Get Mystery Box with random crypto!

የኔው ታሪክ 8315

የቴሌግራም ቻናል አርማ teztash — የኔው ታሪክ 8315
የቴሌግራም ቻናል አርማ teztash — የኔው ታሪክ 8315
የሰርጥ አድራሻ: @teztash
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213
የሰርጥ መግለጫ

D/shu ema kiya8315

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-31 05:20:58 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

#የመጨረሻው_ክፍል

ከባህርዳር ከተመለስን ከሁለት ቀን በዃላ ደብር ዘይት ያለው የሀኒ አባት ከብዙ ደጅ ማስጠናት በዃላ ውሀ አጣጭህ የምትሆነውን ሴት እንዳገኜ እና ለእሷና ለእህቷ ሊያስተዋውቃቼው ቀን ቆርጦ እንደጨረሰ በደስታ ፈንድቆ ይነግራታል ሀኒም በአባቷ ደስታ እጅግ በጣም ተደስታለች ለብቻው በመሆኑ እና እንደጓደኞቹ ጎኑ ሁና የምታደምጠው እና ጎጆውን ሞቅ ሞቅ አድርጋ በጊዜ እቤቱ እንዲገባ የምታደርገው ሴት ባለ መኖሯ በጣም ያሳዝናት ነበር የምትሆነውን አግኝቶም ተረጋግቶ እንዲቀመጥላት የዘወትር ምኞቷ ነበር ዛሬ የምኞቷን መሳካት በአንድ የስልክ ጥሪ አጎቷ አበሰራት እኔም ሀኒ ልትሄድ በመሆኑ እጅጉን ብከፍም እንዲህ ፈክታ ሳያት ግን ለእሷ መደሰቴ አልቀርም። በሚቀጥሉት ቀናት ከዚህ በፊት እንዳደርግነው የሚገዛዙ ነገሮችን ገዛዝተን የሀኒ ጓደኛ እናት ጋር ሄድን
ከመመለሶ በፊት እንደምታያቼው ቃል ስለገባች እና በዛውም የአባቷን የብስራት ዜና ለሳቼውም ለመናገር ነበር የሄደችው ሴትየዋ የአባቷን ሊያገባ መሆን ሲሰሙ የቤተሰብ ያህል በጣም ነበር የተደሰቱት እንደው እንዴትና ከወዴት አገኜዃት አለሽ ሲሉ ሀኒን ጠየቋት ሀኒም ምንም የተጨበጠ ነገር እንዳልነገራት ሁሉንም የሚያጫውታት ስትመጣ እንደሆነ ነገረቻቼው ያው ከዚህ በፊት ስለግንኙነቱ መጀመር እና
ሴቷ ያለችው አዲስ አበባ እንደሆነ ጫፍ ጫፉን ታቃለች እንኳንም ተሳካለት እንኳንም አንችም ከሀሳብ እና ጭንቀት አረፍሽ አሉ ሴትዮዋ በእናትነት ለዛ ።
ከዛ በዃላ ነበር ሀኒ ጓዟን ጠቅልላ ከደሴ ወደ ደብረዘይት አባቷ ጋር የሄደችው ያን ቀን አብረን አድረን ነበር የሼኜዃት እሷን ሼኝቼ ስመለስ የተሰማኝን የብቼኝነት ስሜት እና ባዶነት እንዲህ በቀላሉ በቃል የምገልፅበት ቃልም አልነበረኝም ዳግም የምንገናኝ ሁላ አልመስልህ እስኪለኝ ሆዴ ተላወሰ ለካ ኤርፖርት ላይ ሰው ተቃቅፎ እንደዛ የሚላቀሰው ወዶ አይደለም ከሚወዱት ለቀናትም ቢሆን መለየት ምን ያክል እንደሆነ ስሜቱ የገባኝ በዛን ሰሞን ነበር ። ከሀኒ ጋር ወዲያው ወዲያው ብንደዋወልም በቃ ደርሳ ትናፍቀኛለች ያ ሳቋ ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል ።
አንድ ምሽት ከሀኒ ጋር ተደዋውለን እያወራን አዲሷን እናቴን እኮ የምተዋወቅበት ቀን ነገ ነው ደስ አይልም ደሞ ሳልነግርህ ድርሰቱ ወደ ፊልም እስክሪፕት ተቀይሮ በቅርብ ግዜ ቀረፃው እንደሚጀመርም አጎቴ ነገረኝ ስትል ፍፁም በሚያስታውቅ ደስታ ፍልቅልቅ እያለች አወራችልኝ እኔም የደስታዋ ተካፋይ ለመሆን የአባቷ ትውውቅ ላይ ባልገኝ እንኳ ፊልሙ ሲመረቅ ግን በአካል ቦታው ድረስ እንደምገኝ ቃል ገባሁላት በጣም ደስ ይለኛል ነገ በጧት ለስራ ተነስቼ ጉድ ጉድ ማለት ስላለብኝ በግዜ ልተኛልህ እወድሀለሁ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ
በሚቀጥለው ቀን እህቴና ሀዩ ባሉበት ቁጭ ብለን ቡና እየጠጣን ነው እህቴና ሀዩ ሀኒ ከሄደች በዃላ እኔ ላይ በሚያዩት ድብርት መቀለድ እና መጠቋቆም ከጀመሩ ቆይተዋል የዚች የቆንጆ ጦስ መቼም ሂዳም አለቀቀህማ ትለኛለች እህቴ ሀዩ ግን እህቴ ጋር ስትሆን አብራ ብትቀልድም ለብቻዋ ስትሆን ግን በቻለችው ሁላ ፈታ እንድል የማታደርገው ጥረት አልነበረም በቀልዳቼው መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ ሀኒ ነበረች የአባቷን ሚስት በአካል የምትተዋወቅበት ቀን ዛሬ ስለሆነ አይመቻትም ብየ አልደወልኩላትም ነበር አነሳሁትና እንደሁልግዜው ቆንጆዋ አልኳት ድምፆ የቀዘቀዘ ነበር ምንድነው ድምፅሽ ደህና አይደለሽም እንዴ ሀኒ ስል ጠየኳት ምንም ሳትመልስልኝ የእናትህ ስም ማን ነበር ያልከኝ ስታስተዋውቀኝ የሚል ደረቅ ጥያቄ አስከተለች ከምናወራው ጋር ምን አገናኘው እያልኩ በውስጤ የእናቴን ስም ነገርኳት በዛው በቀዘቀዘ ድምፆ እሺ ብቻ ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ግራ እየተጋባሁ ደወልኩላት አይነሳም ደገምኩት ቴክስትም ላኩኝ ምንም ምላሽ የለም ይባስ ብሎ ስልኳ ጠፍ በእህቴ ስልክም ሞከርኩ ጥሪ አይቀበልም ነው የሚለው ከቀን ጀምሮ ምሽት ስድስት ሰአት እስከሚሆን እየቆየሁ ብሞክርም ስልኳ ግን አሁንም ያው ነው አሁንም አይሰራም ያን ሌት እንዲሁ ስገላበጥ ሀሳብ ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ የሚባል በአይኔ ሳይዞር ነጋ ከአልጋየ እንደተነሳሁም የመጀመሪያ ስራየ ምን አልባት ከሰራ በሚል ወደ ሀኒ መደወል ነበር ምን ዋጋ አለው እንደማታው ነው ጥሪ አይቀበልም ። አንዳንዴ ከሆነው አልያም ከደረሰብን ነገር በላይ እጅጉን ሰላም የሚነሳን እና ውስጣችንን እረፍት የሚነሳው ለምን እና እንዴት ሆነ የሚለው ነገር ነው እኔም አሁን ያ ስሜት ነው የሚሰማኝ ስልኩን ስለዘጋችብኝ ወይ ስላጠፋችው ብቻ ሳይሆን ለምን ያ ሆነ ? እንዴት የእናቴን ስም ጠየቀችኝ ? በቃ ውዝግብግብ ያለ ነገር ሆነብኝ በመሀል ደሞ አንዳች ነገር ገጥሟት ይሆን እንዴ እያልኩ እጨነቃለሁ በደስታዋ ቀን ላይ እንደዛ የመቀዛቀዟ የመረበሿ ነገር ደግሞ ሌላ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው ። እህቴ ቁርስ ሰርታ እኔን እየጠበቀች ነው እኔ ደግሞ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እኔ እቆያለሁ ብያት ከቤት ወጣሁ ወደየት እንደምሄድ ግን አላውቅም እንደ እብድ ብቻየን አወራለሁ በእህቷ ስልክ እንኳ እንዳልደውል የእህቷን ስልክ አላውቀውም አንዲህ ባለ ሁኔታ ነገር እያብሰለሰልኩ ከእንቅልፍ እንደተጣላሁ የሀኒ ስልክም እንደተዘጋ ሶስት ቀን ሞላኝ ከዚ በላይ ግን የውስጤን ጥያቄ ሳልመልስ የሀኒንም ሁኔታ ሳላቅ ታግሶ መቆየት አልቻልኩም የሆነ ነገር መፍጠር እንዳለብኝ ወስኜ ከአልጋየ ተነሳሁ የሰሞኑ ሁኔታየ ከወትሮው የተለየባት እህቴ ከመኝታ ቤቴ መውጣቴን ጠብቃ ምንድነው የሆንከው አንተ ልጅ ስትል አስቁማ አፋጠጠችኝ ምንም እንዳልሆንኩ ላስመስል ብሞክርም በዛ ሁኔታ አልችልም ነበር የግዴን ያለውን ነገር አንድ በአንድ ከሄደችበት ምክኒያት አንስቶ ደውላ የእናታችንን ስም ጠይቃኝ ስልኩ እስከተዘጋበት ደረስ ያለውን ነገርኳት ለአፍታ አንገቷን አቀርቅራ ከቆየች በዃላ ከሰመመን እንደነቃ ሰው አይነት ብንን ብላ አባቷ ሚኖረው ደብረዘይት ነዋ ያልከኝ አለች አዎ ምነው አልኳት ፊቷ ላይ የተወሰነ ግራ የመጋባት አይነት ድንጋጤ አስተውያለሁ አይ ምንም ቆይ ታዲያ በሷ በኩል የምታቀው ሌላ ሰው የለም አንዴ ምን አልባት ያለችበትን ሁኔታ የሚነግርህ አልያም ሌላ ስልክ ካላት የሚሰጥህ አለችኝ እህቷን እና አንድ ጓደኛዋን ብቻ ነው የማቀው የሁለቱም ስልክ ደግሞ የለኝም የኔ መልስ ነበር ይሄን እያወራን ሀዩ እንዴት አደራችሁ ብላ ወደቤት ገባች ሁለታችንም ፊት ላይ መረበሽ ስላየች ምንድነው በጧቱ ቆዝማችዃልሳ ብላ ከእህቴ ጎን ተቀመጠች እኔ ካለሁበት ተነሳሁና የተጫጫነኝ ትንሽ ለቀቅ ቢያደርገኝ ብየ ወደሻወር ቤት ገባሁ እህቴና ሀዩና እዛው በተቀመጡበት ይንሾካሾካሉ የሻወር ቆይታየን ጨርሼ ስወጣ ቁርስ ቀርቦ ነበር ካልበላሁ ስለምትጨናነቅ ለእህቴ ስል እንደነገሩ ቀማመስኩና አንዳች ፊንጭ ባገኝ እንኳ እዛው እቤታቼው ድረስ መሄድ እንዳለብኝ ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደርሼ ከቤት ወጣሁ
95 viewsአምባ, 02:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 21:45:57 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

