Get Mystery Box with random crypto!

የቆንጆዋ ጦስ ክፍል ሀኒ ምንድነው እየደማሽ ነውኮ አልኩ በመጮህ ደንግጨ ነበር እሷ ግን | የኔው ታሪክ 8315

የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

ሀኒ ምንድነው እየደማሽ ነውኮ አልኩ በመጮህ ደንግጨ ነበር እሷ ግን ፍፁም መረጋጋት በሞላበት ሁኔታ ነስር ነው አንዳንዴ እንዲህ ይመጣበታል አለች ጎኗ ካለ ፖርሳዋ ሶፍት እያወጣች የመጅልሲ ትራስ ላይ እራሷን አስደግፌላት ውሀ እና ማስታጠቢያ ላመጣ ሄድኩ ከዛም የሀኒን የደማ አፍንጫ በሶፍትና በውሀ ተጋግዘን አፀዳነው ደሙም ምንም ያህል አልቆየም ወዲያው አቆመላት እና በአዲስ መንፈስ ተረጋግታ ቁጭ አለች አስደነገጥሽኝኮ አልኳት ግንባሯን እየሳምኳት ነስር አለብኝ ግን እየቆየም ቢሆን የሚመጣው ብዙውን ግዜ የሚያነስረኝ በተኛሁበት ነው ቀን ላይ ግን አያቀኝም ነበር የኔ አሳቢ አለች በል አሁን ጆሮየን አቁሜ የንተን እና የቤተሰብህን ታሪክ ለመስማት እየጠበኩ ነው ምንድነው ማረሳሳት አለችኝ ኧረ ምን ቼገረሽ ያው እኔ ከዚ በፊት የሚነገር ታሪክ የለኝም ታሪኬ የሚጀምረው አንቺን ካገኜሁበት ሰአት ጀምሮ ነው ስለቤተሰቡ ግን ልንገርሽ ቆይ እንደውም በደምብ ግልፅ እንዲሆንልሽ በፎቶ የታገዘ ገለፃ ላድርግልሽ አልኳትና ከቴሌቪዥን ማስቀመጫ ስር ያለውን አልበም ወደኛ አቀረብኩትና ቤተሰቤን ለሀኒ ማስተዋወቅ ጀመርኩ
እኔ ለቤተሰቤ ሶስተኛ ልጅ እንደሆንኩና ከኔ በላይ አንድ ትልቅ ወንድም እንዳለኝ ከኔ በታች ደግሞ ያለችው አሁን የየሻት እህታችን ናት አልኳት የሆነ የበአል እለት እኔ ትልቁ ወንድሜና እህቴ ሆነን የተነሳነውን ፎቶ እያሳየኋት ወንድምህም እንደ እናንተ ቆንጆ ነው አለችኝ ሃኒ በፈገግታ
ቀጠልኩና አዎ ያኔ ቁንጅና ሲታደል የኛ ቤተሰብ የመጀመሪያ ሰልፍላይ ከፊት ተሰልፎ እንደነበር አያቴ አውርታኛለች አልኳት አብረን ሁለታችንም ሳቅን ,, ቀጠልኩናም እናቴና አባቴ አብረውን ያሉበትን ፎቶ እያሳየኋት እነዚህ ደግሞ እኛን የመሰሉ ቆንጆዎን ወደዚች ምድር ያመጡን እናትና አባትችን ናቸው። ከዛሬ ስድስት አመት በፊት ነበር የተለያዩት
እያልኩ ሃኒ በመሃል ገብታ በጣም አዝናለው አለችኝ ፊቷን ሳየው መረበሿ ይስተዋልባታል
ምንአልባት የሷም ቤተሰብ ልክ እደኛው አይነት ስለሆነ ስሜቱ ተጋብቶባት እንደ ሆነ ገምቻለው በጣም የሚገርመው ግን የኔ የቤተሰብ መለያየት አባዜ ምክኒያቱ ይለያይ ይሆናል እንጂ የብዙ ቤተሰቦችን ጓዳ ያንኳኳ ጉዳይ ነው የኛ እንኳ ትልቅ ከሆንን እና ክፉ ደጉን ከለየን የሆነ ነው አንዳንዶች ግን ገና በልጅነታቸው በእናትና በአባት መለያየት ኑሯቸው ብልሽትሽት ብሎ አንዴ በእናት ናፍቆት ሌላ ግዜ ደግሞ በአባት ናፍቆት እየተሰቃዩ በጨቅላነታቸው ማግኘት ያለባቸውን የቤተሰብ ፍቅር ሳያገኙ ያድጋሉ
