Get Mystery Box with random crypto!

የኔው ታሪክ 8315

የቴሌግራም ቻናል አርማ teztash — የኔው ታሪክ 8315
የቴሌግራም ቻናል አርማ teztash — የኔው ታሪክ 8315
የሰርጥ አድራሻ: @teztash
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213
የሰርጥ መግለጫ

D/shu ema kiya8315

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-28 10:22:12 ⚀ ክፍል ስድስት ⚀


"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።
"ደህና ነኝ ከየት ነው በዚህ ሰዓት?"አልኳት
"ባሌ ሰለቸሽኝ ሲለኝ ለአንዷ ሰጥቼው መመለሴ ነው አልገርምም?" አለችኝ ይበልጥ ፈገግ እያለች፤ ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል በዚህ ብርዳም ምሽት እሷን በማግኘቴ ተደሰትኩ።
"ይገርምሻል እኔም ሚስቴ የሆነ ሰውዬ ጋ አየናት ያውም የሆነች ቆንጅዬ ሴት ናት አሉ 'ባሌን ውሰጂው ብላ የሰጠችው' ብለውኝ እኮ ጉድ ብዬ ስልኬን ስዘጋ ተገናኘን ወይ መገጣጠም!" አልኳት።
ከት ብላ ስቃ ስታበቃ "አቦ በአላህ ደስ ትላለህ አሳከኝ!" አለች በልስልስ ጥዑም አንደበቷ።
"ይልቅ ከየት ነሽ?" አልኳት ውብ አይኗ ላይ አይኔን ተክዬ
"አጎቴ ከጉዋደኞቹ ጋር አስተዋውቆኝ እቆያለሁ አንቺ ብሎኝ መመለሴ ነው። አንተስ ግሩሜ?" አለች።
አይ እኔማ ወክ እያደረኩ ነበር ካልቸኮልሽ ለምን ተቀምጠን አናወራም ?" አልኳት የመናፈሻውን ግቢ በአይኔ እየጠቆምኳት።
ጭንቅላቷን በመነቅነቅ እሺታዋን ገለፀችልኝና ገብተን የመናፈሻው ወንበር ላይ ተቀምጠን ስለብዙ ነገር አወራን። ወሬያችን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፍሌም በሳቅ ትንከተከት እንደነበር አስታውሳለሁ!።
ጥቂት የማይባል ጊዜ እንዳወራን የሰዓቱን መንጎድ ተመልክታ እንድንሄድ ጠየቀችኝ። ተያይዘን ከመናፈሻው ቅፅር ግቢ ስንወጣ ሰዓቱ ሁለት ሰዓት ከሰላሳን አጋምሶ ለሶስት ሰዓት ግስገሳውን አፍጥኖታል።
ታክሲም ሆነ ባጃጅ ጥድፊያ ነው። በእግራችን አዘገምን በጉዞአችን በበረደኝ ሰበብ ከፍሌሜ ጋር እየተጠጋጋን እየተጠጋጋን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ጉዞአችንን ባጀነው።
የእሷ መታጠፊያ ጋ ስንደርስ ይበልጥ ተቃቅፈን ትንሽ ከቆየን በኃላ "ደህና እደር ግሩሜ " አለችኝ "ደህና እደሪልኝ" ብዬ አፀፋውን መልሼ ወደ ቤት አዘገምኩ።
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያፈራነውን እያመሰኳሁ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።


ከዛች ምሽት ወዲህ ከፍሌም ጋር በሰፊው መገናኘት መቀራረብ ቻልን። ፍሌም ከድሬ በበለጠ እዚህ ከመጣች ወዲህ ደስታዋ እንደጨመረ ዘውትር ታወሳኛለች። አጎቷ ለፊልድ ወጣ ካለ መናፈሻው አይቀረን ሲኒማው አይቀረን የወንዝ ዳር ደፎች አይቀሩን ፣ በየመንገዱ ላይ ስንፈስ ነው የምንውል የምናመሸው!?።
እንዲህ እንዲህ እያልን ክረምቱን ለመባጀት ተቃረብን ሀምሌን ሸኝተን ነሀሴን አጋምሰነዋል። ይሄኔ እኔ ክፉኛ ጨነቀኝ ፍሌሜን ማጣት አልፈለኩም እሷን ማጣት ሞትን የመቀበል ያህል ከበደኝ። ስቀርባት እንደምትርቀኝ አልታወቀኝም ነበር መሰል።
ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።

​​

ክፍል ሰባት ይቀጥላል........

teztash
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21
▃▅▆█ ፍሌም █▆▅▃
45 viewsረድኤተ አምላክ, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:43:05 ⚀ ክፍል አምስት ⚀



......➲ በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።
የሙዚቃው ስሜት በለሆሳስ በውስጤ እየተርመሰመሰ ከንፋሱ ጋር በትዝታ ሰረገላ ላይ በደመና ክምር ውስጥ ይዞኝ እየነጎደ ነው።
ድምፁ በልጅነታችን በተረት የምናውቃትን የተረት ከተማ ኩልል አድርጎ ያስቃኛል። የግጥም እና የዜማው ቁርኝት የልቤን በር ከፍቶ አንድን ሰው እንዳስብ እያደረገኝ ነው።በሌላ በኩል ክረምቱንም በግጥሙ ከትቦታል።
....... የደጃፌን መዝጊያ ክፍት አድርጌው ነበር
ዛሬም አልተዘጋም ሳትመለስ ስትቀር
አይኔ በእምባ ጭጋግ እንደተጋረደ
ስንት ሰኔ ጠብቶ ስንት ክረምት ሄደ

እየቆረቆረኝ እያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነፍሴ..

እያለ ይቀኛል።ግጥም እና ዜማው እንደ ድር እና ማግ ከድምፁ ጋር ተሰፍቷል ማለት ይቻላል። ሙዚቃውን እናጣጣምኩኝ መናፈሻው ጋ ደረስኩኝ። ሁሌም መናፈሻው ጋር ስደርስ ማዘውተሪያው ፊት ለፊት የድንች ጥብስ ከሚሸጡት ሰዎች ድንች ገዝቶ እየበሉ መሄድ ወደቤት መመለስ ልምዴ ነው። ሙዚቃው ከስሜቴ ጋር ዘለአለማዊ ህያው ምጥቀትን ያላበሰኝ ያህል ከደም ዝውውሬ ጋር የተዋሃደ መሰለኝ።
... አንቺው ጋር ይቀመጥ እባክሺ የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን ምን አጥቼ እኔ ልንገላታ

ማዘውተሪያውን ተሻግሬ የጅማ ሙዚየሙ በር አከባቢ ስደርስ ከፊት ለፊቴ ያየውትን ማመን አቃተኝ። ልቤ በደስታ ይሁን በድንጋጤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር። ጭንቀት የመከነበት ፤ ደስታ የተንጠፈጠፈበት ፊት አስተዋልኩ። ስታየኝ ፈገግ አለች። እኔም ፈገግኩ። ፍሌም ናት።
በዚህ የመልዓከ ሞት ፈረስ መጋለቢያ ሜዳ በመሰለው ጭጋጋም ምሽት እሷን ማግኘት መታደል ነው ስል አሰብኩኝ።
አንዳች ደስታ ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል።
የፍሌም ፀዓዳ መሳይ ቀይ ፊቷ እና የሲኦል የፍም ገላ የመሰለው ከንፈሯ ሸሽቶ ጥርስዋ ብቅ ሲል ጉራማይሌዋ በምሽቱ ጭላንጭል ብርሃን ሲታየኝ አለማንም ከልካይ ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍኳት። ምንም አላለችም ይልቁንም አፀፋዋን በማቀፍ መለሰች።
"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።..............


ክፍል ስድስት ይቀጥላል........



▃▅▆█ ፍሌም █▆▅▃
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21
46 viewsረድኤተ አምላክ, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 23:13:11 ⚀ ክፍል አራት ⚀



የጅማ መድሃኒያለም ሰፈር በነጭ ጋቢ ተደርቶ የሚቆዝም ሽማግሌ ይመስል የጉም ጢስ ተከናንቦ ፀሀይ መውጣት፤ወገግ ማለትን ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል።
ከፍሌም ጋር ምንም ሳናወራ ረጅም መንገድ ተጓዝን በጅማ መድሃኒያያለም የመቃብር ስፍራ በኩል ባለው ወደ ዲፖ ቀበሌ ሶስት መታጠፊያ ቅያስ ጋር ስንደርስ ፍሌም ቆም አለች "በዚህ ነኝ "አለችኝ መታጠፊያውን በግራ እጇ እየጠቆመችኝ በገሚሱ መሬቱን በገሚሱ እኔን ገርመም አድርጋ እያየችኝ።
"እሺ ቻዎ " አልኳት እና ወደ ኃላ ተመልሼ ጥቂት እርምጃዎችን እንደተራመድኩ "ግሩም" አለችኝ
ዞር ስል ድብስብስ ባለ ጎህ በሚመስል የንጋት ወሰን ላይ የፈነጠቀች ፈዘዝ ያለች የፀሀይ ብርሃን የፈካባት ትንሽዬ ከተማ የመሰለች ደስታን በክብ ፊቷ ላይ አስተዋልኩ ፤ ለዘብ ባለ ድምፀት "ወዬ "አልኳት
"አመሰግናለሁ " ብላኝ ይበልጥ ፈገግ ብላ፤ በአጭሩ ፈገግታዋን መግባኝ ምላሼን ሳትጠብቅ ፍሌም ነጎደች ....ሄደች .......ራቀች.....ታጠፈች.....ጠፋች።
ቀኑ መሽቶ ነጋ አባቴ ባመጣሁት ውጤት ደስ ብሎት አደረ። ቤታችን ውስጥ ያለነው ሶስት ልጆች ነን።
ትንሹ ወንድሜ ቅዱስ፣ታናሽ እህቴ ትርሃስ እና እኔ ነን።የቤቱ ታላቅ እኔ መሆኔ ነው። አባቴ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሽልማት ላውቶፕ ኮምፒውተር እንደሚሸልመኝ ቃል ገባልኝ።ደስም አለኝ!!
ጠዋት ላይ ፍሌም መጥታ ከእኛ ጋር ስትጫወት ዋለች።ፍሌምን እኔ በአንድ አመት በትምህርት እበልጣታለሁ። የምትኖረው ድሬዳዋ ነበር።ያውም ከዚራ ውስጥ እዚህ ጂማ መድሃኒያለም ሰፈር አጎት አላት። የህንፃ ተቋራጭ ሀላፊ ነው።
እኔ ከምምጣቷ ይልቅ ስትሄድ መሸኘቱ ነው የልቤን የሚያደርሰው። ልክ አመሻሽ ላይ ልሸኛት ተዘጋጅቼ እየጠበቅኳት እያለሁ ትርሃስ "ፍሌሜ ነይ እንሂድ በዛውም ካርድ ገዝቼ ልመለስ!" አለቻት። ይሄኔ ትርሃስን ማነቅ ዳዳኝ፣ ተቃጠልኩኝ። ተሰናብቻት ክፍሌ ገብቼ የአልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጬ በሃሳብ እብከነከን ገባሁ። በዚህ ፍጥነት ለዚህች ልጅ ያለኝ ምልከታ ግራ አጋባኝ።
አይኗን፣ ከንፈሯን ይበልጥ ደግሞ ዲምፕሏን እያሰብኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ። ይሄ ከሆነ ከሁለት ሳምንት በኃላ የሆነ ቀን አመሻሽ ላይ ሀሳብ ጭንቅንቅ ሲያደርገኝ አየር ለመቀበል ብዬ ኮት ደርቤ ኤርፎኔን ከስልኬ ጋር ይዤ ወጣሁኝ። በመድሃኒአለም ቤተክርስቲያኑ አድርጌ ሽቅብ ወደ መንደራ ትምህርት ቤት አቅጣጫ አቀናሁ።
በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።.....


ክፍል አምስት ይቀጥላል.....

▃▅▆█ 웃 ፍሌም 웃 █▆▅▃

ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር teztash
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21
47 viewsረድኤተ አምላክ, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:02:10 ⚀ ክፍል ሶስት ⚀




....."እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?"አለችኝ ፊቷን ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።
እናቴ ደርብ ያለች የሴት ወይዘሮ ነች። እድሜዋ ወደ ሀምሳዎቹ እየሮጠ ነው።አባቴ ሲያገኛት ጠየም ያለች ወይዘሪት ስለነበረች አባቴ"ከአሳ የተቀዳ ውበት እያለ እንደሚያሞካሻት ሁሌም ይነግረን ነበር።
ግን አባቴ ይበልጥ ቀልቡን የሚስበው የጉንጮቿ ስርጉድ(ዲምፕሏ ) እና የጥርሷ ጉራማይሌ ነበር።
"እእ..ማ..ለት ውኃ .." ተንተባተብኩኝ እናቴ ልጅቷን ማናት ላለቻት ጥያቄ!
"ፍሌም እባላለሁ ሱቅ ተልኬ ጫማዬ አንሸራቶኝ ወድቄ ውኃ ስጠኝ ብዬው ነው ይቅርታ" አለች ልጅቷ ቅልጥፍናን በተላበሰ ትሁት አንደበት!!
ቅልጥፍናዋን እና ድፍረቷን ወደድኩት አንዳች ነገር እንደተናገረች ገምቻለሁ! ማለት ምንም የሰማው አልመሰለኝም። ፍሌም እባላለሁ ያለችውን ብቻ ነው በጥራት የሰማውት። ስሟ ውስጤ ቀረ እንደ ገደል ማሚቶ በጭንቅላቴ ውስጥ አስተጋባ! እናቴ ስትመጣ ደንግጬ እጇን ከለቀቅኩኝ ወዲህ ሙቀቷ ዘላለማዊ ይሆነኝ ዘንድ በእጄ ውስጥ የማሰርፀው ይመስል እጄን በእጄ አፋትጋለሁ።
....ዛሬ ግን ምን ነካኝ??
ለዚህች ልጅ ይህን ያህል መሆን ምን አስፈለገ ?
በዛ ላይ በዛሬ ያውም አሁን በአሁን!
ሆሆሆሆሆ ወይ ነዶ!
"ቲዲያ ምን ችግር አለው የኔ ልጅ ! የማነሽ ቆንጆ ደግሞ ነይ ሳሚኝ እስኪ " ብላ እናቴ ተጠጋቻት። ፍሌም ወደ ኃላ ሸሸት እያለች "ልብሴ ጭቃ ብቻ ነው እንዳላበላሽዎት "አለች። እናቴ ተጠግታት ግንባሯን ሳመቻት እና ወደ እኔ ዘወር ብላ"ግሩሜ እስኪ ከሚሚዬ ክፍል የሚሚዬን ቢጃማ አምጣላት! "አለችኝ እሩጬ ትርሃስ ክፍል ስገባ ከኮመዲኖ ላይ ተጣጥፎ የተቀመጠ ቢጃማ አግኝቼ ተመለስኩ።
እናቴ እና ፍሌም ቆመው ያወጋሉ። እናቴ እኔን ስታየኝ
" ጎሽ ግሩሜ ሻወር ቤቱን አሳያትና ሻወር ትውሰድ!"አለች
"አይ እንዲሁ እቤት ብሄድ ይሻላል ለሀገሩም አዲስ ስለሆንኩ አጎቴ ይሰጋል"አለች ፍሌም አንደበቷ ይጣፍጣል።የድምጿ ቅላፄ እንደ ወፍ ዜማ ለጆሮ ይስማማል!!
ከእናቴ ጋር አውግተው ሌላ ጊዜ መጥታ እንደምትጫወት ተነጋግረው ሸኛት ተብዬ ይዣት ከግቢው ወጣሁ።
የጅማ መድሃኒያለም ሰፈር በነጭ ጋቢ ተደርቶ የሚቆዝም ሽማግሌ ይመስል የጉም ጢስ ተከናንቦ ፀሀይ መውጣት፤ወገግ ማለትን ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል።......Selam


