Get Mystery Box with random crypto!

ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የሰርጥ አድራሻ: @szcommunication2012
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.58K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-10 10:44:56
508 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 10:43:16 የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ባለፉት 9 ወራት ሲከናወኑ የቆዩ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች የተመሩበትን አግባብ እና ያሉበትን ደረጃ ታች ተወርዶ ፍተሻ እና ምልከታ ካደረገው የሱፐር ቪዥን ግብረ-ሀይል ጋር የኢንስፔክሽን ግብረ-መልስ ሪፖርት ገምግሟል!

ግንቦት 01/2015 ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

የዚህ ሱፐርቪዥን ዋና አላማው በባለፉት ጊዜያት የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የተመሩበትና የተከናወኑበትን ሂደት የመፈተሽና በየመዋቅሩ የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶች ምን ቁመና ላይ እንዳሉ በመቃኘት በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት ማረምን ያለመ መሆኑን መድረኩን የመሩት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ተናግረዋል።

በ2015 በጀት አመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በተቋማትና በዞኑ በሚገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች እንዲሁም እስከታችኛው የፓርቲ አደረጃጀት ድረስ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት የተከናወኑበትን አኳኃን በመፈተሽ የታዩ መልካም አፈጻጸሞችን ማስቀጠል በሚቻልበት እና በሂደቱ የታዩ ጉድለቶችን ለማረም የመድረኩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ኃላፊው አክለው አንስተዋል።
505 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 18:24:25 የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንግድ ልማት መምሪያ በመምሪያውና በታችኞቹ መዋቅሮች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ!

ሚያዝያ 02/2015 ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

የመምሪያው ማኔጅመንት አካላትና የታችኛው መዋቅር የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በተደረገው የግምገማ መድረክ ላይ በመምሪያውና በየጽ/ቤቶቹ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት በገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ ፣ በመንገድ ደህንነት ቁጥጥር፣ በትራንስፖርት አገልግሎትና መሰል ዘርፎች ላይ የተከናወኑ አባይት ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ከህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች አንፃር በባለፉት ዘጠኝ ወራት በመንገድ ጥርጊያ፣ በድልድዮች ግንባታና ጥገና በገንዘብ መዋጮ እና በሌሎች መስኮች አመርቂ ስራዎች መሰራቱ በውይይቱ ተመላክቶዋል።

ከመንገድ ደህንነት አንፃር በዋናነት በአስፖልት መንገዶች ላይ በከባባድ የጭነት መኪኖችና የላቢያጆ አገልግሎት በሚሰጡ ድርጅቶች ምክንያት በመንገዶች ላይ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ከትራንስፖርት አገልግሎት አንፃር ከመጠን በላይ የመጫንና ከታሪፍ በላይ የማስከፈል ችግሮች በስፋት እንደሚስተዋሉ ተነስቶ ችግሩን ለመቅረፍ በላድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ ተጠይቋል።

የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊና ትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዩብ ሙስጠፋ በበኩላቸው ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር ተያይዞ በየቦታው የሚስታወሉት የትራፊክ አደጋዎች፣ያለ እድሜ ማሽከርከር፣ከመጠን በላይ መጫንና ሌሎችም ላይ አሁንም ዋናኛ ችግሮች መሆነቸውን አንስተዋል።

እነዚህንና መሰል ችግሮቹን ለመቅረፍ እስከ ታችኛው የማህበረሰብ የዘለቀ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አቶ አዩብ ጠቁመዋል።

የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊው አቶ ሱልጣን ራህመቶ በውይይቱ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች እንደነበሩ አንስተዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንግድ ስራዎች፣ የድልድዮች ግንባታና ጥገና፣ የውስጥ ለውስጥ የገጠር ተደራሽ መንገድ ላይና የመሳሰሉት ላይ የተሻለ አፈጻጸም እንደነበር አቶ ሱልጣን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በመንገድ ደህንነት ቁጥጥር፣ ትራንስፖርት ስምሪትና በታሪፍ ቁጥጥር፣ ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን መቆጣጠርና መከታተል፣ የትራፊክ አደጋን መከላከልና የመሳሰሉት ላይ የባለድርሻ አካላትን ቁርጠኝነት የሚጠይቁ ተጨማሪ ተግባራት መኖራቸውን አቶ ሱልጣን አንስተዋል።

