2022-08-28 16:35:10
በባለፈው የ2014 የበጀት አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና በማጠናከር በ2015 የዞኑን ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ አማራጭ ያሌለው ጉዳይ በመሆኑ አመራሩ ከመቼውም በላይ በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር አሳሰቡ።
ዋና አስተዳዳሪው ይህን ያሉት የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ከአጠቃላይ ከዞን ማዕከል አመራሮች እና በዞኑ ከሚገኙ የከተማ አስተዳደሮችና የወረዳ አስተባባሪ አካላት ጋር የ2014 በጀት ዓመት የአመራር የተግባር ግምገማና የ2015 በጀት የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክ በተጀመረት ወቅት ነው።
በዚህ መነሻም የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት "ለብልጽግና ጉዟችን ስኬት በተደራጀ መንገድ እንረባረባለን" በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር የተግባር ግምገማና የ2015 በጀት የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረክን እያካሄደ ይገኛል።
የውይይት መድረኩ የመሩት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር እንዳሉት በሀገራዊ በለውጡ ሂደት ያጋጠሙ ፈተናዎችና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ዛሬ ላይ ደርሰናል።
አሁንም ከተለያዩ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ፈተናዎች እናጋጠሙን ይገኛሉ ያሉት አቶ አሊ ከድር እነዚህንና መሰል የሚያጋጥሙ ሀገራዊና ከባቢያዊ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ሀገርን ማሻገር የሚያስችል አመራር የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን።ይህንን ለማሳካት ደግሞ ይሄ መድረክ ከፍተኛ አስተዋጾን የሚያበረክት በመሆኑ ሁሉም ተሳታፊ አመራሮች በመድረኩ የሁለት ቀናት ቆይታ ውስጥ የሚጠበቁ ግቦችን ለማሳካት ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
መድረኩን ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጋር በመሆን የመሩት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቀድሩ አብደላ ባሳለፍነው የ2014 የስራ ዘመን በዞናችን የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ተግባራትን ለማጠናቀቅ የአመራሩን ቁርጠኛ የሆነ ትግልና ትጋት የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉም አስረድተዋል።
በሳለፍነው የበጀት አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና በማጠናከር በ2015 የዞኑን ህዝብ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአግባቡ መመለስ አማራጭ ያሌለው ጉዳይ ነው ያሉት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አቶ ቀድሩ አብደላ ናቸው።
ይህም በመሆኑ የዞናችን መላው አመራር የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞን የሚያቀጭጩና የሚገዳደሩ ጉዳዮችን ነቅቶ በመከታተል የለገራችንን ብልጽግና ከዳር ለማድረስ በሚደረው ርብርብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተግተን ልንሰራ ይገባል ያሉት አቶ ቀድሩ አብደላ በሌላ በኩል በየደረጃው ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የአመራሩ ውጤታማነት የላቀ ሚና ኣለው ብለዋል።
አጠቃላይ የዞኑን አመራር ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የየመዋቅሮቹ የአስተባባሪ አካላት የመድረኩ ተሳታፊዎች ናቸው።
ይህ መድረክ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን መድረኩ ላይም በ2015 የበጀት አመት በትኩረት ሊሰራባቸው በሚገቡ ነጥቦችና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት በመምከርና በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
573 views13:35