ክፍል አራት ይቀጥላል........



▃▅▆█ 웃 ፍሌም 웃 █▆▅▃
ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር አድርጉ !
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21
71 viewsረድኤተ አምላክ, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:38:40 ⚀ ክፍል ሁለት ⚀



.....የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ። በጣም እንደነጋ ያወቅኩት በሳሎኑ በኩል ወደ ውጪ እየወጣሁ የግድግዳ ሰዓታችንን ተመልክቼው ነበር። ቀኑ ድፍንፍን ያለ ነው። ማታ ዘንቦ ማደሩን የመሬቱ እርጥበት ያሳብቃል። የግቢውን በር ከፍቼ ስወጣ ጭራሽ ሰፈሩ በጉም ተከቧል።መጣ የተባለውን ከሰል ከዘበኛው ጋር አስገብተን ስንጨርስ የከሰሉን ማዳበሪያ የሸፈኑትን ቅጠሎች ከግቢ ውጪ ለመጣል ወጥቼ ጥዬ ወደ ቤት እየገባው የግቢያችን በር ላይ ስደርስ "ወንድም!" የሚል የሴት ድምፅ ሰማው።
ዞር ስል የሙስሊሞችን ሂጃብ የጠመጠመች ቀይ ባለሰልካካ አፍንጫ ፤ ውብ ፀዓዳ መሳይ አይኖችን የታደለች ፤ ቀይ ባለ ትንሽ ክብ ፊት ፤ ባለ ድንቡሽቡሽ ጉንጭ ሴት ቆማለች።
ድንግጥ አልኩኝ! ልቤ ትርክክ ፣ ስንጥቅ አለ። ድንገተኛ መባርቅ የመታኝ ያህል ክው አልኩኝ።
የማሪያምን ምስል የመሰለች ፤ የመላዕክታንን ውበት የታደለች ቆንጆ ልጅ ናት።
ልቤ የደም ዝውውሯን አፈጠነችው ትርታዬ ትር ትር ትል ጀመር።ቃል ሳላወጣ በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ አየዋት። እሷም ፍዝዝ ብላ ታየኝ ጀመር። ደፍሮ ቃል የሚያወጣ ጠፋ።
"ይቅርታ ሱቅ ተልኬ ጭቃ ነካኝ ውኃ..." አለች
እጇ በጭቃ ተበላሽቷል።ዝቅ ስል የለበሰችው ቢጃማም በጭቃ ደክርቷል። ለማየት የሚያሳሱ ውብ የአድማስ ዋልታ፣ የከዋክብት ፍንጣቂ የመሳሰሉ አይኖቿን አንከራተተችብኝ።
ውኃ ላመጣላት ተጣድፌ ወደ ቤት እየገባው ተገረምኩኝ 'ምን አይነት መሬት ቢሆን ነው እቺን ልዕልት የመሰለች ልጅ የጣላት? አይ የምድር ክፋት!' አልኩኝ በልቤ። ውኃውን በጆግ ቀድቼ ስመለስ ልጅቷ ግቢ ገብታ ነበር።
ውኃውን እያፈሰስኩላት እጇን እየታጠበች ልክ እጇ ጥርት ማለት ሲጀምር የቀኝ እጇ መሀከለኛው መዳፍ ላይ ትኩስ ትኩስ ቁስል አየሁኝ።
"እንዴ በእግዚአብሔር እየደማ እኮ ነው!" ብዬ ጆጉን ጣልኩና እጇን ለቀም አድርጌ ያዝኩት እጇን ስይዘው መላው ሰውነቴ በኤሌክትሪክ ሞገድ የተቀጣጠለ ይመስል አንዳች ሀይል መላው ሰውነቴን ነዘረኝ። እሷም ድንግጥ አለች!
ከአይኔ እየሸሸች "አ..ይ ....ትንሽ ነው ማለቴ..እእእ ዝም ብሎ ነው....ማለቴ አለ አይደል .. እእ" አለችና ቀና ብላ ውብ አይኗን አንከራተተችብኝ።
የሲኦል ፍም የመሰለው ፀዓዳ ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል። ከገነት ቅርንጫፎች የተመዘዙ ጭራሮ የመሳሰሉት የውብ አይኗ ሽፋሎች በፍጥነት ይርገበገባሉ።በዚህ ሁነት ውስጥ እንዳለን "ግሩሜ"የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል እናቴ ናት። "እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?" አለችኝ ፊቷን ኮስተር ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።.........


