Get Mystery Box with random crypto!

በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ሊግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ስንችል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለ | ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ሊግ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ስንችል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ርብርብ የሚያበረክተው አስተዋጾ ከፍተኛ ነው፦ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ኃላፊ

ተህሳስ 2015 ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የ2015 የበጀት አመት በአምስት ወራት በዘርፉ በየደረጃው የተከናወኑ ሁሉ አቀፍ ተግባራትን አስመልክቶ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች ባለድርሻ አካላት ጋር በወራቤ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄዷል።

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲቻል የሴቶችን አደረጃጀቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ዋና ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ ለዚህ ተግባር መሳካት ደግሞ በዋናነት የዘርፉ ኃላፊዎች ሚና የጎላ በመሆኑ የተጠናከሩ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

የዘርፉን አደረጃጀቶች ማጠናከር ማለት የብልጽግና ፓርቲን ማጠናከር ከመሆኑም ባለፈ ሴቶች በሚያጋጥሟቸው ችግሮችና እንቅፋቶች ዙሪያ ተደጋግፈውና ተመካክረው መሻገር እንዲችሉ በማድረግ ሴቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን አስተዋጾ በመረዳት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ጠቁመዋል።

በመድረኩም የዞኑ የሴቶች ሊግ በ2015 በጀት አመት በ5 ወር ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ የተመረጡ መዋቅሮች ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በወረዳና በከተማ አስተዳደሮች የተካሄደው የኢንስፔክሽን ሪፖርት ቀርቦ በኢንስፔክሽኑ በተለዩ ጉድለቶችና ጥንካሬዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የ2015 የእቅድ ዝግጅት ሂደት፣የጉባኤ አቅጣጫና ውሳኔዎች መድረክ የተመራበት ሂደትና በሴቶች የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር የጋራ ተደርጎ የእቅድ አካል ሆነው እየተመለሱና እየተፈቱ ያሉበት ሁኔታም ተገምግሟል።

አዳዲስ አባላት ምልመላና መረጃ የማጥራት ስራ፣በአጠቃላይ ከሊጉ የአደረጃጀትና የፖለቲካ ስራዎች በተጨማሪ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በጤናው መስክ የእናቶች ማቆያና ወሊድ ክፍል አካባቢ፣ግብርናው ላይ በእንስሳት ዘርፍና በጓሮ አትክልት ልማት የተሰሩ ስራዎችን ለሊጉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ለፓርቲ አመራሩ የአካል ግብረ-መልስ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

የስልጤ ዞን ብልፅግና ሴቶች ሊግ አደረጃጃት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ መህዲያ ሀምደላ በበኩላቸው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው የሴቶች ሊግ የመሪነት ሚነቸውን በአግባቡ ሲወጡ ነው።

ሁሉ አቀፍ ሴቶችን ከመሰረታዊ ድርጅት እስከ የሊጉ አባል ድረስ ውጤታማ ግንዛቤ በመፍጠር እና በማስጨበጥ የሴቶች አደረጃጀት የተሻለ ቁመና እንዲኖረው ሁሉም ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።