Get Mystery Box with random crypto!

የቆንጆዋ ጦስ ክፍል #የመጨረሻው_ክፍል ከባህርዳር ከተመለስን ከሁለት ቀን በዃላ ደብ | የኔው ታሪክ 8315

የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል

#የመጨረሻው_ክፍል

ከባህርዳር ከተመለስን ከሁለት ቀን በዃላ ደብር ዘይት ያለው የሀኒ አባት ከብዙ ደጅ ማስጠናት በዃላ ውሀ አጣጭህ የምትሆነውን ሴት እንዳገኜ እና ለእሷና ለእህቷ ሊያስተዋውቃቼው ቀን ቆርጦ እንደጨረሰ በደስታ ፈንድቆ ይነግራታል ሀኒም በአባቷ ደስታ እጅግ በጣም ተደስታለች ለብቻው በመሆኑ እና እንደጓደኞቹ ጎኑ ሁና የምታደምጠው እና ጎጆውን ሞቅ ሞቅ አድርጋ በጊዜ እቤቱ እንዲገባ የምታደርገው ሴት ባለ መኖሯ በጣም ያሳዝናት ነበር የምትሆነውን አግኝቶም ተረጋግቶ እንዲቀመጥላት የዘወትር ምኞቷ ነበር ዛሬ የምኞቷን መሳካት በአንድ የስልክ ጥሪ አጎቷ አበሰራት እኔም ሀኒ ልትሄድ በመሆኑ እጅጉን ብከፍም እንዲህ ፈክታ ሳያት ግን ለእሷ መደሰቴ አልቀርም። በሚቀጥሉት ቀናት ከዚህ በፊት እንዳደርግነው የሚገዛዙ ነገሮችን ገዛዝተን የሀኒ ጓደኛ እናት ጋር ሄድን
ከመመለሶ በፊት እንደምታያቼው ቃል ስለገባች እና በዛውም የአባቷን የብስራት ዜና ለሳቼውም ለመናገር ነበር የሄደችው ሴትየዋ የአባቷን ሊያገባ መሆን ሲሰሙ የቤተሰብ ያህል በጣም ነበር የተደሰቱት እንደው እንዴትና ከወዴት አገኜዃት አለሽ ሲሉ ሀኒን ጠየቋት ሀኒም ምንም የተጨበጠ ነገር እንዳልነገራት ሁሉንም የሚያጫውታት ስትመጣ እንደሆነ ነገረቻቼው ያው ከዚህ በፊት ስለግንኙነቱ መጀመር እና
ሴቷ ያለችው አዲስ አበባ እንደሆነ ጫፍ ጫፉን ታቃለች እንኳንም ተሳካለት እንኳንም አንችም ከሀሳብ እና ጭንቀት አረፍሽ አሉ ሴትዮዋ በእናትነት ለዛ ።
ከዛ በዃላ ነበር ሀኒ ጓዟን ጠቅልላ ከደሴ ወደ ደብረዘይት አባቷ ጋር የሄደችው ያን ቀን አብረን አድረን ነበር የሼኜዃት እሷን ሼኝቼ ስመለስ የተሰማኝን የብቼኝነት ስሜት እና ባዶነት እንዲህ በቀላሉ በቃል የምገልፅበት ቃልም አልነበረኝም ዳግም የምንገናኝ ሁላ አልመስልህ እስኪለኝ ሆዴ ተላወሰ ለካ ኤርፖርት ላይ ሰው ተቃቅፎ እንደዛ የሚላቀሰው ወዶ አይደለም ከሚወዱት ለቀናትም ቢሆን መለየት ምን ያክል እንደሆነ ስሜቱ የገባኝ በዛን ሰሞን ነበር ። ከሀኒ ጋር ወዲያው ወዲያው ብንደዋወልም በቃ ደርሳ ትናፍቀኛለች ያ ሳቋ ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል ።