#የመጨረሻው_ክፍል

ከባህርዳር ከተመለስን ከሁለት ቀን በዃላ ደብር ዘይት ያለው የሀኒ አባት ከብዙ ደጅ ማስጠናት በዃላ ውሀ አጣጭህ የምትሆነውን ሴት እንዳገኜ እና ለእሷና ለእህቷ ሊያስተዋውቃቼው ቀን ቆርጦ እንደጨረሰ በደስታ ፈንድቆ ይነግራታል ሀኒም በአባቷ ደስታ እጅግ በጣም ተደስታለች ለብቻው በመሆኑ እና እንደጓደኞቹ ጎኑ ሁና የምታደምጠው እና ጎጆውን ሞቅ ሞቅ አድርጋ በጊዜ እቤቱ እንዲገባ የምታደርገው ሴት ባለ መኖሯ በጣም ያሳዝናት ነበር የምትሆነውን አግኝቶም ተረጋግቶ እንዲቀመጥላት የዘወትር ምኞቷ ነበር ዛሬ የምኞቷን መሳካት በአንድ የስልክ ጥሪ አጎቷ አበሰራት እኔም ሀኒ ልትሄድ በመሆኑ እጅጉን ብከፍም እንዲህ ፈክታ ሳያት ግን ለእሷ መደሰቴ አልቀርም። በሚቀጥሉት ቀናት ከዚህ በፊት እንዳደርግነው የሚገዛዙ ነገሮችን ገዛዝተን የሀኒ ጓደኛ እናት ጋር ሄድን
ከመመለሶ በፊት እንደምታያቼው ቃል ስለገባች እና በዛውም የአባቷን የብስራት ዜና ለሳቼውም ለመናገር ነበር የሄደችው ሴትየዋ የአባቷን ሊያገባ መሆን ሲሰሙ የቤተሰብ ያህል በጣም ነበር የተደሰቱት እንደው እንዴትና ከወዴት አገኜዃት አለሽ ሲሉ ሀኒን ጠየቋት ሀኒም ምንም የተጨበጠ ነገር እንዳልነገራት ሁሉንም የሚያጫውታት ስትመጣ እንደሆነ ነገረቻቼው ያው ከዚህ በፊት ስለግንኙነቱ መጀመር እና
ሴቷ ያለችው አዲስ አበባ እንደሆነ ጫፍ ጫፉን ታቃለች እንኳንም ተሳካለት እንኳንም አንችም ከሀሳብ እና ጭንቀት አረፍሽ አሉ ሴትዮዋ በእናትነት ለዛ ።
ከዛ በዃላ ነበር ሀኒ ጓዟን ጠቅልላ ከደሴ ወደ ደብረዘይት አባቷ ጋር የሄደችው ያን ቀን አብረን አድረን ነበር የሼኜዃት እሷን ሼኝቼ ስመለስ የተሰማኝን የብቼኝነት ስሜት እና ባዶነት እንዲህ በቀላሉ በቃል የምገልፅበት ቃልም አልነበረኝም ዳግም የምንገናኝ ሁላ አልመስልህ እስኪለኝ ሆዴ ተላወሰ ለካ ኤርፖርት ላይ ሰው ተቃቅፎ እንደዛ የሚላቀሰው ወዶ አይደለም ከሚወዱት ለቀናትም ቢሆን መለየት ምን ያክል እንደሆነ ስሜቱ የገባኝ በዛን ሰሞን ነበር ። ከሀኒ ጋር ወዲያው ወዲያው ብንደዋወልም በቃ ደርሳ ትናፍቀኛለች ያ ሳቋ ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል ።
አንድ ምሽት ከሀኒ ጋር ተደዋውለን እያወራን አዲሷን እናቴን እኮ የምተዋወቅበት ቀን ነገ ነው ደስ አይልም ደሞ ሳልነግርህ ድርሰቱ ወደ ፊልም እስክሪፕት ተቀይሮ በቅርብ ግዜ ቀረፃው እንደሚጀመርም አጎቴ ነገረኝ ስትል ፍፁም በሚያስታውቅ ደስታ ፍልቅልቅ እያለች አወራችልኝ እኔም የደስታዋ ተካፋይ ለመሆን የአባቷ ትውውቅ ላይ ባልገኝ እንኳ ፊልሙ ሲመረቅ ግን በአካል ቦታው ድረስ እንደምገኝ ቃል ገባሁላት በጣም ደስ ይለኛል ነገ በጧት ለስራ ተነስቼ ጉድ ጉድ ማለት ስላለብኝ በግዜ ልተኛልህ እወድሀለሁ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ
በሚቀጥለው ቀን እህቴና ሀዩ ባሉበት ቁጭ ብለን ቡና እየጠጣን ነው እህቴና ሀዩ ሀኒ ከሄደች በዃላ እኔ ላይ በሚያዩት ድብርት መቀለድ እና መጠቋቆም ከጀመሩ ቆይተዋል የዚች የቆንጆ ጦስ መቼም ሂዳም አለቀቀህማ ትለኛለች እህቴ ሀዩ ግን እህቴ ጋር ስትሆን አብራ ብትቀልድም ለብቻዋ ስትሆን ግን በቻለችው ሁላ ፈታ እንድል የማታደርገው ጥረት አልነበረም በቀልዳቼው መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ ሀኒ ነበረች የአባቷን ሚስት በአካል የምትተዋወቅበት ቀን ዛሬ ስለሆነ አይመቻትም ብየ አልደወልኩላትም ነበር አነሳሁትና እንደሁልግዜው ቆንጆዋ አልኳት ድምፆ የቀዘቀዘ ነበር ምንድነው ድምፅሽ ደህና አይደለሽም እንዴ ሀኒ ስል ጠየኳት ምንም ሳትመልስልኝ የእናትህ ስም ማን ነበር ያልከኝ ስታስተዋውቀኝ የሚል ደረቅ ጥያቄ አስከተለች ከምናወራው ጋር ምን አገናኘው እያልኩ በውስጤ የእናቴን ስም ነገርኳት በዛው በቀዘቀዘ ድምፆ እሺ ብቻ ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ግራ እየተጋባሁ ደወልኩላት አይነሳም ደገምኩት ቴክስትም ላኩኝ ምንም ምላሽ የለም ይባስ ብሎ ስልኳ ጠፍ በእህቴ ስልክም ሞከርኩ ጥሪ አይቀበልም ነው የሚለው ከቀን ጀምሮ ምሽት ስድስት ሰአት እስከሚሆን እየቆየሁ ብሞክርም ስልኳ ግን አሁንም ያው ነው አሁንም አይሰራም ያን ሌት እንዲሁ ስገላበጥ ሀሳብ ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ የሚባል በአይኔ ሳይዞር ነጋ ከአልጋየ እንደተነሳሁም የመጀመሪያ ስራየ ምን አልባት ከሰራ በሚል ወደ ሀኒ መደወል ነበር ምን ዋጋ አለው እንደማታው ነው ጥሪ አይቀበልም ። አንዳንዴ ከሆነው አልያም ከደረሰብን ነገር በላይ እጅጉን ሰላም የሚነሳን እና ውስጣችንን እረፍት የሚነሳው ለምን እና እንዴት ሆነ የሚለው ነገር ነው እኔም አሁን ያ ስሜት ነው የሚሰማኝ ስልኩን ስለዘጋችብኝ ወይ ስላጠፋችው ብቻ ሳይሆን ለምን ያ ሆነ ? እንዴት የእናቴን ስም ጠየቀችኝ ? በቃ ውዝግብግብ ያለ ነገር ሆነብኝ በመሀል ደሞ አንዳች ነገር ገጥሟት ይሆን እንዴ እያልኩ እጨነቃለሁ በደስታዋ ቀን ላይ እንደዛ የመቀዛቀዟ የመረበሿ ነገር ደግሞ ሌላ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው ። እህቴ ቁርስ ሰርታ እኔን እየጠበቀች ነው እኔ ደግሞ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እኔ እቆያለሁ ብያት ከቤት ወጣሁ ወደየት እንደምሄድ ግን አላውቅም እንደ እብድ ብቻየን አወራለሁ በእህቷ ስልክ እንኳ እንዳልደውል የእህቷን ስልክ አላውቀውም አንዲህ ባለ ሁኔታ ነገር እያብሰለሰልኩ ከእንቅልፍ እንደተጣላሁ የሀኒ ስልክም እንደተዘጋ ሶስት ቀን ሞላኝ ከዚ በላይ ግን የውስጤን ጥያቄ ሳልመልስ የሀኒንም ሁኔታ ሳላቅ ታግሶ መቆየት አልቻልኩም የሆነ ነገር መፍጠር እንዳለብኝ ወስኜ ከአልጋየ ተነሳሁ የሰሞኑ ሁኔታየ ከወትሮው የተለየባት እህቴ ከመኝታ ቤቴ መውጣቴን ጠብቃ ምንድነው የሆንከው አንተ ልጅ ስትል አስቁማ አፋጠጠችኝ ምንም እንዳልሆንኩ ላስመስል ብሞክርም በዛ ሁኔታ አልችልም ነበር የግዴን ያለውን ነገር አንድ በአንድ ከሄደችበት ምክኒያት አንስቶ ደውላ የእናታችንን ስም ጠይቃኝ ስልኩ እስከተዘጋበት ደረስ ያለውን ነገርኳት ለአፍታ አንገቷን አቀርቅራ ከቆየች በዃላ ከሰመመን እንደነቃ ሰው አይነት ብንን ብላ አባቷ ሚኖረው ደብረዘይት ነዋ ያልከኝ አለች አዎ ምነው አልኳት ፊቷ ላይ የተወሰነ ግራ የመጋባት አይነት ድንጋጤ አስተውያለሁ አይ ምንም ቆይ ታዲያ በሷ በኩል የምታቀው ሌላ ሰው የለም አንዴ ምን አልባት ያለችበትን ሁኔታ የሚነግርህ አልያም ሌላ ስልክ ካላት የሚሰጥህ አለችኝ እህቷን እና አንድ ጓደኛዋን ብቻ ነው የማቀው የሁለቱም ስልክ ደግሞ የለኝም የኔ መልስ ነበር ይሄን እያወራን ሀዩ እንዴት አደራችሁ ብላ ወደቤት ገባች ሁለታችንም ፊት ላይ መረበሽ ስላየች ምንድነው በጧቱ ቆዝማችዃልሳ ብላ ከእህቴ ጎን ተቀመጠች እኔ ካለሁበት ተነሳሁና የተጫጫነኝ ትንሽ ለቀቅ ቢያደርገኝ ብየ ወደሻወር ቤት ገባሁ እህቴና ሀዩና እዛው በተቀመጡበት ይንሾካሾካሉ የሻወር ቆይታየን ጨርሼ ስወጣ ቁርስ ቀርቦ ነበር ካልበላሁ ስለምትጨናነቅ ለእህቴ ስል እንደነገሩ ቀማመስኩና አንዳች ፊንጭ ባገኝ እንኳ እዛው እቤታቼው ድረስ መሄድ እንዳለብኝ ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደርሼ ከቤት ወጣሁ
98 viewsአምባ, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:34:33
ተከታተይ እወነተኛ ታሪክ ፍሌም የተሰኘው በቅርብ ቀን እንደሚጀምር ልናሳውቃችሁ እንወዳለን ታሪኩን በጣም እንደሚወዱት እርግጠኛ ነን ሙሉውን ታሪክ ለማግኘት ከስር በምታዮት ሊንክ ይቀላቀሉ

https://t.me/teztash
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash
98 viewsአምባ, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 12:21:19 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል


የመንገዳችን አቅጣጫ ያደረግነው ከደሴ በመነሳት በምእራብ ወረዳ በመካነ ሰላም በኩል ነበር እኔና ሀኒም የፍቅር ወጋችንን እየሰለቅን መርጦ ለማሪያም ፣ ግንደ ወይን፣ ከዛም ሞጣ እና አዴት የሚባሉ ከተሞቼን አንድ አንድ እያልን አልፈን በፅዳቷ የከተሞች ቁንጮ በመበል ከምትታወቀው የጣና ሀይቅ
መናገሻ ከሆነችው ውቢቷ ባህር ዳር ገባን እነዚህን እና ሌሎች ትናንሽ የከተማ ስሞችን ለማወቅ የቻልኩት በሀኒ አማካኝነት ነበር ,,
እውነትም ባህርዳር በወሬ እንደሰማሁላት ፅዱ ከተማ ናት በተለይ በመንገዶች መሀል በእንክብካቤ የተያዙት ዘንባባዎች ከተማዋን የተለየ ውበት አላብሰዋታል ማረፊያ ሆቴላችን ይዘን ጓዛችንን ካስቀመጥን በኻላ ፍሬሽ አሳችንን እና እጅ የሚያስቆረጥም ሽሯችንን እያጣጣምን ጉብኝታችንን ጀመርን
ባህርዳር ካሳለፍናቸው ቆይታዎች ውስጥ ብዙውን ምሽት ማለት ይቻላል ያሳለፍነው በባህል ምሽት ቤቶች ውስጥ ነበር ባህርዳር ከምትታወቅባቸው ብዙ ነገሮቿ ውስጥ አንዱ በባህል ምሽት ቤቶች ነው እኔና ሃኒም ቀን ቀን በተከራያናት ቪትዝ መኪና እና አንዳንዴም የከተማውን ባጃጆች በመጠቀም ስንዞር እንውልና መሸትሸት ሲል ወደ ባህል ምሽት ቤቱ ጎራ እንላለን የባህል ምሽት ቤቱ ባላገሩ ይሰኛል ከመግቢያው ጀምሮ ያለው የመስተንግዶ አቀባበል እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ደግሞ በኢትዮጵያ የባህላዊ መገልገያ እቃዎች በልዩ መልኩ ተውቦና አምሮ ይቀበልዎታል የቤቱ ማዓዘናት ላይ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የምንላቸው ማሲንቆ ክራር እና ዋሽንት ተሰቅለዋል ፊትለፊት ያለው ግድግዳ ላይ ደግሞ ለእይታ በሚስብ አይነት ተሰርተው ሞፈር እና ቀንበር፣ አጎዛ፣ ጋሻና ጦር ይስተዋላሉ አስተናጋጆቹ ሳይቀር ሴቶቹ ፀጉራቸውን ሹሩባ ተሠርተው ወገቡ ላይ በመቀነት ሸብ የተደረገ ሽንሽን ቀሚስ ለብሰዋል ወንዶቹ ደግሞ ከካኪ የተሰራ ተነፋነፍ ቦላሌ አድርገው በወጉ የተበጠረ ጎፈሬያቸው ላይ ሚዶ ማበጠሪያ ሰክተዋል በቤቱ ውስጥ የምሺቱን ጨዋታ ለመታደም ከገባው የከተሜ ሰው ውጪ አንድም ከተማን የሚመስል አልያም አሁን ላይ እኛ የስልጣኔ መገለጫ ብለን የምንጠራቸው ቁሶች ማየት ዘበት ነው በቃ ሙሉ የገጠሪቱ ኢትዮጵያን ድባብ የተላበሰ ነው። ይህ አይነት ስሜት የሚሰማኝ ድሮ ላይ ትምህርት ሲዘጋ ከገጠር ያሉት ዘመዶቼ ጋር ስሄድ ነበር በቃ ጎጆ ቤት አይሁን እንጂ ይሄም ገጠር እንዳሉት የዘመዶቼ ቤት ነው ሌላው በጣም የወደድኩት ነገር ቤቱ ውስጥ ምግብ ሲያዙ የሚቀርብልዎት በሞሰቦ ወርቅ ተደርጎ ነው የሚጠጣው ጠጅና ብርዝ ደግሞ በብርሌ ከኛ ፊትለፊት ባለው የመደብ መቀመጫ ላይ ሁለት ወንድና ሁለት ሴቶች በጋራ ሆነው በመሰቦ ወርቅ የቀረበላቸውን ማድ ከበዉ እየተቋደሱ ወዲህ ደግሞ የብርሌ ጠጃቸውን እየተጎነጩ ይስቃሉ ይጫወታሉ።
እኔም እየጠፋ ያለውን ተሰብስበው ለማድ አብሮ የመቀመጥን ባህል ስላሳዩኝ ደስ ብሎኛል በውስጤ ወድጃቸዋለው። እንደ ዛሬ ወቅቱም ሰውም ሳይከፋ በፊት ለብቻ ሆኖ ማድ መቀመጥ እንደ ነውር እንደሚታይ ገጠር ያለው አጎቴ ነግሮኝ እንደ ነበር በጣም አስታውሳለሁ በነገራችን ላይ ገጠር ያለው አጎቴ ሲበዛ ባህሉን የሚወድና የሚያከብር ያሁኑን ዘመን አመጣሽ የስልጣኔ መደናበር ደግሞ የሚጠየፍ ሰው ነው። እንደዛ የሆነው ገጠር ስለሚኖር አሊያም ገበሬ ስለሆነ ብቻ አይደለም እንደዛ ሚሠማው አሁን ላይ ባለው በብዙ ነገር ስለሚማረር ነው የገጠሩ አጎቴ በድሮው የትምህርት ስርዓት እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ ዘልቋል በዛ በቀሰማት የማንበብ ክህሎት በመነሳት ስለ ሐገሩና ስለ ባህሉ ሚጠቅሱትን ነገሮች ባገኘው አጋጣሚ ያነባል ጉዳይ ኖሮት ወደ ከተማ ከዘለቀም የዛ አይነት ይዘት ያላቸውን መጸሐፍት ከኔ ጋር አብረን ሆነን እንገዛና ይዞ ይሔዳል አመለካከቱና ነገሮችን የሚያይበት ይዘት ከተሜ ነን ከሚሉ ሰዎች እጅግ የላቀ ነው እኔም ገጠር እሔድ በነበረበት ግዜ ብዙውን ሰዓቴን የማሳልፈው ከሱ ጎን ቁጭ ብዬ ወሬዎቹን በማዳመጥ ነበር
የሆነ ግዜ ከሱ ጎጆ እሳት ዳር ሳለን በሌማት የቀረበ ቆሎ እየቆረጠምን በጋራ ተሰብስቦ ማድ ስለመቀመጥ ባህል እያወራልኝ ሳለ አንዴ የደረሰብኝን ገጠመኝ ላጫውትህ ብሎ የነገረኝን ሁሌም ነበር ባስታወስኩት ቁጥር የምስቀው እንዲህ ነው የሆነው, ,,ግዜው በጣም ቆይቷል የገጠሩ አጎቴ ለአንዲት ቀጠን ያለች ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ያመራና እዛ ያሉ ዘመዶቻችን ይቀበሉታል እንዳጋጣሚ የደረሰበት ሰአት ምሳ ሰአት ነበር እና ቡና እየተፈላ ተጠቅልሎ የተቆራረጠ እንጀራ ለየብቻቼው ሁነው በሰሀን በሰሀን ያነሳሉ የገጠሩ አጎቴ ደሞ ተሰብስቦ አብሮ ከመብላት ውጭ ሊያውም እንዲህ እንጀራ አራት አምስት ቦታ ተሸንሽኖ ለእያንዳንዱ ሰው ስለሚታደለው ወይም በእኔና በእናንተ አጠራር "የቁርጥ እንጀራ " ስለሚባለው ነገር የሚያቀው አንዳችም ነገር አልነበረውም ••••
እናላችሁ አንድ ሰሀን ያሲዙትና እንጀራ አንሳ ይሉታል የገጠሩ አጎቴም ያው እንደነገርኳችሁ ለነገሩ አዲስ ስለሆነና ቡናም እየተፈላ ስለነበር እንደነሱ ገጠር የቡና ቁርስ ይሆናል በሚል እሳቤ አንድ ቁራጭ እንጀራ አንስቶ ሰሀኑን ዘወር ያደርጋል ጨምር ቢሉት ደሞ ለቡና ቁርስ ይሄ ምን አነሰው ብሎ በሆዱ ይበቃኛል ሲል ድርቅ ይላል ያጎቴን አሻፈረኝ ማለት ያሰሙት ከተሜ ዘመዶቻችንም መንገድ ላይ በልቶ ይሆናል በሚል ይተውታል እሱም ያችን አንድ ንጣይ እንጀራ ቀምሶ ቡናውን ይጠጣና ይጨርሳል እነሱም የተበላበትን የምግብ እቃና የቡና ረከቦት አነሳስተው ቴሌቪዥን ይከፍቱለትና ተጫዎት ብለውት ወደየ ፊናቼው ይሰማራሉ መንገድ ያንገላታው ሚስኪኑ የገጠሩ አጎቴ ካሁን አሁን ምሳ ይቀርባል እያለ ቢያማትር ቢያማትር ከወዴት መጥቶ ያነሳት ቁራሽ እንጀራ በምሳ ስም የተሰየመች መሆኗን ያወቀው ማታም ለእራት በምሳው መልኩ ሲያቀርቡለት ነበር ቡና ቁርስ ብሎ ተሸውዶ ምሳውን ሳይበላ በራበው ሆድ የቆየው የገጠሩ አጎቴ ብልጥ ያለ አንድየ አይበለጥ ብሎ እራት ላይ ያነሳውን የቁርጥ እንጀራ ብዛት ብነግራችሁ እናንተም ትታዘቡታላችሁ ። እዛው በተቀመጥኩበት የገጠሩን አጎቴን በሀሳቤ ሳልኩና ፈገግ አልኩ የባህል ምሽት ቤቱ ጨዋታ በደንብ መድመቅ ሚጀምረው እና የሚደራው ከሁለት ሰአት በዃላ ነው እኔና ሀኒም ያረፍንበት ሆቴል ካለንበት ብዙም ስለማይርቅ ስለሰአቱ መምሸት ምንም አናስብም ሁሉም በየመቀመጫቼው የሚጠጡትን ይዘው ተቀምጠዋል ብዙወቹ ጥንዶች ቢሆኑም ለብቻቼው ሁነው የገቡም አሉ እኔና ሀኒም በብርሌ የቀረበልንን የብርሌ ጠጅ እየተጎነጨን መሀል ላይ ቁመው ጨዋታውን በሚያከፋፍሉት እንድ ወንድ እና አንድ ሴት አዝማሪ ላይ ፈጠናል መቼም ጨዋታው ለጉድ ነው ተቀበል ይልና አንዱ ለአዝማሪው በቅኔ የታሼ ግጥም ይወረውራል ወዲያው ደሞ ከሌላኛው በኩል ሌላ ግጥም ይወረውራል ሚስቱ ጋር የገባው ለሚስቱ ያስገጥማል ሴቷም አንዲሁ ባሏን ማሞገሻ የሚሆን ቃላትን ሰድራ ታቀርባለች ፣ ፍቅረኛሞችም ፍቅራቼውን በግጥም ያፈኩታል በዛው ልክ የከፋውና , ከሚስቱ ወይ ከፍቅረኛው ጋር ተጣልቶ መጥቶ የሆዱን ብሶት በግጥም የሚተነፍስም ዕልፍ ነው የአዝማሪዎቹ ግንባር ላይ ባለ ሀምሳና ባለ መቶ ብር ኖቶች በሽልማት መልክ ወዲያው ወዲያው ይለጠፋሉ ከዛማ ምን አለ ቤቱ በሳቅና ጨዋታ ባንድ እግሩ ይቆማል የብርሌዋ ጠጅ ስራዋን ሰራች መሰል እኔም አስገጥም አስገጥም የሚል አንዳች የግጥም መንፈስ ንሽጥ ተቀበል አልኩ ማን ከማን ያንሳል
