Get Mystery Box with random crypto!

ከቤት ወጥቼ ትንሽ እንደሄድኩ እስኪ ቢሰራ ደውየ እድሌን ልሞክር ብየ ስልኬን ላወጣ ከኪሴ ስገባ ስ | የኔው ታሪክ 8315

ከቤት ወጥቼ ትንሽ እንደሄድኩ እስኪ ቢሰራ ደውየ እድሌን ልሞክር ብየ ስልኬን ላወጣ ከኪሴ ስገባ ስልኬ የለም ትዝ ሲለኝ ሻወር ከመውሰዴ በፊት የለበስኩት የቱታየ ኪስ ውስጥ እንዳስቀመጥኩት ነበር ሱሪ ስቀይር የረሳሁት ከነበርኩበት በጥድፊያ ወደ ቤት ተመለስኩ በሩ ጋር ደርሼ ልገባ ስል ይልቅ ሰአቱ ሳይረፍድ ሁሉንም ብትነግሪው ይሻላል የሚለው የሀዩ ድምፅ ከውስጥ ወደ ውጭ ጆሮየ ላይ ጥልቅ አለ ባለሁበት ቀጥ ብየ ቆምኩና መላ አካሌን ጆሮ አድርጌ የሚያወሩትን ለመስማት ተዘጋጀሁ እህቴ ቀጠለች እኔኮ በስመ ደብረዘይት ዝምብየ ያልተጨበጠ ነገር ይዤ ከማወራው
መጀመሪያ ማሚ ጋር ልደውልላትና ስሙን ልጠይቃት ከዛም የሀኒን የአባት ስም እሱን ጠይቄ አንድ አይነት ከሆነ በቃ ምንም ማድረግ አልችልም እሱም እንደዚህ ከሚሆን ነግረዋለሁ የእህቴን መልስ የሰማችው ሀዩ ደግሞ እንዲህ ስትል ወሬዋን ቀጠለች እኔም የወሬያቼውን ፍንጭ እና መጨረሻ ለመስማት በቆምኩበት ቋምጫለሁ ግን አንቺ እንዳልሽው የሀኒ አባት በሚስትነት የተዋወቀው የእናንተን እናት ከሆነኮ በጣም ከባድ ነው አስበሽዋል ከአንቺና እናት እና ከልጅቱ አባት ልጅ ቢወለድ እኮ ለሁለቱም ወንድም ወይም እህት ነው የሚሆነው ይሄን ስሰማ ባለሁበት ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ሰውነቴ ድንዝዝ አለ ምኑ ከምኑ ጋር ተገናኝቶ ነው ያ ሊሆን የቻለው እህቴስ ይሄን ከማን እና እንዴት ሰምታው ነው ? በድን ሰውነቴን አንደምንም አንቀሳቅሼ በሩን አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ የሁለቱም አይን በድንጋጤ ፈጦ እኔ ላይ አረፈ ምንም ሳልናገር ፊት ለፊታቼው ሂጄ ተቀመጥኩ ምን ሁነህ ነው አለችኝ እህቴ በመመለሴና በወሬያቸው መሀል ድንገት በመገኜቴ ግማሽ ግርምት ግማሽ ድንጋጤ ውስጥ ሁና ሀዩ እንደፈዘዘች ናት እያወራችሁት የነበረውን በር ላይ ሁኜ ስሰማ ነበር እና አሁን ምንም ሳትደብቂ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገሪኝ አልኳት በጣም ተቆጥቼ ነበር እህቴ ደሞ አደለም በዚህ መልኩ ተናድጄ ይቅርና ድምፄ ትንሽ ለወጥ ካለ ድንብርብር ነው የምትለው ድምፇ ቁርጥቁርጥ እያለ እንዲህ አለችኝ ማሚ ባለፈው ደውላልኝ ነበር እናታችንን ማሚ እያልን ነው የምንጠራት እናም በስራ ምክኒያት ከሆነ ሰው ጋር ትውውቅ ጀምራ ነገሩ ወደ ትዳር እያመራ እንደሆነና አሁን ደሞ ልጆቹን