Get Mystery Box with random crypto!

የቆንጆዋ ጦስ ክፍል ፎቶ ቤት ውስጥ ገብተን የተወሰኑ ፎቶዎችን ለማስታዎሻነት ተናሳን | የኔው ታሪክ 8315

የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ፎቶ ቤት ውስጥ ገብተን የተወሰኑ ፎቶዎችን ለማስታዎሻነት ተናሳን እውነት ለመናገር በኔበኩል ምንም ሀሳቡ አልመጣልኝም ነበር የሀኒ ምርጫ ነበር ።ፎቶ ቤቱ ለቀን ከወጣን በዃላ ለምን እንድንነሳ ፈለግሽ አልኳት በስስት አይኗን እያየሁ ዛሬኮ ለኛ የተለየች ቀን ናት በተለይ ለኔ ጥልቅ ትርጉም የያዘች ቀን ናት እኔን በኔነቴ ብቻ የሚወደኝ፣ የሚሳሳልኝ፣ ለደስታየ የሚጨነቅ፣ ከነበርኩበት የትካዜ ስሜት በቀላሉ እንድወጣ ያደረገኝን ሰው ከጎኔ አድርጊያለሁ ከዚህ በላይ ታዲያ ምን የሚያስደስት ነገር አለ አለችኝ የሀኒ ለኔ ያላት ስሜት በዚህ መልኩ መሆኑ ለኔም ጥልቅ ደስታ የሚሰጥ ነገር ነው ምክኒያቱም በጣም እወዳታለሁ ። ይገርማል ግን የፍቅር ግንኙነት እንዴት እና በምን አጋጣሚ ተጀመሮ እስከምን እንደሚዘልቅ ፍፃሜውስ ምን ይሆን ማናችንም ምናውቀው ነገር የለም አንዳንዶች በተሳሳተ የስልክ ጥሪ ተዋውቀው ለአብሮነት ይበቃሉ፣ አንዳንዶች ደሞ በመስሪያ ቤት እና በትምህርት ቤት ፣ አንዳንዶች ደሞ ሰርግ ላይ፣ ሌሎች ደሞ በዘመድ እና በጓደኛ ትውውቅ በሌላ ጎን ደሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በፌስቡክ በዋትሳፕ ሀይ ብለው ጀምረው እስከ ሀይ ሎጋ የደረሱም በጣም ዕልፍ ናቼው እንደውም በዚህ አጋጣሚ የአንድ ቅርብ ጓደኛየን የፍቅር አጋጣሚ ላውራላችሁ ለኔ ትልቅ ትምህርት ያገኜሁበት ስለሆነ ሁሌም የዚህ አይነት ነገር ሲነሳ ትውስ ይለኛል ጓደኛየ ናቲ ይባላል የታክሲ ሹፌር ነው በጣም ሲበዛ መልከ መልካም እና ተጫዋች ነው ወሬው እና ቀልዱ አይደለም ሴት ልጅን ወንድን እንኳ በቀላሉ ያለምዳል በቃ ምን አለፍችሁ ምላሱ በረዶ ይቆላል ወክ ስናደርግ ፣ ወይ መዝናኛ ቦታ አልያም በሆነ አጋጣሚ አብረን ሁነን ቆንጆ ሴት ቦታው ላይ ከተገኜች ከሁላችንም በፊት ናቲን ነው ቀድመን የምንልከው ናቲ ሂዶ አወራት ማለት ደሞ በቃ የሆነ ታሪክ እንደሚፈጠር እሙን ነው ለናቲ ከሴት ጋር በጓደኝነት መልኩ አብሮ መቆየት የሚባል ነገር አይታሰብም በቃ ባገኜው አጋጣሚ ቆንጆዎችን ማሳደድ ነው ስራው ለምን አንድ ሴት መርጠህ ከሷ ጋር አትሆንም ሲባል ለኔ የምትሆነው ሴት ገና አልተረገዘችም ይላል የሆነ ግዜ በስራ ምክኒያት ሌላ ሀገር በመሄዴ ከናቲ ጋር በስልክ እንጂ በአካል አንገናኝም ነበር የሆነ ቀን ምሽት ናቲ ደወለልኝ እና እንደተለመደው እየተዛዛግን ትንሽ አወራን ከዛም ዛሬ ለቁም ነገር ነው የደወልኩት አለኝ ድምፁን ለወጥ አድርጎ እሺ የምን ቁምነገር ነው ስል እኔም መልሼ ጠየኩት እንደወረደ ላገባ ነው አለኝ ናቲ በጣም ነበር የሳኩት ምንድን ነው የምታገባው መልሼ ጠየኩት አሁንም ከሳቄ አልተፋታሁም ከሰሞኑ ስንደዋወል የሆነ ፎንቃ ቢጤ ሳይገባልኝ አይቀርም እያለኝ እንደነበረ ባስታውስም እኔ ማቀው ናቲ ፣ ከሴት ጋር አንድ ሳምንት እንኳ በቅጡ የማይቆየው ናቲ፣ ቆንጆ አሳዳጁ ናቲ አንዲት ሴት መርጦ ሊያውም በዚ ፍጥነት አግብቶ እስከመጨረሻው ከሷ ጋር ብቻ ሊሆን የሚለው ፈፅሞ አልተዋጠልኝም,, ምን አገባለሁ ሚስት ነዋ አለኝ እና አስከትሎም ምን ያስገለፍጥሀል አለኝ በሳቄ እንደተናደደ ያሳብቅበታል እኔም ነገሩ እንዳሰብኩት ቀልድ እንዳልሆነ ተረዳሁና እሺ ማንን ነው የምታገባው መችስ ነው የምታገባው ስል ጠንከር ባለ ድምፅ ጠየኩት ልጅቱን በአካል ባላቃትም ያቺ ከሰሞኑ ሲነግረኝ የነበረችው ልጅ እንደሆነችና ሌላውን ነገር ደሞ ስትመጣ ትደርስበታለህ ለማንኛውም ቀለል ያለ ሰርግ በቅርብ አስበናል ሚዜ መሆንህን አስብበት ከቻልክ ቀደም ብለህ ብትመጣ ደስ ይለኛል ሲል አበሰረኝ አንተ እንደዚህ ቁምነገረኛ ሁነህ አግባልኝ እንጂ ውየ አላድርም ስመጣ ብየው አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮች አውርተን ስልኩ ተዘጋ በውስጤ ምን አይነት ቆንጆ ሴት ትሆን ናቲን እንደዚህ በቶሎ ያንበረከከችው እያልኩ እያሰብኩ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ ። ከዛ በዃላ ብዙም ቀን አልቆየሁም ነበር ለናቲ ሰርግ ካለሁበት ስሄድ ሚገርመው ከሰርጉ በላይ ናቲ ሚያገባትን ሴት ማየቱ አጓጉቶኝ ነበር አሷን ለኔ ከማስተዋወቁ በፊት የተገናኙበትን አጋጣሚ ነበር ያወጋልኝ እንዲህ ነበር የሆነው የሆነ ቀን እንደተለመደው ስራው ላይ ሁኖ እያሽከረከረ ሌላ የቆመ መኪና ተደርባ መንገድ ልታቋርጥ ያለች ልጅ ትገባበታለች በድንጋጤ
እንደምንም ያለ ሀይሉን ተጠቅሞ የታክሲዋን መሪ ከሷ ተቃራኒ ጠምዝዞ ከመገጨት ሊያድናት ሞከረ ነገር ግን የመኪናው ጫፍ ጎኗን አገኝቷት ኑሮ ከአስፓልቱ ላይ እንደምንጣፍ ተዘረጋች እሱ ሲነግረኝ እንዳወዳደቋ አሱም ሆነ ሌሎች ተሳፋሪዎች በቀላሉ ትተርፋለች ያለ አልነበረም ወዲያው እሷን ከወደቀችበት አንስቶ ወደ ሆስፒታል ይወስዳታል ። ከምርመራው ውጤት በዃላ የአጥንት ቅጥቅጣት