99 viewsአምባ, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 11:30:32 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ሀኒ ምንድነው እየደማሽ ነውኮ አልኩ በመጮህ ደንግጨ ነበር እሷ ግን ፍፁም መረጋጋት በሞላበት ሁኔታ ነስር ነው አንዳንዴ እንዲህ ይመጣበታል አለች ጎኗ ካለ ፖርሳዋ ሶፍት እያወጣች የመጅልሲ ትራስ ላይ እራሷን አስደግፌላት ውሀ እና ማስታጠቢያ ላመጣ ሄድኩ ከዛም የሀኒን የደማ አፍንጫ በሶፍትና በውሀ ተጋግዘን አፀዳነው ደሙም ምንም ያህል አልቆየም ወዲያው አቆመላት እና በአዲስ መንፈስ ተረጋግታ ቁጭ አለች አስደነገጥሽኝኮ አልኳት ግንባሯን እየሳምኳት ነስር አለብኝ ግን እየቆየም ቢሆን የሚመጣው ብዙውን ግዜ የሚያነስረኝ በተኛሁበት ነው ቀን ላይ ግን አያቀኝም ነበር የኔ አሳቢ አለች በል አሁን ጆሮየን አቁሜ የንተን እና የቤተሰብህን ታሪክ ለመስማት እየጠበኩ ነው ምንድነው ማረሳሳት አለችኝ ኧረ ምን ቼገረሽ ያው እኔ ከዚ በፊት የሚነገር ታሪክ የለኝም ታሪኬ የሚጀምረው አንቺን ካገኜሁበት ሰአት ጀምሮ ነው ስለቤተሰቡ ግን ልንገርሽ ቆይ እንደውም በደምብ ግልፅ እንዲሆንልሽ በፎቶ የታገዘ ገለፃ ላድርግልሽ አልኳትና ከቴሌቪዥን ማስቀመጫ ስር ያለውን አልበም ወደኛ አቀረብኩትና ቤተሰቤን ለሀኒ ማስተዋወቅ ጀመርኩ
እኔ ለቤተሰቤ ሶስተኛ ልጅ እንደሆንኩና ከኔ በላይ አንድ ትልቅ ወንድም እንዳለኝ ከኔ በታች ደግሞ ያለችው አሁን የየሻት እህታችን ናት አልኳት የሆነ የበአል እለት እኔ ትልቁ ወንድሜና እህቴ ሆነን የተነሳነውን ፎቶ እያሳየኋት ወንድምህም እንደ እናንተ ቆንጆ ነው አለችኝ ሃኒ በፈገግታ
ቀጠልኩና አዎ ያኔ ቁንጅና ሲታደል የኛ ቤተሰብ የመጀመሪያ ሰልፍላይ ከፊት ተሰልፎ እንደነበር አያቴ አውርታኛለች አልኳት አብረን ሁለታችንም ሳቅን ,, ቀጠልኩናም እናቴና አባቴ አብረውን ያሉበትን ፎቶ እያሳየኋት እነዚህ ደግሞ እኛን የመሰሉ ቆንጆዎን ወደዚች ምድር ያመጡን እናትና አባትችን ናቸው። ከዛሬ ስድስት አመት በፊት ነበር የተለያዩት
እያልኩ ሃኒ በመሃል ገብታ በጣም አዝናለው አለችኝ ፊቷን ሳየው መረበሿ ይስተዋልባታል
ምንአልባት የሷም ቤተሰብ ልክ እደኛው አይነት ስለሆነ ስሜቱ ተጋብቶባት እንደ ሆነ ገምቻለው በጣም የሚገርመው ግን የኔ የቤተሰብ መለያየት አባዜ ምክኒያቱ ይለያይ ይሆናል እንጂ የብዙ ቤተሰቦችን ጓዳ ያንኳኳ ጉዳይ ነው የኛ እንኳ ትልቅ ከሆንን እና ክፉ ደጉን ከለየን የሆነ ነው አንዳንዶች ግን ገና በልጅነታቸው በእናትና በአባት መለያየት ኑሯቸው ብልሽትሽት ብሎ አንዴ በእናት ናፍቆት ሌላ ግዜ ደግሞ በአባት ናፍቆት እየተሰቃዩ በጨቅላነታቸው ማግኘት ያለባቸውን የቤተሰብ ፍቅር ሳያገኙ ያድጋሉ
ያ ነገር ከፍ እያሉ ሲመጡ ውስጣቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦና ጫና ፈጥሮባቸው ከማህበረሰቡ እራሳቸውን አግልለው የብቸኝነት ሂይወት የሚገፉ እልፍ ናቸው እናትም አባታችሁም አሁንም አብረዋችሁ ያላችሁ የእውነት በጣም እድለኛ ናችው
ግን በምን ምክኒያት ነው የተለያዩት ስትል ከሃሳቤ መለሰችኝ በትዝታ የኋሊት ገሰገስኩና አስታወስኩ ያኔ አባቴ በፈቃድ ጅዳ እየተመላለሰ አልባሳትን እና ሽቶዎችን እንዲሁም የ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በማምጣት የንግድ ስራዎችን ነበር የሚሰራው እዛ በሚሄድበት ግዜ አስራአምስት ቀን ገፋ ካለም አንድ ወር እየቆየ ነበር የሚመጣው ይህ ሲሆን ለካ አባቴ በስራ ምክኒያት ካወቃት መኖሪያዋን እዛው ካደረገች ኢትዮጵያዊት ጋር ጉዳይ ጀምሮ ነበር ይሄንን ማናችንም የምናውቀው ነገር አልነበረም ቆይቶ ግን እዛው ባሉ ዘመዶች አማካኝነት ወሬው እናቴ ጆሮ ይደርሳል ከዛ በኋላ ነው ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በሽማግሌ በዘመድ አዝማድ ብትለመን በአንገቴ ገመድ ይግባ ብላ በቃሏ ጸናች አባቴ ሁለት ሚስት የማግባት ፍላጎት እንደ ነበረው ሁላችንም ብናውቅም እንደዚህ በተደባበቀ መልኩ ያደርገዋል የሚል ለአንድም ቀን ጠርጥረን አናውቅም በቃ ሁሉም ያኔ አለቀ ከተለያዩ በኋላ እናቴ አዲስ አበባ ካለች እህቷ ጋር ለኛ ደግሞ አክስታችን ማለት ነው ከሷ ጋር በጋራ ግዙፍ የሚባል ሱፐርማርኬት ከፍተው መስራት ጀመሩ አባቴም ነገር ቁርጡ ከለየለት በኋላ ከዛችኛዋ ጋር አምርሮ መኖር ጀመረ ከዛም ከእህቴና ከወንድሜ ጋር በሰራተኛ መኖር ጀመርን ብዙም ሳይቆይ ትልቁ ወንድሜ በስራ ምክኒያት ወደ ሌላ ሀገር ተዘዋወረ
ከዛም ይኸው እኔና እህቴ አብረን እንኖራለን
አልፎ አልፎና አመት በዓል ሲመጣ አባታችን ቤት እንሔዳለን ከዛ ውጭ ግን በቃ ደስተኞች ነን ያው አንዳንዴ የሆኑ የሆኑ ነገሮች ያለፈውን ሲያስታውሱሽ ትንሽም ቢሆን መከፋት ቢኖረውም ማለት ነው አልኳት አልበሙን እየዘጋሁ እናትህ ለራሱ ገና ወጣት አይደለች እንዴ አለችኝ በመገረም አይነት ኧረ እንደውም አዲስ አበባ ከገባች በኋላ ፋዘርን ለማስቀናት ነው መሰል በጣም በተለየ መልኩ እራሷን እየጠበቀች ዳግም ፍንዳታ ሆናልኛለች ተሳሳቅን, , በዚህ መልኩ የማስተዋወቅ ስራዬን ጨርሼ ከኛ ቤት ወጥተን ትንሽ ወክ ካደረግን በኋላ ሃኒን ወደ ቤቷ ሸኝቻት ወደ ቤት ተመለስኩ።
እቤት ስገባ ሀዩ ቤት ተቀምጠው ነበር
የውሃ ማስጣጠቢያው ላይ የነበረውን ደም የነካ ሶፍት አይታ ምንድንነው ይሄ ጉድ አለቺኝ
ሃኒን ነስሯት እደሆነ ነገርኳት ከዚህ በፊት ፖስታው ላይ የነበረውን ነገር ነግሬያት ስለነበር ከህመሟ ጋር አስተያይታው ኖሮ በጣም ደንግጣ እንደ ነበር ነገረቺኝ ለካ እህቴ የትናንቱን ተሪክ አልሰማችም ሁሉንም ዘርዝሬ ለእህቴም ለሀዩም አወራሁላቸው ደብዳቤው ላይ የነበረው የህክምና ውጤት የጓደኛዋ እንደ ነበርና እሷም ከሞተች እንደቆየች ሃኒም ከደብረዘይት አባቷን ትታ የመጣችው በጓደኛዋ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ድርሰት አዘጋጅታ መታሰቢያነቱ ለጓደኛዋ ገቢው ደግሞ ለጓደኛዋ እናት የሚሆን ፊልም ለማዘጋጀት እንደመጣች ጨምሬ አወራሁላቸው። እና በቃ ግንኙነታቹ ፀደቀ ማለት ነው አለችኝ እህቴ በጥያቄ ቃና ሀዩ ፊቷን ክስክስ አድርጋው ከተቀመጠችበት ተነሳችና ምንም ሳትል ወጣች ምን ሆናነው ሀዩ? እህቴን ጠየኳት ኧረ እኔንጃ ብላኝ ሀዩ በወጣችበት በኩል ተከትላት ወጣች
ቀናቶች በቀናት ሳምንታት በሳምንት እየተተኩ በመክነፍ ላይ ናቸው እኔና ሃኒም ፍቅራችን ጨምሯል ቶሎ ቶሎ እንገናኛለን በጓደኛዋ ዙሪያ ያለው ድርሰትም እየጻፍን ከመቋጫው ላይ አደረስነው ያው ሃኒም የአርት ተማሪ ስለነበረች ምንም ያህል ሳያስቸግራት ነበር በጥሩ ሁኔታ ተጽፎ የተገባደደው አንድ እሁድ ቀን ሃኒ ምሳ እየጋበዘችኝ ድንገት አንድ ሰርፕራይዝ አለኝ አለችኝ ምንድንነው እሱ የኔ ጥያቄ ነበር የድርሰቱን መጠናቀቅ ምክኒያት በማድረግ አባቴ ጋር ከመመለሴ በፊት ሙሉ ወጪውን ሸፍኜ የአንድ ሳምንት የባህርዳር የጉብኝት እንዲኖረን ፈልጌያለው አለችኝ መልሴን ለመስማት እንደ ጓጓች ከፊቷ ላይ ያስታውቃል በጣም ነበር ሀሳቡን የወደድኩት ባህርዳርን ከዚህ በፊት ሂጄባት ባላውቅም በወሬ ደረጃ ግን ብዙ ብዙ ሰምቼላታለው በዛላይ ደግሞ ከሃኒ ጋር ታየኝ ካሁኑ የትም ይመቸኛል አልኩ በውስጤ
እ... ምን ታስባለህ አለች ሃኒ ዝምታዬን አስተውላ በደስታ እንደተስማማሁ ገለጽኩላት እና ከሶስት ቀናት በኋላ የመኪና ኪራይ አመቻችተን ልንሄድ ተስማምተን ጨረስን በቀሩት ሶስት ቀናቶች ውስጥ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በሙሉ ከውነን ጉዞ ወደ ውቢቷ ባህርዳር ተጀመረ •••