ክፍል ሶስት ይቀጥላል......



▃▅▆█ 웃 ፍሌም 웃 █▆▅▃

ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር አድርጉ !
https://t.me/teztash

https://t.me/teztash
171 viewsአምባ, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:09:55 https://t.me/teztash
134 viewsአምባ, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:08:56 ⚀ ክፍል አንድ ⚀

➲ .... የሀምሌን ሰማይ እንደ እኔ ከፍቶታል።ቀኑ ገና በንጋቱ ድብስብስ እያለ ነው የነጋው። ሀምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም እለተ እሮብ ጅማ መድሃኒያለም ሰፈር!
የሰኔ ሰላሳውን ግፊያ ፣ ትዝታ እና ናፍቆቱን አፈር ምሼ የቀበርኩበት እለት ከአስራ አንደኛ ክፍል ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል የመግባቴን ብስራት የሰማውበት ማግስት።
በእለቱ የእለቷ ፀሀይ ገና በሰበካው የተራሮችን ግርዶሽ ቀዳ ብቅ አላለችም።
እኔ አልጋዬ ላይ እንዳለሁ ድብርት ተጫጫነኝ። ከክፍል ጓደኞቼ በመለየቴ ክፍት ፣ ጥብብ ፣ ጭንቅ አለኝ።
ገና በጅማሬው ጠቁሮ እንደ አባቴ ቁጣ የሚያጉረመርመው ሰማይ በላዬ ላይ የወደቀ እስኪመስለኝ ድረስ ድብርት ተጫጫነኝ።
በአስቀያሚ ድብርት ውስጥ እንዳለሁ የክፍሌ በር ሲደበደብ ሰማው፤ እናቴ ናት።
መልሴን ሳትጠብቅ "ግሩም አባትህ ከሰል አምጥቷል ተነስና ከዘበኛው ጋር አስገባልኝ ዛሬ ውሎህን ተጋድመህ መዋልህ እኮ ነው! ግሩም!" አለች
ዝም አልኩኝ
" አንተ ግሩም " አለች ድምጿን ከፍ አድርጋ የበሩን ኳኳታ መጠን እየጨመረች " አቤት " አልኩኝ ድምፄን ከፍቶታል። "ግሩም! ምነው ልጄ አመመህ እንዴ? ድምፅህም ልክ አይደለም " አለች በሩ ላይ ጆሮዋን ልጥፍ አድርጋ።
"ደህና ነኝ" አልኳት በአጭር ቃል።
"ተነስ ቁርስህንም ብላ አባትህም መንገድ ላይ ከሰል አውርዷል እሱንም አስገባልኝ ጎሽ" አለች
"እሺ መጣሁ" አልኩኝ
ከእናቴ አጉል ውትወታ ለመትረፍ ብቻ! እናቴ ብዙም ሳትቆይ እንደሄደች የተረዳውት የኮቴዋ ዳና ከክፍሌ እየራቀ መሆኑን ስረዳ ነው።
አባቴ ልምድ ያለው የNGO ሹፌር ነው። የበርካታ አመታት የአሽከርካሪነት ልምድ አለው። በብዛት የመስክ ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
ለመስክ ስራ ወደሌላ አከባቢ ሲሄድ ሲሄድ በርከት ያሉ ከሰሎችን ይዞ ይመጣል።
ዛሬም ለሰባት ቀናት ከቆየበት የመስክ ስራ መመለሱ ነበር። መምጣቱን ሳውቅ እና ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል መግባቴ ትዝ ሲለኝ በዚህ የድብርት ስሜት አባቴን መቀበል አልፈለግኩም።
የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ።......


ክፍል ሁለት ይቀጥላል..