አጠቃላይ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ተግባራትን በተሳለጠ ሁኔታ በመተግበር የዞኑን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ከፍ ያለ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ይጠበቃል ሲሉም ዋና ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012

ኢንስታግራም https://www.instagram.com/invites/contact/?i=17wjh7vmmcd1h&utm_content=qi2tfsc
241 views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 18:23:03
207 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 18:21:43
205 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 20:14:41 የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሁለተኛ ዙር የሳውዲ አረቢያ የስራ ስምሪት ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ወራቤ-መጋቢት 25/2015 የስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን።
*********************************
በዚሁ የ2ኛው ዙር ስልጠና መርሀ ግብር ላይ 1ሺህ ሰልጣኞች በ3 ባች ተከፋፍለው እስከ 21 ቀን የሚቆይ መሰረታዊ የክህሎት እና የእውቀት ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ቡላድ ናሙዝ በስልጠና ማስጀመሪያ መድረክ ተገኝተው ለሰልጣኞች በስልጠናው ዓላማ፣ ሂደት እና ፋይዳ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት የኮሌጁ ዲን በሰጡት ማብራሪያ የስራና ክህሎት ሚኒስተር ከተለያዩ የአረብ ሀገራት የስራ ስምሪት ውሎችን በመፈራረም ወደ ተግባር መግባቱን መነሻ በማድረግ ኮሌጁ መጀመሪያ ፍላጎት ላሳየችው ሳውዲ አረቢያ የስራ ስምሪት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።

በ2ኛው ዙር ስልጠናም 1ሺህ ሴት ሰልጣኞች መመዝገባቸውን በመግለጽ በ3 ባች ተከፋፈለው በቤት አያያዝ፣በምግብ ዝግጅት፣በልጅ አያያዝ፣በእንተርፕሪነርሺፕ፣ በቤት ስራ መሰረታዊ እውቀቶችና በማሽን አጠቃቀም ዙሪያ እስከ 21 ቀን የሚቆይ ከስራቸው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሙያዎችን እንደሚሰለጥኑ ተናግረዋል።
ለዚህም አስፈላጊ ቁሳቁሶችና አሳልጣኞች ተዘጋጅተው በወደ ተግባር መገባቱን አቶ ቡላድ ገልጸዋል።

የስልጠናው መርሃ-ግብር ቀደም ሲል አረብ ሀገር ሄደው የተመለሱ፣የዲግሪ ምሩቃን በቴክኒክና ሙያ ድፕሎማ እንዲሁም 12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ሴቶች ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ ለተመዘገቡ ወንዶች ጊዜውን ጠብቆ እንደሚሰጥም ተጠቁሟል።

ስልጠናው ከዚህ በፊት ተጓዦች የሚሄዱበትን ሀገር በቂ የስራ እውቀትና ክህሎት እንዲሁም ግንዛቤ ባለመጨበጣቸው ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን አካላዊ ፣ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከመቀነስም ባለፈ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ጠቀሚታ ያለው ነው ሲሉም አቶ ቡላድ ናሙዝ አስረድተዋል።

በኮሌጁ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ከዙኑ ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ፣ ቴክኒክና ሙያ መምሪ፣ እንዲሁም ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያዎች ጋር በቅንጅት ተግባሩ እየተሰራ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ሰልጣኞች የተፈጠረላቸውን መልካም እድል በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውንም ሀገራቸውንም ሊጠቅሙ እንደሚገባ መልእክት ተላልፏል።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012

ኢንስታግራም https://www.instagram.com/invites/contact/?i=17wjh7vmmcd1h&utm_content=qi2tfsc
539 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 09:09:40
363 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 02:16:41
401 views23:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:56:09 ቴክኖሎጂን ለተጠቃሚ ማህበረሰብ ለማሸጋገር የሚያስችል የእንሰት መፋቂያ ማሽን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የፓይለት የቴክኖሎጂ ፕሮግራም የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄዷል!