አንድ ምሽት ከሀኒ ጋር ተደዋውለን እያወራን አዲሷን እናቴን እኮ የምተዋወቅበት ቀን ነገ ነው ደስ አይልም ደሞ ሳልነግርህ ድርሰቱ ወደ ፊልም እስክሪፕት ተቀይሮ በቅርብ ግዜ ቀረፃው እንደሚጀመርም አጎቴ ነገረኝ ስትል ፍፁም በሚያስታውቅ ደስታ ፍልቅልቅ እያለች አወራችልኝ እኔም የደስታዋ ተካፋይ ለመሆን የአባቷ ትውውቅ ላይ ባልገኝ እንኳ ፊልሙ ሲመረቅ ግን በአካል ቦታው ድረስ እንደምገኝ ቃል ገባሁላት በጣም ደስ ይለኛል ነገ በጧት ለስራ ተነስቼ ጉድ ጉድ ማለት ስላለብኝ በግዜ ልተኛልህ እወድሀለሁ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ
በሚቀጥለው ቀን እህቴና ሀዩ ባሉበት ቁጭ ብለን ቡና እየጠጣን ነው እህቴና ሀዩ ሀኒ ከሄደች በዃላ እኔ ላይ በሚያዩት ድብርት መቀለድ እና መጠቋቆም ከጀመሩ ቆይተዋል የዚች የቆንጆ ጦስ መቼም ሂዳም አለቀቀህማ ትለኛለች እህቴ ሀዩ ግን እህቴ ጋር ስትሆን አብራ ብትቀልድም ለብቻዋ ስትሆን ግን በቻለችው ሁላ ፈታ እንድል የማታደርገው ጥረት አልነበረም በቀልዳቼው መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ ሀኒ ነበረች የአባቷን ሚስት በአካል የምትተዋወቅበት ቀን ዛሬ ስለሆነ አይመቻትም ብየ አልደወልኩላትም ነበር አነሳሁትና እንደሁልግዜው ቆንጆዋ አልኳት ድምፆ የቀዘቀዘ ነበር ምንድነው ድምፅሽ ደህና አይደለሽም እንዴ ሀኒ ስል ጠየኳት ምንም ሳትመልስልኝ የእናትህ ስም ማን ነበር ያልከኝ ስታስተዋውቀኝ የሚል ደረቅ ጥያቄ አስከተለች ከምናወራው ጋር ምን አገናኘው እያልኩ በውስጤ የእናቴን ስም ነገርኳት በዛው በቀዘቀዘ ድምፆ እሺ ብቻ ብላኝ ስልኩን ዘጋችው ግራ እየተጋባሁ ደወልኩላት አይነሳም ደገምኩት ቴክስትም ላኩኝ ምንም ምላሽ የለም ይባስ ብሎ ስልኳ ጠፍ በእህቴ ስልክም ሞከርኩ ጥሪ አይቀበልም ነው የሚለው ከቀን ጀምሮ ምሽት ስድስት ሰአት እስከሚሆን እየቆየሁ ብሞክርም ስልኳ ግን አሁንም ያው ነው አሁንም አይሰራም ያን ሌት እንዲሁ ስገላበጥ ሀሳብ ሳወጣና ሳወርድ እንቅልፍ የሚባል በአይኔ ሳይዞር ነጋ ከአልጋየ እንደተነሳሁም የመጀመሪያ ስራየ ምን አልባት ከሰራ በሚል ወደ ሀኒ መደወል ነበር ምን ዋጋ አለው እንደማታው ነው ጥሪ አይቀበልም ። አንዳንዴ ከሆነው አልያም ከደረሰብን ነገር በላይ እጅጉን ሰላም የሚነሳን እና ውስጣችንን እረፍት የሚነሳው ለምን እና እንዴት ሆነ የሚለው ነገር ነው እኔም አሁን ያ ስሜት ነው የሚሰማኝ ስልኩን