ያ ነገር ከፍ እያሉ ሲመጡ ውስጣቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦና ጫና ፈጥሮባቸው ከማህበረሰቡ እራሳቸውን አግልለው የብቸኝነት ሂይወት የሚገፉ እልፍ ናቸው እናትም አባታችሁም አሁንም አብረዋችሁ ያላችሁ የእውነት በጣም እድለኛ ናችው
ግን በምን ምክኒያት ነው የተለያዩት ስትል ከሃሳቤ መለሰችኝ በትዝታ የኋሊት ገሰገስኩና አስታወስኩ ያኔ አባቴ በፈቃድ ጅዳ እየተመላለሰ አልባሳትን እና ሽቶዎችን እንዲሁም የ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በማምጣት የንግድ ስራዎችን ነበር የሚሰራው እዛ በሚሄድበት ግዜ አስራአምስት ቀን ገፋ ካለም አንድ ወር እየቆየ ነበር የሚመጣው ይህ ሲሆን ለካ አባቴ በስራ ምክኒያት ካወቃት መኖሪያዋን እዛው ካደረገች ኢትዮጵያዊት ጋር ጉዳይ ጀምሮ ነበር ይሄንን ማናችንም የምናውቀው ነገር አልነበረም ቆይቶ ግን እዛው ባሉ ዘመዶች አማካኝነት ወሬው እናቴ ጆሮ ይደርሳል ከዛ በኋላ ነው ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በሽማግሌ በዘመድ አዝማድ ብትለመን በአንገቴ ገመድ ይግባ ብላ በቃሏ ጸናች አባቴ ሁለት ሚስት የማግባት ፍላጎት እንደ ነበረው ሁላችንም ብናውቅም እንደዚህ በተደባበቀ መልኩ ያደርገዋል የሚል ለአንድም ቀን ጠርጥረን አናውቅም በቃ ሁሉም ያኔ አለቀ ከተለያዩ በኋላ እናቴ አዲስ አበባ ካለች እህቷ ጋር ለኛ ደግሞ አክስታችን ማለት ነው ከሷ ጋር በጋራ ግዙፍ የሚባል ሱፐርማርኬት ከፍተው መስራት ጀመሩ አባቴም ነገር ቁርጡ ከለየለት በኋላ ከዛችኛዋ ጋር አምርሮ መኖር ጀመረ ከዛም ከእህቴና ከወንድሜ ጋር በሰራተኛ መኖር ጀመርን ብዙም ሳይቆይ ትልቁ ወንድሜ በስራ ምክኒያት ወደ ሌላ ሀገር ተዘዋወረ
ከዛም ይኸው እኔና እህቴ አብረን እንኖራለን
አልፎ አልፎና አመት በዓል ሲመጣ አባታችን ቤት እንሔዳለን ከዛ ውጭ ግን በቃ ደስተኞች ነን ያው አንዳንዴ የሆኑ የሆኑ ነገሮች ያለፈውን ሲያስታውሱሽ ትንሽም ቢሆን መከፋት ቢኖረውም ማለት ነው አልኳት አልበሙን እየዘጋሁ እናትህ ለራሱ ገና ወጣት አይደለች እንዴ አለችኝ በመገረም አይነት ኧረ እንደውም አዲስ አበባ ከገባች በኋላ ፋዘርን ለማስቀናት ነው መሰል በጣም በተለየ መልኩ እራሷን እየጠበቀች ዳግም ፍንዳታ ሆናልኛለች ተሳሳቅን, , በዚህ መልኩ የማስተዋወቅ ስራዬን ጨርሼ ከኛ ቤት ወጥተን ትንሽ ወክ ካደረግን በኋላ ሃኒን ወደ ቤቷ ሸኝቻት ወደ ቤት ተመለስኩ።
