Get Mystery Box with random crypto!

ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የቴሌግራም ቻናል አርማ szcommunication2012 — ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
የሰርጥ አድራሻ: @szcommunication2012
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.58K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-01-09 20:11:51 የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በብልፅግና ፓርቲ የአመራር ምዘና ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ኦረንቴሽን ሰጠ!

ጥር 01/05/2015 ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን

በስልጤ ዞን የትምህርት መምሪያ ሀላፊ በአቶ ሹክራላ አወል የመወያያ ሰነዱ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎል።

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ሙሁራን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመፍጠር ዘላቂ ሰላም መገንባትና ብሔራዊ መግባባት ላይ በተገቢው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በሀገራዊ የሰላም ጉዳይ ላይ በቁርጠኝነት በመሳተፍ የሙሁራን ተሳትፎ በሁሉም ዘንድ ሚናቸውን እንዲወጡ ታሳቢ ያደረገ ስልጠና መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012
267 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:26:08
325 views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 16:13:29 ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግና አባላትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማፍራት የሚያስችል የውስጠ ፓርቲ አመራር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ነው፦ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ!

ጥር 01/05/2015፣ ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን፣ ወራቤ

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በብልፅግና ፓርቲ የአመራር ምዘና ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ለባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያከሄደ ይገኛል።

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይ እውን እንዲሆን በአስተሳሰባቸው፣ በስነ-ምግባራቸው፣ በእውቀታቸው፣ በክህሎታቸው፣ በአፈፃፀም ብቃታቸው የላቁ አመራሮችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማፍራት የሚያስችል የውስጠ ፓርቲ አመራር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ተቋማዊ መሰረት ያለው ከማንኛውም አድሏዊ አሰራር ነፃ የሆነ የአመራር ምዘና ስርዓት በመዘርጋት የአመራር አፈፃፀም ምዘና ውጤት መሰረት ባደረገ እና አሳታፊ፣ ግልፅ ወጥና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ውጤታማነቱን ማሳየት በሚሉ መርሆች የሚተገበር መሆኑን ነው ዋና ሀላፊው የገለጹት።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን በዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ሸረፋ ሌገሶ እና በዞኑ በፕላን መምሪያ ሀላፊው በአቶ አብዱልሰመድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደሬጎበታል።

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012
352 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 22:54:58 በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ የሚፈጸም ማዋከብ ሊቆም እንደሚገባ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ!!

መገናኛ ብዙሃን በሚያከናውኗቸው የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራዎች ላይ በማንኛውም አካል የሚፈጸም ማዋከብ ሊቆም እንደሚገባ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣኑ በተለይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ አጋዥ ተዋናይ መሆን የሚጠበቅባቸው የህፍሕ አካላት ለዚህ ስራ ተባባሪ እንጂ እክል እንዳይሆኑም ጥሪውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዛሬ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ለመገናኛ ብዙሃን ስራ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር በህግ የተጣለበትን ሃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር የምርመራ ዘገባ በሚያከናውኑ ባለሙያዎችና ተቋማት ላይ የሚፈጸም ማዋከብ መቆም እንዳለበት አሳስቧል።

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 እና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 48 መሰረት መገናኛ ብዙሃን የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብት እንዳላቸው ያመለከተው መግለጫው የምርመራ ጋዜጠኝነትን ከማበረታታ አንጻርም እንደ መንግስት አቅጣጫ ተይዞ እንዲሰራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቅሷል።

በመርህ ደረጃ የዜጎች መብት የተረጋገጠበት የዴሞክራሲ ባህል የሚጎለብትበትና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ስርዓት ለመገንባት የፍትህ አካላት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር መስራታቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጿል።

ይህ ሊረጋገጥ የሚችለው መገናኛ ብዙሃን ያለምንም መታወክና እንቅፋት ብቁ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ እንዲሰሩ መረጃ የማግኘት የመሰብሰብና የማሰራጨት መብታቸው ከማንም በላይ በፍትሕ አካላት ሲረጋገጥና ጥበቃ ሲደረግለት እንደሆነም አስታውቋል።

ከዚህ በተቃረነ አግባብ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ ላይ በማንኛውም መንገድ እክል መፍጠር የዜጎች መብትን መደፍጠጥ፣የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠር እንዲሁም ተጠያቂነት እንዳይሰፍን ከአጥፊዎች ጋር እንደመተባበር ይቆጠራል ሲል በመግለጫው አስታውቋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራዎች እንዲቆሙ ትዕዛዝ የመስጠት አዝማሚያ እየተስተዋለ መጥቷል ያለው መግለጫው በማንኛውም አካል የሚፈጸም ማዋከብ ሊቆም እንደሚገባ አሳስቧል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
191 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 22:54:55
185 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-17 18:11:21
399 views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-17 18:10:57 በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ሊግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ስንችል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ርብርብ የሚያበረክተው አስተዋጾ ከፍተኛ ነው፦ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ኃላፊ