12/07/2015 ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

የእንሰት መፋቂያ ማሽን የፖይለት ፕሮጀክት በይፋ ለማስጀመር የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ቡላድ ናሙዝ፣የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምራያ ሀላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሁሴን፣የዞኑ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈድሉ ከድር፣ የወ/ ዩ/የማህ/አገልግሎት/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የዩኒቨርሲቲው ተወካይ አቶ ጀማል ርዱዋንን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የወረዳ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለተጠቃሚዎች ርክክብ ተደርጓል።

የወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ቡላድ ናሙዝ ከወራቤ ዩኒቨረስቲ ጋር በመተባበር የእንሰት መፋቂያ ማሽን የፖይለት ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ለማስተግበር ከተመረጡ ወረዳዎች አንዱ በሆነው በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በጀረሞ ቀበሌ የምክርቤት አባል በሆኑት በወ/ሮ ሀድራ ማመጫ በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂውን ለተመረጡ ወረዳዎች እንደ ፓይለት ፕሮጀክት ለቀጥተኛ ተጠቃሚዎች በማቅረብ እና በቀጣይ ሶስት ወር ውስጥ ከቴክኖሎጂ ፓይለት ፕሮጀክት በሳይንሳዊ መንገድ ከተጠቃሚዎች የተለያዩ ግብረ መልሶችን እና አስተያየቶችን በመሰብሰብ እና በመተንተን የማሻሻል ስራ በመስራት ወደ ሙሉ ትግበራ እና ቴክኖሎጂውን ወደ ገበያ ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የዞኑ ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ሀላፊ አቶ ፈድሉ ከድር በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ስራው አድካሚ የሆነው የእንሰት መፋቂያ የአሰራር ስርአት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ መሰራቱ ጊዜና ጉልበትን ቆጥቦ ለመስራት ጠቃሚ እንደሆነ አንስተዋል።

ለእንደዚህ አይነት የፈጠራ ስራዎች እንዲተገበሩና እንዲሰሩ የሚያስችል የተማረና የሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲኖር ለማድረግ የአከባቢው ማህበረሰቡ በስልጠና ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራበት አስገንውበዋል።

የዞኑ ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ጀሚላ ሁሴን ከዚህ ቀደም እናቶችን በባህላዊ የእንሰት መፋቃያ አሰራር ይደክሙ እንደነበር በመግለፅ አሁን ከዛ ድካም ወጥተው ለዘመናዊ የእንሰት መፋቂያ መብቃታቸውን አብስረዋል።

የረጅም ጊዜ የአከባቢው ህብረተሰብ ጥያቄ የነበረው የእንሰት መፋቂያ ማሽን ሁሉም በመተባበር ማሽኑ ተሰርቶ ለአገልግሎት መብቃቱ የእናቶችንም ድካም የሚቀርፍና ለተሻለ ቴክኖሎጂ የሚያበቃ እንደሆነም ተናግረዋል።

የወራቤ ዩኒቨረስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የዩኒቨርሲቲው ተወካይ አቶ ጀማል ርዱዋን ዩኒቨረስቲው ማህበረስቡን ለመጥቀም የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚትሉ ሁለንተናዊ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ዩኒቨረስቲው ከወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመደጋገፍ እና በመተባበር የፈጠራና የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለመስራት ዝግጅነቱን ገልጿል።

ከነዚህ ከእንሰት መፋቂያ ማሽን በተጨማሪም በ2015 ዓ/ም የበቆሎ መፈልፈያ ማሽን እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ዩንቨረስቲው ድጋፍ በማድረግ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ጋር ወደ ትግበራ ለመግባት እቅድ ይዘው እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል።

ተጨማሪ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012

ኢንስታግራም https://www.instagram.com/invites/contact/?i=17wjh7vmmcd1h&utm_content=qi2tfsc
432 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 16:08:34
243 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