ይቀጥላል
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለteztash
ttps://t.me/teztash
https://t.me/teztash

✎ ክፍል 17 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

@rediy21
90 viewsአምባ, edited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:18:24 ለጠየኩት ጥያቄ ከሱ የተመለሰልኝ መልስ ግን እንዲህ ነበር እዛው ታክሲዋ ውስጥ ሳለን አንዴት ግን ያ እኔ ማቀው ናቲ ያቺንም ያቺንም ቆንጆ ከመልከፍ ታቅቦ አንዲት ልጅ ጋር ለዛውም በአጭር ግዜ ውስጥ በፍቅር ክንፍ ብሎ ለትዳር ማሰብ በቃ ስል ጠየኩት ናቲ ወደ ዃላው ለጠጥ ብሎ በምቾት ተቀመጠና አየህ ቆንጆ ስለሆንክ ወይ ቆንጆ ስላሳደድክ አይደለም ቁምነገሩ ፍቅር አንተ ስለፈለክ የምታመጣው አንተ ስለሼሼህ የምትሼሼው ነገር አይደለም
እርስ በርስ መዋደድ እና መፈላለግም ብቻውን ፍቅር ሚመስላቼው ብዙ ናቼው ግን ያ አይደለም፣ ማሬ ውዴ ሂወቴ መባባልም ሆነ ጥንድ ሁኖ አብሮ መቆየትም ብቻውን ፍቅርን ሊሆን አይችልም። ፍቅር ፍፁም ጥልቅ እውነት ነው ፍፁም እውነት ደሞ ፈጣሪ ብቻ ነው ስለዚህ ለኛም እውነተኛ ፍቅር ሊሆን የሚችለው ከላይ ከአንድየ የሚፃፍልን ብቻና ብቻ ነው ከዛ ውጭ ያለው እኛ በተለምዶ ወይም በኛ ጭላንጭላዊ እይታ ፍቅር እያልን የምንጠራው በጋራ ጥቅም የተሳሰረ አንዱ ባንዱ ላይ ጥገኛ ሁኖ የመኖርን ሁናቴ ነው ። ፍቅር መሰጠት ነው በቃ የተሰጠህን ስታገኝ ያንተን ሰው ስታገኝ ሁሉንም ነገር ትተዋለህ ሌላ አዲስ ሰው ትሆናለህ ደሞ ነገ ከማን ጋር ምን እንደሚኖርህ ምን እንደሚገጥምህ አንተ ብቻ ሳትሆን ሂዎትም አብራ ነው የምቶስነው በፍቅር አምስትና ስድስት አመት አብረው ቆይተው በስተመጨረሻ ግን እሷም ሌላ አግብታ እሱም ሌላ አግብቶ ለየቅል ጎጆ ኗሪ የሆኑትን ቤት ይቁጠራቼው በዛው ልክ ደግሞ በተዋወቁ በጥቂት ግዚያት ውስጥ ተጋብተው ወልደው ከብደው የሚኖሩ ብዙዎች ናቼው ለዛም ነው ፍቅር እና አብሮነት መሰጠት ነው ያለኩህ እንግዲህ ሜሮንም ለኔ የተሰጠች የሂዎት ስጦታ ሁና ይሆናላ ብሎ በፈገግታ ዙሮ አየኝ ምንም አልተናገርኩም ነበር በናቲ መልስ ተገርሜ ፀጥ አልኩ ዛሬ ያሁሉ አልፎ ናቲ ከሜሮን ጋር ተጋብቶ የሁለት ሴት ልጆች የአባትነት ማዕረግ ጋር በደስታ እየኖረ ይገኛል ። እውነትም ፍቅር መሰጠት ነው ሀኒስ ለኔ የተፃፈች እና ከላይ የተሰጠች ሴት ትሆን? ራሴን ጠየኩ መለስ ግን የለኝም ነበር የነገን ነገ ራሱ ያውቀዋል ፣ ሂዎት ራሱ መልስ ይሰጥበታል
በማላቀው የነገ ጥያቄ ዛሬየን ለምን አጨናንቃለሁ ስል ለራሴ ሹክ አልኩት ። እህቴ ጋር ላለብን የምሳ ግብዣ በሰአቱ ለመገኜት እኔና ሀኒ ከፎቶ ቤት ወጥተን መንገዳችንን ወደኛ ቤት አቅጣጫ አድርገናል በዚህ መሀል ከኪሴ ውስጥ ያለው ስልኬ አዲስ መልእክት መግባቱን የሚያበስር ንዝረት ነዘረኝ ሀኒን አቅፎ የነበረውን እጄን ከትከሻዋ ላይ አወረድኩና ስልኬን አወጣሁ እና መልክቱን ከፈትኩት አዲስ ቁጥር ነው ከዚ በፊት አላቀውም ቁጥሩን ተውኩና መልክቱን አነበብኩ " አብራህ ስላለችው ልጅ ምን ያህል ታውቃለህ " ነበር የሚለው •••••

ይቀጥላል...
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ lemagegnit
@rediy21

