Get Mystery Box with random crypto!

ለጠየኩት ጥያቄ ከሱ የተመለሰልኝ መልስ ግን እንዲህ ነበር እዛው ታክሲዋ ውስጥ ሳለን አንዴት ግን | የኔው ታሪክ 8315

ለጠየኩት ጥያቄ ከሱ የተመለሰልኝ መልስ ግን እንዲህ ነበር እዛው ታክሲዋ ውስጥ ሳለን አንዴት ግን ያ እኔ ማቀው ናቲ ያቺንም ያቺንም ቆንጆ ከመልከፍ ታቅቦ አንዲት ልጅ ጋር ለዛውም በአጭር ግዜ ውስጥ በፍቅር ክንፍ ብሎ ለትዳር ማሰብ በቃ ስል ጠየኩት ናቲ ወደ ዃላው ለጠጥ ብሎ በምቾት ተቀመጠና አየህ ቆንጆ ስለሆንክ ወይ ቆንጆ ስላሳደድክ አይደለም ቁምነገሩ ፍቅር አንተ ስለፈለክ የምታመጣው አንተ ስለሼሼህ የምትሼሼው ነገር አይደለም
እርስ በርስ መዋደድ እና መፈላለግም ብቻውን ፍቅር ሚመስላቼው ብዙ ናቼው ግን ያ አይደለም፣ ማሬ ውዴ ሂወቴ መባባልም ሆነ ጥንድ ሁኖ አብሮ መቆየትም ብቻውን ፍቅርን ሊሆን አይችልም። ፍቅር ፍፁም ጥልቅ እውነት ነው ፍፁም እውነት ደሞ ፈጣሪ ብቻ ነው ስለዚህ ለኛም እውነተኛ ፍቅር ሊሆን የሚችለው ከላይ ከአንድየ የሚፃፍልን ብቻና ብቻ ነው ከዛ ውጭ ያለው እኛ በተለምዶ ወይም በኛ ጭላንጭላዊ እይታ ፍቅር እያልን የምንጠራው በጋራ ጥቅም የተሳሰረ አንዱ ባንዱ ላይ ጥገኛ ሁኖ የመኖርን ሁናቴ ነው ። ፍቅር መሰጠት ነው በቃ የተሰጠህን ስታገኝ ያንተን ሰው ስታገኝ ሁሉንም ነገር ትተዋለህ ሌላ አዲስ ሰው ትሆናለህ ደሞ ነገ ከማን ጋር ምን እንደሚኖርህ ምን እንደሚገጥምህ አንተ ብቻ ሳትሆን ሂዎትም አብራ ነው የምቶስነው በፍቅር አምስትና ስድስት አመት አብረው ቆይተው በስተመጨረሻ ግን እሷም ሌላ አግብታ እሱም ሌላ አግብቶ ለየቅል ጎጆ ኗሪ የሆኑትን ቤት ይቁጠራቼው በዛው ልክ ደግሞ በተዋወቁ በጥቂት ግዚያት ውስጥ ተጋብተው ወልደው ከብደው የሚኖሩ ብዙዎች ናቼው ለዛም ነው ፍቅር እና አብሮነት መሰጠት ነው ያለኩህ እንግዲህ ሜሮንም ለኔ የተሰጠች የሂዎት ስጦታ ሁና ይሆናላ ብሎ በፈገግታ ዙሮ አየኝ ምንም አልተናገርኩም ነበር በናቲ መልስ ተገርሜ ፀጥ አልኩ ዛሬ ያሁሉ አልፎ ናቲ ከሜሮን ጋር ተጋብቶ የሁለት ሴት ልጆች የአባትነት ማዕረግ ጋር በደስታ እየኖረ ይገኛል ። እውነትም ፍቅር መሰጠት ነው ሀኒስ ለኔ የተፃፈች እና ከላይ የተሰጠች ሴት ትሆን? ራሴን ጠየኩ መለስ ግን የለኝም ነበር የነገን ነገ ራሱ ያውቀዋል ፣ ሂዎት ራሱ መልስ ይሰጥበታል
በማላቀው የነገ ጥያቄ ዛሬየን ለምን አጨናንቃለሁ ስል ለራሴ ሹክ አልኩት ። እህቴ ጋር ላለብን የምሳ ግብዣ በሰአቱ ለመገኜት እኔና ሀኒ ከፎቶ ቤት ወጥተን መንገዳችንን ወደኛ ቤት አቅጣጫ አድርገናል በዚህ መሀል ከኪሴ ውስጥ ያለው ስልኬ አዲስ መልእክት መግባቱን የሚያበስር ንዝረት ነዘረኝ ሀኒን አቅፎ የነበረውን እጄን ከትከሻዋ ላይ አወረድኩና ስልኬን አወጣሁ እና መልክቱን ከፈትኩት አዲስ ቁጥር ነው ከዚ በፊት አላቀውም ቁጥሩን ተውኩና መልክቱን አነበብኩ " አብራህ ስላለችው ልጅ ምን ያህል ታውቃለህ " ነበር የሚለው •••••

ይቀጥላል...
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ lemagegnit
@rediy21

✎ ክፍል 16 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።