▃▅▆█ ፍሌም █▆▅▃

ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር ማድረግ ttps://t.me/teztash
https://t.me/teztash
138 viewsአምባ, edited  19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 05:33:00 Channel photo updated
02:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 05:20:59 አይነት ሁኖ ያለፈውን መጥፎ ገፅ ቢያስረሳህስ, ,, አየህ ሂወት ይቀጥላል ስለዚህ አንድ ገፅ ተበላሸ ብለህ አትቁም አንተ ገልጠህ ያላያሀቸው ብዙ መልካም ገፆች ይኖራሉኮ ማን ያውቃል በዛ ላይ አሁንም ወደ አንድ ቤተሰብ ልተሰበሰቡ ሆነ እንጂ ጭርሱን አላጣሀት እስኪ ቆይ ያኔ መጀመሪያ ስትገናኙ ሹራቧ ውስጥ ያገኜኸው ደብዳቤ የሷ ሁኖ በነበር ዛሬ በሂዎት ትኖር ነበር እንዴ ?? ንገረኛ አለች እኔ አንገቴን እንዳቀረቀርኩ ነው ሀዩ በዝምታየ ላይ ቀጠለች አየህ ሁሉም የሚሆነው በምክኒያት ነው የደረሰብህን እያሰብክ ከማማር ይልቅ ሊደርሰብህ ብሎ በፈጣሪ እዝነት ያልደረሰብህን ነገር አመዛዝነው በተናገረችው ነገር በጣም ተገርሜ እውነትም ያኔ ሙታ በነበር ሀዘኑ ምን ያክል ይጎዳኝ ነበር ስል እራሴን ጠየኩት ሀዩ እውነትም ልክም ነበረች ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክኒያት ነው በዝምታየ ውስጥ እንዳለሁ ጥምጥም አድርጌ አቀፍኳት ካለሁበት ጭንቀት ውስጥ በሷ ውስጥ ልደበቅ እሷም በምላሹ እንደኔው አቀፈችኝ ቤቱ በአንዴ ፀጥ ረጭ ያለ ድባብ ወረሰው እኔም የሀዩ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ይችን ግጥም በውስጤ አነበነብኩ
ብ ናስብም እኛ የሩቁን የማዶ
የጋራችን ፍቅር ላያድግ ተወልዶ
የጧት ጤዛ ሁኖ ውሎ የማያመሽ
ላፍታ ብቅ ብሎ ተኖ እንደሚሸሽ
በወጉ ሳንጠግብ ያብሮነትን ደስታ
የትናንት ፍቅራችን በግዜ ተረታ
የዘራነው መውደድ ይበቅላል በማለት
እንቡጡ ተቀጨ ፍሬው ሆነ ዘበት
እጣ ፈንታ ሆነ አልታደልንም በቃ
ያሁሉ ፍቅራችን ነበር ለደቂቃ
የህሉሀችን ገመድ ልኬቱ ሲሰመር
መርዘም ተገድቦ ተፅፎ ለማጠር
ይብቃችሁ እዚ ላይ በሉ ተለያዩ
ሲል አስቆመን ግዜ ጎጇችህን ለዩ
አንቺም አላጠፋሽ ምን አድርጌስ እኔ
ማንስ ይወቀሳል ምን ሰርቶ ኩነኔ
አባትሽም አይደል ወይንም እናቴ
በቃ የድ ፍርጃ አረገሽ እህቴ ።


°°°°°°\\°°°°°°°\\°°°°°°^^
ታሪኩ ተፈፀመ የህይወታችን ሌላኛው ገፅ ግን ተገለጠ
......//......//.....//...//.....
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

