Get Mystery Box with random crypto!

ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የሰርጥ አድራሻ: @szcommunication2012
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.58K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-06-21 17:16:35
997 views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 14:59:51
ቁጭ ብለን ተጠቅልሎ የሚጎረስ ጉርሻ የምንጠብቅ ከሆነ መቼም ቢሆን ከመለመን አንላቀቅም!!

ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
1.5K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 23:15:41 ከስር ያለው አድራሻ የስልጤ ኤፍ ኤም 92.6 የቴሌግራም ቻናል ነው።ጆይን በማድረግ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

https://t.me/siltieFM
1.5K views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:39:26 ከበልግ አዝመራ ጎን ለጎን በዞኑ ከፍተኛ የቡና አቅም ባላቸው የዞኑ አካባቢዎች በ2014/15 የምርት ዘመን በ1666.6ሄክታር አዲስ መሬት ላይ 6.02 ሚሊየን ቡና ችግኝ በመትከል ለመሸፈን አቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በስልጤ በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ከሚገኙት ሌሎች ወቅታዊ ተግባራት በተጓዳኝ የቡና ተከላና ዝግጅት ላይ በስካሁኑ ሂደትም 5.82ሚሊየን ጉድጓድ በማዘጋጀት 0.37 ሚሊየን ችግኝ የተተከለ መሆኑንም የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን ገልጸዋል።

በዞኑ በቡና ክላስተር በተለዩ በስምንት መዋቅሮች ውስጥ በ19 ቀበሌዎች በ190 አርሶ አደሮች እያንዳንዱ አርሶ አደር እስከ 500 ቡና ችግኝ እንዲተከል ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የዞኑ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ኑሪ ናቸው።

በአጠቃላይ 95000 ችግኝ በሙሉ ፓኬጅ (ጥላ ዛፍ ኮምፖስት) ለማስተከል ታቅዶ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል ያሉት የጽ/ቤት ኃላፊው ይህም በመሆኑ እስካሁን ባለው ሂደት በ20 ቀበሌዎች በ297 አርሶ አደሮች 91267 የጉድጓድ ዝግጅት በማድረግ የተከላ ስራ ተጀምሯል ብለዋል።

በሰሞኑ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የቡና ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ፣በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማንና በሌሎች በዞን ከፍተኛ የአመራር አካላት የተከላ ፕሮግራሙን በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል።

በዞኑ ስምንት ወረዳዎች በቡና ክላስተር የተለዩት ሲሆን እነሱም ስልጢ፣ምስራቅ ስልጢ፣ዳሎቻ፣ሚቶ፣ላንፍሮ፣ ሁልባራግ፣ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳና ሳንኩራ ወረዳ መሆናቸውን ከዞኑ ቡናና ቅመማ ቅመም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ነው
1.4K viewsedited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:39:24
1.1K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