ሊያስተዋውቃት ቀጠሮ እንደያዙ አውርታልኝ ነበር ይሄን ነገር ለኔ ብቻ ነው የነገረችኝ ለእናንተ አሁን ላይ እንዳልነግራችሁ እና አሷ ራሷ በሁኔታው ወስና ከጨረሰች በዃላ እንደምትነግራችሁ ጨምራ ነግራኛለች እናም የተዋወቀችው ሰው ነዋሪነቱ ደብረዘይት እንደሆነ ስለነገረችኝ ቀኑም ሀኒ ከሄደችበት ጋር ስለተመሳሰለብኝ በቃ ይሄን አሰብኩ አለችኝ የእናቴ ይሄን ነገር ለእህቴ ብቻ መንገሯ ምንም አላስገረመኝም ምክኒያቱም ከዚ በፊትም ቢሆን በእናቴ ዙሪያ ምንም አይነት ጉዳይ ሲኖር ከሁላችንም ቀድማ የምትሰማው እህቴ ናት ከሁሉም በፊት የቅርብ አማካሪዋ እሷና እሷ ብቻ ናት ሌሎቻችን ከረፈደ ነው የምንሰማው ያን ስለማቅ አልደነቀኝም አደንዝዞ ያስቀረኝ የነገሩ መገጣጠም ነው የፈለገ እውነቱ ቢመርም አንዴ ቁርጤን ማወቅ ግን ፈልጊያለሁ የሀኒን የአባት ስም አቀው ስለነበር ያን ለማረጋገጥ እህቴ ምንም እንዳልተፈጠረ በመሆን እናቴ ጋር ደውላ ስለትውውቃቼው ወሬ በማንሳት በሆነ መንገድ ስሙን ምናውቅበትን ሀሳብ አወራን ቁርጤን ማወቁ ቢያጓጓኝም ነገሩ እውነት እኛ እንዳሰብነው ቢሆንስ የሚለው ፍርሀቴና ጭንቀቴ ግን አያድርስ ነበር ምንም እንኳ በብቼኝነት ሌትና ቀን የምትገፋው እናቴ ሰምሮላት ለአዲስ ጎጆ የጀመረችው መንገድ እፎይታ ቢሰጠኝም ወዲህ ግን ጅምሩ ፍቅሬ፣ አዲሱ ፍቅሬ፣ ወደማላቀው ደስታ ያስገባኝ ፍቅሬ ብዙ ያሰብኩለት ፍቅሬ መና ሁኖ ሊቀር

መሆኑ ሲታሰበኝ ባለሁበት የሀዘን ጭልመት ከበበኝ በመጨረሻም እህቴ እናቴ ጋር ደውላ እያሳሳቀች ነገሩን መውጣጣት ጀምራለች እኔ መቁነጥነጤን ቀጥያለሁ ካፍታ የስልኩ ቆይታ ቡሀላ መራራው እውነት ፈረጠ እናቴ የተዋወቀችው አዲሱ እንጀራ አባቴ የሀኒ አባት ሁኖ አረፈው ምን ይባላል አሁን በማንስ ይፈረዳል ግዜ እኛ ላይ ሲፈርድ ይሄን የግጥምጥሞሽ ዳስ እኛ ላይ ደፋብን ቤቱ በአንዳች የዝምታ መንፈስ ተዋጠ በዚ መሀል የስልኬ መጥሪያ አቃጨለ እህቴ ከኔ ቀድማ ብድግ ብላ ወደስልኬ በመሄድ አነሳችውና እስክሪኑ ላይ አፈጠጠች ወዲያው የፊቷ ገፅ ቅይር አለና ሀኒ ደወለች አለችኝ ወደኔ ስልኩን እየዘረጋች እጄ እየተርበተበተ ተቀበልኳትና ትንፋሼን ሳብ አድርጌ ለመረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን አነሳሁት ከሷ እስከሚመጣ ድረስ ምንም እንዳልሰማ ሁኜ መቀጠልን መርጫለሁ ።