እናንተ እራሳችሁን የታሪኩ ባለቤት አድርጉና ሴቶቹ ሀኒን ብትሆኑ ወንዶቹ ደግሞ እኔን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር...? እዉነተኛ ስሜታችሁን እና በታሪኩ ዙሪያ ያላችሁን አስታየታችሁን @rediy21
112 viewsአምባ, 02:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 05:20:59 ከቤት ወጥቼ ትንሽ እንደሄድኩ እስኪ ቢሰራ ደውየ እድሌን ልሞክር ብየ ስልኬን ላወጣ ከኪሴ ስገባ ስልኬ የለም ትዝ ሲለኝ ሻወር ከመውሰዴ በፊት የለበስኩት የቱታየ ኪስ ውስጥ እንዳስቀመጥኩት ነበር ሱሪ ስቀይር የረሳሁት ከነበርኩበት በጥድፊያ ወደ ቤት ተመለስኩ በሩ ጋር ደርሼ ልገባ ስል ይልቅ ሰአቱ ሳይረፍድ ሁሉንም ብትነግሪው ይሻላል የሚለው የሀዩ ድምፅ ከውስጥ ወደ ውጭ ጆሮየ ላይ ጥልቅ አለ ባለሁበት ቀጥ ብየ ቆምኩና መላ አካሌን ጆሮ አድርጌ የሚያወሩትን ለመስማት ተዘጋጀሁ እህቴ ቀጠለች እኔኮ በስመ ደብረዘይት ዝምብየ ያልተጨበጠ ነገር ይዤ ከማወራው
መጀመሪያ ማሚ ጋር ልደውልላትና ስሙን ልጠይቃት ከዛም የሀኒን የአባት ስም እሱን ጠይቄ አንድ አይነት ከሆነ በቃ ምንም ማድረግ አልችልም እሱም እንደዚህ ከሚሆን ነግረዋለሁ የእህቴን መልስ የሰማችው ሀዩ ደግሞ እንዲህ ስትል ወሬዋን ቀጠለች እኔም የወሬያቼውን ፍንጭ እና መጨረሻ ለመስማት በቆምኩበት ቋምጫለሁ ግን አንቺ እንዳልሽው የሀኒ አባት በሚስትነት የተዋወቀው የእናንተን እናት ከሆነኮ በጣም ከባድ ነው አስበሽዋል ከአንቺና እናት እና ከልጅቱ አባት ልጅ ቢወለድ እኮ ለሁለቱም ወንድም ወይም እህት ነው የሚሆነው ይሄን ስሰማ ባለሁበት ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ሰውነቴ ድንዝዝ አለ ምኑ ከምኑ ጋር ተገናኝቶ ነው ያ ሊሆን የቻለው እህቴስ ይሄን ከማን እና እንዴት ሰምታው ነው ? በድን ሰውነቴን አንደምንም አንቀሳቅሼ በሩን አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ የሁለቱም አይን በድንጋጤ ፈጦ እኔ ላይ አረፈ ምንም ሳልናገር ፊት ለፊታቼው ሂጄ ተቀመጥኩ ምን ሁነህ ነው አለችኝ እህቴ በመመለሴና በወሬያቸው መሀል ድንገት በመገኜቴ ግማሽ ግርምት ግማሽ ድንጋጤ ውስጥ ሁና ሀዩ እንደፈዘዘች ናት እያወራችሁት የነበረውን በር ላይ ሁኜ ስሰማ ነበር እና አሁን ምንም ሳትደብቂ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገሪኝ አልኳት በጣም ተቆጥቼ ነበር እህቴ ደሞ አደለም በዚህ መልኩ ተናድጄ ይቅርና ድምፄ ትንሽ ለወጥ ካለ ድንብርብር ነው የምትለው ድምፇ ቁርጥቁርጥ እያለ እንዲህ አለችኝ ማሚ ባለፈው ደውላልኝ ነበር እናታችንን ማሚ እያልን ነው የምንጠራት እናም በስራ ምክኒያት ከሆነ ሰው ጋር ትውውቅ ጀምራ ነገሩ ወደ ትዳር እያመራ እንደሆነና አሁን ደሞ ልጆቹን ሊያስተዋውቃት ቀጠሮ እንደያዙ አውርታልኝ ነበር ይሄን ነገር ለኔ ብቻ ነው የነገረችኝ ለእናንተ አሁን ላይ እንዳልነግራችሁ እና አሷ ራሷ በሁኔታው ወስና ከጨረሰች በዃላ እንደምትነግራችሁ ጨምራ ነግራኛለች እናም የተዋወቀችው ሰው ነዋሪነቱ ደብረዘይት እንደሆነ ስለነገረችኝ ቀኑም ሀኒ ከሄደችበት ጋር ስለተመሳሰለብኝ በቃ ይሄን አሰብኩ አለችኝ የእናቴ ይሄን ነገር ለእህቴ ብቻ መንገሯ ምንም አላስገረመኝም ምክኒያቱም ከዚ በፊትም ቢሆን በእናቴ ዙሪያ ምንም አይነት ጉዳይ ሲኖር ከሁላችንም ቀድማ የምትሰማው እህቴ ናት ከሁሉም በፊት የቅርብ አማካሪዋ እሷና እሷ ብቻ ናት ሌሎቻችን ከረፈደ ነው የምንሰማው ያን ስለማቅ አልደነቀኝም አደንዝዞ ያስቀረኝ የነገሩ መገጣጠም ነው የፈለገ እውነቱ ቢመርም አንዴ ቁርጤን ማወቅ ግን ፈልጊያለሁ የሀኒን የአባት ስም አቀው ስለነበር ያን ለማረጋገጥ እህቴ ምንም እንዳልተፈጠረ በመሆን እናቴ ጋር ደውላ ስለትውውቃቼው ወሬ በማንሳት በሆነ መንገድ ስሙን ምናውቅበትን ሀሳብ አወራን ቁርጤን ማወቁ ቢያጓጓኝም ነገሩ እውነት እኛ እንዳሰብነው ቢሆንስ የሚለው ፍርሀቴና ጭንቀቴ ግን አያድርስ ነበር ምንም እንኳ በብቼኝነት ሌትና ቀን የምትገፋው እናቴ ሰምሮላት ለአዲስ ጎጆ የጀመረችው መንገድ እፎይታ ቢሰጠኝም ወዲህ ግን ጅምሩ ፍቅሬ፣ አዲሱ ፍቅሬ፣ ወደማላቀው ደስታ ያስገባኝ ፍቅሬ ብዙ ያሰብኩለት ፍቅሬ መና ሁኖ ሊቀር