ስላገኛት ተኝታ መታከም እንደሚኖርባት ተወስኖ በዛው ሆስፒታል ለተወሰኑ ቀኖች ትቆያለች ናቲም አንዴ ብቻውን አንዴ ደሞ ከእህቱ ጋር በመሆን እየተመላለሰ ልጅቱን መጠየቅ ይጀምራል እንግዲህ በዚህ መሀል ነው ናቲ ከገጫት ልጅ ጋር አንድ አንድ እያሉ መግባባት የጀመሩት "አጋጣሚ አቃጣሪ አይደል" ልጅቱ ከህመሟ አገግማ የሆስፒታል ቆይታዋን ጨርሳ ከወጣች በዃላም እቤቷ ድረስ እየሄደ መጠየቁን አላቆመም ነበር እያለ እያለ እሷም ከቤት መውጣት እና ከናቲ ጋር መገናኜት ጀመረች ያን የማይጠገብ ጨዋታውን አንዴ አይታስ እንዴት ትቀራለች ያ ቆንጆ አሳዳጁ ናቲም በገጫት ልጅ የፍቅር ገመድ ተጠፍንጎ ታስሮ ያን ባህሪውን በመተው ለትዳር እንደወሰነ ዘርዝሮ አጫወተኝ
ይሄን ባጫወተኝ በሁለተኛው ቀን ከልጅቷም ጋር በአካል አስተዋወቀኝ ሜሮን ትባላለች እውነቱን ለመናገር የመልኳ ነገር እንዳየዃት አስደንግጦኛል ጭራሽ እኔ ከናቲ የበፊት ምርጫው ተነስቼ ጠብቄው የነበረው መልክ እና አሁን ያየሁት ፍፁም ተቃራኒ ነበር ባጭሩ ወሬ ሳላንዛዛ ልንገራችሁ "አታምርም" በተለተይ ከናቲ ጋር ሲተያዩማ መግለፅም ይቸግራል ፍቅር እውር ነው የሚባለው ለካ በሆነ ጎኑ እውነታ አለው ከትውውቁ በዃላ እሷን እቤቷ ደረስ ሼኝተናት እየተመለስን እንዴት አየሀት ሜሪን ሲል ጠየቀኝ እኔ ደሞ ባህሪየ ሁኖ ሰውየው ደስ እንዲለው ብየ የሌለን ነገር አስመስየ ወይ ዋሽቼ መናገር አያቀኝም ናቲም ቢሆን ይሄን ባህሪየን አስረግጦ ያቀዋል መልኳን ከሱ ምርጫ አንፃር እኔ ጠብቄው እንደነበረው እንዳላገኜሁት ነገር ግን እሱን እስከትዳር ድረስ እንዲያስብ ማድረግ መቻሏ አንድ እኔ ማላቀው የተለየ የሴትነት ጥበብ ያላት ሴት እንደምትሆን ነገርኩት የታክሲዋን መሪ በጁ እየመታ በጣም ሳቀና ለዚህኮ ነው የምወድህ አለኝ እንዴት ስል ጠየኩት አየህ ሌላ ሰው ቢሆን በጣም ቆንጆ ናት ምናምን እያለ እኔን ደስ ለማሰኜት ይደሰኩር ነበር አንተ ግን እቅጯን አለኝ እና መልሶ የቅድሙን ሳቅ ደገመው ። ሜሪ ቆንጆ ምትባል ሴት እንዳልሆነች እኔም አውቃለሁ ነገር ግን አንተ እንዳልከው ሌሎች ሴቶች ጋር የሌለ ሜሪ ጋር ብቻ ያለ ብዙ ነገር አለ በዛ ላይ እህልውሀ ሚባለው ነገር ሲያገናኝ አገናኜ ነው ምን ታደርገዋለህ በቃ ከላይ ነው ትዛዙ የናቲ ንግግር ነበር በፊት ከማቀው በላይ ደስተኛ እንደሆነ በጣም ያስታውቅበታል ሰው በሂዎቱ ልኩን ካገኜ በትንሽ በትልቁም ደስተኛ መሆን ይቀናዋል የሚል ነገር አንብቤ ነበር ናቲም ልኩን አገኝቶ ይሆናል ማን ያቃል? ይህን ሁሉ አንድነገራችሁ ምክኒያት እና እኔ ናቲን