Get Mystery Box with random crypto!

የቆንጆዋ ጦስ ክፍል የመንገዳችን አቅጣጫ ያደረግነው ከደሴ በመነሳት በምእራብ ወረዳ በ | የኔው ታሪክ 8315

የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል


የመንገዳችን አቅጣጫ ያደረግነው ከደሴ በመነሳት በምእራብ ወረዳ በመካነ ሰላም በኩል ነበር እኔና ሀኒም የፍቅር ወጋችንን እየሰለቅን መርጦ ለማሪያም ፣ ግንደ ወይን፣ ከዛም ሞጣ እና አዴት የሚባሉ ከተሞቼን አንድ አንድ እያልን አልፈን በፅዳቷ የከተሞች ቁንጮ በመበል ከምትታወቀው የጣና ሀይቅ
መናገሻ ከሆነችው ውቢቷ ባህር ዳር ገባን እነዚህን እና ሌሎች ትናንሽ የከተማ ስሞችን ለማወቅ የቻልኩት በሀኒ አማካኝነት ነበር ,,
እውነትም ባህርዳር በወሬ እንደሰማሁላት ፅዱ ከተማ ናት በተለይ በመንገዶች መሀል በእንክብካቤ የተያዙት ዘንባባዎች ከተማዋን የተለየ ውበት አላብሰዋታል ማረፊያ ሆቴላችን ይዘን ጓዛችንን ካስቀመጥን በኻላ ፍሬሽ አሳችንን እና እጅ የሚያስቆረጥም ሽሯችንን እያጣጣምን ጉብኝታችንን ጀመርን
ባህርዳር ካሳለፍናቸው ቆይታዎች ውስጥ ብዙውን ምሽት ማለት ይቻላል ያሳለፍነው በባህል ምሽት ቤቶች ውስጥ ነበር ባህርዳር ከምትታወቅባቸው ብዙ ነገሮቿ ውስጥ አንዱ በባህል ምሽት ቤቶች ነው እኔና ሃኒም ቀን ቀን በተከራያናት ቪትዝ መኪና እና አንዳንዴም የከተማውን ባጃጆች በመጠቀም ስንዞር እንውልና መሸትሸት ሲል ወደ ባህል ምሽት ቤቱ ጎራ እንላለን የባህል ምሽት ቤቱ ባላገሩ ይሰኛል ከመግቢያው ጀምሮ ያለው የመስተንግዶ አቀባበል እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ደግሞ በኢትዮጵያ የባህላዊ መገልገያ እቃዎች በልዩ መልኩ ተውቦና አምሮ ይቀበልዎታል የቤቱ ማዓዘናት ላይ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የምንላቸው ማሲንቆ ክራር እና ዋሽንት ተሰቅለዋል ፊትለፊት ያለው ግድግዳ ላይ ደግሞ ለእይታ በሚስብ አይነት ተሰርተው ሞፈር እና ቀንበር፣ አጎዛ፣ ጋሻና ጦር ይስተዋላሉ አስተናጋጆቹ ሳይቀር ሴቶቹ ፀጉራቸውን ሹሩባ ተሠርተው ወገቡ ላይ በመቀነት ሸብ የተደረገ ሽንሽን ቀሚስ ለብሰዋል ወንዶቹ ደግሞ ከካኪ የተሰራ ተነፋነፍ ቦላሌ አድርገው በወጉ የተበጠረ ጎፈሬያቸው ላይ ሚዶ ማበጠሪያ ሰክተዋል በቤቱ ውስጥ የምሺቱን ጨዋታ ለመታደም ከገባው የከተሜ ሰው ውጪ አንድም ከተማን የሚመስል አልያም አሁን ላይ እኛ የስልጣኔ መገለጫ ብለን የምንጠራቸው ቁሶች ማየት ዘበት ነው በቃ ሙሉ የገጠሪቱ ኢትዮጵያን ድባብ የተላበሰ ነው። ይህ አይነት ስሜት የሚሰማኝ ድሮ ላይ ትምህርት ሲዘጋ ከገጠር ያሉት ዘመዶቼ ጋር ስሄድ ነበር በቃ ጎጆ ቤት አይሁን እንጂ ይሄም ገጠር እንዳሉት የዘመዶቼ ቤት ነው ሌላው በጣም የወደድኩት ነገር ቤቱ ውስጥ ምግብ ሲያዙ የሚቀርብልዎት በሞሰቦ ወርቅ ተደርጎ ነው የሚጠጣው ጠጅና ብርዝ ደግሞ በብርሌ ከኛ ፊትለፊት ባለው የመደብ መቀመጫ ላይ ሁለት ወንድና ሁለት ሴቶች በጋራ ሆነው በመሰቦ ወርቅ የቀረበላቸውን ማድ ከበዉ እየተቋደሱ ወዲህ ደግሞ የብርሌ ጠጃቸውን እየተጎነጩ ይስቃሉ ይጫወታሉ።
እኔም እየጠፋ ያለውን ተሰብስበው ለማድ አብሮ የመቀመጥን ባህል ስላሳዩኝ ደስ ብሎኛል በውስጤ ወድጃቸዋለው። እንደ ዛሬ ወቅቱም ሰውም ሳይከፋ በፊት ለብቻ ሆኖ ማድ መቀመጥ እንደ ነውር እንደሚታይ ገጠር ያለው አጎቴ ነግሮኝ እንደ ነበር በጣም አስታውሳለሁ በነገራችን ላይ ገጠር ያለው አጎቴ ሲበዛ ባህሉን የሚወድና የሚያከብር ያሁኑን ዘመን አመጣሽ የስልጣኔ መደናበር ደግሞ የሚጠየፍ ሰው ነው። እንደዛ የሆነው ገጠር ስለሚኖር አሊያም ገበሬ ስለሆነ ብቻ አይደለም እንደዛ ሚሠማው አሁን ላይ ባለው በብዙ ነገር ስለሚማረር ነው የገጠሩ አጎቴ በድሮው የትምህርት ስርዓት እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ ዘልቋል በዛ በቀሰማት የማንበብ ክህሎት በመነሳት ስለ ሐገሩና ስለ ባህሉ ሚጠቅሱትን ነገሮች ባገኘው አጋጣሚ ያነባል ጉዳይ ኖሮት ወደ ከተማ ከዘለቀም የዛ አይነት ይዘት ያላቸውን መጸሐፍት ከኔ ጋር አብረን ሆነን እንገዛና ይዞ ይሔዳል አመለካከቱና ነገሮችን የሚያይበት ይዘት ከተሜ ነን ከሚሉ ሰዎች እጅግ የላቀ ነው እኔም ገጠር እሔድ በነበረበት ግዜ ብዙውን ሰዓቴን የማሳልፈው ከሱ ጎን ቁጭ ብዬ ወሬዎቹን በማዳመጥ ነበር
የሆነ ግዜ ከሱ ጎጆ እሳት ዳር ሳለን በሌማት የቀረበ ቆሎ እየቆረጠምን በጋራ ተሰብስቦ ማድ ስለመቀመጥ ባህል እያወራልኝ ሳለ አንዴ የደረሰብኝን ገጠመኝ ላጫውትህ ብሎ የነገረኝን ሁሌም ነበር ባስታወስኩት ቁጥር የምስቀው እንዲህ ነው የሆነው, ,,ግዜው በጣም ቆይቷል የገጠሩ አጎቴ ለአንዲት ቀጠን ያለች ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ያመራና እዛ ያሉ ዘመዶቻችን ይቀበሉታል እንዳጋጣሚ የደረሰበት ሰአት ምሳ ሰአት ነበር እና ቡና እየተፈላ ተጠቅልሎ የተቆራረጠ እንጀራ ለየብቻቼው ሁነው በሰሀን በሰሀን ያነሳሉ የገጠሩ አጎቴ ደሞ ተሰብስቦ አብሮ ከመብላት ውጭ ሊያውም እንዲህ እንጀራ አራት አምስት ቦታ ተሸንሽኖ ለእያንዳንዱ ሰው ስለሚታደለው ወይም በእኔና በእናንተ አጠራር "የቁርጥ እንጀራ " ስለሚባለው ነገር የሚያቀው አንዳችም ነገር አልነበረውም ••••