ድምፇ ለመጨረሻ ግዜ እንደሰማሁት አሁንም ቀዝቃዛ ነው ምን ሁነሽ ነው ምን ተፈጥሮ ነው? ይሄን ያክል ቀን ስልክሽን አጥፍተሽ ስታስጨንቂኝ የነበረው ስል ጠየኳት ፀጥ ብላ ቆየችና በቃ ምንብየ እንደምነግርህም አላቅም ከአቅሜ በላይ የሆነ ነገር ሆነብኝ ያሰለፍኳቼውን የስቃይ ቀናት እኔ ብቻ ነኝ የማቀው ወድጄም አይደለም ስልኬን ያጠፋሁት ድምፇ እየተቆራረጠ ወደ ለቅሶ ቃና ተቀየረ ምንም እንኳ ሁኔታውን ቀደም ብየ ብሰማውም አሁን ይበልጥ ህመሙ ወደ ውስጤ ዘልቆ ሲገባ ታወቀኝ አይኖቼ እንባ ቋጠሩ ሀኒ ሳግ እየተናነቃት ወሬዋን ስትቀጥል የእኔም እንባዎች እየተንኳሉሉ መውረድ ጀመሩ እንደዛ አስቦርቆኝ የነበረው የአባቴ ዜና ተገልብጦ የመርዶ ያክል የሚከብድ ዱብዳ ሀነብኝ አባቴ ሚስት ብሎ ያስተዋወቀኝ የአንተን እናት ነው ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሷ ለቅሶ እኔንም ከነጭራሹ አሳጣኝ ከዛ በዃላ ምንም እንዲህ ነው ብየ የምናገረው ቃልም አልነበረኝ ልናገርም ብል አፌ ተያይዞል ደሞስ በዛ ሰአት እኔ ለራሴ አፅናኝ በሚያስፈልግብኝ ከየት አቅም አገኝቼስ ሀኒን አፅናናለሁ እሷ ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች እኔ ደግሞ በዝምታ ወደ ውስጥ እያነባሁ በተገተርኩበት እህቴ ጆሮየ ላይ ያለውን ስልክ ተቀብላኝ ሀሎ ሀኒ እያለች ወደውጭ ወጣች ምን እንደምታወራትም አላቅም ብቻ ብዙ ቆይታለች ።ቤቱ ውስጥ እኔና ሀዩ ቀርተናል ወደተቀመጥኩበት መጥታ ጎኔ አረፍ አለች በክሪሟ ጫፍ ከጉንጮቼ ላይ እንደመጥረግ እያደረገች በቃ አይዞህ እንደዚህ አትሁን እራሳህን አረጋጋ እስከመጨረሻውኮ አላጣሀትም ምንድነው እንደዚህ ባንዴ ተስፋ መቁረጥ አንተ ላይ ሳቅና ጨዋታ እንጂ መቆዘም አያምርብህም ለሰው መካሪ እንዳልነበርክ ዛሬ ምከሩኝ ልትል ነው እንዴ ቀጠለች ሀዩ በስስት እያየችኝ ደሞ ታውቃለሀ ሁሉም ሰው በራሱ ርእስ የተፃፈ መፅሀፍ አለው የገፃችን ብዛት ግን የት ጋር እንደሚቆም ማናችንም አናቀውም ። እና ደሞ የሂወታችን መፅሀፍ ውስጥ እያንዳንዱ ገፆች ላይ የተፃፈው ነገር ይለያያል የደስታ የሀዘን ፣ የመገናኜት የመለያየት፣የመሳቅ የማልቀስ፣ የማግኛት የማጣት፣ የመውደድ የመጥላት ፣ የመውደቅ የመነሳት የጠብ የመታረቅ ፣ የመሄድ የመምጣት ፣ የፈታ የድብርት ፣ የማትረፍ የመክሰር ፣ የመውደቅ የስኬት ብቻ ብዙ አይነት የሂወት ውጣ ውረዶች በገፆቹ ውስጥ ተፅፈውበታል። እናም በመኖር ሂደት ውስጥ ድንገት አንዱ ገፅ ሊበላሽብህ አልያም አንተ እንደጠበከው ሁኖ ላታገኛው ትችላለህ ነገር ግን ያ ሆነ ብለህ ቶሎ ብለህ ተስፋ መቁረጥ የለብህም ራስህንም እንደ እድለ ቢስ ማየትም ደሞ ይሄን አትርሳ ሁሉም የሚሆነው በምክኒያት ነው ሳይደግስ አይጣላም ሲበል አልሰማህም ይልቅ በርታ ብለህ በትእግስት እለፍና ቀጣዩን የሂዎትህን ገፅ ለመግለፅ ሞክር ማን ያቃል አዲስ የምትገልጠው የሂወት ገፅ የተሻለና አንተ የምትፈልገው አይነት ብቻ ሳይሆን ለአንተ የሚያስፈልግህ