Get Mystery Box with random crypto!

የቆንጆዋ ጦስ ክፍል ግቢውን ወተን ትንሽ እርምጃወች እንደተራመድን ቤታቸው የነበርንባቸ | የኔው ታሪክ 8315

የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ግቢውን ወተን ትንሽ እርምጃወች እንደተራመድን ቤታቸው የነበርንባቸው ሴትዮ የምትወዳት የጎደኛዋ እናት እንደነበሩና ከመሞቷ በፊት ስለናቷ አብዝታ አደራ ትላት እንደነበርና አቤል ማለት ደሞ ገና አስረኛ ክፍል ተማሪ እንደነበሩ ጎደኛዋን ይወዳት የነበረ አንደ አባትም እንደፍቅረኛም የምታየው ጎደኛዋ እንደነበረ ነገረችኝ
ተጋብተው አብረው እንዲኖሩ ቢጠይቃትም እሷ ግን ስለህመሙ ከዶክተሩ ከሰማች በዃላ የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረች ጥያቄውን ትቃወመው ነበር በመጨረሻ ግን ህመሙ እየባሰባት ሲሄድ ያን አንተ እኔ ሹራብ ውስጥ ያገኛኸውን ደብዳቤ ፃፈችለት በዛ ወቅት እሱ ለስራ ጉዳይ ካገር ውጭ ነበር የፈጣሪ ነገር ሁኖ ዶክተሩ ያላትን ያክል ግዜ እንኳ በሂወት አልቆየችም ነበር ከዛ ሀዘን ቡሀላ አቤልም እዚህ መሆንን አልመረጠም ነበር ደሴን ለቆ መኖሪያውን ትልቅ ወንድሙ ጋር ሀዋሳ አደረገ ። በጣም የሚገርመው ነገር ስለዚህ ሁሉ ነገር የሰማሁት ከረፈደ ነበር ከሁሉም በላይ ግን እስካሁን የሚገርመኝ ነገር ስለህመሟ ለኔ እንኳ ለምን እንዳልነገረችኝ ነው በተደዋወልን ቁጥር ስለናቷ አብዝታ አደራ ስትለኝ አንኳ አንዳች ነገር አለመጠርጠሬ ለራሴው ይደንቀኛል ።እኔም አሁን ለረፍት ብየ የመጣሁበት ምክንያት እና አንተንም እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ ብየህ የነበረው ነገር በጎዳኛየ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን አንድ የፊልም ድርሰት እየፃፍኩ ነው ድርሰቱን ፅፌ እንደጨረስኩ አንድ የፊልም ሙያ ውስጥ የሚሰራ አጎት አለኝ በሱ ትብብር ፊልሙ እንደሚሰራልኝ ተነጋግረናል የፈጣሪ ፍቃድ ሁኖ እንዳሰብኩት ቶሎ ከተሳካልኝ ማስታወሻነቱ ለጎደኛየ የሆነ ፊልም ይኖረኛል በዛ ላይ ከፊልሙ የሚገኛውን ገቢ ለጎደኛየ እናት አንዲሆን ነው እቅዴ ።ሙሉ የፊልሙ ታሪክ የጎደኛየ ታሪክ ላይ ያተኮረ ስለሆነ ከመሞቷ በፊት ለጎደኛዋ ልካለት የነበረውን ደብዳቤም ድርሰቱ ውስጥ እንዲካተት ስለፈለኩ በስንት ጉድ አሳምኜ አቤልን ተቀበልኩት በወቅቱ እሱ እዚህ አልነበረም ታስታውስ ከሆነ ደሞ የተዋወቅንበት ሰሞን ኢንተርኔትም ተዘግቶ ነበር ስለዚህ ብቸኛው አማራጭ ደብዳቤውን ከሱ ለማግኛት በፖስታ ቤት ነበር እንግዲህ ያን ቀን ነበር እኔና አንተ የተገናኛነው ካቤል የተላከልኝን ደብዳቤ ከፖስታ ቤት አውጥቸ ታክሲ ውስጥ የተገናኛነው አሁን ሁሉም ነገር በደንብ እንደተብራራልህ እና እንደተገለፀልህ ተስፋ አደርጋለሁ
