Get Mystery Box with random crypto!

ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግና አባላትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማፍራት | ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይን እውን ለማድረግና አባላትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማፍራት የሚያስችል የውስጠ ፓርቲ አመራር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ነው፦ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ!

ጥር 01/05/2015፣ ስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን፣ ወራቤ

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በብልፅግና ፓርቲ የአመራር ምዘና ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ለባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያከሄደ ይገኛል።

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይ እውን እንዲሆን በአስተሳሰባቸው፣ በስነ-ምግባራቸው፣ በእውቀታቸው፣ በክህሎታቸው፣ በአፈፃፀም ብቃታቸው የላቁ አመራሮችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማፍራት የሚያስችል የውስጠ ፓርቲ አመራር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ተቋማዊ መሰረት ያለው ከማንኛውም አድሏዊ አሰራር ነፃ የሆነ የአመራር ምዘና ስርዓት በመዘርጋት የአመራር አፈፃፀም ምዘና ውጤት መሰረት ባደረገ እና አሳታፊ፣ ግልፅ ወጥና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ውጤታማነቱን ማሳየት በሚሉ መርሆች የሚተገበር መሆኑን ነው ዋና ሀላፊው የገለጹት።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን በዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ሸረፋ ሌገሶ እና በዞኑ በፕላን መምሪያ ሀላፊው በአቶ አብዱልሰመድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደሬጎበታል።

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012