ስለዘጋችብኝ ወይ ስላጠፋችው ብቻ ሳይሆን ለምን ያ ሆነ ? እንዴት የእናቴን ስም ጠየቀችኝ ? በቃ ውዝግብግብ ያለ ነገር ሆነብኝ በመሀል ደሞ አንዳች ነገር ገጥሟት ይሆን እንዴ እያልኩ እጨነቃለሁ በደስታዋ ቀን ላይ እንደዛ የመቀዛቀዟ የመረበሿ ነገር ደግሞ ሌላ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው ። እህቴ ቁርስ ሰርታ እኔን እየጠበቀች ነው እኔ ደግሞ ምንም የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም እኔ እቆያለሁ ብያት ከቤት ወጣሁ ወደየት እንደምሄድ ግን አላውቅም እንደ እብድ ብቻየን አወራለሁ በእህቷ ስልክ እንኳ እንዳልደውል የእህቷን ስልክ አላውቀውም አንዲህ ባለ ሁኔታ ነገር እያብሰለሰልኩ ከእንቅልፍ እንደተጣላሁ የሀኒ ስልክም እንደተዘጋ ሶስት ቀን ሞላኝ ከዚ በላይ ግን የውስጤን ጥያቄ ሳልመልስ የሀኒንም ሁኔታ ሳላቅ ታግሶ መቆየት አልቻልኩም የሆነ ነገር መፍጠር እንዳለብኝ ወስኜ ከአልጋየ ተነሳሁ የሰሞኑ ሁኔታየ ከወትሮው የተለየባት እህቴ ከመኝታ ቤቴ መውጣቴን ጠብቃ ምንድነው የሆንከው አንተ ልጅ ስትል አስቁማ አፋጠጠችኝ ምንም እንዳልሆንኩ ላስመስል ብሞክርም በዛ ሁኔታ አልችልም ነበር የግዴን ያለውን ነገር አንድ በአንድ ከሄደችበት ምክኒያት አንስቶ ደውላ የእናታችንን ስም ጠይቃኝ ስልኩ እስከተዘጋበት ደረስ ያለውን ነገርኳት ለአፍታ አንገቷን አቀርቅራ ከቆየች በዃላ ከሰመመን እንደነቃ ሰው አይነት ብንን ብላ አባቷ ሚኖረው ደብረዘይት ነዋ ያልከኝ አለች አዎ ምነው አልኳት ፊቷ ላይ የተወሰነ ግራ የመጋባት አይነት ድንጋጤ አስተውያለሁ አይ ምንም ቆይ ታዲያ በሷ በኩል የምታቀው ሌላ ሰው የለም አንዴ ምን አልባት ያለችበትን ሁኔታ የሚነግርህ አልያም ሌላ ስልክ ካላት የሚሰጥህ አለችኝ እህቷን እና አንድ ጓደኛዋን ብቻ ነው የማቀው የሁለቱም ስልክ ደግሞ የለኝም የኔ መልስ ነበር ይሄን እያወራን ሀዩ እንዴት አደራችሁ ብላ ወደቤት ገባች ሁለታችንም ፊት ላይ መረበሽ ስላየች ምንድነው በጧቱ ቆዝማችዃልሳ ብላ ከእህቴ ጎን ተቀመጠች እኔ ካለሁበት ተነሳሁና የተጫጫነኝ ትንሽ ለቀቅ ቢያደርገኝ ብየ ወደሻወር ቤት ገባሁ እህቴና ሀዩና እዛው በተቀመጡበት ይንሾካሾካሉ የሻወር ቆይታየን ጨርሼ ስወጣ ቁርስ ቀርቦ ነበር ካልበላሁ ስለምትጨናነቅ ለእህቴ ስል እንደነገሩ ቀማመስኩና አንዳች ፊንጭ ባገኝ እንኳ እዛው እቤታቼው ድረስ መሄድ እንዳለብኝ ቁርጥ ሀሳብ ላይ ደርሼ ከቤት ወጣሁ