አለች ወሬዋን እንደቋጨች በሚያሳብቅ ሁኔታ ,,,ልክ ነበረች ሀኒ ውስጤ ላይ የነበሩት ብዙ ያወዛገቡኝ እና እንቆቅልሽ የሆኑብኝ ነገሮች በሙሉ ተፈቱልኝ ።ይገርማል አንዳንዴ በስም መመሳሰል የሚፈጠሩ አጋጣሚወች ነገሮችን ሁሉ እንዳልነበሩ ይቀያይሩታል አሁን የኔዋ ሀኒ ፍልቅልቋ ቆንጆዋ ሀኒ ምንም አይነት ህመም ውስጧ አንደሌለ ለመሞትም ቀኑዋን የምትቆጥር የመሰለችኝ ሀኒ ሌላ ሴት ሁና ተገኜች ውስጤን ትልቅ የሆነ ሰላም እና ሀሴት ሲሞላ ተሰማኝ እዚሁ ስሜት ውስጥ ሳለሁ ኪሴ ውስጥ ያለው ስልክ ተንጫረረ አውጥቼ አየሁት እህቴ ነበረች አነሳሁትና ማውራት ጀመርኩ ያገቱህ ሰዎች ዛሬም አለቅም አሉህ እንዴ አለች እየቀለደች አሁን ሀኒ ጋር እንደሆንኩና ለምሳ ግን እንደምመጣ ነግሪያት ስልኩ ተዘጋ ማነው ስትል ጠየቀችኝ ሀኒ ወደኔ እየዞረች እህቴ እንደነበረች እና ለምሳ እንዳቀር እያለችኝ እንደሆነ ነገርኳት ,, በል አሁን የኔን እና የቤተሰቤን መሉ ታሪክ አስለፍልፈኸኛል ተራው ያንተ ነው ስለዚህ ስላንተም እንድታወራልኝ እፈልጋለሁ አለች በፈገግታ ታጂባ እሽ እነግርሻለሁ ነገር ግን በአንድ ነገር ከተስማማን ነው የምነግርሽ ስል መለስኩላት በምን ?አለች ፈገግ ያለውን ፊቷን ወደ ግርምት እየቀየረችው ,,ቤት አብረን ሂደን ምሳ እንበላለን በዛውም ከእህቴ ጋር አስተዋውቅሻለሁ ከዛ ቡሀላ ሙሉውን ስለኔና ስለቤተሰቤ እተርክልሻለሁ አልኳት በሀሳቡ ለመስማማት ምንም አላቅማማችም ነበር እንደውም በደስታ ነበር የተቀበለችው ወዲያው ግን ምኔ ናት ብለህ ነው የምታስተዋውቀኝ አለች እንደመሳቅ አልኩና እሱን ጥያቄ እኮ ትናንት መኝታ ቤትሽ መልሰነዋል ብየ በቀልድ አሸሞርኩባት ማለት የፈለኩት እሷም ስለገባት ሀፍረት ቅልቅል የሆነ ሳቅ ሳቀች ። አሁን ሁለታችንም ደስተኞች እንደሆንን ሁኔታችን በደንብ ይመሰክራል በቀልድ የታጀቡ ወሬወች እያወራን አንደ ልጅ እየቦረቅን አልፎ አልፎ ደሞ በመንገዳችን መሀል የፍቅር ልፊያ እየተላፋን መንገዳችንን ቀጥለናል በዚህ መሀል እኔም ከእህቴ ጋር ደውየ ለምሳ የምመጣው ሀኒ ጋር እንደሆነና እንድትዘጋጅ አሳወኳት በጫወታ የታጀበ መንገዳችንን ቀጥለን ትንሽ እንደሄድን ሀኒ እጄን አንደመሳብ እያደረገች ከመንገዱ ዳር ወዳለ ህንፃ ወሰደችኝ ወዴት ነን ሀኒ? የኔ ጥያቄ ነበር ወደ ፎቶ ቤት አለችኝ እየሳቀች ከዛም ከህንፃው ስር ወዳለው ፎቶ ቤት ሁለታችንም ተያይዘን ገባን••••

ይቀጥላል
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለማግኘት
@rediy21

✎ ክፍል 14 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

​@rediy21

https://t.me/teztash