ተህሳስ 2015 ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የ2015 የበጀት አመት በአምስት ወራት በዘርፉ በየደረጃው የተከናወኑ ሁሉ አቀፍ ተግባራትን አስመልክቶ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት ጋር በወራቤ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄዷል።

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲቻል የሴቶችን አደረጃጀቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ዋና ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ ለዚህ ተግባር መሳካት ደግሞ በዋናነት የዘርፉ ኃላፊዎች ሚና የጎላ በመሆኑ የተጠናከሩ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

የዘርፉን አደረጃጀቶች ማጠናከር ማለት የብልጽግና ፓርቲን ማጠናከር ከመሆኑም ባለፈ ሴቶች በሚያጋጥሟቸው ችግሮችና እንቅፋቶች ዙሪያ ተደጋግፈውና ተመካክረው መሻገር እንዲችሉ በማድረግ ሴቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን አስተዋጾ በመረዳት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ጠቁመዋል።

በመድረኩም የዞኑ የሴቶች ሊግ በ2015 በጀት አመት በ5 ወር ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ የተመረጡ መዋቅሮች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በወረዳና በከተማ አስተዳደሮች የተካሄደው የኢንስፔክሽን ሪፖርት ቀርቦ በኢንስፔክሽኑ በተለዩ ጉድለቶችና ጥንካሬዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የ2015 የእቅድ ዝግጅት ሂደት፣የጉባኤ አቅጣጫና ውሳኔዎች መድረክ የተመራበት ሂደትና በሴቶች የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የጋራ ተደርጎ የእቅድ አካል ሆነው እየተመለሱና እየተፈቱ ያሉበት ሁኔታም ተገምግሟል።

አዳዲስ አባላት ምልመላና መረጃ የማጥራት ስራ፣በአጠቃላይ ከሊጉ የአደረጃጀትና የፖለቲካ ስራዎች በተጨማሪ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በጤናው መስክ የእናቶች ማቆያና ወሊድ ክፍል አካባቢ፣ግብርናው ላይ በእንስሳት ዘርፍና በጓሮ አትክልት ልማት የተሰሩ ስራዎችን ለሊጉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ለፓርቲ አመራሩ የአካል ግብረ-መልስ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

የስልጤ ዞን ብልፅግና ሴቶች ሊግ አደረጃጃት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ መህዲያ ሀምደላ በበኩላቸው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው የሴቶች ሊግ የመሪነት ሚነቸውን በአግባቡ ሲወጡ ነው።

ሁሉ አቀፍ ሴቶችን ከመሰረታዊ ድርጅት እስከ የሊጉ አባል ድረስ ውጤታማ ግንዛቤ በመፍጠር እና በማስጨበጥ የሴቶች አደረጃጀት የተሻለ ቁመና እንዲኖረው ሁሉም ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።
406 views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 19:54:41
416 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 19:54:40
የተለያዩ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በሎ ቀሪሶና በሰሜን ጎቶ ቀበሌ የበጋ የመስኖ ስንዴን የማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተከናወነ!

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ፣የዞኑ ዋና አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር፣የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ቀድሩ አብደላ፣የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብር መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙርሰል አማን፣የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሊያ ሀሰንና ሌሎች የዞኑና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ባለሞያዎች በተገኙበት በሰደ ጎራ ቀበሌ አትጋቦት ክላስተር እና በሎ ቀሪሶ ቀበሌ ለይለተል ቀድር ክላስተር ወረዳዊ የዘር ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ተከናውኖዋል።
424 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 19:54:38
በዞኑ ዋና አስተዳደሪ የተመራው ልዑክ በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በሀይቁ ዙሪያ ብቻ ከ20 ሄክታር መሬት በላይ እየለማ ያለውን የአርባ ምንጭ ዝርያ ያለውን የሙዝ ክላስተር የደረሰበት ደረጃ ምልከታ አድርገዋል!

በሀይቁ ዳርቻ እየለማ በሚገኘው በሙዝ ማሳ ውስጥም ጎመን፣ምጥምጣ፣ቀይስርና ሌሎች አትክልቶችን በማልማት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ ከመሆኑም ባለፈ በዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮባቸው እየተጉ ይገኛሉ።
401 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