መሆኑ ሲታሰበኝ ባለሁበት የሀዘን ጭልመት ከበበኝ በመጨረሻም እህቴ እናቴ ጋር ደውላ እያሳሳቀች ነገሩን መውጣጣት ጀምራለች እኔ መቁነጥነጤን ቀጥያለሁ ካፍታ የስልኩ ቆይታ ቡሀላ መራራው እውነት ፈረጠ እናቴ የተዋወቀችው አዲሱ እንጀራ አባቴ የሀኒ አባት ሁኖ አረፈው ምን ይባላል አሁን በማንስ ይፈረዳል ግዜ እኛ ላይ ሲፈርድ ይሄን የግጥምጥሞሽ ዳስ እኛ ላይ ደፋብን ቤቱ በአንዳች የዝምታ መንፈስ ተዋጠ በዚ መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ እህቴ ከኔ ቀድማ ብድግ ብላ ወደስልኬ በመሄድ አነሳችውና እስክሪኑ ላይ አፈጠጠች ወዲያው የፊቷ ገፅ ቅይር አለና ሀኒ ደወለች አለችኝ ወደኔ ስልኩን እየዘረጋች እጄ እየተርበተበተ ተቀበልኳትና ትንፋሼን ሳብ አድርጌ ለመረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን አነሳሁት ከሷ እስከሚመጣ ድረስ ምንም እንዳልሰማ ሁኜ መቀጠልን መርጫለሁ ።ድምፇ ለመጨረሻ ግዜ እንደሰማሁት አሁንም ቀዝቃዛ ነው ምን ሁነሽ ነው ምን ተፈጥሮ ነው? ይሄን ያክል ቀን ስልክሽን አጥፍተሽ ስታስጨንቂኝ የነበረው ስል ጠየኳት ፀጥ ብላ ቆየችና በቃ ምንብየ እንደምነግርህም አላቅም ከአቅሜ በላይ የሆነ ነገር ሆነብኝ ያሰለፍኳቼውን የስቃይ ቀናት እኔ ብቻ ነኝ የማቀው ወድጄም አይደለም ስልኬን ያጠፋሁት ድምፇ እየተቆራረጠ ወደ ለቅሶ ቃና ተቀየረ ምንም እንኳ ሁኔታውን ቀደም ብየ ብሰማውም አሁን ይበልጥ ህመሙ ወደ ውስጤ ዘልቆ ሲገባ ታወቀኝ አይኖቼ እንባ ቋጠሩ ሀኒ ሳግ እየተናነቃት ወሬዋን ስትቀጥል የእኔም እንባዎች እየተንኳሉሉ መውረድ ጀመሩ እንደዛ አስቦርቆኝ የነበረው የአባቴ ዜና ተገልብጦ የመርዶ ያክል የሚከብድ ዱብዳ ሀነብኝ አባቴ ሚስት ብሎ ያስተዋወቀኝ የአንተን እናት ነው ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሷ ለቅሶ እኔንም ከነጭራሹ አሳጣኝ ከዛ በዃላ ምንም እንዲህ ነው ብየ የምናገረው ቃልም አልነበረኝ ልናገርም ብል አፌ ተያይዞል ደሞስ በዛ ሰአት እኔ ለራሴ አፅናኝ በሚያስፈልግብኝ ከየት አቅም አገኝቼስ ሀኒን አፅናናለሁ እሷ ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች እኔ ደግሞ በዝምታ ወደ ውስጥ እያነባሁ በተገተርኩበት እህቴ ጆሮየ ላይ ያለውን ስልክ ተቀብላኝ ሀሎ ሀኒ እያለች ወደውጭ ወጣች ምን እንደምታወራትም አላቅም ብቻ ብዙ ቆይታለች ።ቤቱ ውስጥ እኔና ሀዩ ቀርተናል ወደተቀመጥኩበት መጥታ ጎኔ አረፍ አለች በክሪሟ ጫፍ ከጉንጮቼ ላይ እንደመጥረግ እያደረገች በቃ አይዞህ እንደዚህ አትሁን እራሳህን አረጋጋ እስከመጨረሻውኮ አላጣሀትም ምንድነው እንደዚህ ባንዴ ተስፋ መቁረጥ አንተ ላይ ሳቅና ጨዋታ እንጂ መቆዘም አያምርብህም ለሰው መካሪ እንዳልነበርክ ዛሬ ምከሩኝ ልትል ነው እንዴ ቀጠለች ሀዩ በስስት እያየችኝ ደሞ ታውቃለሀ ሁሉም ሰው በራሱ ርእስ የተፃፈ መፅሀፍ አለው የገፃችን ብዛት ግን የት ጋር እንደሚቆም ማናችንም አናቀውም ። እና ደሞ የሂወታችን መፅሀፍ ውስጥ እያንዳንዱ ገፆች ላይ የተፃፈው ነገር ይለያያል የደስታ የሀዘን ፣ የመገናኜት የመለያየት፣የመሳቅ የማልቀስ፣ የማግኛት የማጣት፣ የመውደድ የመጥላት ፣ የመውደቅ የመነሳት የጠብ የመታረቅ ፣ የመሄድ የመምጣት ፣ የፈታ የድብርት ፣ የማትረፍ የመክሰር ፣ የመውደቅ የስኬት ብቻ ብዙ አይነት የሂወት ውጣ ውረዶች በገፆቹ ውስጥ ተፅፈውበታል። እናም በመኖር ሂደት ውስጥ ድንገት አንዱ ገፅ ሊበላሽብህ አልያም አንተ እንደጠበከው ሁኖ ላታገኛው ትችላለህ ነገር ግን ያ ሆነ ብለህ ቶሎ ብለህ ተስፋ መቁረጥ የለብህም ራስህንም እንደ እድለ ቢስ ማየትም ደሞ ይሄን አትርሳ ሁሉም የሚሆነው በምክኒያት ነው ሳይደግስ አይጣላም ሲበል አልሰማህም ይልቅ በርታ ብለህ በትእግስት እለፍና ቀጣዩን የሂዎትህን ገፅ ለመግለፅ ሞክር ማን ያቃል አዲስ የምትገልጠው የሂወት ገፅ የተሻለና አንተ የምትፈልገው አይነት ብቻ ሳይሆን ለአንተ የሚያስፈልግህ
94 viewsአምባ, 02:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