የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 5 ወር የአፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ህዳር መጨረሻ ያለው ሪፖርት ቀርቧል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተውም 6,330,753 ለሚሆኑ የወባ ህሙማን ተጠርጣሪዎች ምርመራ ተደርጎ፤ በወባ በሽታ መያዛቸው ለተረጋገጠ 1,330,888 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል። ይሄም ትኩሳት ኖሮባቸው ምርመራ ካደረጉ ሰዎች መካከል 21% ወባ ተገኝቶባቸዋል፡፡
የወባ በሽታን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ከ449 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች እና ከ6435 በላይ ቀበሌዎች ከፍተኛና መካከለኛ የወባ ስርጭት ባለባቸው የወባ ሳምንት ንቅናቄ የተከናወነ ሲሆን የሚዲያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራም ተሰርቷል።
ከ19 ሚሊዮን በላይ አጎበር ከውጭ ተገዝቶ ወደ አገር ዉስጥ እንዲገባ በተደረገው መሰረትም የመጀመሪያው 8,367,000 አጎበር ለክልሎች ተሰራጭቷል። 1,207,897 ቤቶችን ለመርጨት ታቅዶ 96% ቤቶችን መርጨት መቻሉ ተነግሯል።
@tikvahethmagazine
12.6K viewsedited 07:23