እቤት ስገባ ሀዩ ቤት ተቀምጠው ነበር
የውሃ ማስጣጠቢያው ላይ የነበረውን ደም የነካ ሶፍት አይታ ምንድንነው ይሄ ጉድ አለቺኝ
ሃኒን ነስሯት እደሆነ ነገርኳት ከዚህ በፊት ፖስታው ላይ የነበረውን ነገር ነግሬያት ስለነበር ከህመሟ ጋር አስተያይታው ኖሮ በጣም ደንግጣ እንደ ነበር ነገረቺኝ ለካ እህቴ የትናንቱን ተሪክ አልሰማችም ሁሉንም ዘርዝሬ ለእህቴም ለሀዩም አወራሁላቸው ደብዳቤው ላይ የነበረው የህክምና ውጤት የጓደኛዋ እንደ ነበርና እሷም ከሞተች እንደቆየች ሃኒም ከደብረዘይት አባቷን ትታ የመጣችው በጓደኛዋ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ድርሰት አዘጋጅታ መታሰቢያነቱ ለጓደኛዋ ገቢው ደግሞ ለጓደኛዋ እናት የሚሆን ፊልም ለማዘጋጀት እንደመጣች ጨምሬ አወራሁላቸው። እና በቃ ግንኙነታቹ ፀደቀ ማለት ነው አለችኝ እህቴ በጥያቄ ቃና ሀዩ ፊቷን ክስክስ አድርጋው ከተቀመጠችበት ተነሳችና ምንም ሳትል ወጣች ምን ሆናነው ሀዩ? እህቴን ጠየኳት ኧረ እኔንጃ ብላኝ ሀዩ በወጣችበት በኩል ተከትላት ወጣች
ቀናቶች በቀናት ሳምንታት በሳምንት እየተተኩ በመክነፍ ላይ ናቸው እኔና ሃኒም ፍቅራችን ጨምሯል ቶሎ ቶሎ እንገናኛለን በጓደኛዋ ዙሪያ ያለው ድርሰትም እየጻፍን ከመቋጫው ላይ አደረስነው ያው ሃኒም የአርት ተማሪ ስለነበረች ምንም ያህል ሳያስቸግራት ነበር በጥሩ ሁኔታ ተጽፎ የተገባደደው አንድ እሁድ ቀን ሃኒ ምሳ እየጋበዘችኝ ድንገት አንድ ሰርፕራይዝ አለኝ አለችኝ ምንድንነው እሱ የኔ ጥያቄ ነበር የድርሰቱን መጠናቀቅ ምክኒያት በማድረግ አባቴ ጋር ከመመለሴ በፊት ሙሉ ወጪውን ሸፍኜ የአንድ ሳምንት የባህርዳር የጉብኝት እንዲኖረን ፈልጌያለው አለችኝ መልሴን ለመስማት እንደ ጓጓች ከፊቷ ላይ ያስታውቃል በጣም ነበር ሀሳቡን የወደድኩት ባህርዳርን ከዚህ በፊት ሂጄባት ባላውቅም በወሬ ደረጃ ግን ብዙ ብዙ ሰምቼላታለው በዛላይ ደግሞ ከሃኒ ጋር ታየኝ ካሁኑ የትም ይመቸኛል አልኩ በውስጤ
እ... ምን ታስባለህ አለች ሃኒ ዝምታዬን አስተውላ በደስታ እንደተስማማሁ ገለጽኩላት እና ከሶስት ቀናት በኋላ የመኪና ኪራይ አመቻችተን ልንሄድ ተስማምተን ጨረስን በቀሩት ሶስት ቀናቶች ውስጥ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በሙሉ ከውነን ጉዞ ወደ ውቢቷ ባህርዳር ተጀመረ •••

ይቀጥላል
አሪፍ አሪፍ ግጥም እና ታሪክ ለteztash
ttps://t.me/teztash
https://t.me/teztash

✎ ክፍል 17 Vote በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ።

@rediy21