እናላችሁ አንድ ሰሀን ያሲዙትና እንጀራ አንሳ ይሉታል የገጠሩ አጎቴም ያው እንደነገርኳችሁ ለነገሩ አዲስ ስለሆነና ቡናም እየተፈላ ስለነበር እንደነሱ ገጠር የቡና ቁርስ ይሆናል በሚል እሳቤ አንድ ቁራጭ እንጀራ አንስቶ ሰሀኑን ዘወር ያደርጋል ጨምር ቢሉት ደሞ ለቡና ቁርስ ይሄ ምን አነሰው ብሎ በሆዱ ይበቃኛል ሲል ድርቅ ይላል ያጎቴን አሻፈረኝ ማለት ያሰሙት ከተሜ ዘመዶቻችንም መንገድ ላይ በልቶ ይሆናል በሚል ይተውታል እሱም ያችን አንድ ንጣይ እንጀራ ቀምሶ ቡናውን ይጠጣና ይጨርሳል እነሱም የተበላበትን የምግብ እቃና የቡና ረከቦት አነሳስተው ቴሌቪዥን ይከፍቱለትና ተጫዎት ብለውት ወደየ ፊናቼው ይሰማራሉ መንገድ ያንገላታው ሚስኪኑ የገጠሩ አጎቴ ካሁን አሁን ምሳ ይቀርባል እያለ ቢያማትር ቢያማትር ከወዴት መጥቶ ያነሳት ቁራሽ እንጀራ በምሳ ስም የተሰየመች መሆኗን ያወቀው ማታም ለእራት በምሳው መልኩ ሲያቀርቡለት ነበር ቡና ቁርስ ብሎ ተሸውዶ ምሳውን ሳይበላ በራበው ሆድ የቆየው የገጠሩ አጎቴ ብልጥ ያለ አንድየ አይበለጥ ብሎ እራት ላይ ያነሳውን የቁርጥ እንጀራ ብዛት ብነግራችሁ እናንተም ትታዘቡታላችሁ ። እዛው በተቀመጥኩበት የገጠሩን አጎቴን በሀሳቤ ሳልኩና ፈገግ አልኩ የባህል ምሽት ቤቱ ጨዋታ በደንብ መድመቅ ሚጀምረው እና የሚደራው ከሁለት ሰአት በዃላ ነው እኔና ሀኒም ያረፍንበት ሆቴል ካለንበት ብዙም ስለማይርቅ ስለሰአቱ መምሸት ምንም አናስብም ሁሉም በየመቀመጫቼው የሚጠጡትን ይዘው ተቀምጠዋል ብዙወቹ ጥንዶች ቢሆኑም ለብቻቼው ሁነው የገቡም አሉ እኔና ሀኒም በብርሌ የቀረበልንን የብርሌ ጠጅ እየተጎነጨን መሀል ላይ ቁመው ጨዋታውን በሚያከፋፍሉት እንድ ወንድ እና አንድ ሴት አዝማሪ ላይ ፈጠናል መቼም ጨዋታው ለጉድ ነው ተቀበል ይልና አንዱ ለአዝማሪው በቅኔ የታሼ ግጥም ይወረውራል ወዲያው ደሞ ከሌላኛው በኩል ሌላ ግጥም ይወረውራል ሚስቱ ጋር የገባው ለሚስቱ ያስገጥማል ሴቷም አንዲሁ ባሏን ማሞገሻ የሚሆን ቃላትን ሰድራ ታቀርባለች ፣ ፍቅረኛሞችም ፍቅራቼውን በግጥም ያፈኩታል በዛው ልክ የከፋውና , ከሚስቱ ወይ ከፍቅረኛው ጋር ተጣልቶ መጥቶ የሆዱን ብሶት በግጥም የሚተነፍስም ዕልፍ ነው የአዝማሪዎቹ ግንባር ላይ ባለ ሀምሳና ባለ መቶ ብር ኖቶች በሽልማት መልክ ወዲያው ወዲያው ይለጠፋሉ ከዛማ ምን አለ ቤቱ በሳቅና ጨዋታ ባንድ እግሩ ይቆማል የብርሌዋ ጠጅ ስራዋን ሰራች መሰል እኔም አስገጥም አስገጥም የሚል አንዳች የግጥም መንፈስ ንሽጥ ተቀበል አልኩ ማን ከማን ያንሳል