✎ ክፍል 16 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።


100 viewsአምባ, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:16:29 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ፎቶ ቤት ውስጥ ገብተን የተወሰኑ ፎቶዎችን ለማስታዎሻነት ተናሳን እውነት ለመናገር በኔበኩል ምንም ሀሳቡ አልመጣልኝም ነበር የሀኒ ምርጫ ነበር ።ፎቶ ቤቱ ለቀን ከወጣን በዃላ ለምን እንድንነሳ ፈለግሽ አልኳት በስስት አይኗን እያየሁ ዛሬኮ ለኛ የተለየች ቀን ናት በተለይ ለኔ ጥልቅ ትርጉም የያዘች ቀን ናት እኔን በኔነቴ ብቻ የሚወደኝ፣ የሚሳሳልኝ፣ ለደስታየ የሚጨነቅ፣ ከነበርኩበት የትካዜ ስሜት በቀላሉ እንድወጣ ያደረገኝን ሰው ከጎኔ አድርጊያለሁ ከዚህ በላይ ታዲያ ምን የሚያስደስት ነገር አለ አለችኝ የሀኒ ለኔ ያላት ስሜት በዚህ መልኩ መሆኑ ለኔም ጥልቅ ደስታ የሚሰጥ ነገር ነው ምክኒያቱም በጣም እወዳታለሁ ። ይገርማል ግን የፍቅር ግንኙነት እንዴት እና በምን አጋጣሚ ተጀመሮ እስከምን እንደሚዘልቅ ፍፃሜውስ ምን ይሆን ማናችንም ምናውቀው ነገር የለም አንዳንዶች በተሳሳተ የስልክ ጥሪ ተዋውቀው ለአብሮነት ይበቃሉ፣ አንዳንዶች ደሞ በመስሪያ ቤት እና በትምህርት ቤት ፣ አንዳንዶች ደሞ ሰርግ ላይ፣ ሌሎች ደሞ በዘመድ እና በጓደኛ ትውውቅ በሌላ ጎን ደሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በፌስቡክ በዋትሳፕ ሀይ ብለው ጀምረው እስከ ሀይ ሎጋ የደረሱም በጣም ዕልፍ ናቼው እንደውም በዚህ አጋጣሚ የአንድ ቅርብ ጓደኛየን የፍቅር አጋጣሚ ላውራላችሁ ለኔ ትልቅ ትምህርት ያገኜሁበት ስለሆነ ሁሌም የዚህ አይነት ነገር ሲነሳ ትውስ ይለኛል ጓደኛየ ናቲ ይባላል የታክሲ ሹፌር ነው በጣም ሲበዛ መልከ መልካም እና ተጫዋች ነው ወሬው እና ቀልዱ አይደለም ሴት ልጅን ወንድን እንኳ በቀላሉ ያለምዳል በቃ ምን አለፍችሁ ምላሱ በረዶ ይቆላል ወክ ስናደርግ ፣ ወይ መዝናኛ ቦታ አልያም በሆነ አጋጣሚ አብረን ሁነን ቆንጆ ሴት ቦታው ላይ ከተገኜች ከሁላችንም በፊት ናቲን ነው ቀድመን የምንልከው ናቲ ሂዶ አወራት ማለት ደሞ በቃ የሆነ ታሪክ እንደሚፈጠር እሙን ነው ለናቲ ከሴት ጋር በጓደኝነት መልኩ አብሮ መቆየት የሚባል ነገር አይታሰብም በቃ ባገኜው አጋጣሚ ቆንጆዎችን ማሳደድ ነው ስራው ለምን አንድ ሴት መርጠህ ከሷ ጋር አትሆንም ሲባል ለኔ የምትሆነው ሴት ገና አልተረገዘችም ይላል የሆነ ግዜ በስራ ምክኒያት ሌላ ሀገር በመሄዴ ከናቲ ጋር በስልክ እንጂ በአካል አንገናኝም ነበር የሆነ ቀን ምሽት ናቲ ደወለልኝ እና እንደተለመደው እየተዛዛግን ትንሽ አወራን ከዛም ዛሬ ለቁም ነገር ነው የደወልኩት አለኝ ድምፁን ለወጥ አድርጎ እሺ የምን ቁምነገር ነው ስል እኔም መልሼ ጠየኩት እንደወረደ ላገባ ነው አለኝ ናቲ በጣም ነበር የሳኩት ምንድን ነው የምታገባው መልሼ ጠየኩት አሁንም ከሳቄ አልተፋታሁም ከሰሞኑ ስንደዋወል የሆነ ፎንቃ ቢጤ ሳይገባልኝ አይቀርም እያለኝ እንደነበረ ባስታውስም እኔ ማቀው ናቲ ፣ ከሴት ጋር አንድ ሳምንት እንኳ በቅጡ የማይቆየው ናቲ፣ ቆንጆ አሳዳጁ ናቲ አንዲት ሴት መርጦ ሊያውም በዚ ፍጥነት አግብቶ እስከመጨረሻው ከሷ ጋር ብቻ ሊሆን የሚለው ፈፅሞ አልተዋጠልኝም,, ምን አገባለሁ ሚስት ነዋ አለኝ እና አስከትሎም ምን ያስገለፍጥሀል አለኝ በሳቄ እንደተናደደ ያሳብቅበታል እኔም ነገሩ እንዳሰብኩት ቀልድ እንዳልሆነ ተረዳሁና እሺ ማንን ነው የምታገባው መችስ ነው የምታገባው ስል ጠንከር ባለ ድምፅ ጠየኩት ልጅቱን በአካል ባላቃትም ያቺ ከሰሞኑ ሲነግረኝ የነበረችው ልጅ እንደሆነችና ሌላውን ነገር ደሞ ስትመጣ ትደርስበታለህ ለማንኛውም ቀለል ያለ ሰርግ በቅርብ አስበናል ሚዜ መሆንህን አስብበት ከቻልክ ቀደም ብለህ ብትመጣ ደስ ይለኛል ሲል አበሰረኝ አንተ እንደዚህ ቁምነገረኛ ሁነህ አግባልኝ እንጂ ውየ አላድርም ስመጣ ብየው አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮች አውርተን ስልኩ ተዘጋ በውስጤ ምን አይነት ቆንጆ ሴት ትሆን ናቲን እንደዚህ በቶሎ ያንበረከከችው እያልኩ እያሰብኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ። ከዛ በዃላ ብዙም ቀን አልቆየሁም ነበር ለናቲ ሰርግ ካለሁበት ስሄድ ሚገርመው ከሰርጉ በላይ ናቲ ሚያገባትን ሴት ማየቱ አጓጉቶኝ ነበር አሷን ለኔ ከማስተዋወቁ በፊት የተገናኙበትን አጋጣሚ ነበር ያወጋልኝ እንዲህ ነበር የሆነው የሆነ ቀን እንደተለመደው ስራው ላይ ሁኖ እያሽከረከረ ሌላ የቆመ መኪና ተደርባ መንገድ ልታቋርጥ ያለች ልጅ ትገባበታለች በድንጋጤ
እንደምንም ያለ ሀይሉን ተጠቅሞ የታክሲዋን መሪ ከሷ ተቃራኒ ጠምዝዞ ከመገጨት ሊያድናት ሞከረ ነገር ግን የመኪናው ጫፍ ጎኗን አገኝቷት ኑሮ ከአስፓልቱ ላይ እንደምንጣፍ ተዘረጋች እሱ ሲነግረኝ እንዳወዳደቋ አሱም ሆነ ሌሎች ተሳፋሪዎች በቀላሉ ትተርፋለች ያለ አልነበረም ወዲያው እሷን ከወደቀችበት አንስቶ ወደ ሆስፒታል ይወስዳታል ። ከምርመራው ውጤት በዃላ የአጥንት ቅጥቅጣት ስላገኛት ተኝታ መታከም እንደሚኖርባት ተወስኖ በዛው ሆስፒታል ለተወሰኑ ቀኖች ትቆያለች ናቲም አንዴ ብቻውን አንዴ ደሞ ከእህቱ ጋር በመሆን እየተመላለሰ ልጅቱን መጠየቅ ይጀምራል እንግዲህ በዚህ መሀል ነው ናቲ ከገጫት ልጅ ጋር አንድ አንድ እያሉ መግባባት የጀመሩት "አጋጣሚ አቃጣሪ አይደል" ልጅቱ ከህመሟ አገግማ የሆስፒታል ቆይታዋን ጨርሳ ከወጣች በዃላም እቤቷ ድረስ እየሄደ መጠየቁን አላቆመም ነበር እያለ እያለ እሷም ከቤት መውጣት እና ከናቲ ጋር መገናኜት ጀመረች ያን የማይጠገብ ጨዋታውን አንዴ አይታስ እንዴት ትቀራለች ያ ቆንጆ አሳዳጁ ናቲም በገጫት ልጅ የፍቅር ገመድ ተጠፍንጎ ታስሮ ያን ባህሪውን በመተው ለትዳር እንደወሰነ ዘርዝሮ አጫወተኝ
ይሄን ባጫወተኝ በሁለተኛው ቀን ከልጅቷም ጋር በአካል አስተዋወቀኝ ሜሮን ትባላለች እውነቱን ለመናገር የመልኳ ነገር እንዳየዃት አስደንግጦኛል ጭራሽ እኔ ከናቲ የበፊት ምርጫው ተነስቼ ጠብቄው የነበረው መልክ እና አሁን ያየሁት ፍፁም ተቃራኒ ነበር ባጭሩ ወሬ ሳላንዛዛ ልንገራችሁ "አታምርም" በተለተይ ከናቲ ጋር ሲተያዩማ መግለፅም ይቸግራል ፍቅር እውር ነው የሚባለው ለካ በሆነ ጎኑ እውነታ አለው ከትውውቁ በዃላ እሷን እቤቷ ደረስ ሼኝተናት እየተመለስን እንዴት አየሀት ሜሪን ሲል ጠየቀኝ እኔ ደሞ ባህሪየ ሁኖ ሰውየው ደስ እንዲለው ብየ የሌለን ነገር አስመስየ ወይ ዋሽቼ መናገር አያቀኝም ናቲም ቢሆን ይሄን ባህሪየን አስረግጦ ያቀዋል መልኳን ከሱ ምርጫ አንፃር እኔ ጠብቄው እንደነበረው እንዳላገኜሁት ነገር ግን እሱን እስከትዳር ድረስ እንዲያስብ ማድረግ መቻሏ አንድ እኔ ማላቀው የተለየ የሴትነት ጥበብ ያላት ሴት እንደምትሆን ነገርኩት የታክሲዋን መሪ በጁ እየመታ በጣም ሳቀና ለዚህኮ ነው የምወድህ አለኝ እንዴት ስል ጠየኩት አየህ ሌላ ሰው ቢሆን በጣም ቆንጆ ናት ምናምን እያለ እኔን ደስ ለማሰኜት ይደሰኩር ነበር አንተ ግን እቅጯን አለኝ እና መልሶ የቅድሙን ሳቅ ደገመው ። ሜሪ ቆንጆ ምትባል ሴት እንዳልሆነች እኔም አውቃለሁ ነገር ግን አንተ እንዳልከው ሌሎች ሴቶች ጋር የሌለ ሜሪ ጋር ብቻ ያለ ብዙ ነገር አለ በዛ ላይ እህልውሀ ሚባለው ነገር ሲያገናኝ አገናኜ ነው ምን ታደርገዋለህ በቃ ከላይ ነው ትዛዙ የናቲ ንግግር ነበር በፊት ከማቀው በላይ ደስተኛ እንደሆነ በጣም ያስታውቅበታል ሰው በሂዎቱ ልኩን ካገኜ በትንሽ በትልቁም ደስተኛ መሆን ይቀናዋል የሚል ነገር አንብቤ ነበር ናቲም ልኩን አገኝቶ ይሆናል ማን ያቃል? ይህን ሁሉ አንድነገራችሁ ምክኒያት እና እኔ ናቲን
87 viewsአምባ, edited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:13:41 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ግቢውን ወተን ትንሽ እርምጃወች እንደተራመድን ቤታቸው የነበርንባቸው ሴትዮ የምትወዳት የጎደኛዋ እናት እንደነበሩና ከመሞቷ በፊት ስለናቷ አብዝታ አደራ ትላት እንደነበርና አቤል ማለት ደሞ ገና አስረኛ ክፍል ተማሪ እንደነበሩ ጎደኛዋን ይወዳት የነበረ አንደ አባትም እንደፍቅረኛም የምታየው ጎደኛዋ እንደነበረ ነገረችኝ
ተጋብተው አብረው እንዲኖሩ ቢጠይቃትም እሷ ግን ስለህመሙ ከዶክተሩ ከሰማች በዃላ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረች ጥያቄውን ትቃወመው ነበር በመጨረሻ ግን ህመሙ እየባሰባት ሲሄድ ያን አንተ እኔ ሹራብ ውስጥ ያገኛኸውን ደብዳቤ ፃፈችለት በዛ ወቅት እሱ ለስራ ጉዳይ ካገር ውጭ ነበር የፈጣሪ ነገር ሁኖ ዶክተሩ ያላትን ያክል ግዜ እንኳ በሂወት አልቆየችም ነበር ከዛ ሀዘን ቡሀላ አቤልም እዚህ መሆንን አልመረጠም ነበር ደሴን ለቆ መኖሪያውን ትልቅ ወንድሙ ጋር ሀዋሳ አደረገ ። በጣም የሚገርመው ነገር ስለዚህ ሁሉ ነገር የሰማሁት ከረፈደ ነበር ከሁሉም በላይ ግን እስካሁን የሚገርመኝ ነገር ስለህመሟ ለኔ እንኳ ለምን እንዳልነገረችኝ ነው በተደዋወልን ቁጥር ስለናቷ አብዝታ አደራ ስትለኝ አንኳ አንዳች ነገር አለመጠርጠሬ ለራሴው ይደንቀኛል ።እኔም አሁን ለረፍት ብየ የመጣሁበት ምክንያት እና አንተንም እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ ብየህ የነበረው ነገር በጎዳኛየ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን አንድ የፊልም ድርሰት እየፃፍኩ ነው ድርሰቱን ፅፌ እንደጨረስኩ አንድ የፊልም ሙያ ውስጥ የሚሰራ አጎት አለኝ በሱ ትብብር ፊልሙ እንደሚሰራልኝ ተነጋግረናል የፈጣሪ ፍቃድ ሁኖ እንዳሰብኩት ቶሎ ከተሳካልኝ ማስታወሻነቱ ለጎደኛየ የሆነ ፊልም ይኖረኛል በዛ ላይ ከፊልሙ የሚገኛውን ገቢ ለጎደኛየ እናት አንዲሆን ነው እቅዴ ።ሙሉ የፊልሙ ታሪክ የጎደኛየ ታሪክ ላይ ያተኮረ ስለሆነ ከመሞቷ በፊት ለጎደኛዋ ልካለት የነበረውን ደብዳቤም ድርሰቱ ውስጥ እንዲካተት ስለፈለኩ በስንት ጉድ አሳምኜ አቤልን ተቀበልኩት በወቅቱ እሱ እዚህ አልነበረም ታስታውስ ከሆነ ደሞ የተዋወቅንበት ሰሞን ኢንተርኔትም ተዘግቶ ነበር ስለዚህ ብቸኛው አማራጭ ደብዳቤውን ከሱ ለማግኛት በፖስታ ቤት ነበር እንግዲህ ያን ቀን ነበር እኔና አንተ የተገናኛነው ካቤል የተላከልኝን ደብዳቤ ከፖስታ ቤት አውጥቸ ታክሲ ውስጥ የተገናኛነው አሁን ሁሉም ነገር በደንብ እንደተብራራልህ እና እንደተገለፀልህ ተስፋ አደርጋለሁ
አለች ወሬዋን እንደቋጨች በሚያሳብቅ ሁኔታ ,,,ልክ ነበረች ሀኒ ውስጤ ላይ የነበሩት ብዙ ያወዛገቡኝ እና እንቆቅልሽ የሆኑብኝ ነገሮች በሙሉ ተፈቱልኝ ።ይገርማል አንዳንዴ በስም መመሳሰል የሚፈጠሩ አጋጣሚወች ነገሮችን ሁሉ እንዳልነበሩ ይቀያይሩታል አሁን የኔዋ ሀኒ ፍልቅልቋ ቆንጆዋ ሀኒ ምንም አይነት ህመም ውስጧ አንደሌለ ለመሞትም ቀኑዋን የምትቆጥር የመሰለችኝ ሀኒ ሌላ ሴት ሁና ተገኜች ውስጤን ትልቅ የሆነ ሰላም እና ሀሴት ሲሞላ ተሰማኝ እዚሁ ስሜት ውስጥ ሳለሁ ኪሴ ውስጥ ያለው ስልክ ተንጫረረ አውጥቼ አየሁት እህቴ ነበረች አነሳሁትና ማውራት ጀመርኩ ያገቱህ ሰዎች ዛሬም አለቅም አሉህ እንዴ አለች እየቀለደች አሁን ሀኒ ጋር እንደሆንኩና ለምሳ ግን እንደምመጣ ነግሪያት ስልኩ ተዘጋ ማነው ስትል ጠየቀችኝ ሀኒ ወደኔ እየዞረች እህቴ እንደነበረች እና ለምሳ እንዳቀር እያለችኝ እንደሆነ ነገርኳት ,, በል አሁን የኔን እና የቤተሰቤን መሉ ታሪክ አስለፍልፈኸኛል ተራው ያንተ ነው ስለዚህ ስላንተም እንድታወራልኝ እፈልጋለሁ አለች በፈገግታ ታጂባ እሽ እነግርሻለሁ ነገር ግን በአንድ ነገር ከተስማማን ነው የምነግርሽ ስል መለስኩላት በምን ?አለች ፈገግ ያለውን ፊቷን ወደ ግርምት እየቀየረችው ,,ቤት አብረን ሂደን ምሳ እንበላለን በዛውም ከእህቴ ጋር አስተዋውቅሻለሁ ከዛ ቡሀላ ሙሉውን ስለኔና ስለቤተሰቤ እተርክልሻለሁ አልኳት በሀሳቡ ለመስማማት ምንም አላቅማማችም ነበር እንደውም በደስታ ነበር የተቀበለችው ወዲያው ግን ምኔ ናት ብለህ ነው የምታስተዋውቀኝ አለች እንደመሳቅ አልኩና እሱን ጥያቄ እኮ ትናንት መኝታ ቤትሽ መልሰነዋል ብየ በቀልድ አሸሞርኩባት ማለት የፈለኩት እሷም ስለገባት ሀፍረት ቅልቅል የሆነ ሳቅ ሳቀች ። አሁን ሁለታችንም ደስተኞች እንደሆንን ሁኔታችን በደንብ ይመሰክራል በቀልድ የታጀቡ ወሬወች እያወራን አንደ ልጅ እየቦረቅን አልፎ አልፎ ደሞ በመንገዳችን መሀል የፍቅር ልፊያ እየተላፋን መንገዳችንን ቀጥለናል በዚህ መሀል እኔም ከእህቴ ጋር ደውየ ለምሳ የምመጣው ሀኒ ጋር እንደሆነና እንድትዘጋጅ አሳወኳት በጫወታ የታጀበ መንገዳችንን ቀጥለን ትንሽ እንደሄድን ሀኒ እጄን አንደመሳብ እያደረገች ከመንገዱ ዳር ወዳለ ህንፃ ወሰደችኝ ወዴት ነን ሀኒ? የኔ ጥያቄ ነበር ወደ ፎቶ ቤት አለችኝ እየሳቀች ከዛም ከህንፃው ስር ወዳለው ፎቶ ቤት ሁለታችንም ተያይዘን ገባን••••

