2023-05-10 13:33:21
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
"በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፤ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
ቆላስይስ 1፥10-11
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ርክበ ካህናት
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ የዚህ ዓመት (ዘመነ ሉቃስ ፳፻፲፭) ርክበ ካህነት ግንቦት ፪(2) ይሆናል
❖ ርክበ ማለት ረከበ ከሚለው የግእዝ ዘር የተገኘ ሲሆን ረከበ አገኘ ርክበ ማግኘት መቀበል ማለት ነው፤ ርክበ ካህናት ስንልም የክህነት መቀበል ማግኘት መገናኛ ተብሎ ይተረጎማል፡፡
❖ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ከትንሳኤ በኋላ በ25ኛው ዕለት ወይም የበዓለ ሃምሳ እኩሌታ ላይ የሚውል በዓል ሲሆን ምን ጊዜም ዕለተ ረቡዕ ላይ ይውላል፡፡
❖ ርክበ ካህናት ለምን በባዕለ ሃምሳ ኣጋማሽ በዕለተ ረቡዕ ሆነ ቢሉ
❖ ለቅዱስ ጴጥሮስ ( ለቤተክርስቲያን ) በጎቼን ጠብቅ፣ ጠቦቶቼን አሰማራ፣ ግልገሎቼን ጠብቅ በማለት ሥልጣነ ክህነት የተሰጠው በበዓለ ሃምሳ ኣጋማሽ በ25ኛው ዕለት በዕለተ ረቡዕ በመሆኑ ነው፡፡
ዮሐ 21፥15-17
❖ ጌታችን ለሐዋርያት ስልጣነ ክህነትን እንደሰጣቸው ከላይ ካየነው ጥቅስ ባሻገር
‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈቱት በሰማይ የተፈታ ይሆናል›› የሚለው እና ‹‹ …ይህን ብሎ እፍ አለባቸው፤ እንዲህም አላቸው መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችሁላቸው ይሠረይላቸዋል፤ ይቅር ያላላችኋቸው ግን አይሰረይላቸው››
ማቴ 18፥18
ማቴ16፥19
ዮሐ 20፥22-23 ተጨማሪ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
❖ እናት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዕለት ከምታከናውናቸው ሥርዓት አሉ ከእነዚህ መካከልም
፩ . ሲኖዶስ
❖ ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጉሙ ኣባቶች ስለነገረ ክርስቲያን የሚገናኙበት ጉባኤ ማለት ነው፤ ጉባኤ የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ቅዱስ ስብሰባ ማለት ነው፡፡
❖ በክርስቶስ አምነው ክርስትና በተቀበሉት አሕዛብ እና በክርስትና ባመኑት አይሁድ መካከል የተነሳውን ችግር ለማስወገድ
❖ ሐዋርያት የመጀመሪያውን አድርገዋል፤ ይህ ሲኖዶስ /የኃይማኖት ጉባኤ/ ከ49-50 ዓ.ም መካከል በጌታ ወንድም በያዕቆብ አማካኝነት ተከናወነ፡፡
የሐዋርያት ሲኖዶስ ውሳኔ
❖ ከአህዛብ የሚመለሱ ክርስቲያኖች ከዝሙት እንዲጠበቁ "አይሁዳውያን ይህንን ጥያቄ ያነሱባቸው ነበርና ከዚህ ይቆጠቡ ዘንድ ይህንን ውሳኔ አስተላልፈዋል መፈተን ይኖራል ያልተፈተነ ክብር ስለማያገኝ እንዲጠነክሩ በማሰብ"።
❖ አህዛብ ደም ኣንቅቶ የሞተውን እንዳይበሉ "ያልተባረከ ከብት እንዳይመገቡ ሲል ነው"
ለጣኦት የተሰዋውን እንዳይበሉ።
❖ አህዛብን በመምከርና በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲያውቁ ማድረግ እንጂ ማግለል እንደማይገባ ውሳኔ አስተላልፈዋል
❖ በተጨማሪም ስለቤተክርስቲያን፣ ስለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለካህናት አገልግሎት፣ ስለምዕመናን ድርሻ አብጥሊስ ግፅው ዲድስቂልያ በተሰኘ መጽሐፋቸው ወስነዋል፡፡