ይቀጥላል
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለማግኘት
@rediy21

✎ ክፍል 14 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

​@rediy21

https://t.me/teztash
79 viewsአምባ, edited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:09:56 እንዳንጠለጠ ሉ በመጋረጃ ወደተከፈለው ጎዳ እያመሩ ,,ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ትልቋ ሴትዮ ከሀኒ የተገዛላቸውን ነጭ የሀገር ባህል ቀሚስ ለብሰው ፍክት ያለ ፊታቸው ጋር ብቅ አሉ እራሳቸው ለክተው የገዙት ያክል ነበር ሰውነታቸው ላይ ልክክ ያለው በደዝታ ብዛት ፊታቸው ብርት ብሎ የምርቃን መአት አዥጎደጎዱባት ሀኒም ምርቃኑን እየተከተለች አሚንታዋን ቀጠለች ።የሰውን ደስታ እንደማየት ሀሴት የሚሰጥ ነገር ምን አለ ለዛውም ደሞ የደስታቸው ምንጭ አንተ ራስህ ሁነህ ስታገኛው ደስታው እጥፍ ድርብ እንደሚሆን ለማወቅ የሀኒን ፊት በማየት ማወቅ ቀላል ነበር ከዛን ቡሀላ ቤቱ ውስጥ የነበረን ቆይታ አጭር ነበር አባቷ ጋር ከመመለሷ በፊት መጥታ እንደምጠይቃቸው ነገራቸው ከፖርሳዋ ውስጥ ያወጣችውን የተጠቀለለ ገንዘብ ለአንዳንድ ነገር ብላ እጃቸው ላይ አድርጋላቸው ተሰናብተን ከትልቋ ሴትዮ ቤት ወጣን ትልቋ ሴትዮ ከሀኒ የተሰጣቸውን ገንዘብ መጀመሪያ አልቀበልም ብለው አስቸግረው ነበር ሀኒ በስንት ጉድ አሳምናቸው እሽ ብለው ተቀበሉ ።ግቢውን ወተን ትንሽ እርምጃወች እንደተራመድን ቤታቸው የነበርንባቸው ሴትዮ የምትወዳት የጎደኛዋ እናት እንደነበሩና ከመሞቷ በፊት ስለናቷ አብዝታ አደራ ትላት እንደነበርና አቤል ማለት ደሞ ገና አስረኛ ክፍል ተማሪ እንደነበሩ ጎደኛዋን ይወዳት የነበረ አንደ አባትም እንደፍቅረኛም የምታየው ጎደኛዋ እንደነበረ ነገረችኝ •••

ይቀጥላል
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለማግኘት
@rediy21
@rediy21
@rediy21


✎ ክፍል 14 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

@rediy21

​https://t.me/teztash
75 viewsአምባ, edited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:09:46 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