የሐዋ 15/16 1-3
❖ ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተ ክርስቲያናችንም ሐዋርያት አብነት አድርጋ ለነገሮች ሁሉ ምላሽ ለመስጠት በዓመት ሁለት ጊዜ ሲኖዶስን ታደርጋለች፤ ዕለታቱም ጥቅምት 12 እና የበዓለ ሃምሳ እኩሌታ ናቸው፡፡
❖ ጥቅምት 12 ታላቁ ወንጌላዊ ማቴዎስ ሰማዕትነትን የተቀበለበት (ያረፈበት ዕለት ነው) እንደሚታወቀው ይህ ወንጌላዊ ኢትዮጵያ መጥቶ ያስተማረ፣ ስለ ኢትዮጰያውያን ከሌሎቹ ወንጌላውያን በተለየ በወንጌሉ ላይ የጻፈ በወንጌሉ ላይ ስለ ኢትዮጵያውያን መጻፋ ኢትዮጵያ ሃገር መጥቶ እንደነበር ማስረጃ መሆኑን አበው ሊቃውን ያስረዳሉ፡፡
❖ ይኸውም ስለ ኢትዮጵያዊትዋ ንግሥት ማክዳ በምዕራፍ 12 ላይ ጽፏል፤
❖ በምዕራፍ 2 ደግሞ ስለ ሰብዓ ሰገል ጽፏል፤ ከሰብዓ ሰገል መካከል ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ቅዱስ ዳዊት በ71ኛው ዝማሬው
‹‹ የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያመጡልሃል›› ያለው አስረጅ ነው፡፡
❖ ስለዚህ ቅዱስ ማቴዎስ ስለ ኢትዮጵያውያን በወንጌሉ ስለጻፈ እና በሃገራችን መጥቶ ስላስተማረ ለእርሱ መታሰቢያ እንዲሆን በዕለተ ዕረፍቱ በጥቅምት 12 ዕለት ሲኖዶስን ታደርጋለች፡፡
❖ በዓመት ሁለት ጊዜ ሲኖዶስ እንዲደረግ መሆኑ ኦሪታዊ መሠረት አለው ይኸውም በኦሪ. ዘኁ ምዕ 10 ከቁጥ 1 ጀምሮ ስንመለከት
‹‹ እግዚኣብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው ሁለት የብረት መለከቶች አስጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ፡፡ ሁለቱም መለከቶች በተነፋ ጊዜ ማኅበሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ ምስክሩ ድንኳን ይሰብሰቡ ›› እንዳተባለው ይህ መሠረት ሁኖ ሁለቱ መለከቶች ሲነፋ ማኅበሩ ይሰበሰቡ እንደነበረ ዛሬም ይህ ምሳሌ በማድረግ በዓመት ሁለት ጊዜ ቅዱስ ስበሰባ ይደረጋል፡፡
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ
፪ . አምላክ ለመረጠው በቅቶም ለተገኘው ( ሥርዓተ ጵጵስናን ላሟላ ) ሥልጣን ክህነት ( ጳጳሳትን ትሾማለች) ይሰጣል፡፡
❖ ከላይ እንደገለጥነው በዚህ ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ በኩል ለቤተክርስቲያን ሥልጣነ ክህነት የተሰጠበት ስለሆነ በዚህ ዕለት የተገባውን በመሾም በዚያውም የሐዋርያትን ሹመት መታሰቢያ ታደርጋለች፡፡
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
" #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
➘ #እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"
ምንጭ
አምኃ ሥላሴ /መኩሪያ ተስፋዬ/
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ
"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
https://telegram.me/Tewahedo12
FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
http://facebook.com/Tewahedo12
YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
───────────
479 views✞ ባሮክ ✞, 10:33