አንባዎቿ ከቆይታ በሃላ አንደ ማቆም ሲሉ ወሬዋን ቀጠለችልኝ ይቅርታ አንተንም ረበሽኩህ ስለእሷ ሳወራ ስሜቴን መቆጣጠር አልችልም ያቺ እንደ እህቴ የማያት
ለትልቅ ቁም ነገር ተስፋ የተጣለባት የነበረች
ደኛዬ ዛሬ በህይወት የለችም ያ ነው ያስለቀሰኝ አለች ድምፆ ቁርጥ ቁርጥ እያለ እሷ ጋር ያለው የሀዘን ስሜት ባንዴ ወደኔ ተላለፈ እንዴት ይከብዳል ስል አሰብኩት በዚ መጠን የምትቀርበውና የምትወደው ጓደኛ ለዛውም በዚ ለጋ እድሜ በሞት ሲለይ ህመሙ ምን ያህል ከባድ እንደሚሆንና ሁሌ ባስታወስነው ቁጥርም ሀዘኑ መሪር እንደሚሆን ግልፅ
ነው በቻልኩት መጠን አፅናናሁዋት እና በመጠኑም ቢሆን ከዛ ስሜት እንድትወጣ አደረኳት, ,ወደራስዋ እንደተመለሰች የኔና የሷ ነገር እንዲህ በቀላሉ
ተወርቶ የሚያልቅ አይደለም ሌላ ግዜ እጨርስልሀለሁ አሁን የጀመርኩትን የቤተሰቡን ልጨርስልህ አለችና ቀጠለች ለብቻችን መኖር ከጀመርን ብዙም
ሳይቆይ ከዳድ ጋር በሽርክና ይሰራ የነበረው ሰውየ ከነቤተሰቦቹ ጠቅልሎ ወደ ውጭ ሊሄድ እንደሆነና በጋራ የከፈቱትን ፋብሪካ እንዲሸጡት አልያም ግማሽ
ድርሻውን ለሰውየው ሰጥቶ ፋብሪካውን የራሱ እንዲያደርግ ሀሳብ አቀረበለት ዳድም በወቅቱ የነበረው ስራ በጣም አዋጭ ስለነበር ፋብሪካውን ከመሸጥ
ይልቅ ግማሹን ድርሻ ለሰውየው ሰጥቶ ፋብሪካውን የራሱ አደረገ ከዛን ቡሀላ ነበር ዳድ ሁሉንም ነገር በቅርበት ለመቆጣጠር እንዲያመቸው ሲል ጠቅልሎ
እዛው ደብረዘይት መኖሪያውን ያደረገው እኔም ትምርቴን እንደጨረስኩ እሱን ለማገዝ ወደዛው ሄድኩ ትንሿ እህቴና አያቴ ደሞ ከሰራተኛ ጋር እዚሁ ቀሩ አሁን
ረፍት ወስጀ ነው የመጣሁት ረፍት ወስጀ የመጣሁበትን ዋና ምክንያት እነግርህና አንተም እስኪ ታግዘኛለህ ,,,ለዛሬ ይህን ካወክ ቀሪውን ደሞ በሂደት ታውቀዋለህ አሁን ቁርሳችንን እንብላ አለች ሹካዋን እያነሳች እንቆቅልሽ የሆንሽ ልጅ አልኳትና
እኔም አቋርጨ የነበረውን ቁርስ መብላት ጀመርኩ ቆይ ዛሬ ምንድን ነው ፕሮግራምህ አለችኝ ሻዩን ወዳፏ እያደረገች ምንም የተለየ ፕሮግራም እንደሌለኝ መለስኩላት በቃ እምንሄድበት ቦታ አለ ዛሬ ከኔ ጋ ነክ በዛውም ያልተመለሰ ጥያቄ ይመለስልሀል አለችኝ ሌላ ልደት ልትወስጂኝ ካልሆነ ችግር የለውም ብዬ ቀለድኩባት ካፍታ ቆይታ በሗላ ቁርሳችንን ጨርሰን ሀኒም ልብሶን ቀይራ ቤቱን ለቀን እንሄድበታለን ወዳለችው ቦታ ጉዞ ጀመርን ከግቢው ለቀን
ከዋናው ጎዳና እንደገባን ወደ ገበያ አዳራሽ መሄድ አለብን መጀመሪያ አለችና ታክሲ ይዘን ወደዛው አቀናን እዛ እንደደረስን ሀኒ የተለያዩ ነገሮችን መገዛዛት
ጀመርች የባህል ቀሚስ፣ ሽቶ ሱቅ ቀይርን ወተን ደሞ ቡናና ሌላ የተለያዩ ሸቀጦች ጨምራ ገዛች አሁን የምገዛውን እንደጨርሰች ነግራኝ የኮንትራት ላዳ
ተኮናትረን በሀኒ አቅጣጫ ጠቆሚነት ላዳዋ ተንቀሳቀሰች ቆይ ግን አንተስ ስለራስህ መች ነው የምትነግርኝ የኔን ብቻ እያስለፈለፍከኝ አለችኝ ,, እስኪ አንችን በቅጡ አውቄሽ ልጨርስና ወደኔ እንገባለን ደሞ የኔ ላዳ ውስጥ ተጀምሮ የሚያልቅ አይደለም ስል በቀልድ መለስኩላት ካፍታ የመንገድ ቀይታ ቡሀላ እንደደረስን ለሹፌሩ ምልክት አሳየችውና የገዛዛናቸውን ነገሮች ይዘን በግራችን ትንሽ እንደሄድን ከአንድ በእንጨት አጥር ወደታጠረ ግቢ ገባን በትንሽዋ ግቢ ውስጥ ከጭቃ ተሰርቶ ነጭ ኖራ የተቀባ ቤት አለ ወደ በሩ አመራን ከበሩ ላይ እድሚያቸው ገፋ ያለ የሚመስሉ እራሳቸው ላይ ጥቁር ሻሽ ያበቱ ሴትዮ ቁጭ ብለው እሳት ያቀጣጥላሉ ካጠገባቸው እስከምንደርስ ያዩን አይመስሉም ማዘር ስትል ሀኒ ጠራቻቸው ከነበሩበት ሳይነሱ ቀና ብለው እኛ ወደነበርንበት ሲመለከቱ እኔና ሀኒን አዩ ,,, ባዩት ነገር እንደደነገጡ ከሁኔታቸው ያስታውቃል በሞትኩት አሉና ከተቀመጡበት ተነስተው ከሀኒ አንገት ላይ ጥምጥም አሉ ,,በተቃቀፉበት እንዳሉ ሁለቱም ለቅሷቸውን ለቀቁት እኔ እጄ ላይ ያለውን እቃ እንደያዝኩ ከቆምኩበት አልተንቀሳቀስኩም ካፍታ ቆይታ ቡሀላ ተቃቅፈው ሲያለቅሱ የነበሩት ሀኒና ትልቋ ሴትዮ አንዳቸው የአንዳቸውን እምባ በስስት ማበስ ጀመሩ ከዚህ ሁላ ቡሀላ ነበር ሴትዮዋ እኔ መቆሜንም ቁብ ያሉት ሀኒም ወደኔ መዞራቸውን ስላየች ጎደኛየ ነው አለቻቸው ከዛም እንደሚያቁት ሰው አገጨን ይዘው ሁለት ጉንጮቸን እያዟዟሩ በመሳም ሰላምታ ሰጡኝ በዚህ ሁኔታ ሰላምታውን ጨርሰን በትልቋ ሴትዮ የግቡልኝ ግብዣ መሰረት ገርበብ ብሎ የተከፈተውን በር አልፈን ወደ ውስጥ ገባን ብዙም ሰፊ ያልሆነው ባለሁለት ክፍል ቤት ደብዘዝ ያለ ሰምያዊ ቀለም ተቀብቷል ከግርግዳው ላይ አለፍ አለፍ ብለው የተሰቀሉ ስእለ ማሪያሞች ይስተዋላሉ ከክፍሉ መሀል ላይ ከተሰሩ ብዙ ግዜ እንደቆዩ የሚያስተዉቁ አራት ጥንድ ሶፋዎች ቤቷን ይበልጥ ጠባብ አድርገዋታል እኛም አንዛ ሶፋ ላይ አንድንቀመጥ ተጋብዘን አረፍ ብለናል ።ትልቋ ሴትዮ ቤታቸው ድንገተኛ እንግዳ ስለመጣባቸው ከቤት ደጅ እያሉ ሽርጉድ ማለቱን ይዘውታል ሀኒ ምንም እንደማያስፈልገን አሳውቃ እንዲቀመጡ ብጠይቃቸውም እሳቸው ግን በባዶ ቤት የማይሆነውን ብለው ቤት ያፈራውን አቀረቡልን ቁርስ የበላነዉ ቅርብ ስአት ቢሆንም እሳቸውን ቅር ላለማሰኘኘት እንደነገሩ መቅመስ ጀመርን እሳቸውም አብርውን ተቀመጡ በምግቡ መሀል ትልቋ ሴትዯ ስለ ሀኒና ቤተሰብ የሚመለከት የደህንነት ጥያቄወች አከታትለው መጠየቅ ተያይዘዋል እንደዉ አባትሽ አሁንም ብቻውን ነው ወይስ....ብለው ጀምርው አቆሙት ሀኒም ጥያቄያቸው ሰለገባት ፈገግ ብላ እስካሁን ብቻውን ነበር አሁን ግን ያሰበው ነገር ሳይኖር አይቀርም ያው ሙሉውን ባይሆንም የሆነ ወሬ ነካክቶልኝ ነበር አለቻቸው ይሻለዋል ለሱም እስከመቸ ሆቴል እየበላ ይዘልቀዋል አንችም ብትሆኝ ዝም አትበይ አንድ ነገር አድርጊ መቸም እናትሽ ጋር ያለውን ነገር የማይሆን ነው ብለሽኛል አሉ ፊታቸው አዙረዉ ወደኔ እያዬ ያው ታሪኩን እኔ የማላውቅ ከሆነ ገመና ያወጡ እንደሆነ ተሰምቷቸው እስኪ እንግድህ እሱ ያውቃል አለች ሀኒ ወሬውን በዚህ መልኩ እንዲቀጥል የፈለገች አትመስልም አስከትላም አቤል ጋር ተደዋውለን ነበር ባለፈው ያው ስራው ካገር አገር ስለሆነ ብዙ እንደማይመቸውና እዚህ ሲመጣ ግን ሳይጠይቃችሁ እንደማይሄድ ነገረኝ አለቻቸዉ ምን እሱ እዚህስ ባይሆን መቸ እኔን ከመጠየቅ ወደ ኋላ ብሎ ያውቃል ሌላ ሀገረ ሄዶ ከሆነ እንኳን ቶሎ ቶሎ ነው የሚደውለውኮ እዚህ ሲመጣ ደግሞ እንደ ልጅ ምን ያስፈልግሻል ብሎ ጠይቆ ቤቱን ሞልቶት ነው የሚሄደው እመብረሀን እድሚያችሁን ታረዝምልኝ አንችና እሱ ባትኖሩ ዛሬ ማን ዞር ብሎ ያየኝ ነበር እንዲህ ሁሉ በከፋበት ወቅት እናንተን መሰል የልጅ አዋቂ ቁም ነገረኛ ማግኘት በጣም ከባድ ነው ፈጣሪ አንድ የአይኔን ብሌን ሲወስድብኝ እናንተን ባይጥልልኝ ምን ተምን እሆነው ነበር አሉ በጥለታቸው ጫፍ የአይናቸውን ስር እምባ እየጠረጉ በዚህ መልኩ ወሬያቸው ከቀጠለ ሌላ የተዳፈነ ሀዘን መቀስቀስ እንደሆነ የገባት ሀኒ ገዝተን ያመጣነውን እቃ ወደ ሳቸው ገፋ እያደርገች እስኪ ውስጡ ያለውን ቀሚስ እዩት ልኩን በግምት ነው ያደረኩት አለቻቸው ይህን በመጣሽ ቁጥር እያንጠለጠልሽ የምትመጭውን ነገር ተይ ብልሽ በጅ አልልም አልሽ አይደል አሏት ጎናቸው ያለውን እቃ የያዘ ላስቲክ እያነሱ ሀኒን በስስት አይን እያዩ ኧረ ይሄ ምንም አይደል ማዘር ይልቅ እስኪ ይሞክሩትና እንየው ልክዎ ካልሆነ እንደሚቀይርልኝ ስለነገርኩት እንቀይረዋለን አለቻቸው እመብርሀን ትደግፍሽ አሉ የያዙትን ላስቲክ
82 viewsአምባ, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